ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሊሰቃይ ሲሔድ ጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለመለሰው ለቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለመነኰሳት አለቃ ለታላቁ አባ መቃርስ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕቱ አሞንዮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ፦ የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከኢየሩሳሌም ነው የአባቱ ስም ክርስቶፎሮስ ነው ትርጓሜውም ክርስቶስን የለበሰ ማለት ነው ክርስቲያንም ነበረ የእናቱም ስም ቴዎዶስያ ነው እርሷ ግን ጣዖትን ታመልክ ነበረች። ❤ አባቱም በዐረፈ ጊዜ እናቱ ወሰደችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ገንዘብ ይዛ ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደች ልጅዋንም በእስክንድርያ ከተማ ገዥ አድርጎ ይሾመው ዘንድ ለዲዮቅልጥያኖስ እጅ መንሻ ሰጠችው እርሱም ሾመው የሹመት ደብዳቤውንም ጽፎ ክርስቲያኖችን እንዲአሠቃዩ አዘዘው። ❤ ከአንጾኪያም ከተማ ወጥቶ ጥቂት እንደ ተጓዘ ወደእርሱ የሚያስፈራ ቃል ከሰማይ መጣ በስሙ ጠርቶ እንዲህ አለው "ከሀዲው ዲዮቅልጥየኖስ እንዳዘዘህ ብታደርግ አንተ በክፉ አሟሟት ትሞታለህ። እርሱም "ራስህን ትገልጥልኝ ዘንድ ጌታዬ ሆይ እለምህሃለሁ" አለው ወዲያውኑም የብርሃን መስቀል ታየው ዳግመኛም "በኢየሩሳሌም የተሰቀልኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ" የሚለውን ቃል ሰማ። ❤ ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ ተመልሶም ከአንጥረኛ ዘንድ የወርቅ መስቀል አሠራ ከዚያም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ተጓዘ በጒዞውም ውስጥ ሊገድሉት ዐመፀኞች አረማውያን ተነሡበት እርሱም በእነርሱ ላይ በርትቶ ክብር ይግባውና በጌታ ክርስቶስ መስቀል ድል አደረጋቸው። እናቱም "በጦርነት ላይ ለረዱህና ላዳኑህ አማልክት መሥዋዕትን ሠዋ" አለችው እርሱም እንዲህ አላት "እኔስ አዳኝ በሆነ በመስቀሉ ኃይል ላዳነኝ ክብር ይግባውና ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ"። ይህንንም በሰማች ጊዜ ልጅዋ አብሮኮሮንዮስ ክርስቲያን እንደሆነ ወደ ዐመፀኛው ዲዮቅልጥያኖስ ልካ ነገረችው። ዲዮቅልጥያኖስም ጭፍራ ልኮ ወደ ቂሣርያ ከተማ አስወሰደው የቂሣርያውንም ገዥ ስለ ርሱ እንዲመረምርና እንዲአሠቃየው አዘዘው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ በአቀረቡት ጊዜ በፊቱ ቁሞ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ለመሞት እስቲደርስም ጽኑዕ ግርፋትን ገረፈው ከዚህም በኋላ አሠረው። በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ብርሃን ውስጥ ታየው ከእርሱም ጋራ ብርሃናውያን መላእክት ነበሩ ከማሠሪያውም ፈታውና በመለኮታዊ እጁ ዳሰሰው ከቍስሎቹም ሁሉ አዳነው። ❤ በማግሥቱም መኰንኑ ስለ ቅዱሱ ዜና ሙቶ እንደሆነ ወይም አልሞተ እንደሆነ ጠየቀ ለእርሱ የሞተ መስሎት ነበረና። ቅዱሱም በመጣ ጊዜ ጤነኛ ሁኖ አየውና መኰንኑ አደነቀ በዚያ የነበሩ ሕዝቡም አይተው እጅግ አደነቁ እንዲህም እያሉ ጮኹ "እኛ በግልጥ ክርስቲያን ነን በቅዱስ አብሮኮሮንዮስ አምላክ እናምናለን"። ከእነርሱም ጋራ ሁለት መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች እናቱ ቴዎዶስያም ነበሩ መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ። እነርሱም ቆረጡአቸው። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ሐምሌ ስድስት ቀን ተቀበሉ። ❤ ቅዱስ አብሮኮሮንዩስን ግን ምን እንደሚያደርግበት እስቲአስብ ድረስ ሦስት ቀን አሠረው ከዚህም በኋላ አውጥቶ እንዲህ አለው "ልብህ እንዲመለስ ነፍስህንም እንድታድን ለአማልክትም እንድትሠዋ እነሆ በአንተ ላይ ሦስት ቀናት ታገሥኩ"። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "መኰንን ሆይ የለም ልቤ ወደ ስሕተት አይመለስም ክብር ይግባውና ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ አውቄ ተረድቼአለሁ ጣዖታቱም ሁሉ ከዕንጨትና ከደንጊያ በሰው እጅ የተሠሩ ፍጡራን ናቸው እንጂ አማልክት አይደሉም አይጐዱም አይጠቅሙም"። ❤ መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ጐኖቹንም በሰይፍ እንዲሰነጣጥቁ አዘዘ አርኬላዎስ የሚባል ባለ ሰይፍም የቅዱሱን ጐኖቹን ሊሠነጥቅ እጁን ዘረጋ ያን ጊዜም እጁ ደረቀች ወድቆም ሞተ። መኰንኑም ተቆጥቶ በምድር ጥለው ይገርፉት ዘንድ አዘዘ እንደ አዘዘም ገረፉት በሰይፍም ጐኖቹን ሠንጥቀው በቍስሉ ውስጥ መጻጻ ጨመሩ እስከ ወህኒ ቤትም ድረስ በእግሩ ጐተቱት በዚያም ሁለት ቀኖች ኖረ ከዚህም በኋላ አውጥቶ እሳትን በተመላች ጕድጓድ ውስጥ ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችንም አዳነው ምንም ምን አልነካውም። ❤ ብዙ ከማሠቃየቱም የተነሣ መኰንኑ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለአብሮኮሮንዮስ በኢየሩሳሌም ዘተወልደ። እምለባሴ ክርስቶስ አቡሁ በአርዑተ ወንጌል ዘተጸምደ። በትእዛዘ ንጉሥ ሠዊዐ ሶበ ለጣዖት ፈቀደ። ቃል ዘይከልኦ እምሰማይ ወረደ ወበቊስላቲሁ አንበረ መለኮት እደ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 14። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ፡አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ። ንቃሕ እግዚኦ ለምንት ትነውም"። መዝ 43፥22-23። የሚነበቡት 1ኛ ተሰ 4፥1-13፣ 1ኛ ጴጥ 5፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥19-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥1-10። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን ለአገረ ቅፍጥ ኤጲስቆጶስ ከነቢያት ትንቢትም አንዳንዱን መጽሐፍ በሚነብ ጊዜ ትንቢቱ የሚነበብለት ነቢይም ወደርሱ መጥቶ ንባቡን እስቲፈጽም ይቆይ ለነበረ፤ እጆቹን አንሥቶ በሚጸልይ ጊዜ ጣቶቹ እንደ ፋና ይበሩ ለነበር ለታላቁ አባት ለአባ ብስንድዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና በግብፅ ደቡብ ከቡና አውራጃ ከጡሕ ከሚባል አገር ለሆነ ለቅዱስ አሞን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕፋቱ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የአገረ ቅፍጥ ኤጲስ ቆጶስ አባ ብስንድዮስ፦ ይህም ቅዱስ ሰው መንኵሶ በታላቅ ገድል ተጠምዶ ቅዱሳት መጻሕፍትንም አጠና ከቅዱሳት መጻሕፍትም ውስጥ የዳዊትን መዝሙርና የነቢያትን መጻሕፍት አጥንቶ ነበር። ከነቢያት ትንቢትም አንዳንዱን መጽሐፍ ያነብ ነበረ። ትንቢቱ የሚነበብለት ነቢይም ወደርሱ መጥቶ ንባቡን እስቲፈጽም ይቆይ ነበር። ❤ ስለርሱ እንዲህ ተባለ እርሱ እጆቹን አንሥቶ በሚጸልይ ጊዜ ጣቶቹ እንደ ፋና ይበሩ ነበር እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ። እርሱም በዕድሜው ዘመን ሁሉ የሴት ፊት አላየም። ራሱን ወደ ምድር ያዘነብል ነበር እንጂ። በሆድዋ ውስጥ ታላቅ ደዌ የነበረባትም አንዲት ሴት ነበረች ከበዐቱ ደጅ ጠበቀችውና በድንገድ አገኘችው። እርሱም ሮጠ እርሷም ተከትላው ሮጠች ወደ እርሱ መድረስም በተሳናት ጊዜ እግሩ የረገጠቻትን አንዲት እፍኝ አፈር ዘግና በእምነት በላች ከደዌዋም ፈጥና ተፈወሰች። ❤ በአንዲት ዕለትም የሚያበሩ ሦስት ሰዎች አየ እነርሱም "አንተ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ትመግባት ዘንድ አለህ" እያሉ መክፈቻ ቅልፍን ሰጡት። ከዚህ በኋላ ቅፍጥ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ የቊርባን ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜም ጌታችንን እጆቹ በመሠዊያው ላይ ሆነው ይመለከተው ነበር። መላእቶቹንም በዙሪያው ቁመው ያያቸው ነበር። ❤ በአንዲት ዕለትም አንድ ቄስ ሊቀድስ ገባ በቅዳሴ እኩሌታ ላይም በመሠዊያው ፊት እያለ ምራቁን ተፋ። ቅዳሴውም በተፈጸመ ጊዜ ይህ አባት ገሰጸው እንዲህ አለ "በሚያስፈራው ወሠዊያው ፊት በምትቆም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጌትነት የተነሳ አትፈራምን የተፈኸውስ ምራቅ በመሠዊያው ዙሪያ በቆመ ኪሩብ ክንፈች ላይ እንደረሰ አታውቅምን"። ያን ጊዜም ያንን ቄስ መንቀጥቀጥ ያዘው ተሸክመውም ወደ ቤቱ ወሰዱትና ታሞ ሞተ። ❤ ይህም ቅዱስ አባት አንደበቱ ጣዕም ያለው ነበር በሚያነብ ጊዜ በሚያስተም ጊዜ በሚመክርም ጊዜ አይጠገብም ነበር። የዕረፍቱ ቀን በቀረበ ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና አስተማራቸው መከራቸውም በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ። ❤ ከሥጋውም ብዙ ተአምር ተገለጠ ደቀ መዝመሩ ከመግነዙ ጥቂት ቁራጭ ወስዶ በእምነት በሽቶኞችን ሁሉ ይፈውስ ነበር። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ብስንድዮስ ጸሎቱ ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ አሞን፦ ይህም ቅዱስ ከግብጽ ደቡብ ከቡና አውራጃ ጡሕ ከሚባል አገር ነው። ለዚህም ቅዱስ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጸለት ከእርሱ የሚሆነው ሁሉ ነገረው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ሒዶ አውግስጦስ የሚባል መኰንን ፊት ክብር ይግባው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም በመንኰራኵር ውስጥ በእሳት ላይ በመጣል በእሳት በአጋሉት በብረት አልጋ ላይ በማጋደም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ በመጨመር ጽኑዕ ስቃይም አሰቃዩት። የራሱንም ቆዳ ገፈው በራሱ ላይ የእሳት ፍም አኖሩ እግዚአብሔርም ያጸናው ነበር ያለምንም ጉዳት ጤነኛ አድርጎ ያስነሳው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በጎልማሳ አምሳል በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ተገለጠለትና አጽናናው እንዲህም አለው "ወዳጄ አሞን እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለው ስምህን የሚጠራውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ፣ ወይም ገድልህ የሚጽፈውን ሁሉ እኔ በመንግሥቴ ውስጥ አስበዋለሁ ኃጢያቱንም እደመስሳለሁ አገርህም እጠብቃለሁ" ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጥቶ ከእርሱ ዘንድ አረገ። ❤ ይህም ቅዱስ በሥጋው ሳለ ታላላቅ ታምራቶችንና ድንቆችን አደረገ ወዲያውንም በሠይፍ ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። ቅዱስ ዮልዮስም በዚያ ነበር ሥጋውን ወስዶ በመልካም ልብስ ገነዘው ከሁለት አገልጋዮቹም ጋር ወደ አገሩ ላከው በላይኛው ግብጽም ታላላቅ የሆኑ ድንቆችንና ተአምራቶች እያሳየ እስከ ዛሬ አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ሰማዕት በቅዱስ አሞን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 13 ሰንክሳር። + + + ❤ ሰላም ለብስንድዮስ ዘይኔጽር ነቢያት። እስከ ይፌጽም ኣንብቦ ጸሐፍ ትንቢተ። ወሰሚዓ ካዕበ ዘገብረ ትእምርተ። ብእሲት ጥዕየት እምደዌሃ ወሐይወት ሕይወተ። እምአሠረ እግሩ ቅድስት በሊዓ መሬተ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 13። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ 1፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥18-35፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥11-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችን ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ + + + ❤ "ሰላም ለከ ረዳኤ ቅዱሳን ሰማዕት። ወሐዋጼ ጻድቃን ዘውስተ ጾማዕት። ሚካኤል ፀሐይ ጥዒና ቈሪራን አዝርዕት። ያንቅሐኒ ወያንሥአኒ እምዳግም ሞት። ውስተ ክነፊከ ዘሀሎ ሕይወት"። ትርጉም፦ ቅዱሳን ሰማዕታትን በተጋድሎአቸው ጊዜ የምትራዳቸው ስለጽድቅ ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው በዱር በገደል የሚኖሩ ጻድቃንን የምትጎበኛቸው ላንተ ለሚካኤል ሰላም እላለሁ። ሚካኤል ሆይ የለመለሙ አዝዕርቶችን አብስለህ ለመከር የምታበቃቸው ፀሐይ አንተ ነህ። አሁንም በክንፍህ በሥልጣንህ ሥር ያለ ሕይወት ከዳግም ሞት እንቅልፍ ያንቃኝ ያትጋኝ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ12። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን ለከበረ መልአክ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል የፋርስ ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት እግዚአብሔር ለላከበት ቀን ንጉሥ ሕዝቅያስን ረድቶ በአንድ ሌሊት ከሰናክሬም ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ለገደለበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓልና ስርያቆስ ከሚባል አገር ለሆነ ለአባ ሖር ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ የአባ ሖር ማኅበር ከመቶ ሰባት ወንዶችና ከሃያ ሴቶች ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፡፡ + + + ❤ በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን የፋርስ ንጉሥ ወደ ሆነ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት እግዚአብሔር ላከው ከሰናክሬም ሠራዊት ከሰናክሬም ሠራዊትም መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞች ገደለ። ❤ ይህም እንዲህ ነው ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ ሕዝቅያስንና ፈጣሪው እግዚአብሔርን እየዘለፈ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ እንዲህም አለ "እግዚአብሔር ያድናችኋል እያለ ሕዝቅያስ አያስታችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው"። ❤ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እጅግ አዘነ ወገኖቹንና አገሩ ኢየሩሳሌምንም ያድን ዘንድ ማቅ ለብሶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀበሎ ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ላከለት። ድንቅ ሥራንም ሠርቶ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አዳናቸው። ❤ ስለዚህም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ በዚች ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ሖር፦ ይህም አባት ስርያቆስ ከሚባል አገሩ ነው። አባቱም አንጠረኛ ነበር አንዲት እኅቱም ነበረችው። ጎልማሳም በሆነ ጊዜ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደ አገረ ፈርማ ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ከሥቃዩም ድኖ ተነሣ። መኰንኑም በእጁ ላይ ጌታችን ያደረገውን ይህን ተአምር አይቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ አመነ። በሌላ መኰንን እጅም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ በሰማዕትነት ሞተ። ❤ ቅዱስ አባ ሖርን ግን ወደ እንዴናው ላከው በዚያም በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃዩት በመንኰራኵሮችም አበራዩት ዘቅዝቀውም ሰቅለው በእሳት በአጋሉት የብረት በትር ደበደቡት። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 12 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሖር በኀበ እግዚኡ ዘተመዝገነ። አመ ጽዕለተ ተወክፈ ወበትረ ኀፂን ርሱነ። ወሶበ እምኔሁ ነጸረ ዕበየ ተአምር ዘኮነ። ምስለ ብእሲቱ ወደቂቁ ከዊኖ ፍልጣነ። በእደዊሁ መኰንን አምነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ12። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታምእሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 24፥30-36። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ኢይድኅን ንጉሥ በብዝኀ ሠራዊቱ። ወያርብህኒ ኢድኅነ በብዝኃ ኃይሉ። ወፈረስኒ ሐሰት ኢያድኅን"። መዝ 32፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥17-30፣ ይሁ 1፥7-14 እና የሐዋ ሥራ 10፥3-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥1-9። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል የወራዊ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

#ምስባክ መዝሙር ፴፫፥፩ ተፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር ወለራትዓን ይድልዎሙ ክብር ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ #ትርጉም ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ https://t.me/Eotcw

የነገው ምስባክ በድምፅ

photo content

photo content

photo content

❤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከቅዱሳን መካናት ተባረከ በዚያም በቅድስት ትንሣኤ በተሰየመች ቤተ ክርስቲያን በጳጳሱ በአባ ሚካኤል እጅ ቅስና ተሾመ። ከዚያም ወደ ምስር አገር ተመልሶ በማዕልቃ ባለች በእመቤታችን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጻፈ ተቀመጠ። ❤ በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ቄርሎስ ዐረፈ። የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ መንበርም ያለ ሊቀ ጳጳሳት ነበር። ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት የአገር ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበስበው ይሾሙት ዘንድ በአንድ ምክር ተስማሙ ሰይጣን ግን ክፉዎች ሰዎችን አነሣሥቶ ተቃወሙት። ሹመቱንም አልፈቀዱም። ነገር ግን መንሳዊ አባት የነበረውን የከሊል ልጅ አባ አትናቴዎስን ሾሙት። እርሱም መንጋውን በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ። ❤ እርሱም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆሳትና የሕዝቡ አለቆች ዳግመኛ ተሰበሰቡና በእጃቸው ጽፈው አባ ገብርኤል እንዲሾም ፈቀዱ ሁለተኛም በሕቡም መካከል ሁከት ተነሳ ከሌሎችም ጋር እጣ ያጣጥሉት ዘንድ ተስማሙ ስሞቻቸውንም ጽፈው በመንበሩ ላይ አኖሩ በላዩም እየጸለዩና እየቀደሱ ሦስት ቀኖች ሰነበቱ። ከዚህም በኋላ ታናሽ ብላቴና አምጥተው በውስጡ የአባ ዮሐንስ ስም ያለበትን ክርታስ አወጣላቸው። ያም አባ ዮሐንስ ተሾመ ይህ አባ ገብርኤል ግን ለማዕልቃ ቤተ ክርስቲያን ተከራካሪ አድርገው ሾሙት። ❤ በዚያም ወራትም በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሁኖ ነበር። ይህ አባ ገብርኤልም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሒዶ በጾምና በጸሎት በሥግደትም በቀንና በሌሊት ሲጋደል ኖረ። ከቅዱሳን መነኰሳት ብዙዎች መልካም ራእይን አዩለት ከእርሷቸው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ልብስን እንደሚአለብሱት ብዙዎች ከአሕዛብ የተመለሱ ክርስቲያኖችም እንደሚያጅቡት ያየ አለ። ደግሞም ይሾምባት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ሲሔድ ያየለት አለ። ቁጥር የሌላቸውንም መክፈቻዎችን ሲቀበል ያዩ አሉ። ❤ ከገዳሙም ሊወርድ ብዙ ጊዜ ይሻ ነበር ነገር ግን አልተቻለውም። ከዚህ በኋላ አባ እንጦንስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ገዳም ትወርድ ዘንድ እኔ አልፈቅድም ጊዜው ሳይደርስ አትውረድ" አለው። ❤ ከሦስት ዓመት በኋላም አንዱ አረጋዊ የከበረ መልአክ እንግዲህስ አባ ገብርኤልን ወስደው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙታል እያለ እንደሚያነጋግረው ራእይ አየ። በዚያችም ቀን የሀገረ እንጣፊ መኰንን መጣ ከእርሱም ጋር ብዙዎች መሳፍንቶች ነበሩ። አባ ገብርኤልን አምጥተው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ የሚያዝዝ የንጉሥ ደብዳቤም ከእርሱ ጋር ነበረ። ❤ ከዚህም በኋላ ያለ ፈቃዱ ወስደው በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስናን ሾሙት። ቀን እርሱ ለኢየሩሳሌም አንድ ጳጳስና ሌሎችንም ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመ። ከዚህም በኋላ ሦስት ጊዜ ሜሮን አከበረ ባረከ እንደዚህም አድርጎ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኖረ። በዚያን ጊዜም አባ እንጦንስ ተገልጦ እንዲህ አለው "እነሆ ዕረፍትህ ቀርቦአል ከዐሥራ ስምንት ወሮች በኋላ ወደ እግዚአብሔር ትሔዳለህ የዘላለም ሕይወትንም ትወርሳለህ"። ❤ ከዚህም በኋላ በክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራ ሆነ። ይህም አባት ወገኖቹን ያድን ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ሕዝቡን ይቅር አለ። ❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ከመንበረ ሢመቱ ወጥቶ በምስር አገር ዓመት ሙሉ ተሠወረ። ከአንድ ምእመን በቀር ማንም አላወቀበትም በቀንና በሌሊት በገድል ከመቀጥቀጡ የተነሣም መልኩ ተለወጠ ሥጋውም ደረቀ። ❤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እርሱን ለሚፈራው ለአንድ ምእመን ሥራውን ገለጠ። እርሱም ከዚያ ቦታ አውጥቶ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አስቀመጠው በጸሎትና በቅዳሴ እያገለገለ ኖረ። ድኆችንም ይጐበኛቸው ነበር። የሚሹትንም ይሰጣቸው ነበር። ወደ ርሱ የሚመጡትንም ሕዝቦች ያስተምራቸውና ያጽናናቸው ነበር። ❤ በአንዲት ዕለትም ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስ በግልጽ ታየው እንዲህም አለው "ስለዚህ ፈጽሞ አትዘን ከዚህ ብዙ ድካምና መከራ እግዚአብሔር ያሳርፍሃልና አነሆ ምድራዊ ኑሮህን የሚፈጽም ደዌ በአንተ ላይ ይመጣል ነገር ግን ደስ ይበልህ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለሃልና። የዘላለም ሕይወትንና የማያልቅ ተድላ ደስታንም ትወርሳለህና" አለው። ❤ በዚያን ጊዜም በሚያስጨንቅ ደዌ ታሞ እየተጨነቀ ኖረ። ስለ ነፍሱም መውጣትና በእግዚአብሔር ፊት ስለ መቆሙ ይፈራና ይደነግጥ ነበር የእመቤታችን ማርያም ሥዕልም በዚያ ነበረ። ወደርሷም አዘውትሮ ይማልድ ነበረ በዚያን ጊዜም ክብር ይግባውና ራሱ እግዚአብሔር በብሩህ ገጽ "ተገለጠለት መንግሥተ ሰማያትን አግኝተሃልና ደስ ይበልህ እንጂ አትፍራ እስከ ሦስት ቀንም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ትወጣለህ" በማለት አረጋጋው። ይህንንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ በሦስተኛውም ቀን ሐምሌ 11 ቀን በሰላም አረፈ። በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ክብር ተቀበረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ገብርኤል በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 11 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለኢሳይያስ ቀሲስ። ወግኍሥ ባሕታዊ ዘደብረ መቃርስ። ከመ አአምኀከ ዘልፈ በመሥዋዕተ ስብሐት ሐዲስ። አጒይይ እከይየ መንፈስ ቅዱስ። እስመ ለኃጥእ ተብህለ መሥዋዕቱ ርኵስ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 11። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር። ወለራትዓን ይደልዎሙ ክቡር። ግነዩ ለእግዚአብሔር በመሰንቆ"። መዝ 32፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 2፥1-9፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-17፣ የሐዋ ሥራ 14፥20-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ6፥20-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን ለመርባስ ከሚባል አገር ሰዎች ለሆኑ ለቅዱሳን ዮሐንስና ለአባቱ ወንድም ልጅ ለስምዖን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ለሆነው ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ለአባ ገብርኤል ለዕረፍቱ በዓል በሰላሞ አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ በአስቄጥስ ገዳም ከነበረው ከቅዱስ አባት ኢሳይያስና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅዱሳን ዮሐንስና የአባቱ የወንድም ልጅ ስምዖን፦ የዚህም ቅዱስ ዮሐንስ እናቱ መካን ነበረች አባቱም ልጅን ይሰጠው ዘንድ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይለምነው ነበር ከዚህም በኋላ ልጁን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ሊአደርገው ተሳለ። ❤ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም እግዚአብሔር ልጅን እንደሚሰጠው በራእይ ተገልጦ ነገረው። ይህን ቅዱስም በወለደው ጊዜ ዮሐንስ ብሎ ጠራው በመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራ። ❤ ከዚህም በኋላ አድጎ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎች እረኛ አደረገው ምሳውንም ለእረኞችና ለመንገደኞች ሁል ጊዜ ይሰጥ ነበር እርሱ ግን እስከ ምሽት ይጾም ነበር። አባቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ስለዚህ ሊአረጋግጥ ወደ እርሱ ሔደ አባቱንም በአየው ጊዜ ዮሐንስ ፈርቶ ሊሸሽ ወደደ። አባቱም "የዛሬ ምሳህን አሳየኝ" አለው ብላቴናውም "ታይ ዘንድ ግባ" አለው ወደ መጠለያውም በገባ ጊዜ አገልግሉን ትኩስ እንጀራን ተመልቶ አገኘው እጅግም አደነቀ ከልጃቸው የሆነውንም ለሚስቱ ነገራት። ❤ ከዚያችም ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ጸጋ እንደ አደረችበት አወቁ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማር አደረጉት እንጂ በጎችን የሚጠብቅ እረኛ እንዲሆን አልተዉትም። ❤ ከዚህም በኋላ አባቱ ሊአጋባው ወደደ። እርሱ ግን ይህን አልወደደም። ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነውም ጊዜ ቅስና ተሾመ የአባቱ የወንድም ልጅ የሆነ ስምዖንም በጎቹን ትቶ መጥቶ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆነ። እርሱም ስለ ተአምራቱ የተናገረ ነው። እግዚአብሔር በእጆቹ ላይ ድንቆችንና ተአምራቶችን ገልጧልና። ደዌ ያለባቸውንም ሁሉ ያመጡአቸው ነበር እርሱም በዘይቱ ላይ ይጸልይና ይቀባቸው ነበር ወዲያውኑም ከደዌያቸው ይድኑ ነበር። እርሱም ወደርሱ የሚመጡትን ከኃጢአት ይርቁ ዘንድ ያስተምራቸው ነበር። ይመክራቸውና ይገሥጻቸውም ነበር። ከተአምራቱም አንዱ ይህ ነው በአንዲት መበለት የተሸከመችውን ገብስ ቀምቶ ለፈረሱ አበላት ያችም መበለት በዚህ ቅዱስ ዘንድ ከሰሰችው ቅዱስ ዮሐንስም ረገመው ያን ጊዜም ፈረሱ ሞተች። ❤ ዳግመኛም የንጉሥ የጭፍራ አለቃ ግብር ሊሰበስብ መጣ አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ አገልጋይም ነበረው። ከእርሱም ተባርኮ ወዲያውኑም የታወረች ዐይኑ ተገለጠች በእርስዋም ደኅና አድርጎ አየ። ይህም ቅዱስ የሰዎችን ሥራቸውን በግልጽ ያይ ነበር ስለ ኃጢአታቸውም ንስሓ ይገቡ ዘንድ ይገሥጻቸው ነበር። ❤ ዜናው በንጉሥ ማርያኖስ ዘንድ ተሰማ ለእርሱም አንዲት ሴት ልጅ ብቻ ነበረችው ወደ ሆድዋም ከይሲ ገብቶ ለሞት ተቃረበች ከዚህም በኋላ ያድኗት ዘንድ ገንዘቡን ለባለ መድኃኒቶች ሰጠ ነገር ግን አልተቻላቸውም። ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃው የባሪያውን ዐይን እንደ አዳነ የቅዱስ ዮሐንስ ዜና ነገረው ንጉሡም ጭፍራ ልኮ ወደርሱ ሊአስመጣው ወደደ ቅዱስ ዮሐንስም በመንፈስ ዐወቀ እርሱ ግን የመንገዱን ድካምና ባሕሩን ይፈራ ነበር ያን ጊዜም ደመና መጥታ ነጠቀችው ሰርመላስ ከሚባል አገርም ወደ አንጾኪያ ከተማ አደረሰችው። ንጉሡም ዐልጋ ላይ አቆመችው ንጉሡም ደነገጠ ቅዱስ ዮሐንስም "ወደዚህ ወዳንተ ልታስመጣኝ የተመኘኸው ምስኪን ሰው እኔ ነኝ" ብሎ ነገረው። "አሁንም ልጅህን አምጣት" አለው ልጁንም አመጣ። በላይዋም በጸለየ ጊዜ ከይሲው ሳያሳምማት ከሆድዋ ወጣ። ንጉሡም ከቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሁሉ ጋር ከእርሱ ተባረኩ። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ጸጋ የሚሰጥ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ። ❤ እጅ መንሻውንም ብዙ ገንዘብ አቀረበለት እርሱ ግን ምንም አልወሰደም። ንጉሡም በእርሱ ዘንድ ሊያኖረው ወደደ ቅዱሱ ግን አልወደደም ንጉሡም እንዳይሔድበት ቀሚሱን ያዘ ያንጊዜም ንጉሡ ቀሚሱን እንደያዘ ደመና ነጥቆ ወሰደው ቀሚሱም ተቆርጦ በንጉሥ እጅ ላይ ቀረ ቅዱስ ዮሐንስም በዚያች ሰዓት ወደ አገሩ ደረሰ። ❤ ንጉሡም ቤተ ክርስቲያ ሠርቶ የቀሚሱን ቊራጭ በውስጧ አኖረ ቤተ ክርስቲያኒቱም እስከ ዛሬ ድረስ የፊቃር ቤተ ክርስቲያን ተባለች። የቊርባን ቅዳሴ በሚቀደስ ጊዜም ሥጋውንና ደሙን መቀበል የሚገባቸውንና የማይገባቸውን ጻድቃንና ኃጥአንን ያያቸዋል። ❤ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ የጣዖትን አምልኮ በአቆ ጊዜ ለአባቱ ወንድም ልጅ ለስምዖንም ይህን አስረድቶት ወደ እስክንድርያ ከተማ ሔዱ በመኰንኑ ፊትም ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይም አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን ሐምሌ 11 ቀን በሰይፍ አስቈረጣቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ከሥጋቸውም ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ ለበሽተኞችም ታላቅ ፈውስ ተገኘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ዮሐንስና ስምዖን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ትድረስን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ገብርኤል፦ ይህም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባ ስምንተኛ ነው። የዚህም ቅዱስ ወላጆች እግዚአብሔር ሕግ የጸኑ ደጋጎች ፈቃዱንና ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ነበሩ። ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት። ❤ በአንዲት ዕለትም ቅዱሳን መነኰሳት ወደርሱ መጡ ከውስጣቸውም መልካም ገድል ያለው አንድ አረጋዊ ነበረ። እርሱም ብዙዎች ኤጲስቆጶሳት ሕፃኑን ከበው እጃቸውን እንደሚጭኑበት እንደሚባርኩትና ይሁን ይሁን ይገባዋል እንደሚሉ ራእይን አየ። ❤ ሽማግሌውም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ሕፃኑ ታላቅ እንደሚሆን አሰበ ለአባቱም "ይህን ሕፃን አስተምረው ለብዙዎች ሕዝቦች አለቃ ይሆን ዘንድ አለውና" አለው። አባቱም ሰምቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው "ከዚህ ሕፃን ምን ይደረግ ይሆን" አለ። ❤ ሕፃኑ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ አባቱ ዐረፈ። ብህና በሚባል አገርም በገድሉ የተደነቀ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ብሉያትንና ሐዲሳትንም የሚያውቅ የእናቱ ወንድም ስሙ ጴጥሮስ የሚባል ጴጲስቆጶስ ነበረ ሕፃኑንም ወስዶ አስተማረው ከተሰጠውም ጸጋና ዕውቀቱ የተነሣ ያዩት ሁሉ ያደንቁ ነበር ዲቁናም ተሾመ። ❤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሆነው ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ይህንም ኃላፊውን ዓለም ናቀ ኢጴጲስቆጶሱ አባ ጴጥሮስም በገድል ተጸምዶ ለሚኖር ለቀሲስ አባ ጴጥሮስ ሰጠው እርሱም በጥቂት ቀኖች የምንኵስናን ገድል አስተማረው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ታዩ። ❤ ከዚህም በኋላ መምህሩ ቀሲስ አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ከዚያ ተነሥቶ ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሔደ በዚያም በጾምና በጸሎት በስግደት በመትጋት እየተጋደለጨ ያለ ማቋረጥ ብዙ ዘመናት ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አባ መቃርስ ደብር ሔደ። ደብረ ማርስ ባለች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን አበምኔት አደረጉት። ሕንፃዋንም አደሰ።

photo content

photo content

photo content