cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🧕🏽IKRAM ISLAMIC TUBE 🧕🏽

አላህ ውብ ነው ውብ ነገር ይወዳል !! በዚህ ቻናል በየ ቀኑ የጥበብ ስራዎች ጣፋጭና አስተማሪ ታሪኮች የቁርዐን video ኢስላሚክ Pic....join በማለት መቀላቀልና ለወዳጅ ዘመድ share በማድረግ ይተባበሩን ♥ Join @Ikramislamictube

Больше
Рекламные посты
298
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Eid Mubarak 🌴
Показать все...
Ramadan Mubarak to all the Muslims all over the world! 🌙 ❤️
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአፍሪካ 300 መቶ ሺ  ሰዎችን ወደ እስላም ብርሃን የጠሩ ታላቅ ሸይኽ!!👏 ሰዒድ አህመድ ማሽሁር አል-ሀዳድ (Sayyid Aḥmad Mashhūr al-Ḥaddād) ይባላሉ፤ ዘውትር ከቤታቸው ውጪ ይቀመጣሉ እናም በበሩ የመሚያልፉ የሌላ እምነት ተከታይ ሰዎች ባገኙ ጊዜ ለሻይ በፍቅር ወደ ቤታቸው  ግብዣ ያደርጋሉ። ታዲያ ውስጥ የዘለቁ ሰዎች ሻዩን አጣጥመው ሳይጨርሱ "ላ ኢላሃ ኢላ ላሏህ ሙሐመድ ረሱሉላህ" ብለው ሸሀዳ ይይዛሉ፤እስልምናን ይቀበላሉ። ሸይኹ የተለያዩ አማልክትን፤ግዑዝ አካላትን የሚያመልኩ ሰዎችን ማሰለም፤በሚሺነሪዎች የከፈሩትን ወደ እስልምና መመለሰን አላህ አግርቶላቸዋል።ትንሽ የሚያወሩ፤በብዙ የሚያሰላሰሉ፤ሳቃቸው ከፈገግታ ያልተሻገረ፤ ሰዎችን እንደ አረዳዳቸው የሚያስተናግዱ አሊም እንደሆኑ የዘገበው ክላሪፋይንግ ላይት የተሰኘ ገፅ ነው።
Показать все...
አጠር ያለ አስተማሪ ታሪክ አንብቡት ትማሩበታላቹ🍁 አንዲት ሴት በምሬት ስታለቅስ ኑሕ ዐሰ ተመለከቷት'ና፦ «ለምን ታለቅሻለሽ?» አሏት። ሴትዮዋም፦«በለግላጋ የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኝ ጎረምሳ ልጅ ሞቶብኝ ነው» አለቻቸው። ኑሕም ዐሰ፦ «የልጅሽ እድሜው ስንት ነበር...?»አሏት። ሴትዮዋም፦ «ገና እኮ 300 አመቱ ነው» አለቻቸው። ኑሕ ዐሰ ሊያፅናኗት እየሞከሩ፦ «ታድያ እድሜያቸው ከ60-70 የማይሻገሩ ኡመቶች መሀል ብትኖሪ ምን ልትሆኚ ነው?» በማለት ጠየቋት። ሴትዮዋም፦ «እንዴ! ከ60-70 አመት ብቻ የሚኖሩ ኡመቶች አሉ እንዴ?» ብላ በመገረም ጠየቀቻቸው። ኑሕም፦ «አዎን» አሏት። ሴትዮዋም፦ «ግን ይችን ውስን አመት በህይወት ሲቆዩ አላህን ያምፁታል» በማለት አስከትላ ጠየቀቻቸው። (የኛን ጉድ አላየች...) ኑሕም፦ «እንደውም አብዝኻኛዎቻቸው አማፅያን ናቸው» ብለው ጉዳችንን አወጡት። ሴትዮዋም፦ «ግን እነዝያ ኡመቶች ለውስን ግዜ ብለው ዱንያ ላይ ይስገበገባሉ?» ስትል ጥያቄዋን ሰነዘረች። ኑሕም፦ «አዎና! እንደውም ዋና ጭንቀታቸው ዱንያ ነው፤ ጥቂቶቻቸው ሲቀሩ» አሏት። ሴትዮዋም፦ «ታድያ በመካከላቸው በሚፈጠሩ ጉዳዮችስ ይወቃቀሳሉ?» ስትል ጠየቀች። ኑሕም፦ «ኧረ እንደውም በትንንሽ ጉዳዮች ይገዳደላሉ» ብለው መለሱላት። ሴትዮዋም፦ «ግን እንደው ለዚህች አጭር እድሜ ብለው ጎጆ ይሰራሉ...?» ስትል ጠየቀቻቸው። ኑሕም፦ «ወይ ጎጆ...! ኧረ እንደውም ለመቶዎች አመታት የሚቆዩ ትላልቅ ህንፃዎችን ነው ሚገነቡት፤ ግና ትተውት ይሞታሉ» አሏት። ሴትዮዋ በምትሰማው ነገር ተደንቃ፦ «ኧረ ወድያ...! እኔ እዝያ ኡመት ውስጥ ብሆን ህይወቴን በሙሉ አንዲት ዛፍ ስር ሱጁድ አድርጌ እጨርሳት ነበር(ደሞ ለ60 አመት!) » አለቻቸው ይባላል... @Ikramislamictube
Показать все...
በአላህ ስም *🍃 4ቱን እዝነትህን አትንፈጋቸው* ① ሚስትህን ② ልጆችህን ③ ቤተሰብህንና ④ ጓደኞችህን *🍃 4 ነገሮችን ቀንስ* ① እንቅልፍን ② ምግብን ③ መሰላቸትንና ④ ንግግርን *🍃 4ቱ ላይ አትጨክንባቸው* ① የቲም ላይ ② ሚስኪን ላይ ③ ድሃ ላይና ④ ህመምተኛ ላይ *🍃 4 ሰዎችን ቅረባቸው* ① ሙኽሊስ የሆነ ሰው ② ቃሉን ጠባቂ ③ አዛኝንና ④ ታማኝን *🍃 4 ሰዎችን ራቃቸው* ① ጃሂልን ② ተከራካሪን ③ ቂልንና ④ ባዶን *🍃 4 ሰዎችን ጓደኛ* አታድርጋቸው ① ውሸታምን ② ሌባን ③ ምቀኛንና ④ ራስወዳድን *🍃 4 ነገሮችን አትቁረጣቸው* ① ሰላት ② ቁርአን ③ ዚክርንና ④ ዝምድናን *🍃 በ4ቱ ተዋብባቸው* ① በትእግስት ② በቻይነት ③ በእውቀትና ④ በቅንነት *🍃 ከ4 ነገሮች በአላህ* ተጠበቅ ① ከትካዜ ② ከሀዘን ③ ከድብርትና ④ ከስስት *2, ፊትህ እንዲበራ ትፈልጋለህ ?* ÂŽ= የሌሊት ሶላት አደራ ፡፡ 3, ጤና ትፈልጋለህ ? _ÂŽ= ፆምን አጥብቀህ ያዝ ፡፡_ _4, ከጭንቅ ለመዉጣት ትፈልጋለህ ?_ _እሥቲግፋርን እንዳትለቅ ፡፡_ _5, ትካዜን ማሥወገድ ትፈልጋለህ ፡፡_ _ዱአን ሙጭጭ አድርገህ ያዝ ፡፡_ _6, የህይወትን አድካሚ ችግሮች ለማሥወገድ ትፈልጋለህ ?_ _ÂŽ= "ላሀወላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ማለት አብዛ ፡፡_ _7, በረካ ትፈልጋለህ ?_ _ÂŽ= በነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ላይ ሠለዋት አዉርድ ፡፡_ _8, ዘና ማለት ትፈልጋለህ_ ? _ÂŽ= ቁርአንን ረጋ ብለህ በማሥተንተን አንብብ ፡፡_ _9, ያለ ድካም አጅር ትፈልጋለህ ?_ _ÂŽ=አንብበህ ሥትጨርሥ ለሌሎች ሟር አድርግ_ ሟር አረጉት ለሙስሊም ጓደኛቹህ ቢያንስ ለ 20 ሙስሊም ጓደኛቹህ   #እንሻ አላህ ሁላችንም እንጠቀምበት✍✍✍✍✍ 🤝🤝👍👍👍👍 @Ikramislamictube
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሙስሊም ሆነህ ይህ ቻናል የለህም🤯 ቻናሉ ኢስላማዊ ጥቅሶች ይለቅበታል ለረመዳንም😇 ምርጥ ፕሮፋይል ተዘጋጅቷል ምን ትጠብቃለህ ተቀላቀላ🤗
Показать все...
❤️ሙስሊሞች ብቻ❤️
😍😍ኢስላማዊ ጥቅሶች 😍😍
🫶🫶ሀዲሶች🫶🫶
Фото недоступноПоказать в Telegram
በየትኛው ኒዕማህ ላመስግንህ..... አዲስ ጀንበርን ....አዲስ ጅማሮን... ስላሳየኸኝና ስላስጀመርከኝ ...ወይስ የምሽት ወንጀሎቼን ደብቀህ... ዛሬን እድል ስለሰጠኸኝ ..... ለከል ሃምዱ ያ ረቢ.....አልሃምዱሊላህ!😇 @Ikramislamictube
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
‹‹ጀነት እገባለሁ ብለህ ታስባለህ?›› ብለው ገጠሬውን ጠየቁት። የበስራን መስጅድ ለመጎብኘት የመጣው የገጠር ሰውም፦‹‹ወላሂ በፍፁም አልገባም ብዬ ተጠራጥሬ እንኳ አላውቅም። አዎን እገባለሁ! በእልፍኞቿም እየተዟዟርኩ እዝናናለሁ፣ መጠጦቿንም እያማረጥኩ እጎነጫለሁ፣ በጥላዎቿም ተጠልዬ ፍሬዎቿንም እበላለሁ፣ በዛፎቿ የንፋስ ዜማ እየተመሰጥኩ በህንፃዎቿ እደመማለሁ፣ በህንፃዎቿ ከትሜ በቅንጡ ክፍሎቿ እኖራለሁ ›› አላቸው። ሰዎቹም፦‹‹ጀነት እገባለሁ ብለህ ምትፎክረው እምትተማመንበት ፅድቅ አለህን?›› ሲሉ ጠየቁት። ገጠሬውም፦‹‹በአላህ ከማመን እና ከሱ ሌላ የሆነን አማልክት በሙሉ ከመካድ የበለጠ ምን ፅድቅ አለ?›› አላቸው። ‹‹ታድያ እምነት ላይ ሁነህ የምትፈፅማቸውን ሀፅያቶች አትፈራምን?›› ሲሉ ጠየቁት። እሱም፦‹‹አላህ ለሀፅያት ምህረትን አዘገጅቷል፣ ለስህተትም ይቅርታን መድቧል፣ ለአመፅም እዝነትን ወስኖልናል። አላህም ወዳጆቹን በእሳት ከመማገድ የተጥራራ ነው›› አላቸው። ያ አላህ ከአመፃችን በላይ ያካበበውን እዝነትህን ትለግሰን ዘንድ እንለምንሀለን🤲 @Ikramislamictube
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
መንገድህ ቀንቶ በስኬት ማማ ላይ ከመሰቀልህ በፊት የወደዱህን አጥብቀህ ያዝ!… መሄጃ የሌለህ ከርታታ ሆነህ ሳለ ካቀረቡህ ወዳጆችህ አትራቅ!… ጭው ባለ በረሃ የተጎዳኙህን፣ የሚስጥር ካዝናዎችህን፣ የቃልህ አክባሪዎችን፣ የመዓት ሰደድ በመጣህ ጊዜ መጠጊያዎችህን የሙጥኝ በል!… ጣፋጭ ጊዜዎችህን የተጋሩህን፣ በሀዘን እና በመከራህ ያፅናኑህን አትርሳ!… ስታገኛቸው አንተም አንተ፣ እነርሱም ራሳቸውን ሆነው የሚገናኙህን፣ በብድር ቅቤ ወዝተው፣ በተውሶ ኩል ተኩለው የማይወግጉትን ያዝ! እነዚህ የመዓት ጊዜ ምሽጎችህ፣ የእውሩ ዘመን መጠለያዎችህ ናቸው! ወንድሞችህ!… : @Ikramislamictube
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.