cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኑ ወዳጆቻችንን እንወቅ

በዚህ ቻናል አስተማሪ ልብ የሚነኩ፣ውብ እና ማራኪ ✔️ የነብያቶች ✔️ የሰሀባዎች ታሪክ ✔️የታብዕዮችን ገድል ✔️ እና የቀደምት ደጋግ🌹 (ሳሊሆችን) እውነተኛ ታሪክ ብቻ ይለቀቅበታል።💬 pin ከተደረገው ታሪክ ጀምሩ ምክንያቱም ታሪኩን ከጅምሩ ለመረዳት። فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ [٧:١٧٦] ለአስተያያት 👇 @Nuwedajochachin_bot

Больше
Рекламные посты
217
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
-730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሞራል መጠበቅ የሚባል ነገር አታውቅም ?! በዲናችንኮ ይሄም ቦታ ተሰጥቶታል። በበድር ጦርነት አቡ ጀህልን  የገደለው ማን ነው ሲባል ሁለቱ ሙዐዞች رضي الله عنهما እኔ እኔ አሉ። ሁለቱም ሰይፋቸውን እንድያሳዩ ተደረጉ።ሁለቱም ሰይፍ ላይ ደም አለ። ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሁለታችሁም ናችሁ የገደላችሁት ብለው አስደሰቷቸው።እውነታው ግን አቡ ጀህልን በደንብ የጎዳውና ገደለው ሊባል የሚችለው አንደኛው ነው።ሌላኛው ብዙም ሚና አልነበረውም። ግን እኔ ነኝ የገደልኩት ብሎ እየተከራከረ አንተማ አይደለህም ብለው ሞራሉን አልጎዱትም። የገደለውን ጀግና ሚናም አላናናቁም። ይልቁኑ አቡጀህል ላይ የተገኙ ማንኛውም አይነት ንብረቶች ሁሉ ለሙዐዝ ቢን ጀሙህ እንድሰጥ ወሰኑ። ስለሰው የምትናገረው ሀቅ የሆነን ነገር ቢሆንም  ሞራል መጠበቅ የሚባል ባህል ተላበስ። እንደምሳሌ መልከኛ አለመሆኑን ብታውቅም መልከኛ ነኝ ብሎ የቀረበን ሰው አላህ እንዴት አሳምሮ ፈጥሮሃል ብለህ ጀምርና ከዚያም  ጉዳይህን ቀጥል። ጎበዝ ነኝ ብሎ የሚያምንን ወንድምህን ያንተ ጉብዝናማ የተለዬ ነው ግን ..... t.me/kedegagochu_alem
Показать все...
2
በ እውነቱ ነገረ ስራችን የተገለባበጠ መሆኑ እንጂ በዱንያ ከሚደርስብን ሙሲባ የ አኼራው ሙሲባ ይበልጥብን ነበር። ሃቲም አል አሶም رحمه الله ሲናገር ሰላተል ጀመዓ አምልጦኝ አንድ ሰው ብቻ መጥቶ አስተዛዘነኝ፣ ልጄ ሞቶ ቢሆን ከ አስር ሺ ሰው በላይ ባስተዛዘነኝ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ለ ሰዎች የ አኼራ ሙሲባ ከዱንያ ሙሲባ ያነሰ ሆኖ ስለሚታያቸው ነው ብሏል። ታሪኩን ኢማሙ ዘሃቢይ " الكبائر " በተሰኘው ኪታባቸው ላይ አስፍረዋል። እኛስ ቤተሰብ ወይም የምንወደውን ነገር ስናጣ የምናዝነውን ያክል ሰላት ቢያመልጠን እናዝናለን?! t.me/kedegagochu_alem
Показать все...
📚የነቢዩሏህ ዘከሪያ እና የነቢዩሏህ የህያ አለይሂ ሰላም ታረክ                     ክፍል5        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 እነሱም የፎጣውን ጫፍ በዛፉ ላይ ሲመለከቱ ዘከሪያ ዛፏ ውስጥ እንዳለ አረጋገጡ።ይሁን እንጂ ዘከሪያን ከዚህች ዛፍ እንዴት አድርገው ማውጣት እንዳለባቸው በጣም ግራ ተጋብተው ሲመካከሩ ኢብሊስ ብቅ አለ'ና፦"ዛፏን እኩል ግማሿን በመጋዝ ቁረጧት። ያኔ በውስጧ ያለው ዘከሪያም አብሮ ይቆረጣል" በማለት ሀሳብ ሰጣቸው። እነሱም መጋዝ አምጥተው የዛፏን እኩል መሀል ሲቆርጡ ዘከሪያንም ጭምር በመጋዝ ገዘገዙት።(የአላህ እርግማን በነሱ ላይ ይሁን) ዘከሪያም በተወለደ በ 150 አመቱ በጠላቶቹ እጅ ነፍሱ ወጣች።ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን... (የአላህ ሰላም እና እዝነት በዘከሪያ እና በያህያ ላይ ይሁን)        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ከዚያም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከባቢሎን ምድር ጁርደስ የተባለን ንጉስ አስነስቶ እየሩሳሌም በመሄድ ኢስራኢላውያንን እንዲበቀል በሂክማው ላከው። ንጉሱ ወታደሩን አስከትሎ ከባቢሎን ተነስቶ እየሩሳሌምን ሲቃረብ፤ የጦር አዛዥ የሆነው ነቡዛዛንን በመጥራት፦"እኔ ኢስራኢላውያንን ካገኘዋቸው ሁሉንም ገድዬ የምገድለውን እስከማጣ ድረስ እና ደሞቻቸው የሰራዊቴን እግሮች እስኪያርሱ ድረስ ልፈጃቸው ቃል ገብቻለሁ።አንተም ኢስራኢላውያን ቁርባን ወደሚያቀርቡበት ስፍራ በመሄድ ግደላቸው" በማለት አዘዘው። የጦር አዛዡም ሰራዊቱን አስከትሎ ኢስራኢላውያን ቁርባን እሚያቀርቡበት ቦታ ላይ ሰፈረ።የጦር አዛዡ እዚያ ቦታ ላይም የሚንተከተክ ደም ተመለከተ። ኢስራኢላውያንንም ሰብስቦ፦"የኢስራኢል ልጆች ሆይ!! ይህ ደም በምን ምክንያት ነው የሚንተከተከው?" ብሎ ጠየቃቸው።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ኢስራኢላውያንም፦"ይህ እኛ ለጌታችን ያቀረብነው ቁርባን ሲሆን ለረጅም ዘመናት ተቀባይነትን ስላላገኘ ነው የሚንተከተከው" አሉት። የጦር አዛዡም፦"እየዋሻችሁኝ ነው። እውነቱን ንገሩኝ" አላቸው። ኢስራኢላውያንም፦"ንግስና እና ነቢይነት ከኛ ዘር ተቋርጧል።ለዚያ ነው ቁርባናችን ተቀባይነትን ያጣው" አሉት። ያ የጦር አዛዥም 770 (ሰባት መቶ ሰባ) ኢስራኢላውያንን እዚያው አረዳቸው።ይሁን እንጂ ደሙ መንተክተኩን አላቆመም። ከዚያም 700 (ሰባት መቶ) ኢስራኢላውያን ካህናትንም አስመጥቶ ደሙ አጠገብ አረዳቸው።ነገር ግን አሁንም ደሙ አልረጋም በመንተክተክ ለይ ነው። ከዚያም የጦር አዛዡም ኢስራኢላውያንን በሙሉ በመሰብሰብ፦"የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ስለዚህ ደም እውነቱን የምትነግሩኝ እንደሆነ ንገሩኝ።አለበለዚያ ግን ሀቁ እስኪወጣ ድረስ አንድ በአንድ እያረድኩ እፈጃችኋለሁ" አላቸው። ኢስራኢላውያኑም ይሄን ጭካኔውን ሲመለከቱ፦" በል እንግዲያውስ ስለዚህ ደም እውነቱን እንነግርሀለን።አንድ በመልካም የሚያዘን እና ከመጥፎም የሚከለክለን ሳሊህ ነቢይ በመካከላችን ነበር።ስለእናንተም መምጣት ያስጠነቅቀን ነበር ነገር ግን አስተባበልነው፣ በመጨረሻም ገደልነው። ስሙም ያህያ ኢብን ዘከሪያ ይባላል" ብለው እውነቷን አወጡ። የጦር አዛዡም፦"አሁን እውነትን ተናግራችኋል።ለዚህ ነበር ጌታችሁ ሲበቀላችሁ የነበረው" በማለት ሱጁድ አደረገ።           🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ከዚያም የጦር አዛዡ ወደ ወታደሮቹ በመዞር፦"ሁሉም ወታደር የእየሩሳሌምን ምድር ለቆ ይውጣ።የኢየሩሳሌም መግቢያዎች ሁሉም እንዲዘጉ" በማለት አዘዘ። ሁሉም ወታደር እየሩሳሌምን ለቆ ከወጣ በኋላ አዛዡ ብቻውን እዚያ ተንተክታኪው ደም ዘንድ ቀረ። ከዚያም ደሙ አጠገብ ቁጭ ብሎ፦"ያህያ ሆይ! ስላንተ ምን እንደተከሰተ እና ስላንተ ስንት ህዝብ እንደገደልን አላህ ነው የሚያውቀው።ኢስራኢላውያንን አንድም ሳይቀር ስላንተ ጨፍጭፌ ከመጨረሴ በፊት የደምህን መንተክተክ አቁም።" ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ የያህያ ደም መንተክተኩን አቆመ። የጦር አዛዡም ማንንም ላለመግደል ሰይፉን ወደ ማንገቻው መልሶ አስገባ።ከዚያም፦"በአላህ አምላክነት አምኛለሁ።ከሱ ሌላም ጌታ አለመኖሩንም እመሰክራለሁ" ካለ በኋላ አንገቱን ቀና አድርጎ፦"ኢስራኢላውያን ሆይ! ንጉስ ጁርደስ የናንተ ደም የወተደሮቹን እግር እስኪያጥለቀልቅ ድረስ እንድገድላችሁ አዞኛል።እኔ ደሞ የንጉሱን ትዕዛዝ መጣስ አልችልም። እንዴት ይሻላል?" አላቸው። ኢስራኢላውያኑም፦"የታዘዝከውን ፈፅም" አሉት። ከዚያም ሁሉንም ሰብስቦ፦"ከብቶቻችሁን፣ አህዮቻችሁ፣ ፈረሶቻችሁን፣ ግመሎቻችሁን.....ሰብስባችሁ አሁኑኑ አምጡ" አላቸው።          🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ሁሉም ኢስራኢላውያን በቤቱ ያለውን እንስሳት ሰብስቦ አመጣ።ከዚያም የጦር አዛዡም ንጉሱ ወዳረፈቦት ቦት የውሀ ቦይ አስቆፈረ።ልክ ቦዩ እንደተጠናቀቀ የእንስሳቶቹን አንገት በቦዩ ላይ በመቀንጠስ ደሞቻቸው በቦዩ እንዲሄድ አደረገ። በመጨረሻም ቦዩ ውስጥ ያለውን ደም በፍጥነት እየነዳ እንዲወስደው በርካታ ውሀ ቀላቅሎ መጀመሪያ የገደላቸውንም አስክሬኖች ቦዩ ውስጥ አስገብቶ ለቀቀው። ይህ በውሀ የተቀላቀለው ደምም የሙታኑን አስክሬን እየነዳ ኑጉሱ ወዳረፈቦት ቦታ ደርሶ ንጉሱ ይሄን በተመለከተ ግዜ፦"በቃ ተዋቸው። ሚበቃኝን የህል ተበቅያቸዋለሁ" የሚል መልዕክት ላከለት።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 {የአላህ ሰላም እና እዝነት ዳግም በዘከሪያ እና በየህያ ላይ ይስፈን።}          #ተፈፀመ...... _ ምንጮች፦ الحاصل في التاريخ... ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻟﺜﺎﻧﻲ/ صحيح مسلم مسند الإمام أحمد القرءان الكريم              🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹
Показать все...
የነቢዩሏህ ዘከሪያ እና የነቢዩሏህ የህያ አለይሂ ሰላም ታረክ                     ክፍል4          🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 እናላችሁ ይህ ክብረ በአል ደረሰ'ና ሂሮዶስ ህዝቡን ሰብስቦ ያን በአል በማክበር ላይ ሳለ ይህች ሊያገባት ያሰባት ሴት ፊት ለፊቱ መጥታ ልቡን በሚያዋልል ሁኔታ መደነስ ጀመረች።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ሂሮዶስም ልጅቷን፦"የፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ እፈፅምልሻለሁ" አላት። (ዛሬ ንጉስ ቃል ኪዳን ማያፈርስበት ቀን ነው ብያችኋለሁ) እሷም፦"የዘከሪያ ልጅ የሆነውን የያህያን ደም እፈልጋለሁ" አለችው። እሱም፦"ሌላ ነገር ጠይቂኝ" አላት። እሷም፦"በቃ የሱን ደም ነው ምፈልገው!" አለችው። ንጉሱም በሀሳቧ ተስማምቶ ወታደሮቹን ወደ ያህያ ላካቸው።ወታደሮቹም ያህያን ብዙ ከፈለጉት በኋላ በመጨረሻም ሚህራብ ውስጥ ከአባቱ ጎን በተመስጦ ሲሰግድ አገኙት። እዛው ሰላት ላይ እያለም የያህያን አንገት ቆርጠው በድኑን ትተው አንገቱን ይዘው ወደ ንጉሱ ዘንድ ተመለሱ።ልጁ ከአጠገቡ እንደ በግ ሲታረድ ያየው ዘከሪያ ግን ከሰላቱ ፍንክች አላለም ነበር።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ወታደሮቹም ሂሮዶስ እና ሂሮዲያ ባሉበት ቦታ ወስደው የየህያን ጭንቅላት ፊትለፊታቸው አስቀመጡላቸው። ያን ቀን በደስታ እና በፈንጠዚያ ካሳለፉ በኋላ የቀኑ ክፍለ ግዜ ተጠናቅቆ ምሽት ለበቀል ተዘጋጅቶ ብቅ አለ። ልክ መሬት በምሽት ጨለማ እንደተሞላች የሄሮዶስ ቤተ መንግስት ሂሮዶስን፣ሂሮዲያን እና ወታደሮችን በአጠቃላይ ይዞ ወደመሬት ሰመጠ። ሌሊት ስለነበር የእየሩሳሌም ነዋሪያን ስለክስተቱ ምንም ሚያውቁት ነገር አልነበረም ።ልክ ሌሊቱ ነግቶ ሰዉ መንቀሳቀስ ሲጀምር የንጉሳቸው ቤተ መንግስቱ ከነያዘው ነገር በሙሉ እንደሰመጠ ተመለከቱ።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ህዝቡም እዚያ ቦታ ላይ እንደጉድ ከተሰበሰበ በኋላ፦"ትናንት የህያ ስለተገደለ የዘከሪያ ጌታ ተቆጥቶ ነው ዛሬ ንጉሳችንን የተበቀለው። ስለዚህ እኛም ዘከሪያን በመግደል ለንጉሳችን እንበቀልለት" በማለት ተስማሙ። ከዚያም ሁሉም ተሰብስበው ዘከሪያን ፍለጋ ጀመሩ። ከዚያም ሁሉም ተሰብስበው ዘከሪያን ፍለጋ ጀመሩ።ዘከሪያ ይህን ወሬ ሲሰማ ወደ ጫካ መሸሽ ጀመረ.... ነገር ግን ህዝቦቹ እና ኢብሊስም ከኋላው እየተከተሉት ነበር። በመጨረሻም ዘከሪያ ከአንዲት ዛፍ አጠገብ ሲደርስ ዛፏ መሀሏን ከፍታለት፦"ና እኔ ውስጥ ግብ'ና ተደበቅ" አለችው። ዘከሪያም ከኋላው ካሉት ጠላቶቹ ራሱን ለማትረፍ ወደተከፈተችለት ዛፍ ዘሎ ሲገባ ከኋላው ኢብሊስ ነበር'ና የለበሰውን ፎጣ ጎተተበት። ዘከሪያም ሙሉ ለሙሉ ዛፏ ውስጥ ሲገባ ዛፏም እንደመጀመሪያ ድፍን ሆነች፤ ነገር ግን የፎጣው ጫፍ ትንሽ ይታይ ነበር።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ኢስራኢላውያኑ (የዘከሪያ አሳዳጆች) ኮቴውን ተከትለው ሲመጡ ዘከሪያን ሊያገኙት አልቻሉም ነበር። ከዚያም ኢብሊስ በሰው ተመስሎ መጣ'ና፦"ማንን እየፈለጋችሁ ነው" አላቸው። እነሱም፦"ዘከሪያን አይተኸዋል" አሉት። እሱም፦"አዎ እዚህ ዛፍ ውስጥ ገብቷል" አላቸው። እነሱም፦" እንዴት ሆኖ ነው ዛፍ ውስጥ የሚገባው!!" በማለት አሾፉበት። ኢብሊስም፦"ዛፏ ላይ ድግምት ሰርቶ ነው የገባው። ይኸው ካላመናችሁኝም የፎጣውን ጫፍ እዩ" ብሎ አሳያቸው።       ይቀጥላል..............
Показать все...
👍 5
የነቢዩሏህ ዘከሪያ እና የነቢዩሏህ የህያ አለይሂ ሰላም ታረክ                     ክፍል4          🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 እናላችሁ ይህ ክብረ በአል ደረሰ'ና ሂሮዶስ ህዝቡን ሰብስቦ ያን በአል በማክበር ላይ ሳለ ይህች ሊያገባት ያሰባት ሴት ፊት ለፊቱ መጥታ ልቡን በሚያዋልል ሁኔታ መደነስ ጀመረች።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ሂሮዶስም ልጅቷን፦"የፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ እፈፅምልሻለሁ" አላት። (ዛሬ ንጉስ ቃል ኪዳን ማያፈርስበት ቀን ነው ብያችኋለሁ) እሷም፦"የዘከሪያ ልጅ የሆነውን የያህያን ደም እፈልጋለሁ" አለችው። እሱም፦"ሌላ ነገር ጠይቂኝ" አላት። እሷም፦"በቃ የሱን ደም ነው ምፈልገው!" አለችው። ንጉሱም በሀሳቧ ተስማምቶ ወታደሮቹን ወደ ያህያ ላካቸው።ወታደሮቹም ያህያን ብዙ ከፈለጉት በኋላ በመጨረሻም ሚህራብ ውስጥ ከአባቱ ጎን በተመስጦ ሲሰግድ አገኙት። እዛው ሰላት ላይ እያለም የያህያን አንገት ቆርጠው በድኑን ትተው አንገቱን ይዘው ወደ ንጉሱ ዘንድ ተመለሱ።ልጁ ከአጠገቡ እንደ በግ ሲታረድ ያየው ዘከሪያ ግን ከሰላቱ ፍንክች አላለም ነበር።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ወታደሮቹም ሂሮዶስ እና ሂሮዲያ ባሉበት ቦታ ወስደው የየህያን ጭንቅላት ፊትለፊታቸው አስቀመጡላቸው። ያን ቀን በደስታ እና በፈንጠዚያ ካሳለፉ በኋላ የቀኑ ክፍለ ግዜ ተጠናቅቆ ምሽት ለበቀል ተዘጋጅቶ ብቅ አለ። ልክ መሬት በምሽት ጨለማ እንደተሞላች የሄሮዶስ ቤተ መንግስት ሂሮዶስን፣ሂሮዲያን እና ወታደሮችን በአጠቃላይ ይዞ ወደመሬት ሰመጠ። ሌሊት ስለነበር የእየሩሳሌም ነዋሪያን ስለክስተቱ ምንም ሚያውቁት ነገር አልነበረም ።ልክ ሌሊቱ ነግቶ ሰዉ መንቀሳቀስ ሲጀምር የንጉሳቸው ቤተ መንግስቱ ከነያዘው ነገር በሙሉ እንደሰመጠ ተመለከቱ።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ህዝቡም እዚያ ቦታ ላይ እንደጉድ ከተሰበሰበ በኋላ፦"ትናንት የህያ ስለተገደለ የዘከሪያ ጌታ ተቆጥቶ ነው ዛሬ ንጉሳችንን የተበቀለው። ስለዚህ እኛም ዘከሪያን በመግደል ለንጉሳችን እንበቀልለት" በማለት ተስማሙ። ከዚያም ሁሉም ተሰብስበው ዘከሪያን ፍለጋ ጀመሩ። ከዚያም ሁሉም ተሰብስበው ዘከሪያን ፍለጋ ጀመሩ።ዘከሪያ ይህን ወሬ ሲሰማ ወደ ጫካ መሸሽ ጀመረ.... ነገር ግን ህዝቦቹ እና ኢብሊስም ከኋላው እየተከተሉት ነበር። በመጨረሻም ዘከሪያ ከአንዲት ዛፍ አጠገብ ሲደርስ ዛፏ መሀሏን ከፍታለት፦"ና እኔ ውስጥ ግብ'ና ተደበቅ" አለችው። ዘከሪያም ከኋላው ካሉት ጠላቶቹ ራሱን ለማትረፍ ወደተከፈተችለት ዛፍ ዘሎ ሲገባ ከኋላው ኢብሊስ ነበር'ና የለበሰውን ፎጣ ጎተተበት። ዘከሪያም ሙሉ ለሙሉ ዛፏ ውስጥ ሲገባ ዛፏም እንደመጀመሪያ ድፍን ሆነች፤ ነገር ግን የፎጣው ጫፍ ትንሽ ይታይ ነበር።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ኢስራኢላውያኑ (የዘከሪያ አሳዳጆች) ኮቴውን ተከትለው ሲመጡ ዘከሪያን ሊያገኙት አልቻሉም ነበር። ከዚያም ኢብሊስ በሰው ተመስሎ መጣ'ና፦"ማንን እየፈለጋችሁ ነው" አላቸው። እነሱም፦"ዘከሪያን አይተኸዋል" አሉት። እሱም፦"አዎ እዚህ ዛፍ ውስጥ ገብቷል" አላቸው። እነሱም፦" እንዴት ሆኖ ነው ዛፍ ውስጥ የሚገባው!!" በማለት አሾፉበት። ኢብሊስም፦"ዛፏ ላይ ድግምት ሰርቶ ነው የገባው። ይኸው ካላመናችሁኝም የፎጣውን ጫፍ እዩ" ብሎ አሳያቸው።       #ይቀጥላል.............. 📢ሼር ማድረግን አይዘንጉ !
Показать все...
ሱና ኢስላማዊ ታሪኮች

السلام عليكم ورحمةالله وبركاته 🔊በቻናላችን 👇 💎 ውብ እና አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች 📖 ከቁርኣን አንቀፆች 📘 ከነብዩ ﷺ ሓዲሶች 📚 ከትክክለኛ ምንጭ የተቀዱ አስተምህሮቶች 📙 የለተለያዩ ዲናዊ መጣጥፎች 👉ሃሳብ አስተያየት ካለዎት 👉🔰 @sunna02Bot ላይ ያስቀምጡ‼️

❤️❤️❤️
Показать все...
03.mp330.48 MB
4
የነቢዩሏህ ዘከሪያ እና የነብዩሏህ የህያ አለይሂ ሰላም ታረክ                     ክፍል3         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 የህያም፦"ወንድሜ ሆይ! አላህ እኔን ያዘዘኝን ነገር አንተ ቀድመኸኝ ከተገበርከው አላህ እኔን እንዳይቀጣኝ እፈራለሁ" አለው። ከዚያም የህያ(ዐ.ሰ) ኢስራኢላውያንን በቁድስ መስጅድ ውስጥ ሰብስቧቸው መስጂዱን ሞሉት።ከዚያው እሱ ከፍ ባለ ቦታ ላይ ቆሞ፦ "ህዝቦቼ አላህ አምስት ትዕዛዛትን እኔም እንድተገብራቸው ለእናንተም እንዳደርስ አዞኛል።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 1፦አላህን ከሱ ሌላ ምንንም አካል ሳታጋሩ እንድትገዙት። ያ ማለት፤አንድ ሰውዬ አንድን ባሪያ ገዝቶት ሳለ ይህ ባሪያ ግን ለአሳዳሪው ሳይሆን ለሌላ ሰው ነው ሚያገለግለው። ይህ ትክክል ነውን? እንደዚሁ ሁላ እናንተም አላህ ፈጥሯችሁ እሱው እየረዘቃችሁ ሌላን አካል ልታመልኩም አይገባም። 2፦ሰላት እንድትሰግዱም አዟችኋል።አላህ ሰላት በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ላይ ይሆናል።ሰላት ስትሰግዱ ፊታችሁን አታዟዙሩ። 3፦በፆምም አዟችኋል።የፆመኛ አፍ ሽታ አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽቶ ይልቅ የተወደደ ነው።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 4፦ምፅዋትን በመመፅወትም አዟችኋል። የምፅዋት መመፅወት ምሳሌ፤አንድ ሰውዬ ጠላቶች አግተውት ሊገድሉት እጁን ከአንገቱ አጣፍረው ባሰሩት ግዜ እሱም ለኔ መስዋእት ሚሆን ነገር ላምጣ ብሎ ሲጠይቃቸው አጋቾችም በፈቀዱለት ግዜ በትንሽም በትልቅ የመፀወተውን በማስታወስ እራሱን ነፃ እንደማውጣት ነው። 5፦አላህንም በማውሳት እንድትጠመዱ አዟችኋል።አላህን የማውሳት ምሳሌ አንድ ሰውዬ ጠላት ሊገድለው ሲያሳድደው ብርቱ መከላከያን ሲያገኝ እንደሚድነው ሁላ ዚክር ሲያደርግም ከአሳዳጅ ሸይጣን በአላህ ይድናል" በማለት የአላህን ትዕዛዝ አስተላለፈላቸው። (ነቢያችንም ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ትረካ ከተረኩ በኋላ ለባልደረቦቻቸው፦"እኔም አላህ ባዘዘኝ በአምስት ነገሮች አዛችኋለሁ።          🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 1፦በአንድነት (አንድ እንድትሆኑ) 2፦የምላችሁን በማዳመጥ 3፦የማዛችሁን በመታዘዝ 4፦በሂጅራ(በዲን ምክንያት በመሰደድ) 5፦በአላህ መንገድ በመታገል....አዛችኋለሁ።   ከሙስሊሞች አንድነት አፈንግጦ የወጣ ሰው እስኪመለስ ድረስ የእስልምናን ማዕረግ ከአንገቱ እንዳወጣ ይቆጠራል። በማሀይማንም ጥሪ የተጣራ(ዘረኛ) እሱ የጀሀነም ማገዶ ነው" አሉ።   ከዚያም ሰሀቦች፦" ያ ረሱሉላህ ይህ ሰው ቢፆምም ቢሰግድም የጀሀንም ይሆናል?" ብለው ሲጠይቋቸው። ረሱልም ሰዐወ፦"አዎ ቢፆምም ቢሰግድም እኔ ሙስሊም ነኝ ብሎ ቢያስብም። ሙስሊሞችን በስሞቻቸው ጥሯቸው አላህ በሰየማቸው ስም ሙስሊሞች ሙእሚኖች ብላችሁ ጥሯቸው" አሉ።) [አሁን ሙስሊሞች እርስ በርስ ማን ተባብለን እንደምንጠራራ ሆድ ይፍጀው።]       🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ይህ የየህያ ስም በእየሩሳሌም ምድር እጅጉን ይጋነን ጀምሯል።በአስደናቂ እውቀቱ የሰዎችን ትኩረት የሚስብ ልጅ መሆኑን በዘመኑ እየሩሳሌምን ያስተዳድር የነበረውም ንጉስ ሂሮዶስ ጭምጭምታ ከሰማ ሰነባብቷል። ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ ሂሮዶስ የወንድሙ ልጅ የሆነችውን ሂሮድያን ለማግባት ዝግጅት ላይ ሳለ ይህ ጋብቻ የተውራትን ህግጋት የሚፃረር መሆኑን ያህያ ተናገረ። ንጉስ ሂሮዶስን ለማግባት የቋመጠችውም ሂሮድያ የተባለች ሴት የህያን(ዐ.ሰ) ለመግደል ሁኔታዎችን ማመቻቸት ጀመረች። ንጉስ ሂሮዶስ ሁሌ በአመት አንድ ግዜ የሚያከብረው ክብረ በአል አለ። በዚያ ቀን ምንም አይነት ውሸት አያወራም...ስለምንም ነገር ቃል ኪዳን ከገባ ይፈፅማልም።        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹        ይቀጥላል.........
Показать все...
👍 4
Omar Hisham Al Arabi — Al-Baqara (www.mixmuz.ru).mp33.88 MB
የነቢዩሏህ ዘከሪያ እና የነብዩሏህ የህያ አለይሂ ሰላም ታረክ             ✍️ ክፍል 2        🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ዘከሪያም ከመርየም፦"አላህም ለፈለገው ያለ ገደብ ይረዝቃል" የሚለውን ቃል እንደሰሙም ወደ ሚህራብ(ግላዊ የአምልኮ ቦታ) ገሰገሱ። ልክ መስገጃው ላይ እንደቆሙም በተለሳለሰ አንደበታቸው፦"ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴ ደከመ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ፤ አንተን በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምን ጊዜም) ዕድለ ቢስ አልሆንኩም።         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 እኔም ከበኋላዬ ዘመዶቼን በእርግጥ ፈራሁ፡፡ ሚስቴም መካን ነበረች ስለዚህ ከአንተ ዘንድ ለኔ ልጅን ስጠኝ። የሚወርሰኝ ከያዕቆብ ቤተሰቦችም(ነቢይነትን) የሚወርስ የሆነን (ልጅ ስጠኝ)፡፡ ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው፡" ሲሉ አላህን ተማፀኑ። እዚያ በቆመበት አላህም፦"ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ ስሙ የሕያ በኾነ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን" በማለት ምላሽ ሰጣቸው።   ዘከሪያም በመገረም፦"ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስኾን ባልተቤቴም መሐን ስትሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?" አሉ፡፡ አላህም፦"(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡       🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 ጌታህ፡- ከአሁን በፊት ምንም ያልነበርከውን አንተን የፈጠርኩህ ስኾን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው" አላቸው። ዘከሪያም፦"ጌታዬ ሆይ! (እንግዲያውስ) ስለመውለዴ ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ" አሉት። አላህም፦"ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊትን (ከነቀናቸው) ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነው" በማለት መለሰላቸው። ከዚያም ዘከሪያ በጌታቸው ቃል ኪዳን መሰረት ያህያ የተባለ የወንድ ልጅ አባት ሆኑ። 👉(ክብራን አንባቢያን የዘከሪያ እና የየህያ ታሪክ በአንድ ዘመን ከመሆኑም ባሻገር እጅጉን ትስስር ስላለው፤ አንዱን ከአንዱ ነጥዬ ላቀርብላችሁ ባለመቻሌ ሁለቱንም አንድ ላይ ልቀላቅለው ተገድጃለሁ) የህያ በአባቱ ነቢያዊ አስተዳደግ እና በመለኮታዊ ስነስርዐት ታንፆ አደገ።የህያ አላህ የተውራትን ህግጋት እንደ ጉድ አሳውቆታል።           🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹 በእየሩሳሌምም የተውራት ፈራጅ ሆኗል።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለም 30 አመት ሳይሞላው የነብይነትን ማዕረግ ከአላህ ዘንድ ተሰጠው። የህያ ምንም እንኳን የእውቀትን ጫፍ የደረሰ ዓሊም ቢሆንም ምንም አይነት ኩራት የሌለበት ልጅ ሲሆን በዘመኑ ሰዎች ርካሽ የተባለውንም ልብስ ነበር የሚለብሰው። የህያ(ዐ.ሰ) እና ዒሳ(ዐ.ሰ) በአንድ ዓመት የተወለዱ ምርጥ ዘመዳሞች ከመሆናቸውም ባሻገር ማይለያዩ ጓደኛሞችም ናቸው። አንድ ቀን ሁለቱም ቁጭ ብለው በማውጋት ላይ ሳሉ አላህ የህያን 5 ነገሮችን እንዲተገብር እና የእየሩሳሌምን ህዝቦችም እንዲያዝ አዘዘው። ዒሳም ለየህያ(ዐ.ሰ)፦" የህያ አላህ 5 ነገራቶችን እንድትተገብር እና ህዝብህንም እንድታዝ አዞሀል።አንተ ምትፈፅመው ከሆነ ፈፅመው፤ካልፈለግክ ለኔ ተውልኝ" አለው። የህያም፦"ወንድሜ ሆይ! አላህ እኔን ያዘዘኝን ነገር አንተ ቀድመኸኝ ከተገበርከው አላህ እኔን እንዳይቀጣኝ እፈራለሁ" አለው።           🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹      #ኢንሻ_አላህ_ይቀጥላል........💫
Показать все...
👍 2
احرص ان تكون من خير الخلق አሏህ ዘንድ ከሁሉም የተሻለ ፍጥረት ለመሆን ጣር! قال تعالى : إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ "አሏህ ዘንድ በላጩ አሏህን ይበልጥ የሚፈራው ነው። 🌸 قال ﷺ : (خيركم من تعلم القرآن وعلمه) البخاري «ከናንተ ውስጥ በላጫችሁ ቁርዓንን ቀርቶ ያስቀራ ነው ።» 🌸 قال ﷺ (خياركم أحاسنكم أخلاقا) البخاري «ከናንተ ውስጥ በላጫችሁ ስነምግባሩ ያማረው ነው ።» 🌸 قال ﷺ (خياركم في الجاهلية خياركم في الإسلام إذا فقهوا) البخاري "ጃሂሊያ ላይ በላጭ የነበረ እስልምናም ላይ በላጭ ይሆናል ከተማሩና ዲኑን ከተረዱ" 🌸 قال ﷺ ( خيركم أحسنكم قضاءً) البخاري "ከሰዎች በላጫቸው ዕዳውን ሲከፍል አሳምሮ ሚከፍል ነው" 🌸 قال ﷺ (خيركم خيركم لأهله) صحيح ابن حبان «ከናንተ በላጫቻችሁ ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው» " 🌸 قال ﷺ ( خير النساء التي تسره إذا نظر، وتطيعه إذا أمر، ولا تخالفه في نفسها ولا مالها بما يكره». "ከሴቶች ሁሉ በላጭ ስታያት የምታስደስትህ፣ ስታዛት የምትታዘዝህ፣ ስትርቅ እራሷንም ገንዘብህንም የምትጠብቅ ናት።" 🌸 قال ﷺ (خيركم من أطعم الطعام وردَّ السلام) صحيح الجامع «በላጫችሁ ምግብን ያበላ እና ሰላምታን የመለሰ ነው» 🌸 قال ﷺ (خيركم من يُرجى خيره ويُؤمٓن شره) صحيح الترمذي «በላጭ ሰው ማለት ከርሱ መልካም የሚከጀልና መጥፎው የማይፈራ ሰው ነው።» 🌸 قال ﷺ (خير الناس أنفعهم للناس) صحيح الجامع "ከሰዎች ውስጥ በላጭ የሆነው ጠቃሚው ነው" 🌸 قال ﷺ ( خير الناس ذو القلب المخموم واللسان الصادق ) صحيح الجامع "ከሰዎች ውስጥ በላጭ ቀልብ ንፁህ [አላህን የሚፈራ ያ በሱ ላይ ድንበር ማለፍ የሌለበት ነው] እና ሐቅ ተናጋሪ የሆነው ነው።" 🌸 قال ﷺ (خير الأصحاب عند الله خيركم لصاحبه، وخير الجيران عند الله خيركم لجاره) صحيح الأدب «አላህ ዘንድ በላጭ ባልደረባ ማለት ለባልደረባው በላጭ የሆነው ነው አላህ ዘንድ በላጭ ጎረቤት ማለት ለጎረቤቱ በላጭ የሆነው ሰው ነው።» 🌸 قال ﷺ (خيار أئمتكم الذين تحبونهم ويحبونكم) مسلم "ከመሪያችው በላጭ የሆነው የምትወዷቸው እና የሚወዳችው ናቸው" 🌸 قال ( خير الناس من طال عمره وحسن عمله) صحيح الجامع "በላጭ ሰው እድሜው ረዝሞለት ስራውም ያማረለት ነው አ አሏህ ከበላጮቹ ያድርገንን
Показать все...
👍 4