ሰዋስው ☘☘☘☘
Открыть в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Больше1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
1 161
እርሷ እናታቸው እንደ ሆነች ነገረቻቸው አንገት ላንገት ተያይዘው አለቀሱና እርስ በርሳቸው ተሳሳሙ ወደ ኤዎስጣቴዎስም ሔደው ከእነርሱ የሆነውን ሁሉ ነገሩት። እርሱም እርሷ ሚስቱ እንደሆነች እነዚያም ልጆቹ እንደ ሆኑ አወቀ እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ ታላቅ ደስታም ደስ አላቸው ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
❤ ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ስለ አደረገው በጎ ነገር እያደነቁና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በአንድነት በአንድ ቦታ ኖሩ። ኤዎስጣቴዎስንም የሚወደው ንጉሥ በሞተ ጊዜ በእርሱ ፈንታ ጣዖት የሚያመልክ ሌላ ንጉሥ ነገሠ። ኤዎስጣቴዎስንም ጠርቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ወደርሱ አቅርቦ ለአማልክት ዕጣን አሳርጉ አላቸው። እሊህ ቅዱሳንም እንዲህ ብለው መለሱለት እኛ የረከሱ አማልክትን አናመልክም የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እናመልከዋለን እንጂ። በዚያንም ጊዜ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ጽኑ ሥቃይንም አሠቃዩአቸው እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት አስነሣቸው።
❤ ሁለተኛም በበሬ አምሳል በተሠራ ነሐስ ውስጥ እንዲጨምሩአቸው አዘዘና በዚያ ጨምረው እሳትን በላያቸው አነደዱ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ በሁለት ልጆቹና በሚስቱ ጸሎት ይማረን በረከታቸው እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የቀራጮች አለቃ የነበረ ቅዱስ አንጢላርዮስ፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ በማንም ላይ ርኅራኄ የሌለው ነበረ በአንዲትም ዕለት ድኆች በአንድ ቦታ እያሉ በአንጻራቸው አልፎ ሲሔድ በአዩት ጊዜ ስለርሱ እንዲህ አሉ። "ይህ ባለጸጋ በድኆች ላይ ምንም ምን ርኅራኄ የሌለው ነው" ከእነርሱም አንዱ "እኔ ሔጄ ከእርሱ ምጽዋት ተቀብዬ ብመጣ ምን ትሰጡኛላችሁ" አላቸው እነርሱም አንተ ከእርሱ ምጽዋትን ካገኘህ ያልከውን እንሰጥሃለን አሉት በዚህም ነገር ከተከራከሩ በኋላ ወደ አንጢላርዮስ ቤት ሒዶ ምጽዋትን ለመነው አንጢላርዮስም ከመሶቡ እግር የደረቀ ለከት ዳቦ አንሥቶ በመበሳጨት ወርውሮ የድኃውን ራስ ፈቃው ድኃውም ወደ ባልንጀሮቹ ተመልሶ ያንን ለከት አሳያቸው።
❤ በዚያቺም ሌሊት አንጢላርዮስ በሕልሙ ራእይን አየ እርሱ በፍርድ አደባባይ ቁሞ ሳለ የጠቆሩ ሰዎች ስለ ክፋቱ ብዛት ሲከራከሩት ብርሃን የለበሱ ሰዎች ደግሞ ከዚች ለከት ዳቦ በቀር በርሱ ዘንድ ያደረገውን ምጽዋት አላገኘንም ብለው ሲያዝኑ በሚዛንም በመዘኑዋት ጊዜ ከኃጢአቱ ሁሉ ተስተካከለች። በዚያንም ጊዜ ነቃ በልቡም "ሳልወድ የሠራሁት ይህን ያህል ጠቃሚ ከሆነ ወድጄ ብሠራውማ እጥፍ ድርብ የሆነ ዋጋ የማገኝ አይደለምን" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ገንዘቡን ጥሪቱን ሁሉ አውጥቶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ። ገንዘቡንም ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ቦታ ድኆች መጥተው ምጽዋትን ለመኑት እርሱም ገንዘቡን ሁሉ እንደ ጨረሰ ነገራችውና እጅግ አዘኑ እንዳዘኑም አይቶ እንዲሸጡት ፈቀደላቸው እነርሱም ሸጡትና የሽያጩን ገንዘብ ተከፋፈሉ። በተሸጠበትም እንደባሪያ እያገለገለ ኖረ የጌታው ባሮችም በሚያሳዝኑት ጊዜ ብርሃናዊ ሰው ተገልጦ "አትዘን የተሸጥክበትን ዋጋ እኔ ተቀብዬዋለሁ እነሆ በእጄ ውስጥ አለና" ይለዋል።
❤ ከዚህም በኋላ አስቀድሞ ከነበረበት የመጡ ሰዎች ሥራውን በገለጡበት ጊዜ በሥውር ሸሽቶ ወደ ከተማው በር ደረሰ በሩን የሚጠብቀውም ዲዳና ደንቆሮ ነበር። አንጢላርዮስም "በሩን ክፈትልኝ" በአለው ጊዜ ከአፉ በእሳት አምሳል ወጥቶ በረኛውን ነካው ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈታ ጆሮዎቹም ሰሙ በሩንም ከፍቶለት ወደ በረሀ ሔደ በዚያም ገድሉን ፈጽሞ መስከረም 27 ቀን ዐረፈ።
❤ ሰዎችም በአጡት ጊዜ ወደ በሩ መጡ በረኛውም የሆነውን ሁሉ ነገራቸው ከቅድስናውና ከተአምራቱም የተነሣ እጅግ አደነቁ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አንጢላርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 27 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለአንጢላርዮስ ጳኵሲማ ኅብስቱ። ዘይበሌዕ ለሲሲቱ። መድኃኒተ ነፍሱ ኮነቶ ወበቋዒተ ሎቱ። ያብአኒ ቤተ ፃማሁ እንተ ድኅነ ቦቱ። በአንጎግዎ ዘስኂት ኢይጥፋእ በከንቱ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 27።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አኅለፍከነ ማእከለ እሳት ወማይ። ወአውጻእከነ ውስተ ዕረፍት። እበውእ ቤተከ ምስለ መባእየ"። መዝ65፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 27፥1-26።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወረከብናሁ ውስተ ኦመ ገዳም። ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር። ወንሰግድ ውስተ መካን በኃ ቆመ እግረ እግዚእነ"። መዝ 131፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥8-26፣ ያዕ 2፥5-14 እና የሐዋ ሥራ 17፥1-10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 19፥16-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን አስቀድሞ በማንም ላይ ርኅራኄ የሌለው (ንፉግ) ለነበረ፤ በሕልሙ እግዚአብሔር በሳየው ራእይ ተመልሶ ስለ ምጽዋት ሲል ያለው ንብረት በሙሉ ከሰጠ በኋላ እራሱ ለሸጠ ለቀራጭች አለቃ ለነበረ ለቅዱስ አንጢላርዮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት አምና ለተጠመቀች ያለ ደም መፍሰሰ ሰማዕት ለሆነች ለቅድስት ጤቅላ (ቴክላ) ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ ለቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ለሁለት ልጆቹና ለሚስቱም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከመድኃኒታችን ከስቅለቱ (ከመድኃኔዓለም) ከወራዊ ከመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለጤቅላ (ቴክላ) ዘሞአቶ ለተኵላ በገድል ንጽሕት ድንግል"። ትርጉም፦ ንጽሕት ድንግል በገድል ተኵላውን ያሸነፈችው ለኾነች ለጤቅላ (ቴክላ) ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ሐዋርያዊት ቅድስት ጤቅላ፦ የዚች ቅድስት ወላጆቿ ከመቄዶንያ ሰዎች ውስጥ ባለጸጎች ናቸው እርሷንም እንደ ሀገራቸው ባህል በተግሣጽ በምክር አሳደጓት እነርሱ ጣዖትን የሚያመልኩ ናቸውና።
❤ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም ወደዚች አገር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲህ እያለ ሊአስተምር ጀመረ "ዐውቀው ድኆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት ለነርሱ ናትና። ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው እነርሱ ደስ ይላቸዋልና።
ስለ ዕውነት የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ ናትና። ሚስት እያላቸው እንደ ሌላቸው የሚሆኑ ብፁዓን ናቸው። እነርሱ የዘላለም ሕይወትን ይወርሳሉና"። ይህንንና ይህን የመሰለውን በሰማች ጊዜ ቅድስት ጤቅላ ከቤቷ ደርብ ሳትወርድ ያለ መብልና መጠጥ ሦስት ቀን ኖረች። እናቷም "ከቤትሽ ደርብ የማትወርጂ ለምንድን ነው እህልስ ለምን አትበዪም" አለቻት።
❤ ከዚህም በኋላ በጭልታ ወረደች ለሚጠብቃትም ዘበኛ እንዳይናገርባት የወርቅ ወለባዋን ዋጋ ሰጠችውና ወደ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሔደች። እርሱም በደስታ ተቀብሎ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት።
❤ በማግሥቱም እናቷ እየፈለገቻት በመጣች ጊዜ ከቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ አብራ ተቀምጣ አገኘቻት ከዚያም ወደ መኰንን ሒዳ ልጇን ክርስቲያን እንደሆነች ከሰሰቻት። መኰንኑም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋራ እንዲያመጧት አዘዘ አስቀድመው ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው። መኰንኑም የቅድስት ጤቅላን ቅጣት እንዲያዩ የሀገር ልጆችን ሰበሰበ ከዚህም በኋላ ወደ እሳት እንዲወረውሩዋት አዘዘ። በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ማዕተብ ራሷን አማትባ ራስዋን በራስዋ ወደ እሳት ወረወረች ማንም ያያት ሳይኖር ከእሳት ውስጥ ወጥታ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሔደች የራስዋን ጠጒር ቆርጣ ወገቧንም ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው።
❤ መኰንኑም ደኅንነቷን በሰማ ጊዜ ያዛት ሃይማኖቷንም እንድትተው አስገደዳት አይሆንም ባለችውም ጊዜ አንበሶችና ድብ ከሚያድሩበት እንዲጨምሩዋት አዘዘ። እነርሱም ሰገዱላትና የእግሮቿን ትቢያ ላሱ። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው መኰንኑና ወገኖቹ አመኑ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠመቁ በክርስቶስም መንጋዎች ውስጥ ሆኑ።
❤ እርሷ ቅድስት ጤቅላም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በማስተማር ቅዱስ ጳውሎስን እያገለገለችው ኑራ መስከረም 27 ቀን በሰላም ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስ ጤቅላ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ትሩር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሁለቱ ልጆቹና ሚስቱም፦ ይህ ቅዱስም ለሮም መንግሥት የጭፍራ አለቆች ከሆኑት ውስጥ ነው የቀድሞ ስሙ ቂዶስ ነው እግዚአብሔርንም አያውቅም ነበር ግን ብዙ ምጽዋትን በመስጠት ለድኆችና ለችግረኞች ይራራል ስለዚህም ክብር ይግባውና ጌታችን ድካሙ ከንቱ ሁኖ እንዲቀር አልወደደም።
❤ በአንዲት ቀንም አውሬ ሊያድን ኤዎስጣቴዎስ ወደ ዱር ወጣ እርሱ አዳኝ ነውና ዋልያም አግኝቶ በቀስት ሊነድፈው ወደደ ያን ጊዜም በዋልያው በቀንዶቹ መካከል በመስቀል አምሳል ጌታ ተገለጸለት። የመስቀሉም ብርሃን እስከ ደመና ደርሶ ነበር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያ ብርሃን ውስጥ ተናገረው ስሙንም አስረዳው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ወደ ኤጲስቆጶስ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን እንዲጠመቁ አዘዘው።
❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ በኋላ ችግርና ፈተና እንደሚመጣበት በመጨረሻም ስለ ከበረ ስሙ ምስክር ሁኖ ደሙን አፍስሶ እንደሚሞት አስረዳው። ኤዎስጣቴዎስም ሰምቶ ከተራራው ወርዶ ወደ ቤቱ ሔደ። ጌታችን ያዘዘውንም ለሚስቱ ነገራት ከዚህም በኋላ ወደ ኤጲስቆጶሱ ሔደው ከልጆቻቸው ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ የቀድሞ ስሙንም ለውጦ ኤዎስጣቴዎስ ተባለ።
❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላ በዚያች አገር ታላቅ ችግር መጣ የኤዎስጣቴዎስም ገንዘቡ ሁሉ አልቆ ወንዶችና ሴቶች ባሮቹ ተበተኑ ወደሌላ አገርም ሊሰደድ ወዶ ልጆቹንና ሚስቱን ይዞ በመርከብ ተጫነ። ወደ ወደቡም በደረሱ ጊዜ መርከበኞች የመርከብ ዋጋ ከእርሱ ፈለጉ የሚሰጣቸው የመርከብ ዋጋ ባላገኘ ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ የመርከቡ ሹም ሚስቱን ወሰዳት የአታክልት ጠባቂም አደረጋት። ከዚያም ኤዎስጣቴዎስ እያዘነና እያለቀሰ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ሔደ ውኃ ወደ መላበትም ወንዝ ደረሰ አንዱንም ልጁን ከእርሱ ጋር ሊአሻግረው ይዞት ገባ አሻግሮትም ከወንዙ ዳር አኖረውና ሁለተኛውን ልጁን ሊአሻግረው ተመለሰ ግን አላገኘውም። ተኵላ ወስዶታልና ያሻገረውንም አንበሳ ነጥቆ ወሰደው ኤዎስጣቴዎስም ከሚስቱና ከልጆቹ ስለ መለየቱ ታላቅ ኀዘንን አዝኖ መሪር ልቅሶን አለቀሰ ምክሩ ታላቅ የሆነ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ግን ሁሉንም በየአሉበት ያለ ጥፋት ጠበቃቸው።
❤ ከዚህ በኋላም ኤዎስጣቴዎስ ወደ አንዲት አገር ሒዶ በዚያ የአትክልት ጠባቂ ሁኖ ብዙ ቀኖችን ኖረ። ከእነዚያ ቀኖችም በኋላ የሮም ንጉሥ ሙቶ በርሱ ፈንታ ለኤዎስጣቴዎስ ወዳጁ የሆነ ሰው ነገሠ ኤዎስጣቴዎስንም ፈለገው ግን አላገኘውም ኤዎስጣቴዎስንም ይፈልጉት ዘንድ ወደ ሀገሩ ሁሉ መልእክተኞችን ላከ። ከመልእክተኞችም አንዱ ኤዎስጣቴዎስ ወዳለበት ደርሶ በአታክልቶች ዘንድ አግኝቶት አወቀው እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሡ ወሰደው ንጉሡም በበጎ አቀባበል ተቀብሎ የጭፍራ አለቃ አድርጎ ሾመው።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ከሚገዛቸው አገሮች ሁሉ ወጣቶችን ሰብስቦ የጦር ሠራዊት ጭፍራ ያዘጋጅ ዘንድ ኤዎስጣቴዎስን አዘዘው እነዚያ ተኵላና አንበሳ የወሰዳቸው የኤዎስጣቴዎስ ሁለት ልጆቹ በአንዲት አገር አድገዋል። ግን እርስበርሳቸው አይተዋወቁም ወጣቶችንም የሚመለምሉ መልምለው ወደ አባታቸው ኤዎስጣቴዎስ አቀረቧቸው እርሱም ሳያውቃቸው የመዛግብት ቤት ጠባቂዎች አደረጋቸው።
❤ እናታቸውንም አረማዊ የሆነ የመርከቡ ሹም በወሰዳት ጊዜ የአታክልቶች ጠባቂ አደረጋት። እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ በንጽሕና ጠብቋታልና እነዚያ ሁለቱ ልጆቿ እርሷ ወዳለችበት የአታክልት ቦታ ደረሱ እነርሱም የልጅነታቸውን ነገር ይነጋገሩ ነበር። እርሷም ሰምታ ልጆቿ እንደሆኑ አውቃ ያን ጊዜ ጠራቻቸውና
1 161
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስርአተ ማህሌት ዘቀዳማይ ጽጌ በዓለ እግዚእነ ወአርሴማ ቅድስት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCWW
✨መልክዓ ስላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCWW
🌱ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ትወጽሕ በትር እምሥርወ ዕሤይ፤ ወየዓርግ ጽጌ ይዕቲ በትር አምሳለ ማርያም፤ቅድስት ይዕቲ፤ ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ፤ አምሳሉ ለወልድ ኀደረ ላዕሌሃ፤ ቃል ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ
@EOTCWW
✨🔸ዚቅ(ሌላ)
ወየዓርግ ጽጌ እምጒንዱ፤ወየዓርፍ መንፈስ ቅዱስ መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌሁ፤መንፈሰ ጥበብ መንፈሰ አዕምሮ፤ይቀንት ጽድቀ ውስተ ሐቔሁ፤ወይትአጸፍ ርትዓ ውስተ ገቦሁ፤ብርሃን ለቅዱሳን
@EOTCWW
✨ማኅሌተ ጽጌ፦
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምዓጽሙ፤ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ ጣዕሙ፤ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡
@EOTCWW
@EOTCWW
❣❣ወረብ
መዓዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ ሶበ ሶበ ሐወዘኒ/፪/
ወበእንተዝ ማርያም አኅሊ ለተዓምርኪ/፪/
@EOTCWW
🌱ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ ወመንክር ስብሐቲከ፤ለዕረፍት ሰንበት ሠራዕከ፤
@EOTCWW
@EOTCWW
✨ማሕሌተ ፅጌ
ከመ ይትፌሳሕ መርዓዊ ውስተ ገነቱ ዘወረደ፤ ጽጌያተ ይርአይ በጊዜ ፈቀደ፤በተአምርኪ ድንግል እትፌሣሕ ፈድፋደ፤ዘያቀልል እምኃጥአን ፆረ ኃዘን ክቡደ፤እስመ እምኔኪ ፍስሐ ተወልደ
@EOTCWW
❣❣ወረብ፦
ዘያቀልል እምኃጥአን ፆረ ኃዘን/፪/
እስመ እምኔኪ"ፍስሐ ተወልደ"/፫/ እምኔኪ /፪/
@EOTCWW
🌱ዚቅ፦
ከመ ፍስሖ ቀይሕ ከናፍርኪ ቡርክት አንቲ እምአንስት መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፤እሞሙ ይዕቲ ለሰማዕት፤ወእኅቶሙ ለመላእክት መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፤ ወተወልደ ፍስሐ እምኔኪ
@EOTCWW
@EOTCWW
✨ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCWW
@EOTCWW
❣❣ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ /፪/
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/
@EOTCWW
@EOTCWW
🌱ዚቅ፦
በሰላም ንዒ ማርያም፤
ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም፤ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም፤ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም
ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም፤ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም፤ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።
@EOTCWW
@EOTCWW
✨ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCWW
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
@EOTCWW
@EOTCWW
🌱ዚቅ
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ :ጌራ ባሕሪይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል በብስራትክሙ መሐይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀሰመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው
@EOTCWW
✨ሰቆቃወ ድንግል
አይቴ ሀሎ ንጉሰ እስራኤል ዘተወልደ፤ከመ ነሀብ ሎቱ አምኃ ወሰጊደ፤እንዘ ይብሉ ሰብአ ሰገል ሰሚዖ ገሃደ፤ሄሮድስ አሜሃ በእሳተ ቅንአት ነደ፤ከመ ይቅትሉ ሕፃናተ ወኢያትረፉ አሐደ፤ እስከ ቤተልሄም ወገሊላ ሐራሁ አዖደ
@EOTCWW
❣❣ወረብ፦
አይቴ ሀሎ ንጉሰ እስራኤል ዘተወልደ ንጉሰ እስራኤል/፪/
እንዘ ይብሉ ሰብአ ሰገል ሰሚዖ ገሃደ አሜሃ ሄሮድስ በእሳተ ቅንአት ነደ/፪/
@EOTCWW
🌱ዚቅ፦
እም ብሔረ ጽባሕ አምጽኡ ወርቀ ወጋዳ፤ ለንጉሥነ ለወልደ ማርያም፤ኮከብ ኮነ ሐዋርያ ወዜነዎሙ ፍስሐ
@EOTCWW
🌱ዚቅ(ሌላ)፦
ቀቲለ ሕፃናት ንጉሠ ገሊላ አመ ኀሠሠ በዘባነ እሙ ኅዙለ ተግኅሠ ዮሴፍ አረጋዊ እንዘ የዓቅብ መቅደሰ ሐራ ሄሮድስ አላዊ ተለውዎ ርእሰ
@EOTCWW
🔺🔻መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ትወጽሕ በትር እምሥርወ ዕሤይ፤ ወየዓርግ ጽጌ ይዕቲ በትር አምሳለ ማርያም፤ቅድስት ይዕቲ፤ ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ፤ አምሳሉ ለወልድ ኀደረ ላዕሌሃ፤ ቃል ሥጋ ኮነ ወተወልደ እምኔሃ
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
1 161
✝ቤተሰቦቻችን ፅጌ ፆም የፍቃድ ፆም ቢሆንም በብዙ ያረሰ በብዙ ያጭዳል እና #ስለሀገራችን
ስለቤተክርስቲያናችን
#ስለሰላም
እያሰብን እንድንፆም በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።መልካም በዓል።
1 161
✝ቤተሰቦቻችን ፅጌ ፆም የፍቃድ ፆም ቢሆንም በብዙ ያረሰ በብዙ ያጭዳል እና #ስለሀገራችን
ስለቤተክርስቲያናችን
#ስለሰላም
እያሰብን እንድንፆም በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።መልካም በዓል።
1 161
ወርኀ ጽጌ ምስጢረ ጽጌ ...የአበባ ወር የአበባ ምስጢር
ኹላችንም እንደምናውቀው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኀዳር ፮ ድረስ ያለው ወቅት በአንድ በኩል አበቦች ጌጠኛ ሸማ ሆነውላት በልብስነታቸው ምድር የምትደምቅበት ጊዜ በመሆኑ በሌላ በኩል ድንግል ማርያም ፲፰ ዓመት እንኳ በቅጡ ባልደፈነው የአበባነት እድሜዋ ከሄሮድስ ጥፋት ለመሸሽ ልጇን አዝላ ተሸክማ፣ ወደ ግብጽ የተሰደደችበት በረሃ ለበረሃ የተንከራተተችበት ‹‹በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል›› ያሰኘ ወደር የሌለው ጽዋትወ መከራን በልጇ የተነሳ የተቀበለችበት ወቅት በመሆኑ ወርኀ ጽጌ (የአበባ ወቅት) በመባል ይታወቃል፡፡
ክርስቲያኖች ነገረ ስደቷን በመዘከር ማኀሌተ ጽጌን በመቆም በመጾም በመፀለይ የበረከት ፍሬ ለቃሚ በዚያን ጊዜ የሆነውን ስቃይ ኀሳር ለልጇና ለወዳጇ ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳስባ ምሕረት እንድታሰጣቸው በመለመን የምልጃዋ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ወቅት ከዚህ በተጨማሪ በወርኀ ጽጌ ጊዜያቸውን የጠበቁ እንዲሁም ሰፊና ጥልቅ መንፈሳዊ ምስጢርን ያዘሉ ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ ጊዜው የልም ላሜና የአበባ ወቅት እንደመሆኑ ስለ አበባና ስለ መንፈሳዊ ምስጢሩ ይነገራል፡፡
kiya...
