cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Qubee media

Median kun kessan beksisaa qabdan beksisuu dandessu የናንተ ሚድያ ማዕከል ነው

Больше
Рекламные посты
542
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ፕሮፌሰር ገመቺስ ፊሌን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ሾሟል። @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዳሎል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለሀገር ግንባታ ተመስርቷል። ፎረሙ በአራት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማለትም በሰመራ፣ ወልድያ፣ ወሎ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች አባልነት መመስረቱ ተሰምቷል፡፡ አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን በማቀፍ ስለ ሀገር ግንባታ በመወያየት አስተዋፅዖ ለማበርከት መድረኩን ይጠቀሙበታል ተብሏል፡፡ ፎረሙ የተቋቋመው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ''ለሀገራዊ ማንነትና እሴት ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና" በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ወቅት ነው፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቻይናው ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዘንድሮ ያስመርቃል፡፡ የቤጂንግ የውጭ ጉዳይ ጥናት ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትምህርት ጥናት ላይ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሰን ዮዥንግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዳይሬክቶሬት አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትምህርት ጥናት ላይ መስራቱ ለኢትዮ-ቻይና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ መጎልበት ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን እንዲያስተምር ጠይቀዋል፡፡ #ኢፕድ @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#WolkiteUniversity በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ላቋረጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ህዳር 24/2016 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➤ መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበት ሰርተፍኬት፣ ➤ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ ➤ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ኮፒው፣ ➤ አራት 3x4 ፎቶግራፍ፣ ➤ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
#DireDawaUniversity በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ በማምጣት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ሴሚስተርን ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal የሞላችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 23 እስከ 25/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➤ የ8ኛ ክፍል ስርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➤ ከ9-12ኛ ከፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➤ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➤ 3×4 ፎቶግራፍ (8) ➤ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሰባት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ የምሁራኑን የማስተማር ሥራ፣ የምርምር ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ ጉዳይ ያላቸውን አስተዋፆ በመገምገም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው፦ 1. ዶ/ር ኢንጂነር ፍቃዱ ፋፋ 2. ዶ/ር መንበሩ መንገሻ 3. ዶ/ር ኦሉ ኢማኑኤል 4. ዶ/ር ደጀኔ ገመቹ 5. ዶ/ር ደምሰው አመኑ 6. ዶ/ር ቸርነት ቱጌ 7. ዶ/ር አበራ ጉሬ @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው መደበኛ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። በ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን በቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal የሞላችሁ ተማሪዎችን የሞላችሁበትን ቅፅ በመያዝ በተገለፁት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
#KUE በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ለ2016 የትምህርት ዘመን ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➢ የ8ኛ ክፍል ስርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ አንድ 3×4 ፎቶግራፍ ➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ። @tikvahuniversity
Показать все...