2 358
Подписчики
Нет данных24 часа
-67 дней
-1630 дней
Архив постов
2 358
🌹 በውበቷ ከባሏ የምትበልጥ መልካም ሴት ለባሏ ልታሳይ የሚገባት መልካም ስነ-ምግባርና በትዳር ላይ ልትሰጠው የሚገባው ፍቅር ምን መምሰል አለበት🌹📚 ኢማሙ አዝ-ዘሀቢይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ፦ «ሴት ልጅ ባሏ በእሷ ላይ ያለውን መብት ማወቅ ይገባታል። በራሷም ሆነ በንብረቷ ላይ ያለ ፈቃዱ እንዳትወስን፣ የባሏን መብት ከራሷ መብት አስቀድማ እንድትመለከት፣ የባሏን ዘመዶች መብትም ከራሷ ዘመዶች መብት በፊት እንድታስቀምጥ ይገባታል። ባሏ ከእሷ ጋር በሚገናኝበት ጊዜ ምቾትና ደስታ እንዲያገኝ በንጽሕናና በሌሎችም መልካም ዝግጅቶች ራሷን ማስዋብ ይገባታል። በውበቷ ምክንያት በባሏ ላይ መመካት የለባትም፤ እሱም አስቀያሚ መልክ ካለው በዚያ ምክንያት ልትነቅፈውና ልትንቀው አይገባትም።» 🌿 አል-አስማዒይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ «ወደ በረሃ ሄድኩ። በዚያም በጣም ቆንጆ የሆነች ሴት አገኘሁ፤ ባሏ ግን መልኩ ያማረ አልነበረም። እኔም፦ “እንደዚህ ያለ ሰው ሚስት ሆነሽ ለመኖር እንዴት ተስማማሽ?” አልኳት። እሷም እንዲህ አለችኝ፦ “አንተ ሰውዬ፣ አዳምጠኝ! ምናልባት እሱ በእሱና በፈጣሪው መካከል ካለው ግንኙነት አንጻር ከእኔ የተሻለ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እኔን ለእሱ ምንዳ አድርጎ ሰጠው ይሆናል፤ እኔ ደግሞ ምናልባት በአላህ ዘንድ የማይወደድ ነገር ፈጽሜ ስለነበር እሱን ለእኔ ቅጣት አድርጎ ሰጠኝ ይሆናል።”» 🌸 ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የተነገረ ንግግርም አለ፦ «እናንት ሴቶች ሆይ! ባሎቻችሁ በእናንተ ላይ ያላቸውን መብት ብታውቁ ኖሮ፣ ከእናንተ መካከል አንዷ በባሏ እግር ላይ ያለውን ቁስል አቧራ በምላሷ በማበስ ታጸዳ ነበር።» 🌷 ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ «ከሴቶቻችሁ የጀነት ሰዎች የሆኑት አፍቃሪና ለባሎቻቸው ርኅሩኅ የሆኑት ናቸው። እነሱ ባሎቻቸውን ቢያስቀይሙ ወይም ባሎቻቸው ቢያስቀይሟቸው፣ ወደ ባሎቻቸው ይመጣሉ፤ እጃቸውንም በእጃቸው ውስጥ በማስገባት፦ “አንተ እስክትረካና እስክትደሰት ድረስ አይኖቼን አላሳርፍም” ይላሉ።» 🌺 በመጨረሻም የሚስት ሥነ-ምግባርና ከባሏ ጋር የሚኖራት አያያዝ ያማረ ሊሆን ይገባል፦ ሚስት በባሏ ፊት ሐያእንና ክብርን መጠበቅ፣ እሱን በምትመለከትበት ጊዜ አክብሮትን ማሳየት፣ በሸሪዓ የሚፈቀዱ ነገሮች ላይ ትእዛዙን መታዘዝ፣ ሲናገር በጥሞና ማዳመጥ፣ ወደ ቤት ሲመጣ በመልካም አቀባበል መቀበልና የሚያስቆጣውን ነገር በተቻላት መጠን መተው ይገባታል። ከቤት ሲወጣ በሚገባ መሸኘት፣ ወደ መኝታ ሲመጣ ለግንኙነት ለጅማዕ ዝግጁ መሆንና በሚፈልገው መልኩ ማስደሰት፣ በሌለበትም ጊዜ በአልጋው፣ በንብረቱና በቤቱ ላይ አደራዋን መጠበቅ ይገባታል። ሽታዋን ማሳመር፣ አፏን በሲዋክ ማጽዳት፣ ሚስክና ጥሩ ሽቶ መጠቀም፣ ባሏ ባለበት ጊዜ ራሷን ማስዋብ፣ ሐሜትን መተው፣ የባሏን ቤተሰቦችና ዘመዶች ማክበር፣ ከባሏ የምታገኘውን ትንሽ መልካም ነገር እንኳን እንደ ትልቅ ጸጋ መቁጠር ይገባታል።» 📚 ምንጭ፦ ኪታቡል ከባኢር፣ ገጽ 174–175 ተብሎ ተጠቅሷል።
2 358
እሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ በማብዛት ወንጀሎች እንደሚስ'ሰረዙና የሚያሳስቡ ሓጃዎች/ጉዳዮችም እንደሚሳኩ የነገሩን ነቢያችን ሙሐመድ ላይ ሰለዋት እናብዛ፤
اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى آلہ وصحبہ وسلم
عدد ما ذكرہ الذاكرون وعدد ما غفل عن ذكرہ الغافلون.
ዛዱል-መዓድ

ለቀለብህ ብቻ ሳይሆን ለቀልብህም ተጨነቅ!
ሆድ እንደሚራበው ሁሉ ቀልብም ይራባል፤ አካል እንደሚታመመው ሁሉ ቀልብም ይታመማል፤ ቆዳ እንደሚደርቀው ሁሉ ቀልብም ይደርቃልና ቀልብ ከሚያረጥቡ ነገሮች በጭራሽ አትራቅ!
በፅኑ የታመሙ ሰዎችን ጎብኝ፤ ጀናዛ እጠብ/ሸኝ፣ ለሕድ ውስጥ ገብተህ የሞተን ሰው ቅበር፣ ይህን ማድረግ ባትችል እንኳ ጠጋ ብለህ ሲቀበር ተመልከት፣ ተሳተፍ፤
ሱናውን ጠብቀህ ቀብር መዘየር አብዛ፤
አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ጋር መዋል አዘውትር።
አላህን በሚገባ የሚፈሩ ሰዎችን ዘይር/ ቅረብ።
ቁርኣንን በጥሞና ማንበብና ማዳመጥ አብዛ።
ሰላትህን በሰዓቱና በስርዓቱ ልብና ሃሳብህን ሰብሰብ አድርገህ ተረጋግተህ ስገድ።
ከዚክርና ዱዓ መቼም አትራቅ።
ሐላልን እንጂ ሐራምን፣ ወይም አጠራጣሪን አትመገብ።
በዚህ ዘመን ይህንና መሰል ነገሮችን አድርገህም ከቀልብ ድርቀት መዳን ሊከብድ ይችላልና የልብህን ጤንነት ችላ አትበል/ይ!
ቀን ከለሊት ለቀለብ እየተጨነቅክ የልብህን ጉዳይ አትርሳ/ ሺ።
رزقني اللہ وإياكم قلبا سليما، ورزقا كريما.
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ዛዱል-መዓድ
2 358
ኒካሕና ቃዲ
~
እንደሚታወቀው በኢስላም የትኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
ወሊይ ከሌለስ? በዚህን ጊዜ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ስለዚህ ኒካሕ ለማሰር ቃዲ የሚያስፈልገው ወሊይ ለሌላት ሴት ነው ማለት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له)
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል]
በተጨማሪም ወሊዮች ያለ ተጨባጭ ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ከዚህ ውጭ አባት ወይም ሌላ ወሊይ ወይም ወኪል ካለ ኒካሑን የሚያስሩት እነሱ እንጂ ቃዲዎች አይደሉም። ወሊይ ወይም ወኪሉ "ሰጥቻለሁ" ካለ፣ አግቢው ወይም ተወካዩ "ተቀብያለሁ" ካለ ኒካሑ ታስሯል። ኹጥባውን (ሸርጥ ካለመሆኑም ጋር) ወሊይ ወይም ሌላ ቦታው ላይ የተገኘ ሰው ሊያደርገው ይችላል።
ኒካሕ ለማሰር የተለየ ውስብስብ መስፈርት የለም። የዐረብኛ ቃላት መጠቀምም አይጠበቅም። መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን መስጠትና መቀበል ከተገኘ ኒካሕ ታስሯል። ስለዚህ በሃገራችን በሰፊው እንደሚደረገው ወሊይ እያለ ቃዲ መጥራት አይጠበቅም። ቃዲዎች ወሊይ ባለበት ሁኔታ ኒካሕ ለማሰር አትቀደሙ።
ወሊይ የሆናችሁ ሰዎች ደግሞ ቃዲዎችን ለሰርግ ከጠራችሁ እንደማንኛውም እድምተኛ ተስተናግደው ይመለሱ እንጂ እዚያው ተቀምጣችሁ ለነሱ ውክልና አትስጡ። "ልጄን እከሊትን ድሬሃለሁ" ማለት ያቅታችኋል እንዴ? ምንም የተለየ የተቀመጠ ቃል የለምኮ። እሱም "ተቀብያለሁ" ካለ፣ ቦታው ላይ ሁለት ታማኝ ምስክሮች ከኖሩ ኒካሑ ታስሯል አለቀ። በሀገር እያለህ፣ ዐቅልህ ጤነኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ከፊትህ ለሚፈፀም ጉዳይ ውክልና ትሰጣለህ? ምንም የሚያስፈራ ነገር የለምና እራስህ ፈፅመው። ሁሉም ነገር በቃዲ በኩል እንዲያልፍ መደረጉ አንዳንድ የእርጎ ዝንብ የሆኑ ሹማምንት በማያገባቸው የእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር እየከፈተ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 14/2017)

ያ ረቢ !!
መረጋጋትንና እርካታን ፍለጋ
ብዙ መንገድ ተጓዝን ነገር ግን...
አንተ ዘንድ ብቻ እንጂ አላገኘናቸውምና
እባክህን ወደ አንተ ጥሩ አመላለስን መልሰን ።
2 358
የአቡ በክር (ረዲየላሁ ዓንሁ) ዱዓ ከነበሩት ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡-
«አላህ ሆይ! እምነትን (ኢማንን) እርግጠኝነትን የቂንን ደህንነትን እና ቅንን ሀሳብ ኒያ ለግሰኝ።»
كانَ مِنْ دُعَاءِ أَبِي بَكْرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
«اللَّهُمَّ هَبْ لِي إِيمَانًا وَيَقِينًا وَمُعَافَاةً وَنِيَّةً».
[اليقين لابن أبي الدنيا(٣٣)].
This was among the supplications (du'a) of Abu Bakr (may Allah be pleased with him):
"O Allah, grant me faith, certainty, well-being, and a sound intention."
[Al-Yaqin by Ibn Abi Al-Dunya (33)]
2 358
ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን። ትዕግስት እንደ
ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ
መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው።
2 358
ክብሩን ሲያጣ...
ፈረስ ለግልቢያና ለውብ ኮርቻ አልበጅም ሲል ልክ እንደ አህያ እቃ መጫኛ ይሆናል፤
ላምና በሬም ለርቢና ለእርሻ አልበጅም ሲሉ ለቢላዋ ይዳረጋሉ፤
ቢላዋም ስጋ አልቆርጥም ሲል እንጨት መሰንጠቂያ ይደረጋል፤ ወዘተ... ማንኛውም ለተሰራለት ዓላማ የማይውል ነገር ክብርና ደረጃውን ያጣል።
አንተም/ቺም ለመልካም ሥራና ለጀነት አልበጅም ካልክ/ሽ (አላህን سبحانہ وتعالى ካልታዘዝን) ጀነትን ተነፍገን ለጀሀነም እሳት መዳረግ አይቀርምና ጠንቀቅ እንበል!
በሁለቱም ዓለም ውድና ክቡር እንድንሆን ለተፈጠርንለት ዓላማ እንኑር።
ዛዱል መዓድ
2 358
*✨ የቀኑ ማስታወሻ ✨*
_"በህይወትህ ውስጥ ምንም ያህል ነገር ቢበላሽ እና በሩ ቢዘጋብህም ተስፋ አትቁረጥ!_
_አላህ አንድን በር ሲዘጋብህ፣ ከዛ የተሻለ እና የበለጠ በር ሊከፍትልህ ስለፈለገ ነው።_
_እሱ የሰጠህንም ሆነ የከለከለህን ነገር በምክንያት እና ለበጎ እንደሆነ አምነህ በምስጋና ተቀበል፤ ልብህ ሁልጊዜ ሰላም ያገኛል!"_
*🤲 አላህ ቀናችንን ሙሉ በሙሉ በሰኪና እና በበረካ ይሙላልን!
2 358
የሰው ልጂ ትልቁ የህይወት ስኬቱ ለጌታው ምርጥ ባሪያ መሆን ነው ።
2 358
በነገራችን ላይ...አግብቶ ዝሙት የፈጸመ ሰው በሸሪዓ ፍርዱ በድንጋይ ተወግሮ እስከ ሞት መቀጣት ነው። ይህ ደግሞ የዱንያ ውርደቱ ብቻ ሲሆን፣ የአኼራው ቅጣት ግን እጅግ የከፋ ነው!
ትዳር ያላችሁም ሆናችሁ ያላገባችሁ፡ ከማይፈቀድላችሁ (አጅነቢይ) ጋር በስልክም ሆነ በሶሻል ሚዲያ፣ የምትቀላለዱና
የምትንዘላዘሉ ሁሉ ልብ በሉ! ሸይጧን በአንድ ጀምበር ዝሙት ውስጥ አይጥላችሁም፤ መንገዱን የሚጀምረው በ«ቀላል ወሬ»እና «በንጹህ ጓደኝነት» ስም ነው።
አላህ «ዝሙትን አትቅረቡ!» ያለው ለዚህ ነው። ዛሬ ቀላል የመሰላችሁ ማውራት መጨረሻው ወደማይቀለበስ ውርደት፣ ወደ ቤተሰብ መፍረስና ወደ አላህ ቁጣ እየነዳችሁ ነው።
2 358
فَلْيَضْحَكُوا۟ قَلِيلًۭا وَلْيَبْكُوا۟ كَثِيرًۭا جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
ጥቂትንም ይሳቁ፡፡ ይሠሩት በነበሩት ዋጋ ብዙን ያለቅሳሉ፡፡
2 358
ኢላሂ!
አንተ ጌታዬ ነህ፤ እኔ ደግሞ ደካማ ባርያህ ነኝ።
አንተ ፈጣሪ ነህ፤ እኔ ደግሞ ወንጀለኛ ፍጡርህ ነኝ።
አንተ ሰጪ ነህ፤ እኔ ደግሞ ለማኝህ ነኝ።
ኢላሂ…ወንጀሌ ቢያንስ ኖሮ እኮራ ነበር፤ እዝነትህ ባይኖር ኖሮ እጠፋ ነበር። ግን የኔ ወንጀል ታላቅ፣ ያንተም እዝነት ከዚያ በላይ ታላቅ ሆነና ይኸው ደጅህ ላይ ተደፍቻለሁ።
ያ ረብ! አንተ ካባረርከኝ ወዴት እሄዳለሁ? ያንተ በር ከተዘጋብኝ የማንን በር አንኳኳለሁ? አንተ ከኔ ሌላ ብዙ ባርያዎች አሉህ፤ ለኔ ግን ካንተ ሌላ አምላክ የለኝም። ወንጀሌን ሳስብ እፈራለሁ፤ ራህመትህን ሳስብ ግን እረጋጋለሁ።
አላህ ሆይ! ያንተን ትዕዛዝ በመጣስ በድፍረት ያሳለፍኳቸውን እድሜዎቼን ይቅር በለኝ። ይህንን እንባዬን እንደ ቶውባት ቆጥረህ፣ ያንን የጠቆረ መዝገቤን ይቅር በለኝ። እኔ ወንጀለኛው ባርያህ ነኝ፤ አንተ ግን ሩሩህ ጌታ ነህና ማረኝ።