cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ከ ሁሉም ፈሰስ ፈሰስ🕋🌄✈️

(የቀልብ እርጋታ ሚገኘው አላህን በማስታወስ ነው)

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
227
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

«እኔ ስልጣን አልፈልግም» እያሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚናገሩት ሐጅ ዑመር እድሪስ ተስማምተው ለፈረሙበት ቃላቸው ጭምር የማይታመኑ፣ ሕግና መመሪያን ሲጥሱ ጭራሽ ማፈርም ሆነ መሳቀቅ የማያውቁ፣ የመጅሊስን ችግር በመነጋገርና በሽምግልና ለመፍታት ስድስት የተለያዩ የሽማግሌ ቡድኖች ተቋቁመው ሁሉንም ሙከራ አድረገው በርሳቸው አምብተኝነት የከሸፉ ናቸው። በእስቴ መስጊዶች ሲቃጠሉ ዝምታን መርጠው፣በቢቸና መሰጊድ ላይ ቦንብ ተወርዉሮ ሙስሊሞች ሲገደሉ ባለየ አልፈው፣በሞጣ ሙስሊሞች ላይ ሽብር ሲፈጸም ድምጻቸውን አጥፍተው፣ነጃሺ መስጊድ ሲጠቃ በተአቅቦ አልፈው፣በወሎ ያሁሉ የሱፊያ ሀሪማ ሲወድም ሱፍይነት ትዝ ብሏቸው እንድረስላቸው ሳይሉ፣ ሰበጎንደር ሙስሊሞች ሲገደሉና የሽብር ጥቃት ሲፈፀምባቸው እንደመሪ ተቆጥተው ፍትህ መጠየቅ ሲገባቸው «የጎዳና ላይ ኢፍጣር በእስልምና የለም» ብለው ለከሳሾቸ ዋቢ ምስክር የሆኑት ሰው፣ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ከመሪነት አንስቶ በፈትዋ ዘርፍ ሲመድባቸው ለኢስላምና ለሙስሊሞች መብት ተቆርቁረው ለመናገር ምላሳቸውን የያዛቸው በስልጣኔ መጡ ስሜት ተሞልተው «ተነሱ።ለትግል ተዘጋጁ።» ብለው ወደ ደም መፋሰስ ሀጂ ዑመር የቀሰቀሱት «አላህ ሽቶባቸው ነው እንጂ ለስልጣን ብለው እይደለም እኮ።» ብሎ የሚያስብ የዋህ አይጠፋም። ያም ሆኖ ተቋሙ የሕዝበ ሙስሊሙ እንጂ የእርሳቸው የግል ርስት ስላልሆነ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ በድምጽ ብልጫ እሳቸውና ሌሎች 3 ዑለሞች ወደፈትዋ ክፍል እንዲዛወሩ ውሳኔ አሳለፈ። ይህንን የወሰኑት ዑለሞች ናቸው። ሙፍቲ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ የቆዩት በሕግም በሸሪዓውም የሌሎችን ዑለሞች የአብላጫ ውሳኔ የመሻር ቬቶ ስላላቸው ሳይሆን በተግባር ለአንድነት እየተባለ እየታለፉ፣ በተጨማሪም እርሳቸውን "አይዞህ" በሚላቸው ስውር አካል እየተደገፉ ነው ያሻቸውን ሲፈጽሙ የቆዩት። በተደጋጋሚ መመሪያ ተጥሷል። ስምምነት ተሽሯል። እርሳቸው የሚፈልጉት ካልሆነ እንደማይስማሙ እየታወቀ በስምምነት እንጂ በድምጽ ብልጫ አትወስኑ እየተባለላቸው የህዝበ ሙስሊሙ መብትና ጥቅም ላይ እንዲረማመዱ ተፈቅዶላቸዋል። እርሳቸው አሁንም ከሕግም ከመመሪያም በላይ ሆነው ለመቀጠልና «ደም ይፈሳታል እንጂ» እንዳሉት ሁሉ ሙስሊሞችን ለማበጣበጥና ደም ለማፋሰስ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። ይህ ግን በዝምታ ሊታይ አይገባም። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእነርሱ የሆነና ለእነርሱ የቆመ፣ በሕግ የበላይነት የሚመራ ጠንኳራ ተቋም ባለቤት የመሆን መብታቸውን በተግባር መጎናጸፍ ከፈለጉ ጠንክረው መቆም አለባቸው። የየትኛውንም ግለሰብ ማስፈራሪያ በመስማት ከህግ የበላይነት ይልቅ ግለሰቦችን ኡሹሩሩ ማለት መቆም አለበት። ይህን እሹሩሩ ሳያቆሙ የታሰበው የሕዝበ ሙስሊሙ ተቋም ፈጽሞ እውን ሊሆን አይችልም።» ©: አሕመዲን ጀበል
Показать все...
አሕመዲን ጀበል ያቺኑ እቅጯን ጽፏታል‼ ============================ ✍ ««አላህ ሽቶብኝ ነው እንጂ እኔ ስልጣን አልፈልግም።» ❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ አልፎ አልፎ ሚዲያ ባለበት ሕዝባዊ ስብሰባዎችም ሆነ መግለጫ ላይ ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ ስልጣንና ዱንያዊ ጥቅማ ጥቅምን እንደማይፈልጉ የሚገልጹባቸው ቃላቶች ይገኙባቸዋል። የዱንያዊው ጥቅም ጉዳይ ለጊዜው በይደር ይቆየኝና ስልጣን እንደማይፈልጉ ከሚገልጹባቸው መካከል «አላህ ሽቶብኝ ነው እንጂ እኔ ስልጣን አልፈልግም» ከሚለው ጋር በተያያዘ ጥቂት ልበል። በቅርበት የማያውቃቸው ሰው "ታዲያ ስልጣን የማይፈልጉ ከሆነ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) በይፋ ከተመሠረተበት እስከ ዛሬ (ከመጋቢት 4 ቀን 1968 እስከ 2014 ግንቦት) መንግስታት ሲቀያየሩ ጭምር ቦታ እየቀያየሩና እየተመሳሰሉ እንዴት መጅሊስ ዉስጥ ለ46 ዓመታት በስልጣን ላይ መቆየት ቻሉ?" የሚል ጥያቄ በአዕምሮው ሊያጭርበት ይችላል። ሙፍቲ የመጅሊስ ምርጫ ጉዳይ ሲነሳ ምርጫ ከተደረገ ከስልጣን እንደሚለቁ ስለሚያውቁ አጀንዳውን ለማዳፈን በተደጋጋሚ የሚያቀርቡት ማስፈራሪያ ከመጅሊስ ስልጣን ከተነሱ «መጅሊስ ለሁለት ይከፈላል» የሚለው ዛቻ ነው። ለሁለት ሲከፈል እሳቸው የአንዱ ክፋይ መሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ሲባል ማለት ነው። መጀመሪያ ዑለሞችና የቦርድ አባላት ሲመረጡ የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ። ለስድስት ወራት በተባለው የሽግግር ጊዜ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሳይወጡ 3 ዓመት አለፋቸው። ቆይተው ደግሞ በግልጽና በይፋ የተሰጠ ኃላፊነት ሆኖ ሳለ አንዴ «ስድስት ወር ብሎ ነገር የለም። ቋሚ ነን»፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ «እንደ ፓትሪያርኩ አንዴ ተመርጫለሁ እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ አልወርድም» ማለት ጀመሩ። በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ሥር የመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብን እንዲያዘጋጅ ተሰይሞ የነበረው የነበረው ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንቡን ለዋናው ኮሚቴው ሲያቀርብ የሚመረጠው ዋና ሙፍቲ በንቃት ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል እንዲችል «እድሜው ከ40 ያላነሰና ከሰማንያ ያልበለጠ» የሚለው ነጥብ ሲጠቀስ ከሐጅ ዑመር ተቃውሞ ገጠመው። «ከሰማንያ ያልበለጠ የሚለው የእድሜ ገደቡ ይነሳ» አሉ። ይህም ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ መሆኑ ግልጽ ነው። ቀጥሎም ሌላኛው መስፈርት «ዐረብኛ ቋንቋ መናገር፣ መጻፍና ማንበብ መቻል አለበት» የሚለው ነጥብ ጋር ሲደረስም «የሀገራችን ብዙ ዑለሞች ዐረብኛ መናገር ስለማይችሉ የዐረብኛ ቋንቋ መስፈርቱ ይቅር» ብለው ተቃወሙ። በኋላ ስረዳ እሳቸው «ይህ መስፈርት እኔ እንዳልመረጥ ሆነ ብላችሁ ያስገባችሁት ነው» ብለው መተዳደሪያ ደንቡን በአሉታዊ ጎኑ ማየት መጀመራቸውን ተረዳሁ። ለስድስት ወራት ከ26 ዑለማና ቦርድ ጋር የጊዜያዊ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሾሙም አንዱ በጊዜው እንዲሰሩ በይፋ የተቀመጠው በባለሞያዎች የተዘጋጀው ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተጨማሪ ዉይይት በማድረግ ማፅደቅ ቢሆንም ባለፉት 3 ዓመታት አንዴ እንኳን ዞር ተብሎ ሳይታይ ያ መተዳደሪያ ደንብ ተትቶ ሌላ ተዘጋጅቶ በቅርብ ጊዜ ለውይይት ቀረበ።በእርሳቸው መሪነትም ዉይይት ተደረገበት።በመጨረሻም በአብላጫ ድምፅ ጸደቀ። መጅሊስ በ1968 ሲመሠረት በመተዳደሪያ ደንቡ ምርጫ እንደሚደረግ በግልጽ እንደሚደነግግ የሚያውቁና መተዳደሪያ ደንቡ ላይ የፈረሙ፣ በተደጋጋሚ ጊዜም በመጅሊስ ምርጫ ላይ የተሳተፉ ነበሩ። ሌላው ቀርቶ በ2005 ሕዝበ ሙስሊሙ በፌደራል ጉዳይ አማካኝነት በየቀበሌ ተደረገ በተባለው ምርጫ እንኳን በመራጭም ሆነ በተመራጭነት የተሳተፉ ነበሩ። ሆኖም እርሳቸው ለጊዜያዊነት ተብሎ ለስድስት ወር የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ከቦታው ላለመነሳት አንዴ «በእስልምና ምርጫ የለም» ሲሉ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ «የክርስቲያኖች ፓትሪያርክ አንዴ ከተመረጠ በሕይወት እስካለ ሌላ ምርጫ አይደረግም። የኛም እንደዚህ ቢሆን ጥሩ ነው» የሚል ሐሳብ አመጡ። ይህም ተቀባይነት ሲያጣ በሕዝባዊ ምርጫ እሳቸው መሪ ሆነው እንደማይመረጡ ሲረዱ «ዑለማ ዑለማን ይመርጣል እንጂ ሕዝቡ ምርጫው አይመለከተውም፞። የሚመርጡትን ዑለሞች ደግሞ እኛ እንመርጣቸዋለን። የመረጥናቸው ዑለሞች ደግሞ መሪዎቻቸውን ይመርጣሉ» የሚል አቋም አራመዱ። ሐጅ ዑመር እድሪስ ከ1968 እስከ 1985 ለ18 ዓመታትም የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ አባል፣ ከ1985-1986 ድረስ የመጅሊስ ሊቀመንበር (ፕሬዝዳንት) አማካሪ ሆነው አገለገሉ። በየካቲት 14 ቀን 1987 በአንዋር መስጂድ ግርግርና በመንግስት ጥቃት 10 ሙስሊሞች በመንግስት የጸጥታ አካላት ከተገደሉ በኋላ ሕዝቡን እንዲያረጋጉና የኢድ ሰላት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ ተደረገ። በ1988 ከቢሾፍቱ ከተማ መንግስት ለርሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ሰብስቦ የመጅሊስ አመራር ሲመርጥ ሐጅ ዑመር እድሪስም በድጋሚ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤና የዑለማ ምክር ቤት አባል ሆነው ተመረጡ። እስከ 1992 ድረስም በዚያው ቆዩ። ከ1993 እስከ ሚያዚያ 2001 የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት፣ ከሚያዚያ 2001 እስከ መስከረም 2005 የፌደራል መጅሊስ መስጊድና አውቃፍ ዘርፍ ኃላፊ፣ ከ2005 እስከ 2010 የፌደራል መጅሊስ የጠቅላላ ጉባኤው አባል፣ የመስጊድና አውቃፍ ዘርፍ ኃላፊ፣ እንዲሁም የዑለማ ምክር ቤት አባል ሆነው ቆዩ። ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ህዝበ ሙስሊሙና የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው በመጅሊስ ጉዳይ ጥያቄ ሲያቀርብ መጀሊስን በመወከል ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጋር ከቀረቡት መካከል ነበሩ። ከ2010 ሰኔ 26 እስከ ሚያዚያ 23 2011 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባቋቋሙት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብሳቢ ተደርገው ተሾሙ። በሚያዚያ 23/2011 የጊዜያዊ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ተደርገው ለ6 ወራት ተሹመው በሕገ ወጥ መንገድ ከ3 ዓመታት በላይ ቆዩ። ከሰሞኑ ደግሞ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ሐጅ ዑመር እድሪስንና ምክትላቸውን ዶ/ር ጄይላንን ጨምሮ አራት ዑለሞችን ከአመራርነት አንስቶ ወደ ፈትዋ ዘርፍ መደባቸው። ተቋሙ ከተመሠረተ ጀምሮ ላለፉት 46 ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች በአመራር ወንበር ላይ የነበሩት ግለሰብ ተቋሙ በዚህ ሁሉ ዘመኑ ለሕዝበ ሙስሊሙ ተገቢውን አገልግሎት ባለመስጠቱ ይቅርታ ጠይቀው በራሳቸው ፈቃድ ሊሰናበቱ ይገባቸው ነበር። ዕድሜያቸው 90 ሞልቷል። በፈትዋ ክፍል በሙፍቲነት እንዲያገለግሉ ሲወሰን በእምቢተኝነት ሕዝበ ሙስሊሙን ወደ መክፈል ድረስ የሚያደርሰው የስልጣን ፍቅር እንዴት ስር ቢሰድ ነው አቅል እስከ ማሳት የሚያደርሰው? ከ3 ሳምንታት በፊት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የመንግስታዊ ተቋማት ሪፎርምን እንዲገበኙ ተሰናድቶ በነበረው ጉብኝት ማጠናቀቂያ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሩት ስብሰባ ላይ 120 የምንሆን ሙስሊሞች ተገኝተን ነበር። ስለመጅሊስ ምርጫ አጀንዳ ሲነሳ ግን በተለያዩ መድረኮች «አላህ ሽቶብኝ ነው እንጂ እኔ ስልጣን አልፈልግም» ያሉትን ንግግር ተቃርነው ዛቻ ጀመሩ። ያው በተለመደው የሱፊያ ካባ ስር ሆነው «ደም ይፈሳታል እንጂ አልለቅም» ሲሉ በግልጽ ተናገሩ። ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂኡን!
Показать все...
# የሩሲያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ቪያቼዝላቭ ፖሎሲን በእስልምና ሕይዎቱን አስውቧታል!! ==================== ቬያቼዝላቭ ፖሎሲን በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በከፍተኛ ማዕረግ ያገለገሉ የተከበሩ ሰው ናቸው። በJune 26 1956 በሞስኮ የተወለዱት ቬያቼዝላቭ በ1980 በቤተ-ክርስቲያኗ ውስጥ የመፀሐፍ ጥቅሶችን እንዲያነቡ በአንባቢነት ተቀጠሩ። ከሞስኮ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ትምሕርት ዘርፍ አጥንተዋል፤ በ1978 በሶሾሎጂ ዲፓርተመንት ከሞስኮ ዩኒቨርስቲ ዲግሪያቸውን ጭነዋል። በኋላም ሞስኮ ውስጥ በሚገኝ ሴሚናሪ በስነ-መለኮት የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘት ችሏል። በ1983 በቤተ-ክርስቲያኗ ሲሰጥ የነበረውን ትምሕርት ተከታትሎ የድቁንና ማዕረግን ተቸሯል። በመቀጠልም የፔላናን ቤተ-ክርስቲያን መምሕር እና የቅዳሴ መሪ ሆኖ እንዲመራ በሐላፊነት ተሾሟል። ፖሎሲን እስከ 1985 ድረስ በተለያዩ ፓሪሾች በድቁንና አገልግሏል። በዱሻምቤ ከተማም የቤተ-ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ሆኖም ሰርቷል፤ ነገር ግን በሶቪዬት ኮሚኒስት አገዛዝ በደረሰበት ከባድ ጫና ምክንያት ከግዛቱ ሊሰደድ ችሏል። ከዚያም በሞስኮ ዲዮሲስ በሚገኘው በቸኛ የማተሚያ ቤት ውስጥ የትርፍ ጊዜ አስተርጓሚ ሆኖ ሰርቷል። በ1990 ፖሎሲን ወደ ሊቀ ካሐንነት በማደጉ የሩሲያ ፌደሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የሶቪዬት የበላይ አስተዳደር በመሆን ተመርጠዋል። እስከ 1993 የሐይማኖት ነፃነት ዓለማቀፍ ተጠሪ በመሆንም በሐላፊነት አገልግለዋል። በተመሳሳይ ጊዜም በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቲክ አካዳሚ ትምሕርቱን አጠናቆ በፖለቲካል ዘርፍ PHD ዶክትሬቱን ተቀብሏል። በከፍተኛ የመንግስት እና የቤተ-ክርስቲያን ሐላፊነት ያገለገለው ቪያቼዝላቭ ከብዙ ጥናት እና ልፋት በኋላ አዕምሮዬን ሲያስጨንቁ የነበሩ ጥያቄዎቼን ምላሽ በእስልምና ውስጥ ተሰድረው አገኘኋቸው፤ ለዓመታት የተጨፈኑት ዓይኖቼ ተገለጡ! ለረጅም ጊዜያት ምክንያቱን በማላውቀው ጭንቀት የተወጠረችው ልቤ ሸሐዳን በተቀበልኩ ቅፅበት በሐሴት ተፍነከነከች! ሲል ቬያቼዝላቭ እስልምና የሕይወት መድሕን መሆኑን ገልጿል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አልሰበሰብም . ጋዳፊ ከሞሞቱ በፊት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሆነውን ለሱ የመጨረሻ ስብሰባ የሆነውን ስብሰባ አልታደም። አልሰበሰብም ነበር ያለው። የጋዳፊ ዘመኖች የሚለው የሂዎት ታሪኩ ነው የተባለው መፀሀፍ ከታተመ በኋላ ብዙ ነገሮች ናቸው የተሰሙት። ለሱ የመጨረሻው የሆነው ስብሰባ ላይ ግን አልሰበሰብም ነበር ያለው። . ለምን እሰበሰባለሁ። ሄጀ ምንም ነገር ወደ ተግባር መለወጥ የማይችሉ፣ ምዕራባዊያን እና አሜሪካን ሳልጠይቅ ሚስት ማግባት አልችልም የሚል ስነልቦ ያለው የአፍሪካ መሪዎች ጋር አልሰበሰብም። ስለ ምዕራባዊያን ማንነት ስለ አሜሪካ ማንኛውም ነገር ሲነገሩ የሚያማቸው መሪዎች ናቸው አፍሪካ ህብረት ላይ የሚሰበሰቡት ስለዚህ አውቃቸዋለሁ። 32 አመት የጋራ ጥምር ጦር እንገንባ፣ ኒኩሌር በጋራ እናምርት፣ የጋራ መገባያያ ገንዘብ እንፍጠር፣ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ መርጠን እናድርግ፣ ምዕራባዊያንን በዚህ እንታገላቸው፣ ስትላቸው እጃቸውን አገጫቸው ላይ አድርገው ከማየት ውጭ ልመናን እንደ ሙያ ወርሰው ከሚኖሩ መሪዎች ጋር አልሰበሰብም። ለሰላምታ ከሆነ የሁሉም አገር መሪዎች ስልክ አለኝ ደውየ ሰላምታየን መጠየቅ እችላለሁ ነበር ያለው። ጋዳፊ በዛ በጨለማ ዘመን የምዕራባውያን ማንነት ተርድቶ በየ መድረኩ ፊትለፊት የተናገረ በኋላ ጥርስ ተክሶበት በኔቶ ጥምር ጦር የተገደለ ምረጥ የአፍሪካ መሪ ነበር። በምስሉ ላይ የሚታዪቴ ቀዳማዊ ሀይለስላሴን ጨምሮ ሌሎች ለአፍሪካ ጥሩ ሰርተዋል የተባሉ መሪዎች ናቸው። እሱ ፎቷቸውን በልብሱ ላይ አሰርቶ በኩራት ነበር እንዲህ የሚለብሳቸው። ሱሌማን አብደላ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ትልቅ ተመኝ! የሰው ልጅ ትልቁ ድክመቱ ትልቅ አስቦ አለመሳካቱ አይደለም ትንሽ አስቦ ተሳክቶለት ማቆሙ ነው፤ አንተ አጥብቀህ ፈልገኸው ፈጣሪ ያልሰጠህ ነገር የለም! ካለ ደግሞ ወይ ጊዜው አልደረሰም ወይ የተሻለውን ሊሰጥህ ነው። ወዳጄ ትልቁ ቦታ ይገባሀል! ትልቅ ተመኝ፣ ትልቅ ጠይቅ ከዛ እሱን ለማግኘት የምትችለውን ያህል ሞክር በተረፈው አምላክ ይጨመርበታል!
Показать все...
ስኬት! አሁን ዋጋ ከፍለህ ከጣፋጭ እንቅልፍህ ስትነሳ ስኬማ ሆነሀል፤ ምክንያቱም ስኬት በየቀኑ የምትኖረው ህይወት ነው እንጂ አሳደህ የምትይዘው ጭራ አይደለም! ስለዚህ ለፈጣሪህ ምስጋናህን ስታቀርብ ስኬታማ ነህ፣ ስፖርቱን ስትሰራ ስኬታማ ነህ፣ ሺወሩን ወስደህ ቁርስህን በልተህ ወደ ስራ ስትገባ ስኬታማ ነህ፤ ወዳጄ ራስህን ለማሳደግ በየቀኑ ዋጋ ስትከፍል በየቀኑ ከፍ የሚል የስኬት ፎቅ እየገነባህ ነው!
Показать все...
በጣም ኮ ሚገርም ነው እስኪ ስሙት እማ🙊🙊
Показать все...
00:34
Видео недоступноПоказать в Telegram
1.72 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.