ሰዋስው ☘☘☘☘
Открыть в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Больше1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
1 161
ታኦግንስጣም ወስዳ በብብቷ ታቅፋ በመስቀል ምልክት አማተበችበት በዚያንም ጊዜ ዳነ ከእርሷም ስለ ተደረገው ተአምር የዚች የከበረች ድንግል ታኦግንስጣ ዜናዋ በሀገሩ ሁሉ ተሰማ ከዚያችም ቀን ወዲህ በእነርሱ ዘንድ እንደ እመቤት እንጂ እንደ አገልጋይ አልሆነችም።
❤ ከዚህም በኋላ የህንድ ንጉሥ ወደ ጦርነት በሔደ ጊዜ ጉም ጭጋግ ዐውሎ ነፋስና ጨለማ በላዩ መጣ ንጉሡ ግን የከበረች ታኦግንስጣ ስታማትብ ስለአየ በመስቀል ምልክት ማማተብን ያውቅ ነበርና ያን ጊዜ በጭጋጉ በጉሙ በጨለማውና በጥቅሉ ነፋስ ላይ በመስቀል ምልክት አማተበ። ወዲያውኑ ፀሐይ ወጣ ታላቅ ጸጥታም ሆነ ጠላቶቹንም በዚሁ የመስቀል ምልክት ድል አደረጋቸው እጅግም ደስ አለው።
❤ ንጉሡም ከጦርነት በተመለሰ ጊዜ ለከበረች ታኦግንስጣ። ከእግርዋ በታች ሰገደ እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉ የሀገሩንም ሰዎች የከበረች የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ ለመናት ቅድስት ታኦግንስጣም እንዲህ አለችው "ይህን አደርግ ዘንድ ለእኔ አይገባኝም የሚያጠምቃችሁን ካህን ይልክላችሁ ዘንድ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ ላኩ"። ያን ጊዜም ከወገኖቹ ጋር የሚያጠምቀውን ካህን እንዲልክለት የህንድ ንጉሥ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ መልእክተኞችን ላከ ንጉሥ አኖሬዎስም ልመናውን ተቀብሎ የሚያጠምቃቸውን ቄስ ላከ ቄሱም አጠመቃቸው መሥዋዕትንም ቀድሶ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው እግዚአብሔርንም የምትወድ የከበረች ድንግል ታኦግንስጣ እጅግ ደስ አላት ያንንም ቄስ መንፈሳዊ ሰላምታ ሰጠችውና ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለች እርሱም ከእርሷ በረከትን ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ ለራስዋ ገዳም ሠራች ብዙዎች ደናግልም ተሰበሰቡ የምንኩስና ልብስንም በመልበስ እንደርሷ መሆንን ወደዱ እርሷም እመ ምኔት ሆነች። ያም ባሕታዊ ቄስ የክርስትና ጥምቀትን ከአጠመቃቸው በኋላ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ ተመልሶ የህንድን ሰዎች እንዳጠመቃቸውና ክብር ይግባውና ወደ ክርስቶስ ሃይማኖት እንደገቡ ነገረው። ንጉሥ አኖሬዎስም እጅግ ደስ አለው የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳትንም ይህን ባሕታዊ ኤጲስቆጶስ አድርጎ እንዲሾምላቸው አዘዘው እርሱም ኤጲስቆጶስነት ሹሞ ከህንድ ሰዎች ላከላቸው እጅግም ደስ አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩ ጀመሩ ምሰሶዎችንም በፈለጉ ጊዜ አላገኙም በዚያም አከባቢ ታላቅ የጣዖት ቤት ነበረ በውስጡም ያማሩ ምሰሶዎች አሉ። ድንግሊቱ ታኦግንስጣም ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብዙ በማልቀስ ለመነች ያን ጊዜም እሊያ ምሰሶዎች ከጣዖት ቤት ፈልሰው ሐናፂዎች ከሚሹት ቦታ በቤተ ክርስቲያን መካከል ተተከሉ አማንያን ሁሉ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት ጣዖትን ሲያመልኩ የነበሩም ጣዖቶቻቸውን ሰብረው ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ተመልሰው ገቡ በዚያችም አገር ታላቅ ደስታ ሆነ።
❤ ቅድስት ድንግል ታኦግንስጣም ተጋድሎዋን ከፈጸመች በኋላ እግዚአብሔርንም አገልግላ ደስ አሰኝታ በዚያ ገዳም በደናግሉ መካከል በሰላም በፍቅር ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ታኦግስጣ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ አባት አባ ዲዮናስዮስ፦ ይህም አባት የእስክንድርያ ዐሥራ አራተኛ ሊቀ ጳጳሳት ነው። ይህንንም ቅዱስ ንጉሥ ዳኬዎስ ሊገድለው ፈልጎት ነበር ግን እግዚአብሔር ሠወረው ይህም አባት ብልህ አዋቂ ስለነበረ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ተረጎመ።
❤ በዘመኑም በሮም ንጉሥ በከሀዲ ዳኬዎስ እጅ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሰማዕትነት ዐረፈ። ሁለተኛም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው ነቁ እሊህም ለጣዖታት ሊአሰግዳቸው በፈለጋቸው ጊዜ ከዳኬዎስ ፊት የሸሹ ከኤፌሶን አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን የሆኑ ናቸው።
❤ ዳግመኛም በዘመኑ የመነኰሳት አለቃ ገዳማትን የሠራ ግብጻዊው ታላቁ እንጦንዮስ ለመጀመሪያ ጊዜ መነኰስን ሆነ። ይህም ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሊቀ ጵጵስናው ሹመት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ። መንጋዎቹንም በትክክል በፍቅር አንድነት ጠበቃቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዲዮናስዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም። ምንጭ፦ የመስከረም 17 ስንክሳር።
+ + +
❤መልካም የመስቀል በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት ለከበረ ለመስቀሉ በዓል (ቁፍሮ ለተጀመረበት)፣ ለከበረች ለሮማዊት ለቅድስት ታኦግስጣ ለዕረፍቷ በዓልና ለእስክንድር ዐሥራ አራተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት ለአባ ዲዮናስዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ሊቢባ፣ ከኪርያኖስ፣ ከዮስጢና፣ ከቴክሴልጥስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ ምልጣን ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሞገሰ መስቀሉ የኀሉ ምስሌነ ለኢየሱስ ክርስቶስ እስመ ውእቱ ሰላምክሙ ዘረሰዮሙ አሐዱ ለክልዔሆሙ ወነሰተ አረፍተ ማእከል እንተ ጽልእ"። ትርጉም፦ ቅድመ ዓለም የነበረ ዛሬም ያለ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የጌታችን የመስቀሉ ሞገስ ከሁላችን ጋር ይኑር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላማችሁ ነውና፤ ሁለታቸውን አንድ ያደረገ የጸብን ግድግዳ አፈረሰ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ "መስቀል ጒድበ ሙስና ዲበ ሰይጣን ወሰይፈ ሙቃየ አርእስቲሆሙ ለአጋንንት፤ መስቀል ረምኃ እሳት ዘይረግዞሙ ለመናፍስት ርኵሳን፤ ወሐፀ መብረቅ ዘይደጒፆሙ ለሠራዊተ መስቴማ። መስቀል ፀወን ዘኢይክል በጺሐ ኀቤሁ ዘኢነሥአ ማኅተመ ሥላሴ። መስቀል ወልታ ጽድቅ ዘእምየማን ወእም ጸጋም። መስቀል ንዋየ ሐቅል ለፀብዕ በከመ ይቤ ጳውሎስ ሐዋርያ እስመ ቀትልክሙ ኢኮነ ምስለ ዘሥጋ ወደም። መስቀል ጽርዐ ሃይማኖት ዘኢይክል ሰጢጦቶ ሥጽረተ ሐፀ ወኢደርብዮቶ ኵያንው ወአርማኅ። መስቀል ዘገብረ በአምሳሊሁ ለእደ ሙሴ በገዳም ራፊድ በእንተ ፀብዐ አማሌቅ። መስቀል ዘአጥዐሞ ለማይ መሪር በገዳም ሱር ሶበ ተወድየ ውስቴቱ በእደ ሙሴ። መስቀል ማኅተመ ቅድስና ወንጽሕ። መስቀል አክሊለ መዊዕ ዘመስተጋድላን ወሠርጎ ትርሲት ለእለ ተዓሥሩ ውስተ መርዐ በግዑ። መስቀል ነቅዕ ዘኢይነጽፍ ወአዘቅተ ክብር ዘምሉዕ ረባሐ"።ትርጉም፦ መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው፤ የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው፤ መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው፤ የአመስቴማውያንንም (የጠላት፣ የከሳሽ፣ የጠበኛ) ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው። መስቀል ማኅተመ ሥላሴ (የሥላሴ ልጅነት) የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራ ከቀኝም ለሚመጣ (ጠላት) የጽድቅ ጋሻ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ "ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም" እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው። መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፤ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመውጋት በራፊድ በረሐ በዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው። መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው። መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፤ በቁዔትም (ጥቅምም) የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በውዳሴ መስቀል ላይ1፥3።
+ + +
❤ መስከረም ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ለከበረ መስቀል በዓሉ ነው። ይህም የጻድቁ ንጉሥ የቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ከተሠወረበት የገለጠችው ነው።
❤ የጎልጎታን ኮረብታ በአስጠረገች ጊዜ የከበረ መስቀልን አገኘችው ታላቅ ኮረብታም የሆነበት ምክንያት እንዲህ ነው። ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብሩና ከመስቀሉ የሚገለጡ ሁነው ሙታን ይነሡ ነበርና የጎበጡና በሽተኞች ሁሉ ይፈወሱ ነበር።
❤ ስለዚህም አይሁድ ተቆጡ እንዲህም ሥርዓትን ሠርተው አዘዙ በይሁዳ አገር ሁሉና በኢየሩሳሌም ቤቱን የሚጠርግ ሁሉ ወይም አፈር ወይም ጉድፍ የሚጠርግ በናዝሬቱ ኢየሱስ መቃብር ላይ ይጥል ዘንድ እንዲህም እያደረጉ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣች ድረስ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ ኖሩ። እርሷም በመጣች ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብርን እስከ አሳዩዋት ድረስ አይሁድን ይዛ አሠቃየቻቸው ያንን ኮረብታም እስከ ጠረጉ ድረስ አስገደደቻቸው የከበረ መስቀሉም ከተቀበረበት ተገልጦ ወጣ።
❤ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራች በዚች ቀንም አከበሩዋት ለመስቀሉም በዓልን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን አከበሩለት። የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ከሀገሮቻቸው በመምጣት ክብር ይግባውና ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤውን በዓል እንደሚያከብሩ ለመስቀልም ታላቅ በዓልን የሚያክብሩ ሆኑ።
❤ ክርስቲያኖችም በጎዳና እየተጓዙ ሳሉ ስሙ ይስሐቅ የሚባል አንድ ሳምራዊ ሰው ከእርሳቸው ጋር ነበር ከእርሱም ጋር ብዙዎች ሳምራውያን ነበሩ ይህ ይስሐቅም የክርስቲያን ወገኖችን "ለምን በከንቱ ትደክማላችሁ ለዕንጨትስ ልትሰግዱ እንዴት ትሔዳላችሁ" እያለ ይሣለቅባቸው ነበር። ከክርስቲያን ወገኖችም ስሙ አውዶኪስ የሚባል አንድ ቄስ አለ ሕዝቡም በጎዳና ሲጓዙ የሚጠጡት ውኃ አላገኙም ነበርና ተጠሙ።
❤ ወደ አንድ ጉድጓድም ሔዱ በውስጡም መሪር የሆነና የገማ ውኃ አገኙ እጅግም በውኃ ጥማት ተሠቃዩ። ይስሐቅም እጅግ ይሣለቅባቸው ጀመረ "የቀናች ሃይማኖት ካለቻችሁ ይህ የገማና የመረረ ውኃ ተለውጦ እስቲ ጣፋጭ ይሁን ይላቸው ነበር"። ቀሲስ አውዶኪስም በሰማ ጊዜ መንፈሳዊ ቅናትን ቀንቶ ከዚያ ሳምራዊ ይስሐቅ ጋር ተከራከረ ያ ሳምራዊም "በመስቀል ስም የተአምራት ኃይልን ከአየሁ እኔ በክርስቶስ አምናለሁ" አለ። ያን ጊዜም ቀሲስ አውዶኪስ በዚያ በገማ ውኃ ላይ ጸለየ ውኃውም ወዲያውኑ ጣፋጭ ሆነ ከእርሱም ሕዝቡ ሁሉ እንስሶቻቸውም ጠጡ።
❤ ሳምራዊ ይስሐቅ ግን በተጠማ ጊዜ በረዋት ከያዘው ውኃ ሊጠጣ ፈለገ ግን ገምቶ ተልቶ አገኘውና መሪር ለቅሶን አለቀሰ። ወደ ከበረ ቄስ አውዶኪስም መጥቶ ከእግሩ በታች ሰገደ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመነ በከበረ ቄስ በአውዶኪስ ጸሎት ጣፋጭ ከሆነው ከዚያ ውኃም ጠጣ። በዚያም ውኃ ውስጥ ታላቅ ኃይል የሚሠራ ሆነ እርሱ ለአማንያን የሚጣፍጥ ሲሆን ለከሀዲያንና ለአረማውያን የሚመር ሆነ በውስጡም የብርሃን መስቀል ታየ በአጠገቡም ውብ የሆነች ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩ።
❤ ሳምራዊ ይስሐቅም ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ በደረሰ ጊዜ ወደ ኤጴስቆጶሱ ሒዶ ከቤተሰቡ ጋር የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። የከበረ መስቀልም ዳግመኛ የተገለጠበት መጋቢት ዐሥር ቀን ነው ዜናውንም በዚሁ ቀን ጽፈናል።
❤ ምእመናንም በታላቁ ጾም መካከል በዓሉን ማክበር ስለአልተቻላቸው በዓሉን ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት ቀን አደረጉ ይህም መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ነው በዚህም ቀን አስቀድሞ ከከበረ መቃብር በንግሥት ዕሌኒ እጅ የተገለጠበት ነው። በመስቀሉ ላዳነን ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ክብር ምስጋና ገንዘቡ ነውና ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሮማዊቷ ቅድስት ታኦግንስጣ፦ ይቺም ቅድስት በደጋጎች ነገሥታት በአኖሬዎስና በአርቃዴዎስ ዘመን የነበረች ናት። በዚያም ወራት የህንድ ንጉሥ መልእክተኞች እጅ መንሻ ይዘው ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ መጡ በሚመለሱም ጊዜ ይችን ድንግል ታኦግንስጣን አገኟት የምታነበውም መጽሐፍ በእጅዋ ውስጥ ነበር ወደ አገራቸውም ነጥቀው ወሰዷት ለህንድ ንጉሥም ሚስቶቹንና ቤተሰቦቹን የምትጠብቅ ሆነች።
❤ በአንዲት ዕለትም የንጉሡ ልጅ አስጨናቂ በሆነ ደዌ ታመመ የከበረች
1 161
ደርሷ ሲገቡ ሁሉንም ስለገደላቸው ስለዚህ የአባቷ አገልጋዮች ያሽሟጥጧት ነበርና ከሽሙጣቸው ያድናት ዘንድ እያለቀሰች ወደ እግዚአብሔር ትለምን ነበር ጸሎቷና የጦቢት ጸሎትም በልዑል እግዚአብሔር በጌትነቱ ልዕልና ፊት ተሰማ።
❤ ጦቢትም በገባኤል ዘንድ አደራ ያስጠበቀውን የብሩን ነገር አሰበ ልጁ ጦብያንም ጠርቶ "ሳልሞት በገባኤል ዘንድ አደራ ያስጠበቅሁትን ብር ትቀበል ዘንድ ከአንተ ጋራ የሚሔድ በደመወዝ የሚቀጠር አሽከር ፈልግ" አለው።
❤ ጦብያም "አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለ ከዚህም በኋላ አሽከር ሊፈልግ ሔደ ቅዱስ ሩፋኤልንም አሽከር በሚሆን ሰው አምሳል አገኘው እርሱም ከጦብያ ጋር መጣ "ስሙንም አዛሪያ ነኝ" አለ ጦቢትም ላካቸው። ሲሔዱም በመሸ ጊዜ ወደ ጤግሮስ ወንዝ ደረሱ ጦብያም ገላውን ይታጠብ ዘንድ ወረደ። ታላቅ ዓሣም ሊውጠው ተወረወረ ሩፋኤልም ጦብያን "ዓሣውን ያዘው አትፍራው እረደውና ጉበቱን፣ ልቡንና፣ ሐሞቱን ያዝ" አለው እርሱም እንዳዘዘው አደረገ።
❤ ጦብያም ሩፋኤልን "አንተ ወንድሜ አዛርያ ይህ የዓሣ ሐሞት ጉበቱና ልቡ ምን ይደረጋል" አለው። አዛርያ የተባለ መልአክም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ጋኔን ያደረበት ሰው ወንድ ወይም ሴት ጉበቱንና ልቡን ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ያጤሱለት እንደሆነ ጋኔን ይሸሻል ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩ ሰውን ቢኩሉት ይድናል"። ሁለተኛም የራጉኤልን ልጅ ሣራን ያገባት ዘንድ ተናገረው እግዚአብሔርም ይጠብቀዋልና እንዳይፈራ አጽናናው። ወደራጉኤል ቤትም በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሣራን ወደዳት። እርሷንም ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው አባቷም ለሰባት ባሎች አጋብቷት ሰባቱም እንደሞቱ ነገረው ጦብያም "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ። ወደ ጫጉላ ቤትም በአገቧቸው ጊዜ ሩፋኤል የነገረውን ቃል አስታወሰ የዓሣውንም ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋር አጤሰ ያን ጊዜ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን ሸሸ መልአክ ሩፋኤልም ይዞ ለዘላለሙ አሠረው።
❤ ጦቢያም ሚስቱን ሣራን ይዞ ደስ ብሎት ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ አባትና እናቱም በደስታ ተቀበሉት የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሁኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ ዐይኑን አሸ ወዲያውኑ ድኖ ልጁን አየ። ከዚህም በኋላ የከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ራሱን ገለጠላቸው ብዙ ነገርንም ነግሮአቸው ወደ ሰማይ ዐረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ከወገኖቹ ጋር ተድላ ደስታን አደረገ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ መከራ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "እርሱ በኃጢአታችን ይገርፈናል ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል" ሁለተኛም "መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው። እነርሱ ክብርህን በአዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና" አለ።
❤ ዳግመኛም ስለ ኢየሩሳሌም መታነፅ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ኢየሩሳሌም ሰንፔር መረግድ በሚባል በከበረ ዕንቁ ትሠራለች ድልድልዋ፣ ቅጽርዋ፣ አደባባይዋ፣ ደጆቿም በከበረ ዕንቊ በጠራም ወርቅ ይሠራሉ አደባባይዋም ቢረሌ፣ አትራኮስ፣ ሶፎር በሚባል ዕንቁ ይሠራልና በመንገድዋ ሁሉ ሁሉም እግዚአብሔርን አስቀድሞ የነበረ ወደፊትም የሚኖር እያሉ ያመሰግኑታል ደግሞም ከዓለማት ሁሉ ጽዮንን ከፍ ከፍ ያደረጋት እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ"።
❤ ሁለተኛም የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢት ተናገረ ሁለተኛም ደግሞ ዮናስ ከነነዌ እንዲወጣ ልጁን ጦብያን አዘዘው። ዳግመኛም ልጁን እንዲህ አለው "ልጄ ሆይ ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት" ይህን ተናግሮ በዐልጋው ላይ ሳለ በመቶ ኀምሳ ስምንት ዘመኑ ዐረፈ በክብርም ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጦቢት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 16 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለጦቢት መፍቀሬ ምጽዋት ዘተብህለ። እስመ ይገብር ምጽዋተ ወብዙኅ ሣህለ። እንዘ ምስለ ሕዝቡ ይሄሉ ሀገረ ነነዌ ማዕከለ። እምከመ ረከበ በእሴ ቅቱለ። እንበ ይቅብሮ አይጥዕም እክለ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 16።
+ + +
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ለታነፀችበትና ለተቀደሰችበት በዓል፣ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ ለተሠሩበትና ለከበሩበት በዓል (ለደመራ በዓል)ና በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር ለተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ ለሆነ ለገባኤል ልጅ ለቅዱስ ጦቢት ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ከወርቅላ፣ ከስምዖን፣ ከመርቄኖስ፣ ከሐሊ፣ ከሮቂኖስ፣ ከሉክያኖስ፣ ከአርዝማኖስ፣ ከጴጥሮስ፣ ከሐና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ፦ ሃሌ ሉያ "ዝኒ ኮነ በፈቃደ እግዚአብሔር ዝንቱ ኵሉ ኮነ ወአንቲኒ ታቦት እምኀበ መጻእኪ ወኀበኒ ተሐውሪ መድኃኒተ ኩኒ ታቦት ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ"። ትርጉም፦ የንጉሥ የሕጉ ታቦት መድኃኒትን ሁኚ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ሆነ፤ አንቺ ታቦት ከወዴት መጣሽ ወዴትስ ትሄጃለሽ።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "ሐነፅዋ ለቤተ ክርስቲያን ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ እንተ ተሐንፀቶ በእደ ካህናት ወተቀደሰት በአፈ ጳጳሳት ወተአትበት በማይ ዘውኅዘ እምገቦሁ አመሕማማቲሁ ለሰማይ አቅዲሙ ፈጠሮ ወበምድር ተከለ ደብተራ ቀደሳ አብ ወማኅደሮ ረሰያ። ትርጉም፦ ቤተ ክርስቲያንን ሠሯት በመንፈስ ቅዱስም አነጿት በካህናት እጅ የታነፀች በጳጳሳት አፍም የተቀደሰች በሕማሙ ጊዜ ከጎኑ በፈሰሰው ውኃ የተጠመቀች ናት አስቀድሞም ሰማይን ፈጠረ በምድርም ድንኳንን ተከለ አብ ቀደሳት ማደሪያውም አደጋት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ በዚች ቀን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን የታነፀችበትና የተቀደሰችበት ነው። ደግሞ በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ።
❤ ይህም እንዲህ ነው ልጇ ቈስጠንጢኖስ በነገሠ በሃያ ዓመት ቅዱሳን የሆኑ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶችን በኒቅያ ከተማ ከሰበሰበ በኋላ ቅድስት እናቱ ዕሌኒ እንዲህ አለችው "ልጄ ሆይ እኔ ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም በመሔድ የክብር ንጉሥ የሆነ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል ፈልጌ አወጣ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስዕለትን ተስያለሁ"።
❤ ቈስጠንጢኖስም ሰምቶ በዚህ ነገር ደስ አለው ከብዙ ሠራዊትም ጋር ብዙ ገንዘብ ሰጥቶ ላካት የከበሩ የግምጃ ልብሶችንም ሰጣት እርሷም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ ከከበሩ ቦታዎች ተባረከች። ከዚህም በኋላ ስለ ከበረና አዳኝ ስለ ሆነ ዕፀ መስቀል መረመረች በታላቅ ድካምና ችግር አገኘችውና ታላቅ ክብርን አከበረችው በታላቅ ምስጋናም አመሰገነችው።
❤ ከዚህም በኋላ በጎልጎታ በቤተ ልሔምም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዋሻ ደግሞ በጽርሐ ጽዮን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ በተቀበረበት በጌቴሴማኒ በደብረ ዘይትም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ የቤተ መቅደስ መሠዊያ እንዲሠሩ አዘዘች። ዳግመኛም በዕንቁ በወርቅና በብር እንዲአስጌጧቸው አዘዘች።
❤ በኢየሩሳሌምም ስሙ መቃርስ የሚባል ኤጲስቆጶስ አለ። እርሱም ንግሥት ዕሌኒን እንዲህ ብሎ መከራት "ይህን እንዲህ አትሥሪ ከጥቂት ዘመናት በኋላ በዚህ አገር ሊነግሡ አሕዛብ ይመጣሉ። ሁሉን ይማርካሉ ቦታዎችንም ያፈርሳሉ ወርቁን፣ ብሩን፣ ዕንቁውን ይወስዳሉና ነገር ግን ጠንካራ የሆነ የማይናወጽና የማይፈርስ ጥሩ ሕንፃ ልታሠሪ ይገባል ከዚህ የሚተርፈውንም ለድኆችና ለችግረኞች ስጪአቸው" አላት። እርሷም የአባ መቃርስን ምክሩን ተቀብላ መኳንንቱ ሁሉ ለአባ መቃርስ በመታዘዝ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲአንፁ አዘዘቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ንግሥት ዕሌኒ ወደ ልጅዋ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በተመለሰች ጊዜ በኢየሩሳሌም ያደረገችውን ሁሉ ነገረችው ሰምቶ እጅግ ደስ አለው እንደገና ሌላ ብዙ ገንዘብና ሕንፃውን ተቆጣጥረው የሚያሠሩ ሹሞችን ላከ ለሚገነቡና ለሕንፃው ሥራ ለሚአገለግሉ ሁሉ ደመወዛቸውን ሳያጓድሉ ሁል ጊዜ ወደ ማታ እንዲሰጧቸው ንጉሡ አዘዘ። ስለ ደመወዛቸው እንዳይጮኹና እንዳያዝኑ እግዚአብሔርም ስለ ጩኸታቸው በእርሱ ላይ እንዳይቆጣ ይፈራልና።
❤ ጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ በ፴ ዓመቱ የከበሩ ቦታዎች ሕንፃቸው በተፈጸመ ጊዜ ንዋየ ቅዱሳትን ዋጋቸው ብዙ ድንቅ የሆነ የከበሩ የግምጃ ልብሶችንም ላከ። ደግሞም ወደ ቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳቶቹን በመያዝ እንዲዘጋጅ እንዲሁም ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳትና ወደ እስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስ ኤጲስቆጶሳቶቹን በመያዝ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ኢየሩሳሌም ተሰብስበው በከበሩ ቦታዎች ውስጥ የተሠሩትን ወይም የታነፁትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያከብሩ።
❤ ንጉሡም እንዳዘዘ ሁሉም ተሰበሰቡ እስከ መስከረም ወር ዐሥራ ስድስት ቀን ኑረው በዚች ቀን ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት መሠዊያቸውንም አከበሩአቸው የቁርባን ቅዳሴንም ቀድሰው ለምእመናን ሥጋውንና ደሙን አቀበሉ በዚችም ቀን ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታን ሆነ።
❤ የከበረ መስቀልንም በመሸከም በነዚያ በከበሩ ቦታዎች ዞሩ በውስጣቸውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ አመሰገኑትም መስቀሉንም አከበሩት ወደ ሀገሮቻቸውም በሰላም በፍቅር ተመልሰው ገቡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በስቀሉ ኃይልም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ጦቢት፦ ይህም ጻድቅ በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር የተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ የገባኤል ልጅ ነው፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው ከወገኖቹም ጋር ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉ ዐሥራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች የሚሰጥ ነው።
❤ በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሁሉም ክደው በዓልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሠው ነበር። ወገኖቹም ወደ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር የአሕዛብን መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና።
❤ በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት ወዲያውኑ እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረው ፀሐይ ሲገባም ቆፍሮ ቀበረው በዚያች ሌሊትም እንደ ኃጢአተኛ ሁኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ። በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስለ አላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ኩሳቸውን ከዐይኖቹ ላይ ጣሉበት ዓይኖቹም ተቃጠሉ ከእሳቸውም ጢስ ወጣ ታወሩም ባለመድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም።
❤ በዚያንም ጊዜ ጦቢት ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ለመነ "አቤቱ በቸርነትህ አስበኝ ወደ ችግረኛነቴም ተመልከት ለመማረክና ለመዘረፍ በአደረግኸን በእኔና በአባቶቼ ኃጢአት ተበቅለህ አታጥፋኝ። አሁንም በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን ነገር አድርግ ከመኖር ሞት ይሻለኛልና በሞት እሰናበት ዘንድ አፈርም እሆን ዘንድ ነፍሴን የሚቀበል መልአክን እዘዝ"።
❤ በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ ሣራን በጭኗ ያደረ ክፉ አስማንድዮስ የሚባል ጋኔን ለሰባት ባሎች አጋብተዋት ወ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፲፮ (16) ቀን።
❤እንኳን ለታላቁ አባት ተርታ ነገርንም እንዳይናገር ደንጊያ በአፉ ጎርሶ ለኖረ ለአባ አጋቶን ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አባ አጋቶን፦ ይህም አባት ወደ ቲቤያድ ገዳም ሲመጣ ገና ሕፃን ነበር። ያሳደገው ያስተማረው አባ ጴማን ነው። በመቀጠልም ወደ አስቄጥስ ተጉዞ ከአባ እስክድር እና ዞይለስ ጋር ለጥቂት ጊዜ ኖሯል። ገዳመ አስቄጥስ ለመጀመርያ ጊዜ ሲጠፋ አባ አጋቶን ከደቀ መዝሙሩ ከአባ አብርሃም ጋር በመሆን ከደብረ ትሮኤ ሳይርቅ ከዓባይ ወንዝ አጠገብ መኖር ጀመረ።
❤ አንድ ጊዜ ስለ አባ አጋቶን፡ትሕትና የሰሙ መነኰሳት ሊያዩት መጡ። የቁጣ ስሜቱን ወተውንና አለመተውን ለማረጋገጥ ብለው "አመንዝራውና ትዕቢተኛው አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት። አባ አጋቶንም "አዎ ትክክል ነው" አላቸው። ቀጥለውም "ፍሬ የሌለው ነገር ዘወትር የምታወራ አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት "አዎ ነኝ" አላቸው። "መናፍቅ አጋቶን ማለት አንተ አይደለህምን?" ሲሉ ጠየቁት ያን ጊዜ ግን "መናፍቅስ አይደለሁም" ሲል መለሰላቸው። በዚህ ጊዜ "እስካሁን የተናገርንብህን ሁሉ ተቀብለህ የመጨረሻውን ለምን ተቃወምክ?" አሉት። አባ አጋቶንም "የመጀመሪያያዎቹን ወቀሳዎች ለነፍሴ ተስማሚዎች ናቸውና ተቀበልኳቸው። ኑፋቄ ግን ከእግዚአብሔር መለየት ነው እናም እኔ ከፈጣርዬ መለየት አልፈልግም" አላቸው። በዚህ የተነሣም የርሱ ሕይወት አስደነቃቸው።
❤ አንድ ቀን አባ አጋቶን በእጁ የሠራቸውን ነገሮች ለመሸጥ ወደ ገበያ ሲወጣ በመንገድ ዳር አንድ ሽባ ሰው አገኘ። ሽባውም የት እንደሚሄድ አባ አጋቶንን ጠየቀው። "አንዳንድ ነገሮች ለመሸጥ ወደ ገበያ እሔዳለው" አለው። ሽባው ሰውም "እባክህ ተሸከምህ ወደዚያ ውሰደኝ" ሲል ለመነው። አባ አጋቶንም ያንን ሰው ተሸክሞ ወደ ከተማ ወሰደው። ሽባው ሸውዬ "ዕቃዎችን ከምትሸጥበት ቦታ አጠገብ አኑረኝ" አለው። አባ አጋቶንም እንደዚያው አደረገው። አባ አጋቶን የመጀመርያውን ዕቃ ሲሸጥ "ምን ያህል ሸጥከው?" ብሎ ሽባው ሰው ጠየቀው። እርሱም ዋጋውን ነገረው። ያም ሽባ ሰው "እባክህ ዳቦ ግዛልኝ" ሲል ለመነውና ገዛለት።
❤ አባ አጋቶን ሁለተኛው ዕቃ ሲሸጥ "ምን ያህል ሸጥከው" ሲል ያሰው ጠየቀው። እርሱም ዋጋው ነገረው "እባክህ ይህን ነገር ግዛልኝ" ሲል ለመነው። አባ አጋቶንም ገዛለት። በዚህም መልኩ ሁሉንም ዕቃዎች ሸጦ በጨረሰ ጊዜ ያሽባ ሰው "ወደ በዓትህ ትመለሳለህን?" ሲል ጠየቀው "አዎ" "እንግደውስ እባክ ቀድሞ ወደአገኸኝ ስፋራ አዝለህ መልሰኝ" አለው። አባ አጋቶንም ያን ሽባ ሰው ተሸክሞ ወደ ቀድሞ ቦታው መለሰው። በዚህ ጊዜ ሽባው ሰው "አባ አጋቶን በሰማይና በምድር በረከት ተሞላህ" ብሎ ተናገረው። ወድያው አባ አጋቶን አይኑን አንስቶ ሽባው ቢያየው በቦታው የለም። ሊፈትነው ይህን ያደረገው መልአከ እግዚአብሔር ነበር። ከአባታች ከአባ አጋቶን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ በበረሐው ጉያ ውስጥ ከሚለው መጽሐፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከጻፈው።
+ + +
❤ "ሰላም ለአጋቶን አምሳለ በቀልት ዘፈረየ። ክምረ ክምረ ጽድቁ እስከ አስተርአየ። ሰዓተ ፍዳ ወደይን ሶበ ውእቱ ሐለየ። ለዘይነብብ ጽሩዐ ከመ ቦ ሥቃየ። በከናፍሪሁ ማዕፆ ዕብን ወደየ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 16።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ከመስከረም ፱ እስከ ፲፭ ፍሬ🇪🇹
ይተበሀል መዝሙር እኩት አንተ።
የመስከረም ፲፭ ምስባክ🇪🇹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ዘቅዳሴ ምስባክ
፪ቆሮ፦ ፱፥፩-ፍ
ያዕቆብ፦ ፭፥፩-፲
ግብ.ሐዋ፦ ፲፱፥፳፩-ፍ
ወንጌል፦ ማር ፬፥፳፬-፴፱
ቅዳሴ፦ ዘወልደ ነጎድጓድ
ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ፣
ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ፣
ወይባርከነ እግዚአብሔር ።
✝
✝🇪🇹✝ መዝ ፷፮፥፮
✝
https://t.me/Eotcw
1 161
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መዝሙር እኩት አንተ ከመስረም ፱ - ፲፭
❣❣❣❣❣❣❣❣❣
(በ፭/ር) እኩት አንተ ወስቡሕ ስምከ ወዓቢይ ኃይልከ ዘተአርፍ በአርያም ወትሴባሕ በትሑታን ዘአንተ ሠራዕከ ሰንበተ ለዕረፍት ወወሀብከ ሲሳየ ዘበጽድቅ ለኵሉ እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርኅብት እንተ ጸግበት ተአኵተከ
አመላለስ፦
ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርኅብት/፪/
እንተ ጸግበት ተአኵተከ/፬/
https://t.me/Eotcw
# Join & share
1 161
ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥30-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@eotcww
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን ለዲያቆናት አለቃ ለቀዳሜ ሰማዕት ለቅዱስ እስጢፋኖስ ለሥጋው ፍልሰት ለመታሰብያ በዓልና ጠራው ከሚባል አገር ለሆኑ እግራቸው በውኃው ሳይርስ በእግራቸው በባሕር ላይ ሲራመዱ ለነበሩት ለከበረ ለጻድቁ ለአባ ጴጥሮስ በዓለ በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ "ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ ዘተረክበ እምተከብቶ። አመ ፲ወ፭ ለወርኅ መስከረም ቲቶ። ተወኪፈከ እስጢፋኖስ መሥዋዕተ ሰላምየ በኢያስትቶ። ምስሌየ ግበር እግዚኦ ለሠናይቲከ ትእምርቶ። ናሁ ለውዳሴከ ርኢኩ ማኅለቅቆ"። ትርጉም፦ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ ቲቶ በሚባል መስከረም 15 ቀን ከተቀበረበት ለተገኘ ለሥጋህ ፍልሰት ሰላምታ ይገባል። ጌታዬ ባለማቃለልም የሰላሜን መሥዋዕት ተቀብለህ የበጎነትህን ምልክት ከእኔ ጋር አድርግ። የምስጋናህንም ፍጻሜ እነሆ አይቻለሁ። መልክአ ቅዱስ እስጢፋኖስ።
+ + +
❤ የዲያቆናት አለቃ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት፦ ይህም እንዲህ ነው ከዐረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፉኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ "እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ" አለ።
❤ ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ።
"በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ" እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።
❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።
❤ በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።
❤ ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።
❤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ "የቅዱስ እስጡፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ" ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።
❤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም ለተመሰገነና ለተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ እስጢፋኖስ ሥጋው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አቡነ ጴጥሮስ ዘሃገረ ጠራው፦ ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ክልቡ በቆራጥነት ተነሣ በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ። ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ። ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ማመስገን ነው። በዚህም ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና የሆነ መላእክትን መሰላቸው።
❤ አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ተገባው እግሮቹም አይርሱም ሥጋ እንደ ሌለው መንፈስ እስከ ሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ ወደርሱ ሔደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 15 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም እብል ለጴጥሮስ ብሕትወ። ኮከበ ጠራው። ወውስተ ዓለም ኅሩም እምበሊዐ ኅብስት ወጼው። እስከ አስተርአየ በአምሳለ ምትሐት ሕስው። ተሴስዮ ሣዕር አብደረ በበድው"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም15።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወጾሩ ዘርዖሙ። ወሶበ የአትዉ ወጽኡ እንዘ ይትፌሥሑ። ወፆሩ ከላስቲሆሙ። መዝ 125፥6። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥39-45።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ብፁዕ ዘኀረይኮ ወዘተወከፍኮ። ወዘአኀደርኮ ውስተ አዕፃዲከ። ጸገብነ እግዚኦ እምበረከተ ቤትከ"። መዝ 64፥4። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 3፥6-12፣ 2ኛ 2፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥55-ፍ.
1 161
ቢስማቸው ነፍሳቸው ከሥጋቸው መስከረም 15 ቀን ተለይታለች፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ገብረ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
