cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Mejnun ❤❤

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#መጅኑኑ_ለይላ *** መጅኑኑ ለይላ መፅሀፍ እነሆ በቅርቡ የህትመት ጣጣውን ጨርሶ ወደናንተ ይደርሳል። በመፀሀፉ ላይ ቀድመን የለቀቅነው የሽፋን ምስልም ለውጥ ተደርጎለታል። የመፅሀፉን የምርቃት ፕሮግራም በድምቀት የምናከብርበትንና በይፋ ለገበያ የሚበቃበትን ቀንም በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል። ደራሲው ሷሊህ አስታጥቄ እና የአል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ባለቤት ፋሩቅ ጋሊብ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
* ማንነትህ ተግባርህ! * የማንኛችንም ማንነት የሚገለፀው በተግባራችን ነው። የአንተ ማንነት መገለጫ ምንድነው? ምን እየሰራህ ነው? በምን እንድትታወቅ ትፈልጋለህ? ምንም እያደረግህ ካልሆነ አሁኑኑ ጀምረው። መሆን የምትፈልገውን፤ ልትታወቅበት የምትፈልገውን፤ ከሞት በኋላ ልትታወስበት የምትሻውን የአንተን ትክክለኛ ማንነት ዛሬውኑ ጀምረው። ያ የአንተ ማንነት ራስህ የምትኖረው ሌላውም የሚከተለው በዚህ ምድር ላይ ትተኸው የምትሄደው ታሪክህ ይሆናል። እናም ወዳጄ ሆይ ይህንን ማንነትህን በተግባር ዛሬውኑ ኑረው! አሁን ዛሬም ነገም ወደ ፊትም ወደ ፊት ነው በዚህ ምድር ስንኖር በማግኝት በማጣት በከፍታ በዝቅታ ተዋቂ ብንሆን ባንሆንን ብታገኝ ባይኖርህ አንድ ነገር እወቅ የያዝከው ፈጣሪ ይበልጠል ስለዚህ ከፈጣሪ ጋር ወደ ፊት እና ወደፊት።
Показать все...
✿ ዳኛ :- የመግደል ሙከራ ወንጀል መፈፀምህን ታምናለህ? ✿ አዎን ✿ በድርጊትህ አለም አዝኗል አንተስ ምን ተሰማህ? ✿ እኔም በጣም አዝኛለሁ ✿ ደርሰህ ለማዘን ታዲያ ወንጀሉን ለመፈፀም ምን አነሳሳህ? ✿ ያዘንኩት ወንጀሉን በመፈፀሜ አይደለም የዘመኔ ጀግና ❤ ✿ ታዲያ ምንድን ነው ያሳዘነህ? ✿ የዛ ከሀዲ ህይወት በመትረፉ የረሱልን ስም ያንቋሸሸውን ሰው ለመግ*ደል የሞኮረው ጀገና
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እውነት ነው ወንዶች ቢኖሩ ኖሮ ኢስላም ባልተደፈረ ሂጃቦች ተገፈው ሴቶችና ህፃናት ባልተሰው ነበር። #Ethiopia | አንዲት ፍልስጤማዊ ሴት "ሙስሊሞች ሆይ የት ናችሁ?" እያለች ትጮሀለች ። ከአጠገቧ የነበሩት አሊም ተጠጓትና እንዲህ አሉ "ድምጽሽ አውራ ነውና ቀነስ አርጊው" እሷም በአግራሞት ገርመም አርጋ እያየቻቸው "እኔ ዝም እል ዘንድ የታሉ ወንዶች?!" ስትል መለሰችላቸው። እውነት ነው ወንዶች ቢኖሩ ኖሮ ኢስላም ባልተደፈረ ሂጃቦች ተገፈው ሴቶችና ህፃናት ባልተሰው ነበር።
Показать все...
ከሙሐረም ወር አስረኛው ቀን ላይ በ61ኛው አመተ ሂጅራ እጅጉን አስደንጋጭ አሳዛኝና ድንገተኛ የሙስሊሞችን ልብ ያሳመመች በመሪር ሀዘን ያስተከዘች ክስተት ተከሰተች። ይህች ክስተትም በጁሙዐ ቀን የሰይዳችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የልጅ ልጅ የሆኑት የተከበረችው ፋጢማ ልጅ የሆኑት ሰዪዱና ሑሰይን በ56 አመታቸው በበዳዮች እጅ ሸሂድ ሆነው የተገደሉበት ቀን ነው። የተከሰተውን ባጭሩ ስናይ ሰዩዱና ዐሊይን በዙልም የተዋጋቸው ሙዓዊያ ሊሞት ሲል የዚድ የተባለውን ልጁን በደማስቆ ላይ የሱ ኸሊፋ አድርጎት ነበር የሞተው።ይሁንና የዒራቅ ሰዎች የዚያድን ሁኔታ ስለሚያውቁ ለሱ ተከታዮች መሆንን ስላልፈለጉ ወደ ሰዪዱና ሑሰይን ደብዳቤ በመላክ እሱ እንዲያስተዳድራቸውና ለሱም በይዐህ እንደሚያደርጉ አሳወቁት።ሰዪዱና ሑሰይንም ከላኩት መልክተኛ ጋር የአጎታቸውን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂልን በማድረግ ምላሽን ላኩላቸው።ሙስሊም ኢብኑ ዐቂልም ዒራቅ እንደደረሱ ካገኟቸው የሑሰይን ደጋፊዎች ጋር በመሰባሰብ ከሑሰይን ጎን ሆነው እንደሚቆሙ ቃላቸውን ተቀበለ ወዲያውኑም ለሑሰይን ወደ ዒራቅ እንዲመጡ የተከሰተውን ነገር ፅፎ ደብዳቤ ወደ መዲና ላከ።ይህን የሰማው የሙዐዉያ ልጅ ዚያድ ዒራቅ ላይ ዑበይዱሏህ ኢብኑ ዚያድን ሀላፊ አድርጎ ሾመው እንዲሁም ሙስሊም ኢብኑ ዐቂልን እንዲገለው አዘዘ።ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ተገደለ።ለሑሰይን ቃል የገቡት እንዳሉ ተበታተኑ።ይህ መከሰቱን ያላወቁት ሰዪዱና ሑሰይን ቤተሰቦቻቸውን እንዳለ አዘጋጅተው ከመዲና ወደ ዒራቅ ከአንድ ቀን በፊት መንገድ ጀምረው ነበር። ነገሩ ከጅምሩ ያላማራቸው ታላላቅ ሶሐበቶች ሰዪዱና ሑሰይን እንዳይሄዱ ብዙ ወትዉተዋቸውና ሀሳባቸውን አቅርበው ነበር አሏህ የሻው ሆነ እንጂ! እነ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር ጃቢርን ይመስል አትሂድ በማለት ደጋግመው ለምነዋቸው ነበር። ኢብኑ ዐባስ “ወደ ዒራቅ አትሂድ እዛ በቃላቸው የማይገኙ ይበዛሉ ከሄድክ ወደ የመን ሂድ እዛ የአባትህ ወዳጆች አንሷሮች አሉ፣ ከመሄድ ቅሮት የለኝም ካልክ ቤተሰብህን ይዘህ አትሂድ እኔ ሰዪዱና ኡስማን ከቤተሰባቸው ፊት እንደተገደሉት አንተም እንዳትገደል እፈራለሁ ” ብለዋቸው ነበር። ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመርም ከመዲና የሁለት ወይም የሶስት ቀን ጉዞ የሚሆን መንገድ አብረው ተከትለው አትሂድ በማለት ለምነዋቸው ነበር በስተመጨረሻ እቅፍ አርገው እያለቀሱ አሏህ ከገዳዮች ይጠብቅህ በማለት ተመለሱ። እነ አቡሰዒድ አልኹድሪይ አነ ጃቢርና ሌሎችም የቻሉትን ያክል ለማስቀረት ሞክረው ነበር ይሁንና አሏህ በአዘል የወሰነው ከመከሰት ቅሮት የለውምና ወደፊት ተጓዙ። ሰዪዱና ሑሰይንና ባልደረቦቻቸው እንዲሁም አህለልበይቶች ባንድ ሆነው መንገድ ጀመሩ ዒራቅ እንደደረሱም ዑበይዱሏሂ ኢብኑ ዚያድ የሰራውንና የዒራቅ ሰዎችም የገቡትን ቃል ማጠፋቸውን አወቁ አንድም ሰው ከነሱ ሳያገኙም ቀሩ።ዑበይዱሏህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ሰዪዱና ሑሰይን አራት ሺህ የሚሆኑ ፈረሰኞችን ዑመር ኢብኑ ሰዕድ እየመራቸው እንዲሄዱ አዘዘ።ከርበላእ ላይም ተገናኙ ሰዪዱና ሑሰይንም ሶስት ነገሮችን ጠየቁ 1ኛ)በሰላም ወደመጡበት እንዲመለሱ 2ኛ)በሰላም ወደ የዚድ ኢብኑ ሙዐዊያ እንዲሄዱ 3ኛ)ወይም ለመዋጋት ከሚያስችላቸው ቦታ እንዲሄዱ ይፈቅዱላቸው ዘንድ ዑመር ኢብኑ ሰዕድ በሀሳቡ ተስማምቶ ወደ ኢብኑ ዚያድ መልእክት ላከ ኢብኑ ዚያድም እነ ሑሰይን ወደ እኔ መጥተው ሙባየዐ ካላደረጉ ባቀረቡት እንዳይስማማ መልክት ላከበት።ይህን ሀሳብ ያቀረበው ሺምር ኢበኑ ዚል ጀውሸን የተባለ መጥፎ ሰው ነበር። ይህን የሰሙት ሑሰይንም ወሏሂ ይህን አላደርግም አሉ።ዑመር ኢብኑ ሰዕድ ለመዋጋት አልፈለገም ነበርና ወደ ኀላ ሲል ኢብኑ ዚያድ ሺምር ኢብኑ ዚል ጀውሸንን ላከና ዑመር ኢብኑ ሰዕድ ከተጋደለ አብረህ ተጋደል እምቢ ካለ እሱን ገድለህ አንተ ቦታውን ያዝ አለው።ከሰዪዱና ሑሰይን በተቃራኒ የነበሩት ከፊል ተዋጊዎች ሀሳባቸውን ቀይረው ከሑሰይን ጎን ቆሙ ዑመር ኢብኑ ሰዕድ ስለፈራ የኢብኑ ዚያድን ቃል ለመፈፀም ተነሳ እነ ሑሰይንን ከባድ የሆነ ማካበብን አካበቧቸው።ውሀ ወዳለበት ቦታም እንዳይደርሱ አደረጓቸው። የሙሐረም 10ኛው ቀን ንጋት ላይ ሰዪዱና ሑሰይን ከ32 ፈረሰኛና 40 እግረኛ ተዋጊዎች ጋር በመሆን 4000 ጦረኞች ጋር ተዋጉ።(በነፍስ ወከፍ አንድ ሰው ለ55 ሰው ሊጋደል እንደማለት ነው።) እንደዛም ሆኖ የሑሰይን ባልደረቦች የቻሉትን ያክል ተጋደሉ የመጀመሪያው ሟች የሑሰይን ልጅ ዐሊይ አል አክበር ነበር።በዚህ ጊዜ እህታቸው ዘይነብ ወጣች ሑሰይንም በእጃቸው መለሷት ከዚያም ዐብዱሏህ ኢብኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ከዚያም ዐውን እና ሙሐመድ የዐቂል ልጆች ከዚያም ቃሲም የሐሰን ልጅ አቡበክር አል ዐባስ ዑስማን ጀዕፈር ሙሐመድ እነዚህ ሁሉ ሞቱ። ሰዪዱና ሑሰይን ብቻቸውን ቀሩ የውሀ ጥም ጠናባቸው ግን ወደ ውሀው መድረስ አልቻሉም እንደምንም ብለው የሚከለክሏቸውን ከፊታቸው አስወግደው ከውሀው አጠገብ ሲደርሱ አንዱ በቀስት አንገታቸው ላይ መታቸው ደማቸው ፈሰሰ። ሑሰይን ዱዓ አደረጉባቸው።(ይህ በቀስት የመታቸው ብዙም አልቆየም አሏህ የውሀ ጥም ለቀቀበት ቀዝቃዛ ውሀ በወተት እየተቀላቀለ ይጠጣል ግን ጥሙን አይቆርጥለትም ነበር በዛው ሞተ) ሰዪዱና ሑሰይን በግራም በቀኝም በሰይፋቸው ይከላከላሉ በዳዮቹም ይበተናሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ዙርዐተ ኢብኑ ሹረይክ የተባለ መጣና ግራ እጃቸውን መታቸው ሌላኛው አንገታቸውን መታቸው ሲናን ኢብኑ አነስ በቀስት ወጋቸው አንዱ ወደሳቸው ተጠግቶ አንገታቸውን ሊቆርጥ ሲል እጁ ሺባ ሆነች ከዚያ ሺምር ኢብኑ ዚል ጀውሸን መጣና የተባረከ አንገታቸውን ከተከበረው አካላቸው ለየው። ሰዪዱና ሑሰይን በተገደሉ ጊዜ 33 ቦታ ተወጋግተው 43 ቦታ ተመተው ነበር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ይህ ሺምር የተባለው መጥፎ ሰው ሰዪዱና ዐሊይ አል አስጘር ማለትም ዘይኑል ዓቢዲን ተብለው የሚታወቁትን የሑሰይንን ልጅ ለመግደል አስቦ ነበር።እሳቸው በዛ ጊዜ ህፃንና በጣም አሟቸው ነበር።ከዚያም ሌሎቹ ከለከሉት። በዚህ ቀን 72 ከሰዪዱና ሑሰይን ጋር የነበሩት ሲገደሉ 20 የሚሆኑ ከአህሉል በይት ተገድለዋል።ሰዪዱና ሑሰይን ሲሞቱ የ56 አመታቸው ነበር።ቀኑም ጁሙዐ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጀራ ሙሐረም 10 ነበር። የዚድ ኢብኑ ሙዐዊያ ሑሰይን እንዲገደሉ እንደማይፈልግ ነበር ያሳየው ይሁንና ገዳዮቹን ምንም አይነት ቅጣትን አላስተላለፈባቸውም።ቢሆንም አሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የሑሰይንን ገዳዮች ከፊሎቹ እያበዱ ከፊሎቹ ከባድ ህመም እየታመሙ አለቁ ኢብኑ ዚያድም ብዙ አልቆየም እራሱ ተቆርጦ ሲሞት። ኢብኑ ዐሳኪር እንደዘገቡት የተወሰኑ ሙስሊሞች ለጦርነት ወደ ሮም ሀገር በሄዱ ጊዜ አንድ ቤተክርሰቲያን ወስጥ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አገኙ "ሑሰይንን የገደሉት ሰዎች የሑሰይን አያት የሆኑትን የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽምግልና የውመል ቂያማ ይከጅላሉን?" ጠየቋቸው ማን እንደፃፈው።እነሱም “ይህ ነቢያችሁ ከመላካቸው 300 አመት ቀድሞ ነው የተፃፈው”አሉ። አዎ ሙስሊሞች በዚህ ክስተት እጅጉን ልባቸው ተሰብሯል አዝነዋል ይሁንና መከራዎች በሚወርዱብን ሰአት ሶብር ከማድረግና ከአሏህ ምንዳን ከመከጀል ውጭ ልብን እየደቁም ሆነ እራስን እየጎዱ ማሳለፍ በጭራሽ ያልታዘዝነው ነገር በመሆኑ ከዚህ አይነት የሺዐዎች ተግባር መራቅ ይኖርብናል። رضي الله عن سيدنا الحسين بن علي

<<ሐጂ ለምንድ ነው ከልጅዎ ገዳይ (መንግስቱ ኃ/ማርያም) ጎን የሚቀመጡት ሰውስ ምን ይልዎታል?>> አላህ በጀነተል ፊርደውስ ያኑራቸውና ታላቁ አሊም ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ በደርግ ስርዓት የቀይ ሽብር ዘመቻ አንድ ልጃቸው ተገድሎባቸው የልጃቸውን አስክሬን ደግሞ እግቢያቸው በር ላይ ነበር የጣሉላቸው። በዚህም ምክንያት ሐጂ ሳኒ እድሜ ልካቸውን እግቢያቸው ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በጠባቡዋ በር ነበር የሚጠቀሙት። የልጃቸው አስክሬን የተጣለበት ቦታ በእግራቸውም ሆነ በመኪና አይሻገሩትም ነበር ሐዘናቸው ቀላል አልነበረም። ከዚህም በመነሳት የቅርብ ወዳጃቸው ሐጅ በሽር ዳውድ (አላህ የጀነት ያድርጋቸው) አንድ ቀን ለሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ "ሐጂ ለምንድ ነው ከልጅዎ ገዳይ (መንግስቱ ኃ/ማርያም) ጎን የሚቀመጡት……ሰዉስ ምን ይልሆታል?!" ሲሉ በግሳፄ መልክ ጠየቋቸው፤ የሐጂ ሳኒ መልስ "በእኔ እዚያ መቀመጥ ሰበብ አላህ ለኢትዮጵያ ሙስሊም መልካም ነገር ቢያመጣለት ብዬ እንጂ ሌላ ምን እፈልግ ኖሯል?" የሚል ነበር። አላህ ይዘንላቸው እና ልጃቸውን በማጣት ልባቸው ቢሰበርም ከደረሰባቸው ሀዘን በላይ ለኡማው በሚደረግ መልካም ነገር በላጭ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል። አዎ! አንድ ሰው ለነፍሱ ብቻ ከሚያደርገው መልካም ስራ ይልቅ ለነፍሱም ለኡማውም የሚጠቅም ነገር ማድረግ ይበልጥ በላጭ ነው። ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ አላህ በጀነተል ፊርደውስ ያኑሮ🤲
Показать все...
የክር ሲህር እናንተ ሰዎች ሆይ የምትበሉትን በደምብ ፈትሹ!! በዶክተር አል ዘንዳኒ አንድ አህያን እና ሰውን የሚለያቸው ባህሪ አለ፡፡ አህያ ያየውን ነገር ምግብ ነው ብሎ ይግጣል፡፡ ሰው ግን ሊበላ ሲል በተመስጦ ቢስሚሏህ በማለት ወደ ምግቡ ሲቀርብ ምግቡንም በደምብ አተኩሮ ሊያይ አሏህም የሰጠውን ኒእማ ሊያመሰግን ብሎም እያንዳንዱ ጉርሻዎቹ ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል፡፡ ከታሪኩ የምንማረው ሰው እንጂ አህያ አንሁን የሚለውን ነው፡፡ ቢስሚሏህ ይህን ሲህር ብዙ ታካሚዎቻችን ላይ እያገኘን ነውና ተጠንቀቁ፡፡ ያም በአዝካር አልሩቅያህ ላይ ህክምና ሲያደርጉ በሚደረገው ምርመራ ላይ ውስጣቸው የተበላ ሲህር መኖሩን እናረጋግጣለን፡፡ በመቀጠልም ህክምና በሚሰጣቸው ሰአት ቢያንስ ከ 7ቱ ታካሚዎች አምስቱ ላይ የምናገኘው በሰገራ ምክንያት የሚወገድ የተተበተበ ክር ነው፡፡ እና እባካችሁ ስትበሉ በቢስሚሏህ የምትመገቡትንም ተመልከቱ!! ክፍል 1 ምልክቶቹ! 1.የሆድ ህመም የሆድ መቁረጥ ተቅማጥ እና ማስማጥ ሲሆን፡፡ ይህም ግዜን እየጠበቀ ነው የሚመጣው፡፡ 2.ምንም ብትበላ ውስጥህ ጠብ አይልም ይህ ማለት ሰውነት አይሆንህም አይሆንሽም ሊያውም መክሳቱን ትያያዢዋለሽ፡፡ 3.የምግብ ፍላጎት ማጣት፡፡ ከሚበሉ ባይበሉ ይሻላቸዋል፡፡ የነርሱን ምግብ ፍላጎት ማግኘት ከባድ ነው፡፡ 4.ትኩረተ ቢስ መሆን፡፡ አንድ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ አይችሉም፡፡ ትኩረታቸው አሁንም አሁንም ይሰረቃል፡፡ ማስታወስ እያቆሙ ይመጣሉ፡፡ ያ ሲባል ትውስታ ቢኖራቸውም ቀላል ነገሮችን ማስታወስ አይችሉም፡፡ 5.ድብርት፡፡ ይህ ድብርት አይደለም በቡና አይደለም አእምሮን በሚያነቃቃ ነገር በእንቅልፍ እንኳ አይተውም፡፡ በእንቅልፋቸው ስር እንኳ ሆነው በድብርት ሲሰቃዩ ይስተዋላሉ፡፡ በረጅሙ ይተነፍሳሉ ያለቅሳሉ ይጫጫናቸዋል፡፡ 6.የሰውነት ጡንቻ መሸማቀቅ፡፡ አንዳንዴ ከተቀመጡበት መነሳት አይቻላቸውም፡፡ ህመሙ ብርቱ ነው፡፡ 7.ደምስራቸው ስር የሚሄዱ ነገሮች እንዳሉ ይሰማቸዋል፡፡ ውስጣቸው የሚንቀሳቀስ ነገር ያለ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ የክሩ ሲህር ይሁን ሌላ አሏሁ አእለም፡፡ 8.ሃኪም ቤት መመላለስ ግን ምንም የሚገኝላቸው ነገር የለም፡፡ ሰውነታቸው መርፌና መድሃኒት ይወዳል፡፡ እነኚህን አይነት ምልክቶች ሲያዩ ባፋጣኝ ሩቅያህ ያስፈልጎታል፡፡ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ኡስታዞችን በማናገር ሩቅያም ይጀምሩ!! https://t.me/Qallbdoc 👇ኡስታዞችን ያናግሩ👇 @freeeeeeeeeeeere
Показать все...
የቀልብ ዶክተር (طبيب القلب)

ጥቅማችን ጀነት ነው! ጥቅማችን የአላህ ውዴታ ነው የላከንም አላህ ነው እኛም የርሱ ባሮች *ሙስሊሞች ነን👈 💡አሏህን የያዘ ሰው ብቻ አንበሳ ነው💡 👉 የውሾች_ጩሀት_የአንበሳውን_ጉዞ_አያስተጓጉልም👈 @freeeeeeeeeeeere 👈 ዶ/ር ወይ @UstazulQallb 👈 ኡስታዝ ያገኛሉ 👇የዩቲይብ አድራሻችን👇

https://www.youtube.com/c/የቀልብዶክተር

👉 አደራ አደራ 👈 *ይህ አብዛኞቻችን የምንፈፅመው ስህተት ነው* አብዛኞቻችን አዛን እያለ ወሬ እናወራለን። የተከበሩት የአለማት ነብይ ሙሀመድ (ሱለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ይሉናል “አዛን ሲል ምንም ነገር መስራት አቁሙ። ቁርዐን መቅራት እንኳ ቢሆን። አዛን እያለ የሚያወራ ሰው ሲሞት የሸሀዳ ቃል አይገጥመውም፣ *መልዕክቱን ለወንድም እህቶቻችን ባገኘነው መንገድ እናስተላልፍ። ለአላህ ስትሉ ቢያንስ ለ 10 ሰው ሸር አድርጉ
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.