cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethiopia first(ቅድምያ ለሀገር)

ሀገር ከግል ፍላጎት በላይ ናት

Больше
Рекламные посты
205
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የትግራይ ሀይሎች አላማጣ ከተማ አቅራቢያ ተቆጣጥረዋቸው ከነበሩ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን አቶ ጌታቸው አስታወቁ‼️ የትግራይ ሀይሎች በአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ “ገርጃሌ” እና “በቅሎ ማነቂያ” ከተባሉ መንደሮች ለቀው መውጣታቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ። የትግራይ ሀይሎች ከመንደሮቹ ለቀው እንዲወጡ የተደረገው ከፌደራል መንግስቱ እና ከአማራ ክልል መንግስት ጋር የተደረሰውን መግባባት በማክበር መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል። በተጨማሪም ከአከባቢው ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል ሁኔታዎችን ለማመቻችት መሆኑን ገልጸዋል። በረካታ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ስራ በሂደት ላይ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመላክተዋል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአሜሪካ ኤምባሲ ሁለት ቀን ተዘግቶ ይውላል‼️ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤሜሪካ ኤምባሲ ሰኞ እና ማክሰኞ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አስታውቋል። ኤምባሲው ፥ ሰኞ ግንቦት 19/2016 ' ሚሞሪያል ዴይ 'ን ወይም በግዳጅ ላይ የተሰዉ የአሜሪካ አርበኞች መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ እንደሚዘጋ አመልክቷል። በነጋተው ማክሰኞ ግንቦት 20 የ ደረግ መንግሥት የወደቀበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ተዘግቶ እንደሚውል ገልጿል። ኤምባሲው ዳግም የሚከፈተው ረቡዕ ግንቦት 21 መሆኑን አሳውቋል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢራን የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አደረገች‼️ የኢራን የጦር ኃይሎች፤ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን አሳፍሮ በነበረ ሄሊኮፕተር ላይ የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ ከአደጋው ጋር የተያያዙ የቴክኒክና አጠቃላይ መረጃዎችና ግኝቶች እንደተሰበሰቡና እንደተመረመሩ ተገልጿል። ለምርመራ ተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቁ አንዳንድ መረጃዎች መኖራቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። በቅድመ ምርመራው መሰረት ሄሊኮፕተሩ የበረራ መስመሩን ሳይቀይር አስቀድሞ በወሰነው መስመር መጓዙ ተጠቁሟል፡፡ የሄሊኮፕተር አብራሪ አደጋው ከመከሰቱ ከአንድ ደቂቃ ከሰላሳ ሰከንድ በፊት ከሌሎች ሁለት ሄሊኮፕተሮች አብራሪዎች ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ተረጋግጧል። በቀሪዎቹ የሄሊኮፕተሩ ክፍሎች በመሳርያ የመመታት ምልክትም ሆነ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳልተገኘና ከአደጋው በኋላ ሄሊኮፕተሩ በእሳት እንደተያያዘ ዘገባው አመልክቷል። አካባቢው ወጣ ገባ የሆነ የመሬት አቀማመጥ ያለው መሆኑ እንዲሁም ቀዝቃዛና ጭጋጋም  የአየር ጸባይ የፍለጋ ሥራውን  ከባድ አድርጎት እንደነበር ተመላክቷል። የምርመራው የመጨረሻ ውጤት በቅርቡ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ መገለፁን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ባሳለፍነው እሁድ በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በአደጋው  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት እና የሄሊኮፕተር በረራ ክፍል አባላት ህይወት አልፏል።
Показать все...
በእሳት አደጋ የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል ወደመ‼️ አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 10:10 ሰዓት አቡኒ የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ተነስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፋብሪካዉ በከፊል መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ። የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢፕድ በሰጡት መረጃ እንዳሉት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦታ ከ56 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርቷል። ባለሙያው የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። በአደጋዉ ለመልሶ መጠቀም ግልጋሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ፋብሪካዉ በከፊል ወድሟል። በፋብሪካዉ የአደጋ ደህንነትን መስፈርት ያልጠበቁ ያገለገሉ የፕላስቲክ ዉጤቶች ክምችት እንዲሁም ስፍራዉ የአደጋ መቆጣጠር ተሽርከርካሪውችን የማያስገባ መሆኑ ለአደጋዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ አድርጓል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን  በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። (ኢ ፕ ድ)
Показать все...
ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡ ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ  ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው  የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
Показать все...