ru
Feedback
TMPC 1917

TMPC 1917

Закрытый канал
1 146
Подписчики
-224 часа
-47 дней
-1930 день
Архив постов
photo content

photo content

photo content
+8

ዕለተ ሐሙስ የካቲት 28/2017ዓ.ም በተመራቂ ሠልጣኞች የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጀ ። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል የዘርፉ 2ኛ ዙር የ201
+8
ዕለተ ሐሙስ የካቲት 28/2017ዓ.ም በተመራቂ ሠልጣኞች የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጀ ። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል የዘርፉ 2ኛ ዙር የ2017ዓ.ም ተመራቂ የደረጃ 4  ማርኬቲንግ ሠልጣኞች ለአሠልጣኞቻቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ የነበረን ቆይታ መልካም ነበር ፤እኛን ለማብቃት ዋጋ ከፍላችኋል፤ ክበሩልን አሠልጣኞቻችን  ለማለት የተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ነው ትላለች የክፍሉ ተጠሪና አስተባባሪ ሠልጣኝ ጥሩ ቀን ገመቹ። በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቀድሞ የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ጌታሁን ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት ሠልጣኞች ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ለሚጠብቃቸው የCOC ምዘና ጠንካራ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበው ለአሠልጣኞቹም እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል። በተመሳሳይ ምስጋና የቀረበላቸው አሠልጣኞችም  ከሠልጣኞቻቸው ጋር ስለነበራቸው ቆይታና ስለቀረበላቸው  ምስጋና አክብሮታቸውን ገልጸው በቀጣይ ለምዘና ስለሚኖራቸው ዝግጅት መዘናጋት እንዳይፈጠር ጠቁመው  መልካም ውጤትን እና መልካም የስራ ግዜ እንዲሆንላቸው  ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል።                     ኮሙኒኬሽን ቡድን

ዕለተ ሐሙስ የካቲት 27/2017ዓ.ም በተመራቂ ሠልጣኞች የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጀ ። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል የዘርፉ 2ኛ ዙር የ2017ዓ.ም ተመራቂ የደረጃ 4  ማርኬቲንግ ሠልጣኞች ለአሠልጣኞቻቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ የነበረን ቆይታ መልካም ነበር ፤እኛን ለማብቃት ዋጋ ከፍላችኋል፤ ክበሩልን አሠልጣኞቻችን  ለማለት የተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ነው ትላለች የክፍሉ ተጠሪና አስተባባሪ ሠልጣኝ ጥሩ ቀን ገመቹ። በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቀድሞ የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ጌታሁን ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት ሠልጣኞች ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ለሚጠብቃቸው የCOC ምዘና ጠንካራ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበው ለአሠልጣኞቹም እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል። በተመሳሳይ ምስጋና የቀረበላቸው አሠልጣኞችም  ከሠልጣኞቻቸው ጋር ስለነበራቸው ቆይታና ስለቀረበላቸው  ምስጋና አክብሮታቸውን ገልጸው በቀጣይ ለምዘና ስለሚኖራቸው ዝግጅት መዘናጋት እንዳይፈጠር ጠቁመው  መልካም ውጤትን እና መልካም የስራ ግዜ እንዲሆንላቸው  ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል።                     ኮሙኒኬሽን ቡድን

ዕለተ ሐሙስ የካቲት 28/2017ዓ.ም በተመራቂ ሠልጣኞች የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጀ ። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል የዘርፉ 2ኛ ዙር የ201
+8
ዕለተ ሐሙስ የካቲት 28/2017ዓ.ም በተመራቂ ሠልጣኞች የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጀ ። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል የዘርፉ 2ኛ ዙር የ2017ዓ.ም ተመራቂ የደረጃ 4  ማርኬቲንግ ሠልጣኞች ለአሠልጣኞቻቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ የነበረን ቆይታ መልካም ነበር ፤እኛን ለማብቃት ዋጋ ከፍላችኋል፤ ክበሩልን አሠልጣኞቻችን  ለማለት የተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ነው ትላለች የክፍሉ ተጠሪና አስተባባሪ ሠልጣኝ ጥሩ ቀን ገመቹ። በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቀድሞ የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ጌታሁን ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት ሠልጣኞች ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ለሚጠብቃቸው የCOC ምዘና ጠንካራ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበው ለአሠልጣኞቹም እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል። በተመሳሳይ ምስጋና የቀረበላቸው አሠልጣኞችም  ከሠልጣኞቻቸው ጋር ስለነበራቸው ቆይታና ስለቀረበላቸው  ምስጋና አክብሮታቸውን ገልጸው በቀጣይ ለምዘና ስለሚኖራቸው ዝግጅት መዘናጋት እንዳይፈጠር ጠቁመው  መልካም ውጤትን እና መልካም የስራ ግዜ እንዲሆንላቸው  ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል።                     ኮሙኒኬሽን ቡድን

photo content
+1

photo content
+2

photo content

ዕለተ ማክሰኞ የካቲት 25/2017ዓ.ም አርቲስት ሳሚ ዳን የህይወት ተሞክሮውን ለሙዚቃ ትምህርት ክፍል ሠልጣኞች አጋርቷል ። የሙዚቃ ትምህርት ክፍል ሠልጣኞች በየወሩ ከሚያዘጋጁት የተቀናጀ ህብራዊ የሙዚቃ ፣ የሥነ-ስዕልና የስነ-ጽሁፍ ምሽት በተጨማሪ በዛሬው ዕለት አርቲስት እና ኢንጅነር ሳሚ ዳንን በመጋበዝ የህይወት ተመኩሮውን ለሠልጣኞች አጋርቷል። ሠልጣኞች ወደ ስኬት ለሚያደርጉት ጉዞ ያግዛቸው ዘንድ በህይወቱና በጉዞው ያሳለፈውን ውጣ ውረድ እንዲሁም የስኬቱን መንገድ  በሰፊውአጋርቷል። አንድ ሙዚቀኛ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለበት ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጥ ግለሰቡ በጥረቱ የሚያመጣው መሆኑን ተናግሯል ። ጠንክረህ ከሠራህ ሙያው /ዘርፉ የምትከበርበት፣ አንቱታን የምታተርፍበት ዘርፍ በመሆኑ ጠንክራችሁ እንድትሰሩ በማለት መልእክቱን አስተላልፏል ።                   ኮሙኒኬሽን ቡድን

ዕለተ ማክሰኞ የካቲት 25/2017 ዓ.ም የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጃ ሽግግር  ከጉለሌ ክ/ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ ኢንተርፕራይዞች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሄደ። የመድረኩ ዓላማ ፣ኢንተር ፕራይዞች ስለ ድጋፍ ማዕቀፉ እንዲረዱ ማድረግ ነው ፤      - የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ምንድ ነው ? - የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አስፈላጊነት - አራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች የተብራሩበት ሲሆን ድጋፉ የኢንተር ፕራይዞችን ችግር የለየ እና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆን ይጠበቅበታል ። እንደየ አስፈላጊነቱና ኢንተርፕራይዞቹ በሚፈልጉት የድጋፍ ማዕቀፍ መሠረት ድጋፍ የተደረገላቸው ኢንተር ፕራይዞች ከድጋፍ በኋላ ሃብት እንዲያፈሩ ፣  ከደረጃ ወደ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ይጠበቃል በማለት መረጃውን ያጋሩት የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ መርዴ ናቸው ። በመቀጠልም ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ  ከኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት የተገኙት አቶ ነብዩ የፕሮግራሙን አስፈላጊነት አብራርተው በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቱ እንደሚደረግ አቅጣጫ አስይዘዋል ። - የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ያለውን ጠቀሜታና    ምን ለውጥ አመጣላችሁ ? - በስልጠናና ድጋፍ አሠጣጥ ያለውን ክፍተት        ከኢንተር ፕራይዙን እና ከድጋፍ አንጻር - አሁን ያለው የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አሠጣጥ ላይ    ምን ይሻሻል ? ምንስ ይጨመር ? ምንስ ይቀነስ ? በሚሉ ርእሶች ላይ  ተሳታፊዎችን ለውይይት ጋብዘዋል ። ተሳታፊዎች ይቸግረናል ለስራችን ማነቆ ናቸው ያሏቸውን  የገበያ ትስስር ያለመኖር ፣ ሼድ ልቀቁ መባል ፣ ስራዎችን በዘመድ አዝማድ ለአንድ ወገን ብቻ መስጠት ፣ የብድር አቅርቦት አለመመቻቸት ፣ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች ገቢያችንን ያላገናዘበ  ከ5000ብር በታች እንዳትከፍሉ ብሎ ማለት ፣ በእድገት ደረጃ ላይ ያልደረስንበትን ደርሳችኋል በማለት ማስገደድ ፣ የድጋፍ አግባቡ ከንግግር የተሻገረ አለመሆን ፣ ድጋፍ በአግባቡ ሳያደርጉልን ማህተምና ፊርማ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ባለሙያዎች መኖራቸው ፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰጠው ስልጠና 15ቀን ብቻ በመሆኑ በቂ አይደለም የ3 ወራት ቢሆንልን ፣ ከየቢሮው የምንሰበስበው የነበረ ወረቀት ባለመኖሩ ተቸግረናል ወይ ዘርፍ ቀይሩልን አሊያም የሚስተካከልበትን መንገድ ብታፈላልጉልን ወ.ዘ.ተ እሚሉ ጥያቄዎች ከሞላ ጎደል ተነስተው በመድረኩ ምላሽ እሚሰጥባቸው በሁለቱም አካላት ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ያሉትን ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርቡት እና ምላሽ እንደሚሰጥባቸው  ከመድረኩ ተጠቁሟል።                     ኮሙኒኬሽን ቡድን

photo content
+7

ዕለተ ሰኞ የካቲት 24/ 2017ዓ.ም የሌዘር ትምህርት ክፍል በአጫጭር ስልጠና የውስጥ ገቢ ማመንጨት የሚያስችለውን ፕሮፖዛል በአስገመገመ። ተቋማት ከማስተማር ባሻገር የራሳቸውን የውስጥ ገቢ ለማመንጨ
+4
ዕለተ ሰኞ የካቲት 24/ 2017ዓ.ም የሌዘር ትምህርት ክፍል በአጫጭር ስልጠና የውስጥ ገቢ ማመንጨት የሚያስችለውን ፕሮፖዛል በአስገመገመ። ተቋማት ከማስተማር ባሻገር የራሳቸውን የውስጥ ገቢ ለማመንጨትና ለማሳደግ እንዲችሉ እና አሠልጣኞችን በውስጥ ገቢ ለመደገፍ  የሚረዳ ሥራ መስራት እንዳለባቸው የሚጠቁም አቅጣጫ በመንግስት ተቀምጧል። ይህንን አቅጣጫ መሠረት ያደረገ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀርቦ በተሣታፊዎች እንዲተች ተደርገዋል። ሰነዱ የተሳታፊዎችን ግብረመልስ አካቶ  ወደ ስራ ለማስገባት እና ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችል ይታመናል ። የቆዳ ሥራ ውጤቶችን ለመሥራት በሚያስችል ሥልጠና ላይ አተኩሮ የተዘጋጀው ሰነድ በአጫጭር ስልጠና ከ3ወር - ስድስት ወር በሚደርስ የግዜ ገደብ ብዛት ያለውን የማህበረሰብ ክፍል ተሳታፊ የሚያደርግ ነው ተብለዋል። የመነሻ ሃሳቡን ለውይይት ያቀረቡት ባለሙያ በስልጠና ዘርፉ አሰልጣኝ ብርሃኑ ረዳኢ ናቸው ። በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ መብራራት ያለባቸው ነጥቦች ፣ አልተካተቱም ያሏቸውን ይዘቶች እና ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ከቤቱ ቀርበው በአወያዪና ተሳታፊዎች ከሁለቱም አቅጣጫዎች በተሰጠ ምላሽ ግልፅ እንዲሆኑ ተደርጓል ። ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው በመንግስት ከተሰጡ አቅጣጫዎች  ዋነኛው ተቋማት ኢንተርፕራይዝ  አቋቁመው ወደ ስራ መግባት እንዲችሉና ምርት በማምረት ተጨማሪ ገቢ እንዲኖሮ ማስቻል ነው ። በመሆኑም ይህን ጅማሮ ወደ ስራ ማስገባት አሌ የማይባል ተግባር ሊሆን ይገባልም ተብሏል። በተመሳሳይ  ሌሎች ስልጠና ዘርፎችም ይህንን ፈለግ በመከተል ወደ ስራ እንዲገቡ መልእክት ተላልፏል።          ኮሚኒከሽን ቡድን

ዕለተ ሰኞ የካቲት 24/2017ዓ.ም በሠልጣኞች እርካታ ላይ ለሚሰራ ጥናት ግንዛቤ መፍጠሪያ ሥራ ለተሳታፊዎች ተሠጥተዋል። በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና አሠጣጥን እና የሠልጣኞች እርካታ
+4
ዕለተ ሰኞ የካቲት 24/2017ዓ.ም በሠልጣኞች እርካታ ላይ ለሚሰራ ጥናት ግንዛቤ መፍጠሪያ ሥራ ለተሳታፊዎች ተሠጥተዋል።  በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና አሠጣጥን እና የሠልጣኞች እርካታን አስመልክቶ በሚሠራው ጥናት ላይ ከየስልጠና ዘርፉ የተውጣጡ አንድ አንድ አሠልጣኞች የሚሳተፉበት የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥራ ተሠራ። የጥናትና ምርምር ሥራው በሪሰርችና ፐብሊኬሽን ቡድን የሚመራ ሲሆን በስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች አስተባባሪነት  ክትትልና ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የጥናቱ ወሰን አሁን ላይ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ያሉ በናሙናነት የተመረጡ ሰልጣኞች የሚካተቱበት ነው። የግንዛቤ መስጫ ነጥቦቹ በዋናነት በአሰለጣጠን ስልት፣ በወርክሾፕ አደረጃጀት፣ በምዘና ሥርዓት እና - የሰልጣኝ ውጤት በሰዓቱ መግባቱን አስመልክቶ የሚዳስሱ መሆናቸውን በአስተባባሪው በአቶ ዘላለም ሲሳይ ተገልጸዋል።                    ኮሙኒኬሽን ቡድን

Repost from N/a
Na🌱Na Event is excited to welcome the talented musical artist, Sami Dan to our next event! Have a burning question for him?
+1
Na🌱Na Event is excited to welcome the talented musical artist, Sami Dan to our next event! Have a burning question for him? Whether it's about his musical journey, creative inspirations, or his favorite moments on stage-this is your chance to ask! @nana_event

ዕለተ ዓርብ ታህሳስ 21/2017ዓ.ም ለአሠልጣኞች የክህሎት ክፍተት መሙያ ስልጠና                       ተሰጠ። በአውቶሞቲቭ ስልጠና ዘርፍ የአሠልጣኞች የክህሎት ክፍተት መሙያ ስልጠና ለ15 ቀናት የተሰጠ ሲሆን ዓላማውም አሠልጣኞችን ለምዘና ብቁ እንዲሆኑ ማስቻልና ከምዘናው በኋላም  በማሰልጠን ስራ ላይ ተጨማሪ ክህሎት በማደበር ውጤታማ የማሰልጠን ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ አጋዥ እንዲሆን ታስቦ ነው ያሉን የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ደሳለኝ አዱኛ ናቸው። በስልጠና ዘርፉ ያሉ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች አብዛኞቹ  የቆዩ በመሆናቸው አሁን ካለው ቴክኖሎጂ ጋር የማይጣጣሙ ሆነው ቆይቷል። ከባለፈው ዓመት ወዲህ የተወሰኑ አዳዲስ ማሽነሪዎች የገቡ ቢሆንም ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስችል ዕውቀት በተሟላ መልኩ አልተገኘም።  ችግሩን ለመቅረፍ ማኑዋሎቹን እና በመጀመሪያ ዙር ምዘናውን ውጤታማ የሆኑ 6 አሰልጣኞችን በመጠቀም የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ ተሞክሯል በተጨማሪም  እርስ በርስ በመማማር ሌላውን በማሰልጠን ለምዘና ዝግጁ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል ። ይሁን እንጂ በስልጠና ዘርፉ የሌሉ  ብዙ ማሽኖች በመኖራቸው ከምዘናው በፊት ኮሌጁ ተመዛኞቹ ሌላ ቦታ ሄደው የሚሰለጥኑበትን መንገድ እንዲመቻችላቸው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ዘርፉ 10 ሴክሽን ሰልጣኝ ተቀብሎ እያሰለጠነ ያለ ቢሆንም በየግዜው የሚጠየቁና የተጎደሉ ዘመናዊ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች የተወሰኑ ቢገዙም በአብዛኛው ያልተሟላ በመሆኑ በስልጠናው ውጤታማነት ላይ ተጽኖ እንዳያሳድር በአፋጣኝ ቢሟላልን እሚል ሃሳባቸውንም ሰንዝረዋል ። አሠልጣኝ ማጌጫ ተሾመ ይባላሉ በመጀመሪያው ዙር ተመዝነው ብቃታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን  እርስ በርስ መደጋገፋችን እና መረዳዳታችን ተመዛኞችን ውጤታማ ለማድረግ እና በሁሉም ዘርፍ ተመሳሳይ የሆነ እውቀት ማስተላለፍ እንድንችል ያግዘናል፤ በተጨማሪም ክፍተት ቢፈጠር እርስ በርስ ለመሸፋፈን የሚያስችል ዕውቀትን እንለዋወጥበታለን ይላሉ ።  በክፍተት መሙያ ስልጠናው በስልጠና ላይ ያገኘናት ሰብለ በላይ ይህ የእርስ በእርስ ስልጠና ክፍተታችንን ለመሙላት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነግራናለች። የየዘርፉን ዕውቀት ለመጋራት /ለመለዋወጥም ያግዘናል፣ ለማሰልጠን ስራውም  ዝግጅት ስለሆነ ጠቀሜታው የጎላ ነው ትላለች። በስልጠና ቦታው የተገኙት የኮሌጁ የተቋማት አቅም ግንባታ ምክትል ዲን ዶ/ር ከበደ ቡዬቻ የእርስ በእርስ መደጋገፉን እና መከባበሩ ውጤታማ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው ምዘናው በውጤት እንዲጠናቀቅ ምኞታቸውን ገልፀዋል። ሌሎች የስልጠና ዘርፎችም ይህንን በጎ ልምድ በመጋራት ቢጠቀሙበት መልካም ነው እንላለን ።                      ኮሙኒኬሽን ቡድን

photo content
+9