cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethiopian University ExitExam Preparation

Our channel is committed to assisting students in successfully passing the #Ethiopian_University_Exit_Exam. We understand that not everyone has access to coaching services, which is why we provide free tutorial sessions and practice exams to offer support

Больше
Рекламные посты
9 407
Подписчики
+324 часа
-567 дней
+16130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ልዩ ነን! አንድ ሰው በአስገራሚ ሁኔታ ያስቀመጠውን አንድ ሃሳብ ላጋራችሁ፡- “አሉኝ የምትሏቸውን ነገሮች በሙሉ (ገንዝብ፣ ቁሳቁሱ፣ እውቀት፣ ውበት …) ተመልከቷቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሌሎች ሰዎች ጋር አሉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ሌላ ሰው በፍጹም የሌለው አንድና ብቸኛ ነገር እኛነታችን ብቻ ነው፡፡ የቀሩት አሉኝ የምንላቸው ነገሮች በሙሉ ሌሎች ሰዎች ጋር አሉ”፡፡ ለዛ ነው  ልዩ ናችሁ ያልኳችሁ  !! አዎ! ልዩ ናችሁ! እናንተነታችሁ ማንም ሰው ጋር ኖሮ አያውቅም፣ አሁንም የለም፣ ወደፊትም አይኖም! ስለዚህ ከሁሉም በፊት ራሳችሁን ሁኑ፣ ራሳችሁን ተቀበሉ፣ ራሳችሁን አክብሩ፣ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፣ ራሳችሁን ምሩ፣ ራሳችሁን ይቅር በሉ፣ ከራሳችሁ ጋር ደስተኞች ሁኑ፣ የግል ራእያችሁን ለይታችሁ እወቁና ኑሩት  ፡፡ "እዚህ ምድር ላይ ምንም አምሳያ የሌለው ልዩ ነገር እኔ ነኝ"። መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!
Показать все...
👍 8 2
ስለ CV አዘገጃጀት መማር ይፈልጋሉ ⁉️ አዎ ከሆነ መልስዎ አሁኑኑ ይህን ቻናል ይቀላቀላሉ @ethio1_exit_exam @ethio1_exit_exam @ethio1_exit_exam እድሰራለዎት ከፈለጉ @Ethio1_exam_bot ያናግሩን በሶስት(3) ቀን ውስጥ አዘጋጅተን እናስረክበዎታለን 🆚🙏መለያችን በጥራትና በታማኝነት አባሎቻችን የሚፈልጉትን service መስጠት ነው‼️
Показать все...
1
ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን 🎓 ሃሳብ እና አስተያየታችሁን እንዲሁም አብራችሁን መስራት ለምትፈልጉ መልዕክታችሁን አስቀምጡልን
TO ALL GRADUATE STUDENTS 🎓 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ❣️Heartfelt  CONGRATULATIONS to All the Graduates for their years of..                       💪hard work               🙇‍♂️unwavering perseverance,       🧑‍💻countless hours of dedication, 🙅‍♂️tireless efforts, and unyielding commitment to excellence! 🧑‍🎓 🎉Your remarkable achievements are a testament to your resilience and determination.🎉 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ❇️ For those who did not pass the Exit Exam, remember that setbacks are just stepping stones to success. Stay determined, keep working hard, and use this experience as motivation to do even better next time. ❗️Please be informed that our channel will provide you with all the necessary study materials and model exams at all times. ❤️ Best of luck to all of you ❤️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🅾️ For Fast and Reliable info..⬇️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬          @Ethio1_exit_exam @Ethio1_exit_exam @Ethio1_exit_exam
Показать все...
ለ ተፈታኞች Tip‼️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊 🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:  •📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ። •📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።  •📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። 📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ 🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ 🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።  🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ። 🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።  🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።  🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ 🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።   🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።  🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። 🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር።  🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ 🍁  • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። 🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።  🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት። 
Показать все...
👍 5 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ወደፊት!!! “ከጀርባችሁ ሆነው እማይጠቅማችሁን  ወሬ ስለሚያወሩ ሰዎች አትጨነቁ፡፡ ከጀርባችሁ የሆኑት እኮ በምክንያት ነው” ስለ እነሱ ማሰብና ለወሬያቸው ምላሽ መስጠት ማለት እነሱ ወዳሉበት ወደ ኋላ መመለስ ማለት ነው፡፡ ወደ ፊት! መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!
Показать все...
7👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል? የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል። የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ይህንንም ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ አድርሰዋል። በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል። "ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን" የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል። "ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል" ብለዋል። የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው፤ "ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ" ለቲክቫህ ተናግረዋል። ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡ ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።
Показать все...
👍 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግብ አስቀምጦ እንዴት ይሆናል ብሎ የሚጨነቅ ሰው ዘር ዘርቶ ተፈጥሮአዊ ጊዜውን እና አበቃቀሉን ከመጠበቅ ይልቅ እንዴት ? የሚለው ላይ ያተኮረ እንደሚበቅል ያላመነ ገበሬን ይመስላል . . . ~ ተፈጥሮን ያላመነ ገበሬ መሬት ውስጥ መቆየቱ ስለሚያሳስበው አለጊዜው እየቆፈረ ለማረጋገጥ ይሞክራል ዘሩንም ያበላሻል። ~ ዘሩን ከመሬት ያገናኘ ገበሬ በቅሎ እስኪያየው ድረስ በእምነት ይጠብቃል ምክንያቱም መሬት ውስጥ ነው ያለው ማለት፤ በወቅቱ መሬቱን ሰንጥቆ አይታይም ማለት ስላልሆነ ነው ። ~ ምን የዘሩት እና የሚያጠጡት ህልም አልዎት ? አለመብቀሉ የሚያሳስብዎት ? የሰው ልጅ ማተኮር ያለበት ዘሩ ላይ እና ከእርሱ የሚጠበቀው እንክብካቤ ላይ ነው። ሌላው ተፈጥሯዊ ጊዜውን ጠብቆ ይከናወናል። ~ ማንጎ የተከለ እና ስንዴ የዘራ በእኩል ወቅት እንዲበቅል አይጠብቅ ፣ አፈሩን አለስልሶ የተከለ እና እንዲሁ ደረቅ መሬት ላይ የዘራም እኩል ውጤት አይጠብቅ ፣ በየወቅቱ ያጠጣ የተንከባከበ እና ዘርቶ አረም እንዲውጠው በግድየለሽነት የተወ እኩል ምርት አይጠብቅም ። ~ ወዳጆቼ ; 1. ምንድነው የዘራውት ? 2. በየጊዜው እየተንከባከብኩ ነው ? 3. ውጤቱን አውቀዋለው ? 4. ትኩረቴ እንዴት ላይ ነው ወይስ የምሻው ውጣት ላይ ? ሌላው ተፈጥሯዊ ነው ። በእምነት መጠበቅ ብቻ ነው !!! መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!
Показать все...
👍 15
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ። ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት። ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ። ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል። ውድና የተከበራችሁ ተማሪዎች የሌሎቻችንም officially እስከሚለቀቅ በትእግስት እንጠብቅ። ይቀላቀሉን 👇👇👇
Показать все...
👍 11 2👏 1😁 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
Congratulations 🎉🎉🎉🎉🎉🎆🎆🎆 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ ☑️ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ☑️አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ☑️ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ☑️ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም ☑️ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ☑️ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ☑️አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ደብረ ብርሃን - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ☑️አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ተመራቂዎች አሁን ስራችሁን ጨርሳችኋል ይሄንን ነገር
Показать все...
👍 8 7
ራስን መቀየር! የማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ጊዜህን ልታጥፋ ስትል ንፋስ ልትጨብጥ እየሞከርክ እንደሆነ አስብ፤ የሰዎችን ፀባይ፣ የሀገርህን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱን፣ የአለቃህን ወይ የአሰሪዎችህን ፀባይ መቀየር አትችልም! ግን እንደምትችለው እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ ነገር አለ...ራስህን መቀየር ግን ትችላለህ! እመነኝ ወዳጄ አንተ ከተቀየርክ ነገሮች ሁሉ ይቀየራሉ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ብሎ ማመን እና የተግባር ሰው መሆን ነው።         መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬    ⬇️  join and Share⤴️ FOR MORE👇           🔶    @Ethio1_exit_exam   ✳️          🔶    @Ethio1_exit_exam   ✳️          🔶    @Ethio1_exit_exam   ✳️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Показать все...
👍 14🔥 2
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.