cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Yeshua Apologetics Ministry

➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር ▼ @Yeshua_Apologetics_Ministry

Больше
Рекламные посты
1 416
Подписчики
+924 часа
+317 дней
+10630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ከእኔ አብ ይበልጣል? ብዙ አርዮሳውያን ሆነ ሙስሊም ወገኖቻችን ይህንን ጥቅስ መሠረት አድርገው ኢየሱስ ፍጡር ነው ከአብ ያንሳል ይሉናል። እስኪ እንቃኘው! “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ #ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”   — ዮሐንስ 14፥28 ክርስትና አንድ አምላክ ብቻ መኖሩን ቢያስተምርም ይህ አንዱ አምለክ ሦስት አካላት እንዳሉት ስለሚያስተምር በነዚህ አካላት መካከል የሥራ ድርሻ (function) ወይም የደረጃ (rank) ብልጫ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ በእግዚአብሔር በራሱ ሕላዌ ውስጥ የሚገኝ እንጂ ከእርሱ ውጪ የሚገኝ ባለመሆኑ በሥላሴነት ከሚኖረው ከአንዱ አምላክ ውጪ የሚገኝ አካል ብልጫ እንዳለው እስካልተነገረ ድረስ ምንም የሚፈጥረው ችግር የለም፡፡ በነዚህ ቦታዎች የተጠቀሰው μείζων(ሜይዞን)  የሚለው የግሪክ ቃል ደረጃን እንጂ የግድ የባሕርይ ብልጫን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ማሳያ አንድ፦ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚያንሰው #ይበልጠዋልμείζων[ሜይዞን]።   — ማቴዎስ 11፥11 ይህ ማለት በመንግሥተ ሰማይ ያለው አካል በባሕርይ ይበልጠዋል ማለትም በመንግሥተ ሰማይ ያለው ፈጣሪ ዮሐንስ ፍጡር ነው ማለት ማለት አይደለም። ሁለቱም ፍጡሮች ናቸውና ነገር ግን በሥራ ድርሻ የደረጃ ብልጫን ነው የሚያሳየው። ማሳያ ሁለት፦“እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ ከእነዚህም #የሚበልጥ ሜይዞን[μείζων]  ያደርጋል።”   — ዮሐንስ 14፥12 ይህም ማለት እኛ በባሕሪያችን ከክርስቶስ እንበልጣለን ማለት አይደለም። በአጭሩ አንድ አካል ከሌላው በሥራ ድርሻ፣ በሥልጣን ወይም በደረጃ ይበልጣል ማለት የባሕርይ ብልጫ አለው ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ለምሳሌ ያህል የአንድ አገር መሪ በሥራ ድርሻ፣ በሥልጣንም ሆነ በደረጃ በስሩ ከሚተዳደሩት ዜጎች ይበልጣል፡፡ ይህ ማለት ግን እንደ ሰው ያለው ዋጋ (Value) ከማንም ይበልጣል ማለት አይደለም፡፡ ባል የቤተሰብ ራስ እንደመሆኑ መጠን ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ከሚስቱ ሊበልጥ ይችላል ነገር ግን ወንድ እንደ ሰውነቱ ከሴት ይበልጣል ወይም ሴት ከወንድ ታንሳለች ማለት ግን አይደለም፡፡ የግሪክ አዲስ ኪዳን የባሕርይ ብልጫን ለማመልከት “ዲያፎሮስ”[διάφορος] የሚል ሌላ ቃል የሚጠቀም ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርዩ ከመላእክት የላቀ መሆኑን ለማመልከት ዕብራውያን 1፡4 ላይ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ #ይበልጣል[διαφορώτερον]።   — ዕብራውያን 1፥4 በሥላሴ አካላት መካከል የሚገኘውን ግንኙነት ለማመልከት ግን ይህ ቃል ጥቅም ላይ ውሎ አናገኝም፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብ ከወልድ መብለጡ መነገሩ የመለኮታዊ ባሕርይ ብልጫን ሳይሆን የሥራ ክፍፍልን እና ወልድ ሥጋን በመልበስ መለኮታዊ ክብሩን ትቶ ወደ ምድር እንደመምጣቱ መጠን (ፈልጵስዩስ 2፡5-11) የደረጃ ብልጫን ብቻ የሚያመለክት በመሆኑ የኢየሱስን አምላካዊ ባሕርይ ከአብ የሚያሳንስ አይደለም፡፡
Показать все...
👍 10 8👏 2
ኢየሱስ አምላክ ነውን? እስኪ ይህቺን ቪዲዮ እንጋብዛችሁ። ብዙዎቹን በቻናላችን ላይ ዳሰሳ አድርገናል ወደ ላይ ከፍ ስትሉ ታገኙዋቸዋላችሁ። ይቺን ቪዲዮ ተጋበዙ፦ https://vm.tiktok.com/ZMrdWgekn/
Показать все...
👍 6

👍 3
🚩 ይህ የወንድማችን የመሐመድ አበባው YouTube ገጽ ነው። ይህ ወንድማችን በእስልምና ዙሪያ የሚያገለግል የተወደደ ወንድም ነው። Subscribe እና Share በማድረግ አግዙት!
Показать все...
12👍 5
Показать все...
በእስልምና የድነት ዋስትና አለን?

https://vm.tiktok.com/ZMr1jdhMc/ 🚩 ለፈገግታ 😁
Показать все...
🥰 5
በእንተ መስቀሉወ ትንሣኤ ❞ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ             ✟አሐዱ አምላክ✟ “ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው #ለዚህም_ነገር_እኛ_ሁላችን_ምስክሮች #ነን፤” — ሐዋርያት 2፥32 የታሪክ መዛግብት ድምጻቸውን ከሚሰጧቸው ከአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ክስተቶች መካከል አንደኛውና እውቁ ክስተት የጌታችን እና መድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤው ነው። ይህንን ታሪካዊ ሐቅ ሊካድ እና ሊሸፈን የማይቻል በመሆኑ የክርስትና ተቃዋሚዎች በዘመናቸው የተለያዩ መላምታዊ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ ይስተዋላሉ። በክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ላይ ኢአማንያን በዋነኝነት ሶስት አይነት የክህደት ርዕዮተ ሐሳቦች ያነሳሉ፦ ♦️1ኛው ነባቤ ቃል Mythic Theory ይባላል። ሁሉም የክርስቶስ ተአምራቶች እና በታሪኩ ላይ የተዘገቡት ክስተቶች ሁሉ ከአይን ምስክሮቹ በኋላ የተፈጠሩ ፈጠራዎች እንጂ ከመጀመሪያዎቹ ምንጮች የተቀዱ አይደሉም የሚል መላምት ነው። በዚህ መላምት የክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ ሐሳብ የሐዋርያቶቹ አልያም የመጀመሪያዎቹ የአይን ምስክሮች ዘገባ ሳይሆን ከእነርሱ በኋላ የተፈጠረ አፈታሪክ ነው ባይ ሐሳብን የያዘ ነው። ♦️2ኛው ነባቤ ቃል Conspiracy Theory ነው። በዚህ መላምት የታሪኩ ደራሲያን ወይም ፈጣሪዎች ደቀመዛሙርቱ እንጂ የክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ክውን እውናዊ ገሀድ አይደለም የሚል መላ ምት ነው። ♦️3ኛው ነባቤ ቃል Hallucination Theory ነው። በዚህኛው እሳቤ ሐዋርያቱም ሆኑ ኢየሱስ ተገለጠልን ያሉ ሌሎች ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ሞት እና ትንሣኤ እምነት ድምዳሜ ላይ የደረሱት በጭንቅላታቸው በተፈጠረው የሳይኮሎጂ ችግር ምክንያት ባዩት ቅዠት (Hallucination) ነበር የሚል መላምት ነው። ምንም እንኳን አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ሐይሎች ታሪኩን ለማድበስበስ ቢሞክሩም አብዝሃኞቹ የታሪክ እና የክታባት ስኮላሮች(ሊቃውንት) በአንድነት የሚመሰክሩለት ነባራዊ ሐቅ የክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ሞት እና ትንሳኤ ነው ። ጌሪ ሃበርማስ የተባለው የስነ መለኮት አጥኚ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ላይ በምሁራን የተዘጋጁትን ጽሑፎች በመሰብሰብ ባደረገው ጥናት መሠረት ወደ 75 በመቶ የሚሆኑት ምሁራን ክርስቶስ ከሞት መነሳቱን መቃብሩ ባዶ መሆኑን የሚደግፉ መሆናቸውን አሳይቷል[¹]።  አብዝሃኞቹ አጥባቂያን ሆኑ ለዘብተኛ ምሁራን በዚህ ታሪካዊ ክስተት እማኞች እና አቀንቃኞች ናቸው። እንደ ፓሪሽ ሳንደርስ የመሳሰሉ ሙህራን የክርስቶስን ታሪክ ዙሪያ ገባውን ሁሉ ካጠና በኋላ <<ጥርጣሬ አልቦ ወይም የማይካዱ ሐቆች>> ብሎ ከዘረዘራቸው 8 ነጥቦች መካከል አንደኛው የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት እንደሆነ ይገልጽልናል[²]። ጆን ዶሚኒክ ክሮሳን የተባለው ምሁር ደግሞ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት ታሪክ እንደ ማንኛውም እውናዊ ታሪካዊ ክስተት እርግጠኛ የምንሆንበት ክስተት እንደሆነ ይነግረናል[³]። በነገረ መለኮት ትንታኔውና በምንባባዌ ህያሴው የሚታወቀው ስመጥሩ ኤቲስቱ ባርት ኧርማን የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ላለመቀበል ጥረት ቢያደርግም የክርስቶስ ተከታዮች ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ ማመናቸው በፍጹም አጠረጣሪ ጉዳይ እንዳልሆነ ይነግረናል። ይህም የሆነበትም ምክንያት ሲያስረዳ ክታባዊ ቀዳማይ ምንጮች በዚህ ዙሪያ ላይ ያላቸው ወጥነት እንደሆነ ያስረዳል[⁴]። ምሁራን በዚህ ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ያስቻላቸው ጉዳይ የታሪኩ ማስረጃዎች በታሪክ መዛግብት ተአማኒነት ሚዛን ላይ ሲሰፈሩ ሚዛን ደፍተው ስለሚገኙ ነው። የአንድ ታሪክ የማስረጃ ጥንካሬው ከፍተኛ ነው የሚባለው ለትርክቱ ቅርብ የሆኑ የአይን ምስክሮች ሲኖሩና የምስክሮቹ ተአማኒነት ከፍተኛ ሲሆን ነው። የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት እና ትንሳኤ ታሪክ ይበልጡን ጠንካራ ክስተት የሚያደርገው ሌላኛው ማስረጃ በገለልተኛ የታሪክ ድርሳናትም የሚደገፍ እውነታ መሆኑ ነው። ይሄም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ስለራሱ ከመመስከሩም ባሻገር ሌሎች የታሪክ መጽሐፍት ስለ እውነተኝነቱ ምስክሮቹ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ በዘመናችን ባሉ ምሁራን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘው የአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሮማዊው የታሪክ ጸሐፊ እና ፖለቲከኛ ታሲተስ (Tacitus) ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ከጥቂት ቀናት በኋላ መነሳቱን ኔሮ ደግሞ በክርስቲያኖች ላይ ያደረሰውን አረመኔያዊ ስደት ሁሉ ጽፏል[⁵]። ሌላው የአንደኛው መቶ ክፍለዘመን (52 AD.)  ግሪካዊው የታሪክ ጸሐፊ ታለስ (Thallus) ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስቅለትና በወቅቱ ምድር ጨለማ እንደነበረች ዘግቧል። ይህ ዘገባ ደግሞ ከሉቃ 23:44-46፣ ማቴ 27:45-50፣ ማር 15:33-37 ከተዘገበው ዘገባ ጋር አንድ አይነት መሆኑ የመጽሐፍ ቅዱሳችንን እውነተኝነት እና ተአማኒነት ከፍ ያደርገዋል። ክርስትናን በመቃወም የሚታወቀው የሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኬልሰስ (Celsus[117 AD]) <<ኢየሱስ ታላቅ[አምላክ] ቢሆን ኖሮ ከተሰቀለበት መስቀል በድንገት ለመጥፋት መለኮታዊ ትዕዛዝን በራሱ ላይ ያውጅ ነበር>> የሚልን ሐሳብ ሲያንጸባርቅ እንመለከታለን[⁶]። በተጨማሪም የሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጸሐፊ እና የክርስትና ተቃዋሚ የታሪክ ጸሐፊ ሉቺያን (Lucian of Samosata) ስለ ክርስቶስ ስቅለት እና ተከታዮቹ በመጽሐፉ/"The Passing of Peregrinus"/ ማስፈሩ በአዎንታዊ መግገድ ባይሆንም ምስክርነቱን ሰጥቷል። እነዚህ ሁሉ የታሪክ ዘጋቢዎች ድምጻቸውን የሚሰጡለት ሐቅ የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት እና ትንሣኤ አረጋጋጭ ህያው የታሪክ ምስክሮች መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው። ስለዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ነባቤ ቃል (Resurrection Theory) ከላይ  ከተመለከትናቸው ከሶስቱ መላምቶች አንጻር ሲስተያይ ከፍተኛ ተአማኒነትን የተጎናጸፈ ሐቅ ነው። ❝...ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አስሮ ለሰይጣን - አግዓዞ ለአዳም ሰላም - እምይዜሰ ኮነ - ፍሰሐ ወሰላም...❞ ✍Jonathan(Yeshua Apologetics) 🔖ማጣቀሻዎች፦ [¹] Resurrection Research from 1975 to Present, What are Critical Scholars Saying?, Journal for the Study of the Historical Jesus,3.2(2005), page 135-153 [²] E.P Sanders, Jesus & Judaism, p.11 [³] John Dominic Crossan, Jesus:A Revolutionary Biography, p.145 [⁴] Bart Ehrman, How Jesus Become GOD?,page 98 [⁵] Tacitus, The Annals, Book xv.44[Loeb edition, vol.V, p.283,1981] & Book 15, Chapter 44 [⁶] Origen: Contra Celsum, p.68
Показать все...
3👏 3👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 7 2