cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ https://t.me/lafto_qirat

Больше
Рекламные посты
1 407
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
+2630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ኡስታዝ ባጋጣሚ ስላልተመቻቸው መምጣት አልቻሉም! አፉወን!
Показать все...
👍 4
ማስታወሻ❗️ ባማረ አቀራረብ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ እየተሰጠ የሚገኘው የተፍሲር ደርስ በአላህ ፍቃድ #ነገም የሚቀጥል ይሆናል❗️ 🔖 🔖"ለዓይን ብርሃን እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ለልብም ቁርኣንና የቁርኣን እውቀት ያስፈልገዋል"።
Показать все...
👍 4
✍      የዳኑ ሰዎች……… "እንዴት ዳኑ?" ብለህ ብትጠይቅ መልሱ: የታዘዙትን "እሺ!" በማለታቸው ብቻ ነው።ኑሕﷺ አላህ መርከብ እንዲሰራ ባዘዘው ጊዜ:    "እሺ!" ብሎ መርከቡን ሰራ እንጂ;    “ጌታዬ ሆይ! በዚህ በደረቅ መሬት ላይ መርከብ ምን ሊሰራ?” ብሎ አልጠየቀም። ☘ኢብራሂምﷺ አላህ ልጁን እንዲያርድ ባዘዘው ጊዜ: "እሺ!" ብሎ ልጁን አረደ እንጂ;    “ጌታዬ ሆይ! ልጄን በመታረዱ ጥበቡ ምንድን ነው?” ብሎ አልጠየቀም። ☘የሙሳﷺ እናት አላህ ልጇን ውሃ ውስጥ እንድትጥል ባዘዛት ጊዜ: "እሺ!" ብላ ልጇን ጣለች እንጂ;   “ጌታዬ ሆይ! ሌላ ቀለል ያለ አማራጭ የለም ወይ?” ብላ አልጠየቀችም። ☘ኢብራሂምﷺ አላህ ሃጀራ እና ልጇን ምንም በሌለበት በረሃ እንዲያስቀምጣቸው ባዘዘው ጊዜ: ሃጀራ የጠየቀችው አንድ ጥያቄ ብቻ ነበር "አላህ ነውን ይህንን ያዘዘህ?" ስትለው "አዎን!" አላት;   "እንግዲያውስ አላህ አይጥለነም!!" ነበር ምላሽዋ። ከዝያም ነገሮች ተቀያየሩና……… 💫ምድርቷ በውሃ ተጥለቅልቃ መርከቧ መዳኛ ሆነች; 💫ሊታረድ ቀርቦ በነበረው ልጅ ምትክ አላህ ሙክት ቀየረ; 💫በውሃ የተጣለውም ልጅ ውሃውን በእንክብካቤ ወደሚያድግበት ቤት ተሸክሞ ወሰደው; 💫ምድረበዳ ሜዳ ላይ ከጨቅላ ህፃኗ ጋ ተትታ የነበረችዋም ቦታው እስከቂያማ ድረስ የሙስሊሞች መቀጣጫ እና መሰባሰቢያ ሆነ። መዳን ከፈለክ………    ያለ ምንም ዝርዝር ጥየቃ ከጌታህ የታዘዝከውን ሁሉ "እሺ!" በል።   በተጓዙበት ተጓዝ, የደረሱበት ትደርሳለህ!! منقول
Показать все...
👍 2
✍️    "  እንደ ምትሞት ታምናለህ ኣ?    የሞትህ ቀን ቤተሰቦችህ ወደ መዝናኛ ወይም ወደ መቃሚያ አይደለም የሚወስዱህ;   ወደ መስጂድ ነው የሚወስዱህ።   የሞትህ ቀን የሚፈለጉት ዛሬ ላይ የምታደንቃቸው የምትከታተላቸው ቲክቶከሮች ወይም አርቲስቶች ወይም ተጫዋቾች አይደሉም;    ዛሬ ላይ ችላ ያልካቸው የናቅካቸው ሷሊሆችና ደረሳዎች  ናቸው እንዲሰግዱብህ የሚፈለጉት።    ጀናዛህን ተሸክመው ወደ መስጂድ ከማስገባታቸው በፊት; ሕያው ሳለህ ወደ መስጂድ ግባ ስገድ ተማር።   በድን ኾነህ በሷሊሆች ከመከበብህ በፊት;       ሷሊሆች ተገናኝ ተማር። ወንድ ሁን!! ዲንህን: ተማር… ተግብር… አስተምር"
Показать все...
👍 3
🌱 " የሙባረክ ልጅ ሆይ ራስህን ካወቅክ ስላንተ የሚወራው ወሬ አይጎዳህም። " [አብደላህ ቢን ሙባረክ]
Показать все...
"አስደንጋጭ ገለፃ : በእኛ ምክር በዙርያችን ያሉት ድነው እኛ ከመጥፋት እንፍራ።‼"
Показать все...
👍 11
"የወንድ ልጅ ግርማ ሞገሱ👇 አዛን ሲሰማ ወደ መስጂድ መቻኮሉ ነው❗️"
Показать все...
👏 12👌 4💯 3👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
👌ምዝገባ ተጀምሯል❗️
Показать все...
3
✍      "ኡማው ቢስተካከል እስልምና ይነሰራል!!   ይህ የሁሉም ሙስሊም እምነት እና ምኞት ነው። ግን ትልቁ ችግራችን: ሁላችንም ሌሎች ተስተካክለው እንዲገኙ እንመክራለን እንጂ ራሳችንን ለማስተካከል አንጥርም።።   ወንድም አለም "ኡማ" የሚባለው እኮ እኔ እና አንተ ነን። "የኡማው መስተካከል" ሲባል የሆነ እንደ ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም "ሆ" ብሎ ወጥቶ ተስተካክሎ የሚገባበት ፕሮግራም አይደለም፤ እኔ ራሴን ሳስተካክል፣ አንተም ራስህን ስታስተካክል: የዛኔ ኡማው ይስተካከል እና ነስሩ ይመጣል።   አሁንም ሌላ ሰው እንዳታስብ 🫵አንተ! አዎን አንተ ራስህ! እስኪ ቆም በልና ከእስልምና ጋ ያለህን ትስስር ፈትሽ። ወላህ! በአላህ እዝነት እንጂ ጥፋት ላይ ነው ያለነው፤ አላህ ከእዝነቱ ከጥፋት ስንመለስ ያጣነው ክብር ይሰጠናል እናም ዛሬውኑ እንመለስ!!"
Показать все...
👍 3 3
አንድ ቀን... አይቀርም! 🔅ሰው የሆነ በሙሉ አንድ ቀን መሞቱና ከዱኒያ መውጣቱ አይቀርም!።     💥ሞት ጽዋ ነው፤ ሁሉም ይጎነጨዋል!     💥ሞት በር ነው ሁሉም ያልፍበታል! 🔅ምንም እንኳ ብዙዎቻችን ብንረሳውም ሞት ግን አይረሳንም፤ ተራችን ሲደርስ መጥቶ ያለ ምንም ድርድር ዳግም ወደ ዱኒያ ላንመለስ ነፍሳችንን ይዞ ይሄዳል!። 🔅ቀድሞ የተዘጋጀ፤ ቀብሩንና የኣኺራህ ቤቱን በመልካም ስራ የገነባ ሰው በመሄዱ (በመሞቱ) ይደሰታል። ሳይዘጋጅ የሄደ ግን ይሰቃያል፤ ይከስራል። 🔅ወደ ዱኒያ ተመልሶ መልካም ስራ ሰርቶና ጥፋቱን አስተካክሎ መመለስን ይመኛል፤ ጌታውንም ይማጸናል፤ ግን ከንቱ ምኞት ብቻ ሆኖ ይቀራል!። 🔅ማስተዋልን የታደለ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል ሳይገጥመው በፊት ቀድሞ ይዘጋጃል። { كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ }    [ آل عمران : 185] ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 02/01/1445 ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ 🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
Показать все...
👍 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.