cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

16 - ሚዲያ

እንኳን ወደ 16 - ሚዲያ ቴሌግራም ቻናል በሰላም መጡ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት በደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ። YOUTUBE ~> https://www.youtube.com/@16_media16

Больше
Рекламные посты
3 258
Подписчики
-624 часа
-237 дней
+11530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ዳግማይ ትንሳኤ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ_ትንሳኤ ተብሏል።
ሁለተኛ ለምን ተገለጠ ?
፩~ ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን ፪~ ሰንበትን ሊያጸናልን ፫~ ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት
~> ቶማስ ለምን ተጠራጠረ ?
መጠራጠሩ ስለ 2 ነገር ነው፡፡ 1 ሰዱቃዊ ስለነበረ፡፡ ሰዱቃውያን ደግሞ ትንሳኤ ሙታን የለም ብለው የሚጠራጠሩ ናቸውና ሳላይ አላምንም ብሎ 2 ሌሎች ሐዋርያት ትንሳኤውን ሲሰብኩ ተነስቶ አይተነዋል ሲሉ እርሱ ደግሞ መነሳቱን ሰምቻለሁ ብሎ ማስተማር ስለሌለበት ለማየት ሳላይ አላምንም አለ፡፡ ጌታ የተገለጠላቸው ደጆች ተዘግተው ሳሉ ነበር ፡፡ ዮሐ 20፥26 ገብቶ ሰላም አላችሁ አስታረቅኀችሁ አላቸው፡፡
~> በተዘጋው ቤት እንዴት ገባ ?
ኤልሻዳይ ስለሆነ ፡፡ ዘፍ 17፥1 ሳራ ማሕጸኗ ተዘግቶ መውለድ ባልቻለች ጊዜ ልጅ የሰጣት ኤልሻዳይ ነው፡፡ ሀና ፣ ኤልሳቤጥ ሌሎችም እንዲሁ፡፡ ሉቃ 1፥ 37 እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር ፡፡ እንዲል ረቂቅ መለኮት ስጋን እንደተዋሃደ ለማጠየቅ በተዘጋ ቤት ገባ፡፡   | @sixteen_media | ጠቃሚ ከሆነ #ሼር ይደረግ!
Показать все...
🥰 11 4👍 2
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃ
Показать все...
🙏 1
✝✝✝ እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" 🌷ልደታ ለማርያም ድንግል🌷 "*+ ✝ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: ✝ " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " =>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: +ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: +እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8) =>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: +ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: +ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: +እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: +በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: +እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) +"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9) +እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- -ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: =>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ) 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቴክታና በጥሪቃ 4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር =>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጧም ሰው ተወለደ:: እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Показать все...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Фото недоступноПоказать в Telegram
🕊 [ ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት ፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት ፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ ] [ አባ ጽጌ ድንግል ] " ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል ፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት [ ጌታ ] መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” [  ቅዱስ እንድርያስ  ] ------------------------------------------- " ኢያቄምና ሐና  በጸለዩ በአለቀሱ ጊዜ ለሁላችን ምእመናን መጠጊያ የምትሆን ኃጢአት ይቅር የምታስብል ሴት ልጅ አገኙ።ሁለቱ ሽማግሌዎች ሰማይን ወለዱ ሰማያቸውም ጸሐይን አስገኘች። "                          [  ነግሥ ዘልደታ  ] ------------------------------------------ [ ዮም ፍስኃ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም ]       💖   እንኳን አደረሳችሁ   💖                        †                              🕊  [ ልደታ ለማርያም ]  🕊      [ በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ]          💖    ድንቅ ትምህርት    💖 †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Показать все...
👍 1
................የለመኑትን የማይረሳ ጌታ በእስተርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው አንድ ቀን እርግቦች ከጫጭቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች ።"እንስሳትና አራዊትን እፅዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጠርሀት" ብላ አዘነች። - ይህን ከተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራው ወጥቶ ሱባኤ ያዘ ለአርባ ቀናም ሲጸልይና ሲማልል ቆየ በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ እርሱ ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ በማኅጸኗ ስትደርስ አየ - እርሷ ደግሞ የኢያቄም በትር አብቦ አፍርቶ ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ - በሰባተኛው ቀን ማለትም (ነሃሴ ሰባት ) መላዕከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ። "ዓለም የሚድንበት የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳለች ።"ብሏቸው ተሰወረ እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔን አመሰገኑ - እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች "ኦ ድንግል አኮ በፍትወት ደነስ ዘተጸነስኪ" " ድንግል ሆይ ኃጥያት ባለበት ሥጋዌ ፍትወት የተጸነሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ ( ቅዳሴ ማርያም) - " ለጽንሰትኪ በከርሥ እንበለ አበሳ ወርኩስ ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ........" -" ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው ፤ የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው ። ( መጽሐፈ ሰዓታት ፣ኢሳ ፩፥፱ ) - እመቤታችን ነሐሴ ሰባት ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ ፣ ፍቅሯ ፣ ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን ።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Показать все...
👏 14 2👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግንቦት ፩ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማይ ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐይ ኢያቄም እና ሐና ሰማይን ወለዱልን ሰማያቸውም ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን | @sixteen_media | ጠቃሚ ከሆነ #ሼር ይደረግ! - የዓለማችን ወላጆች ነብያት ሐዋርያትን፣ጻድቃንን፣ሰማዕታትን ወልደው ከብደዋል ተመስግነዋል ። - ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችወን ትቢያ እንኳን መሆን የማይችል የሰማይና የምድር ንግሥት የእግዚአብሔርን እናት እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን ኢያቄምና ሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹ ተባሉ ። - እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው። ጸልየዋል ንጽህናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል። - ከአዳም ስህተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች። -ኢሳ ፩፥፱ - ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ አንድም ትንቢቱ እና ምሳሌው ይፈፀም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚች ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች - "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ።" መኃ ፬፥፰ - ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ቅድስት ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በህጉ ፀንተው በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር ። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር ። - ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኃጡዕ በረከተ ጸጋ እግዚአብሔር የራቀው" ብለው ያምኑ ነበር ኢያቄም እና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ - እነርሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና የሣራ አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም........................ይቀጥላል | @sixteen_media | ጠቃሚ ከሆነ #ሼር ይደረግ!
Показать все...
👍 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
ድንቅ ከበሮ አመታት በና/ደ/ገ/ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ለመመልከት👇👇👇👇 https://youtu.be/8AOWqruQ2Hs?si=GBR5ym36nXXhK2mu
Показать все...
👏 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
፩~መልካሙ_ዓርብ_ይባላል ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
Показать все...
👍 8 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
፩~ይህ እለት ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል ፪~የምስጢር_ቀን_ይባላል ፫~ የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል ፬~የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል | @sixteen_media | ጠቃሚ ከሆነ #ሼር ይደረግ!
Показать все...
🥰 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰሞነ ሕማማት ረቡዕ ፩~ምክረ_አይሁድ_ይባላል ፪~የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል ፫~የእንባ_ቀን_ይባላል
Показать все...
😢 11👍 3🙏 1