ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
ቀምሶም ለአባታችን ሰጠው፤ ጣዕሙ ደስ ባሰኘው ጊዜ አባታችን ከሩቅ ሀገር የመጡ የተራቡ ሰዎች ከቤቱ ደጃፍ እንዳሉ አወቀ፡፡ መነኰሳቱንም "አባቶቼ፣ ወንድሞቼና ልጆቼ ፈቃዳችሁ ከሆነስ ለክርስቶስ እንሰጠው ዘንድ ለነዳያንና ለችግረኞች እንስጣቸው" አላቸው፡፡ ❤ በቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ወንድሞች መነኰሳት፣ ክቡራን ካህናት፣ ዲያቆናትና ሕዝቡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ፣ በወንጌል ወተት ያደገ፣ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ የአባታችንን ትሕትና፣ ትሩፋትና ቅድስና ባዩ ጊዜ አዘኑበት፡፡ ምንም ቃል አልመለሱለትም፤ በቦታቸው ወይም በቤታቸው አልነበሩምና፤ በልባቸው "እኛስ ከሩቅ ሀገር የመጣን አይደለምን?" አሉ፡፡ እነርሱ ግን ከዚያው ይኖሩ ነበር፤ አባታችን ግን ነዳያንን ሰብስቦ ያንን ምግብ ሰጣቸው፡፡ ❤ ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡ እነዚያ መነኰሳትም አንዲት ቃል አልተናገሩም፤ ነገር ግን በልባቸው ተቆጡ፤ በጣምም አዘኑ፤ አባታችን ግን ደቀ መዛሙርቱን ሌላ ማእድ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘ፤ ከመንገድ ስንቅ ይመገቡ ነበርና ጥቂት አመጡ፡፡ ገና ሳይቀምሱም ከሕዝብ አንዱ "አባቴ ሆይ! ጸልይልኝ፤ ይህን ጥቂት በረከትም ተቀበል" ብሎ ብዙ ጠላ ላከ፤ እነዚህ መነኰሳት ግን ይህን ባዩ ጊዜ ፈጽመው ተደነቁ፤ ፈጽመው ፈሩ፤ ተንቀጠቀጡም፡፡ አባታችንም ተነሥቶ ለክርስቶስ ሰጠሁት፤ ለተራቡትም አስቀደምሁ፤ ለድኆች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር ያበድራል የሚል ተጽፏልና አላቸው፡፡ ❤ እነዚህ መነኰሳትም "አባታችን መምህራችን ሆይ! ይቅር በለን አንተ ብዙ ሐዘንን ታውቃለህና፤ እኛ ስለሆዳችንና ስለልብሳችን አዘንን፤ አንተ ግን እንደ ጌታህ ክርስቶስ የድኆችና የችግረኞች ወዳጅ ነህና›" አሉት፡፡ "አላወቅንምና አባታችን ይቅር በለን፤ አንተ ፈቃደ እግዚአብሔርን ትፈጽማለህ፤ እርሱም ልመናህን ይሰማልና" አሉት፡፡ "እንዲሰጥህ አላወቅንም፤ ነገር ግን ጎተራህን ሁሉ እንደሚሞላልህ ሰምተን ነበር፤ የተዘጋጀ ምግብንም እንዳወረደልህ ሰምተን ረሳን፤ "አሁንም አባታችን ይቅር በለን፤ ባንተ ላይ ተቆጥተን ነበር፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነ አላወቅንም፤ አንተ ግን አስቀድመህ ለተራቡት ሰጠህ፤ ቀጥሎም ከአምላክህ በረከት ለእኛ ለመብላት ለተዘጋጀን ሰጠኸን" አሉት፡፡ ❤ አባታችን ዘግሩምም "ወንድሞቼና ልጆቼ ይህን የማደርገው ለሰው ልታይ ብዬ አይደለም፤ ለትምክህትም አይደለም፤ እግዚአብሔር የሰጠኝ ሀብት ነው እንጂ" አላቸው፡፡ "እኔ እሰጣለሁ፤ እርሱም የሚያስፈልገኝን ነገር አላሳጣኝም" አላቸው፤ እነርሱም ከእርሱ ተባረኩ፤ ከዚህም በኋላ ታላላቅ ተአምራትና ድንቅ ነገርን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን ገናናነት ተነጋገሩ፡፡ ❤ ከዕለታት አንድ ቀንም አባ ዘግሩም ቆሞ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጣ፤ ቅድስት የሆነች የጎኑን መወጋትና ቁስሎቹን ሁሉ አሳየው፡፡ በደሙ መፍሰስም ተደሰተ፤ ሰግዶም እንዲህ አለ፤ "ጌታየ የሚፈሰውን ደምህን እዳስስ ዘንድ ፍቀድልኝ" አለው፤ ጌታችንም ቅዱስ የሆነ ደሙን ይዳስስ ዘንድ ፈቀደለት፤ እንደ ቶማስም ጎኑን ዳሰሰ፤ ቶማስስ ደቀ መዛሙርቱን ስላላመነ ነበር፤ ይህ አባታችን ግን ጌታችን "ሳያዩኝ የሚያምኑኝ ብፁዓን ናቸው" ብሎ እንደተናገረው ሳያይ ያመነ ነው፡፡ ይህ አባታችን ግን ሳያይ አመነ፤ በቅዱስ ደሙ መፍሰስም ደስ አለው፤ ወንድሞቼ ሆይ ለአባታችን የተሰጠውን ጸጋ ተመልከቱ፤ የመድኃኒታችንን ቁስሎች ዳስሷልና፤ ለድኆች የማዘን ፍሬው ይህ ነው፤ "ለድኆች የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል" ተብሏልና፡፡ ❤ ለሰው ልጅ የሚሰጥ ታላቅ ጸጋን አገኘ፤ ከሀገሮች ሲመለስም ወደ ደብረ ጽዮን ለመሄድ ግባ ከተባለ ታላቅ ወንዝ ደረሰ፤ ከፈሳሹ ብዛት የተነሣ ስትበረታታ አገኛት፡፡ ብዙ ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የሚያደርጉትንም አጡ፤ ብፁዕ አባታችን ግን ከወንዙ ዳር ቆመ፤ በምርጉዙም በባሕሩ ላይ አማተበ፤ ያን ጊዜ ወንዙ ወዲያና ወዲህ ተከፈለ፤ በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተሻገሩ፡፡ ነቢዩ ሙሴ የኤርትራን ባሕር በከፈላት ሕዝቡንም በመራ ጊዜ እንደ ተሻገሩ ሁሉ ተሻግረዋልና እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ይህም አባታችን ባሕርን በየብስ አሻገራቸው፤ ከዚህ በኋላ በሰላም ወደ ቤቱ ደረሰ፡፡ ከአባታች ከአቡነ ዘግሩም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። + + + ❤ "ሰላም ለኪ ጸበለ ማርያም ተሐራሚት። እምወይነ መዓዛ ወእክለ ወራዙት። ተውላጠ ሕማምኪ ዘመነጠነ ኀምሳ ዓመት። በገነተ ጽጌ ኀበ ተነጽፈ ዕረፍት። ከመ ንባእ አኃውኪ አስተብቊዒ እኅት"። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 24። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ቸው መሠረት ተሸክመውት የነበረውነ በአህያው ላይ ጫኑት፡፡ ነገረ ግን አህያው መንቀሳቀስን ፈጽሞ እምቢ አለ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ ሲገፉትና ሲደበድቡት ብዙ ደከሙ፤ እንዲህ እያደረጉ ሳሉ አንድ አገልጋይ የንጉሥ መልእክት ይዞ መጣ፡፡ እኒህን ስሕተተኞችም አገኛቸውና "ጌቶቼ ለምን ትደክማላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም "ይህ አህያ አልሄድም አለን" አሉት፤ የንጉሡ መልእክተኛም መንፈስ ቅዱስ አነሳሳውና ከፊታቸው ቆመና "የዚህ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው?" አላቸው፡፡ እነርሱም "ይህን አህያ ከአንድ መንፈስ ቅዱስ ካደረበት ቀሲስ አመጣነው፤ በዚህ ቀሲስ ቃል ላይ በጨመርን ጊዜ መሔድን እምቢ አለን" በማለት የሠሩትን ነገሩት፡፡ "እስኪ የጨመራችሁትን ቀንሱለት" አላቸው፤ ቀነሱለትና ያን ጊዜ አህያው ተነሥቶ እነርሱም ወደሚፈልጉበት ቦታ ሔዱ፡፡ ይህንንም ሁለት ጊዜ ሦስት ጊዜ ደጋግመው አደረጉ እምቢም አላቸው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የቅዱሱን ቃል በመተላለፋቸው እንደሆነ አወቁ፤ ያም የንጉሡ አገልጋይ ተደንቆ "ኑ ይህ ቅዱስ ካለበት አድርሱኝ" አላቸው፡፡ አባታችን ካለበት ቦታም ደርሶ ከእርሱ ዘንድ ተባረከ፡፡ ❤ ያም አህያውን የወሰደው ሰው ከአቡነ ብርሃነ መስቀል እግር ሥር ተንበርክኮ "በፊትህ በድያለሁና ቃልህንም አሳብያለሁና አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ፤ አህያውም መሄድን እምቢ አለ፤ የጨመርንበትን ሸክም በቀነስንለት ጊዜ ግን ይሄዳል" አለው፡፡ ዳግመኛም ሀሀሀ…እኔ ግን እንደ እኔ አይነት ሰው ነህ መስሎኝ ቃልህን አፈረስሁ፤ አንተ ግን በፍቅርህ ገመድ ሳብኸኝ፡ሀ አለው፡፡ አባታችን ብርሃነ መስቀልም "ለምን ሐሰት ተናገርህ? መጽሐፍ "ሐሰት የኀጢአት መጀመሪያ ናት፤ ሐሰተኞችም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም› ይል የለምን?" በማለት ከመከረው በኋላ በሰላም ወደቤቱ እንዲሔድ ነገረው፡፡ ❤ ያም ሰው ከአቡነ ብርሃነ መስቀል ዘንድ ወጥቶ መንገዱን ሔደ፤ ያ የንጉሡ መልእክተኛም አብርሃም ከተባለ ከአቡነ ዘግሩም ዘንድ ተባርኮ ወጣ፤ የቤተ ክርስቲያኗንም አሠራር አይቶ የአባታችን የአብርሃምን ተአምር አደነቀ፤ የንጉሡን ትእዛዝ ይፈጽም ዘንድም መንገዱን ሄደ፡፡ ከብዙ ቀናት በኋላ ያ መልእክተኛ ከንጉሡ ዘንድ ደረሰ፤ ስመ መንግሥቱ ቆስጠንጢኖስ ለተባለ የእግዚአብሔር ወዳጅ ለሆነ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩን ነገረው፡፡ "ጻድቅ ንጹሕ የሆነ ቀሲስ አለ፤ በዚህ ዘመን በመንግሥትህ ሀገር ሁሉ እንደርሱ ያለ ሰው የለም፤ ሥራው ሁሉ እንደቀደሙት አባቶች ነውና" አለው፡፡ ❤ በዐይኑ ያየውን፤ በጆሮው የሰማውን ሁሉ ስለሠራት ቤተ ክርስቲያንም ነገረው፤ ንጉሡም ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በልቡ ተደሰተ፤ በመንፈሱም ሐሴትን አደረገ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነው፤ እንዲህም አለ፡- ‹‹በዘመነ መንግሥቴ የተሰወረውን የሚያውቅ፤ ተአምራትን የሚያደርግ እንዲህ ያለ ጻድቅ ሰውን የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይክበር፡፡ አባቴ ቤተ ክርስቲያን ማነጽ በፈለግህ ጊዜ ወደ እኔ ለምን አልላክህም ብሎ ላከበት፤ እኔ ከደቀ መዛሙርትህ እንደ አንዱ አይደለሁምን በረከትህን በተቀበልሁ ነበር አለ፡፡ በዚህ የመንግሥት ዙፋን ላይ ያለሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንጂ በራሴ ፈቃድ ይመስልሃልን በእስረኞች መካከል ሳለሁ ከእስረኞች መካከልም ተኝቼ ሳለ ከዚያ አውጥቶ በአባቶቼ በሰይፈ አርዕድና በዐምደ ጽዮን ዙፋን ላይ አስቀመጠኝ፡፡ አንተ ግን በኀጢአቴ አትናቀኝ፤ ለቤተ ክርስቲያን የምትፈልገውን ይህን ገንዘብ ውሰድ"፡፡ ዳግመኛም ለአባታችን ልብስ ላከለት፤ ሚስቱም እንዲሁ ላከች በጸሎትህ አትርሳን" አሉት፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ይመነኵስ ዘንድ ወደደ፤ የመላእክትና የቅዱሳን ልብስ የምትሆን የምንኩስና ልብስን ያለብሰው ዘንድ የአቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድእ ወደ ሆነው ወደ አባ ብሶይ መጣ፡፡ ወደ እርሱ ደርሶ ሥርዐተ ምንኩስና ከፈጸመለት በኋላ አባታችን አብርሃም "የቀድሞ ስሜን ተውልኝ" አለው፤ አባ ብሶይም ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ስም እንደ ለወጠላቸው ስምህን እለውጣለሁ እንጂ አይሆንም" አለው፡፡ "ስምህንም አብርሃም፣ ጳውሎስ፣ ዮሐንስ ከሚሉት መካከል ዕጣ በማጣጣል እሰይምሃለሁ" አለው፡፡ ❤ ሦስት ጊዜም ዕጣ ጣሉ፤ አብርሃም የሚለውም ስም ወጣ፤ ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆነ አወቀ፡፡ከታናሽነቱ ጀምሮ የአብርሃም ምግባር የሆነውን እንግዳ መቀበልን፣ እግር ማጠብንና የተራበውን ማብላት ጀመረ፤ ስለዚህ አብርሃም መባል ተገባው፡፡ "ከታናሽነቴ ጀምሮ የአብርሃምን ሃይማኖት እንደወደድሁ፣ እንግዳ በመቀበል እንደ ኖርሁ ይህን ስም የሰጠኝ እግዚአብሔር ይመስገን" አለ፡፡ መንኵሶ በፈቃዱ አብርሃም ተብሎ ተጠርቷልና በብዙ ገድልና በትሕርምት በዚያች ቦታ ኖረ፡፡ ❤ የነዳያን ፍቅር በልቡ ውስጥ አለ፤ ሁል ጊዜ ስለ ምግባቸውና ስለ ልብሳቸው ያስብ ነበር፤ ለሚያስፈልጋቸው ነገርም ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ለድኆች ልብሱን ያካፍላል፤ ለእነርሱም ሰጥቶ እርሱ ራቁቱን ይቆማል፤ ልጆቹም ይመጣሉ፤ ‹‹ልብስህ ወዴት ነው?›› ይሉት ነበር፤ እርሱም ‹‹ሌቦች በማያገኙበት ቦታ አለ›› ይላቸው ነበር፡፡ ልጆቹ ግን ሥራውን አያውቁም ነበር፤ ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ሁሉን ይሠውር ነበር፤ አይገልጥላቸውም ነበር፤ ድኃ ባየ ጊዜ አጽፉን ይሰጥ ነበር፤ አጽፉን ይቅርና ምንም ልብስ አያስቀርም ነበር፡፡ ❤ አንድ ቀን አንድ ድኃ መጥቶ ስለ እግዚአብሔር ስም ምግብና ልብስ ለመነው፡፡ አባታችን ያን ድኃ ባየው ጊዜ አጽፉን ሰጠው፤ ዳግመኛ አንድ ድኃ መጣ፤ በቤቱም የሚሰጠውን አጣ፤ መጠምጠሚያውን አውርዶ እርሷንም ለድኃው ሰጠውና በቤቱ ተቀመጠ፡፡ አንድ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ መጥቶ ራቁቱን አገኘውና ተቆጣበት፤ "ክቡር አባቴ ሆይ! ለምን እንዲህ ትሆናለህ?" አለው፡፡ "ለምትበላውና ለምትለብሰው ሳታስቀር ያለ አቅምህ ለምን ምጽዋት ትሰጣለህ? ልብስህንና መጎናጸፊያህን ሰጥተህ አንተ ራቁትህን ትሆናለህ"፡፡ አባታችንም "ልጄ ሆይ! ፈጽሞ ስለሚያረጅና ስለሚጠፋ የዚህ ዓለም ልብስ ፈንታ የብርሃን መጎናጸፊያ የሚያለብሰኝ አምላኬ አለልኝ" አለ፤ ልጆቹም ሌላም ልብስ አምጥተው አለበሱ፡፡ "ይህንም እንደ ቀደመው አታድርግ" አሉት፤ እርሱ ግን ስለ ድኆችና ስለ ችግረኞች ፍቅር ብዙ ጊዜ ምጽዋት ያደርግ ነበር፤ ቅብዓት በሰውነት፣ ውሃ በአንጀት እንዲገባ የነዳያን ፍቅር ወደ ልቡ ገባ፡፡ ❤ የነዳያንን የጩኸት ድምፅ በሰማ ጊዜ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለመነሣት ይፈልጋል፤ ከማእድ ላይ ቢሆንም እንኳን ድምፃቸውን ከሰማ እጁን ወደ ማእድ አያወርድም ነበር፤ ይሰጣል እንጂ ምንም ነገር አያተርፍም ነበር፡፡ ነዳያን ግን ዘወትር ጩኸትና ልመናን አያቋርጡም ነበር፤ አባታችን ስለ ምግባቸውና ስለ ልብሳቸው እንደሚያስብ አውቀው ከቤቱ አይርቁም ነበር፡፡ ❤ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ አንዲት ታላቅ ሀገር ሔዶ ከዚያ ደረሰ፤ በሰንበት ምሽት ለእሑድ አጥቢያ ከዚያ አደረ፤ ሥርዓተ ቁርባን ከተፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሩን "ልጄ የምንበላው ነገር አለህ ወይስ የለህም?" አለው፤ ያ ደቀ መዝሙርም "አባቴ አዎን አለኝ" አለው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ያያቸውን ታላላቅ መነኰሳት ሰበሰበ፤ ቁጥራቸውም ዐራት መምህራን ነበሩ፡፡ የተዘጋጀ ምግብና ጠላ ያን ጊዜ እነርሱም ከቤታቸው እንጀራ አመጡ፤ ሁለት ያመጣ አለ፤ ሦስትም ያመጣ አለ፤ ሁላቸውም እንደ አቅማቸው አመጡ፤ አባታችንም ጸሎት ያደርግ ዘንድ ተነሣ፤ ባረከላቸውም፡፡ ደቀ መዝሙሩንም "ጠላውን አምጣው" አለው፤ ሁለት መነኰሳትም እንሥራውን አመጡት፤ ከመካከላቸው አንዱን ጠጣ አለው፤

ሳለች ለአንደ ደገኛ ቄስ ነገረችው፡፡ ❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አምላክን በድንግልና የወለደች ክብርት እመቤታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገለጠችላትና "ስሜን የተሸከምሽ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን" አለቻት፡፡ እመቤታችንም ብዙ ምሥጢርን ከነገረቻት በኋላ ጡቶቿንም አጠባቻትና በጸጋ የከበረች አደረገቻት፡፡ በስሟም ብዙ ተአምራትን የምታደርግ ሆነች፡፡ ❤ ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ እንደነቢያት የሚመጣውን ሁሉ እንዳለፈ አድርጋ ትናገራለች፡፡ ዳግመኛም የትምህርታቸውን ፍለጋ ስለተከተለችና ለሕጋቸው ስለተገዛች ከሐዋርያት ጋር ዕድል ተሰጣት፡፡ ሦስተኛ ግድ ሳይሏት በፈቃዷ ስለተቀበለቻቸው ግርፋቶቿና ስላገኛት መከራ የሰማዕታት ዕድል ተሰጣት፡፡ ከደናግል መነኰሳትም ዕድል ተሰጣት መነኵሲትም ድንግልም ናትና፡፡ ቅድስት እናታችን ጸበለ ማርያም መልካም የሆነውን ተጋድሎዋን ከፈጸመችና ጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከገባላት በኋላ በሰላም ዐርፋለች፡፡ እንደ ንግሥት ዕሌኒም የሞቷን መስቀል ተሸክማ ተጠብቆላት ወዳለ ተስፋዋ በክብር ሄደች፡፡ ከእናታችን ከቅድስት ጸበለ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ ጸበለ ማርያም። + + + ❤ መፍቀሬ ነዳያን አባ ዘግሩም፦ አባታቸው ገርዜነ ጸጋ የተባለ ደገኛ ካህን ሲሆን እናታቸው ደግሞ ነፍስተ እግዚእ ትባላለች፡፡ እነዚህም ደገኛ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ብዙ ዘመን ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለመኑት ነበር፡፡ ልዑል እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ አበሰራቸው፡፡ አባ አብርሃምም በመልአኩ ብሥራት ግንቦት ሃያ አራት ቀን በተወለዱ ጊዜ ወላጆቻቸው ብርሃነ መስቀል ብለው ጠሩት፡፡ በኋላ የተጠራበት ስመ ጥምቀቱ ግን ማኅፀንተ ሚካኤል ነው፡፡ ❤ ወላጆቹም በመንፈሳዊ አስተዳደግ ስላሳደጉት ከልደቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አደረበት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አደገ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያንም መሄድን አላስታጎለም፡፡ እንደ ነቢዩ ሳሙኤል ከታናሽነቱ ጀምሮ በእግዚአብሔር ቤት አድጓልና፡፡ አድጎ ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ መጻሕፍተ ነቢያትን፣ መዝሙረ ዳዊትን ይማር ዘንድ አባቱ ለመምህር ሰጠው፡፡ ሕፃኑም በትምህርቱ አስተዋይ ሆነ፡፡ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ ከመምህሩ መረዳትን ያበዛ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል የጸና ሆነ፡፡ ዲቁናም ተሾመ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ እናቱና አባቱ ያለ ፈቃዱ ሚስት ያጩለት ዘንድ ወደዱ፡፡ በመጽሐፍ "የልጅ ልጅህን ታያለህ፣ አንተ ብፁዕ ነህ፣ መልካምም ይሆንልሃል" የሚል በመጽሐፍ ተጽፏልና፡፡ ስለዚህም ያጋቡት ዘንድ አቻኮሉት፤ እርሱ ግን ዓለመን ፍጹም ንቆ በምንኩስና በተጋድሎ መኖርን ወደደ፡፡ ለምንኩስናም ስሙ አባ ክርስቶስ ይባርከነ ወደተባለ አንድ መነኩሴ ወዳለበት ገዳም ሲሄድ በመንገድ መደራ በተባለች ቦታ በታላቅ ገዳም ውስጥ ከእንግዶች ጋር አደረ፤ በሌሊት በነቃ ጊዜ አንድ ድኃ በዚያች ቤት ውስጥ አገኘ፤ የድኃውን ልብስ ወስዶ የእርሱን ልብስ ሰጥቶተ በሌሊት ወጥቶ መንገዱን ሔደ፡፡ በነጋም ጊዜ ያ ድኃ ያደረገለትን ለሰዎቹ ተናገረ፡፡ "በእንግዳ ማደሪያ ከእኔ ጋር አብሮ ያደረ አንድ ሰው እኔ የለበስሁትን ልብስ ወስዶ የእርሱን መልካም ልብስ ተወልኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም "… የእግዚአብሔር ሰው ነውና መልካም ሥራ አደረገልህ አንተ ግን ሔደህ ስለ እርሱ ጸልይለት" አሉት፡፡ ❤ አባ አብርሃም ግን ከአባ ክርስቶስ ይባርከነ ከቀድሞ ቤቱ በደረሰ ጊዜ በዚያም አላገኘውም፤ ውኃ ከሌለበት፤ ፀጥታ ከሰፈነበት ምድረ በዳም ሔደ፡፡ የፀሐይ ወቅት ነበረና በዚያ ሲመላለስ ሳለ ውኃ ጥም ያዘው፡፡ ያን ጊዜም በገዳሙ ውስጥ ባዶ ወጭት አገኘና በፊቱ አስቀምጦ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ወዲያው ብዙ ዝናም ዘነመ፤ በወጭቷም አጠራቀመና እስኪበቃው ድረስ ከእርሷ ጠጣ፡፡ ❤ ከዚያም አባታችን ክርስቶስ ይባርከነን አገኘውና ሊያደርግ የሚፈልጋቸውን ምሥጢሩን ሁሉ ነገረው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ አባታችንን "…በደመና ተጭነህ ወደ ዳሞት አገር ሂድ" አለው፤ አባታችንም በደመና ተጭኖ ፍራጽ ከተባለ ገዳም ደረሰ፤ በዚያም ምድርን ባረኮ ውሃ አፈለቀ፤ መልአኩም "ወደ ቀኝህ ተመልከት" አለው፡፡ ወደ ቀኙ ሲያይ ዐደልን ብርሃን ከቧት ተመለከተ፤ ዕፅዋትም ጭፍቅ ያሉ ነበሩ፤ አባ ዘግሩምም "ይህች ቦታየ ናት?" አለ፤ የጻሕናንን ምድር እየባረከም ይሄድ ዘንድ ወደደ፡፡ ብዙ ውሃ አፈለቀ፤ ዐደልም ደረሰ፤ በዚያም ውሃ አፈለቀ፤ አባታችን ዘግሩም ወደ ውስጧ ገባ በዚያም ተቀመጠ፣ የገዳሙ አራዊትም በዚህ ተደሰቱ፡፡ ❤ ሙሴ ጽላትን እንደተቀበለ ሁሉ ጥቅምት ሃያ አራት ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና የመድኃኔዓለምን ታቦት ሰጠው፡፡ ዳግመኛም የእግዚአብሔር መልአክ የተዘጋጀ ኅብስትና የተቀዳ ጽዋን፤ ለመሥዋዕት የሚሆነውንም ሁሉ ሰጠው፤ አባታችንም ከካህናት ጋር በዚያች ቤተ ክርስቲያን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን አጠገብ አንዲት የዋንዛ ዛፍ ነበረች፤ ሕዝቡም ይሰበሰቡባትና በሥሯ ተቀምጠው ክፉ ሥራ ይሠሩ ነበር፤ አባታችንም "ለምን እንዲህ የማይገባ ሥራ ትሠራላችሁ?" ሲላቸው እነርሱ ግን አልሰሙም፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችንም ያቺን ዛፍ "ከበታችሽ ካሉት ሕዝብ ጋር ተነሥተሽ ሒጂ" ብሎ በቃሉ አዘዛት፡፡ ያን ጊዜም ያች ዛፍ ከሕዝቡ ጋር ተነሥታ የሁለት ጦር ውርወራ ያህል ሔደች፡፡ ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ "የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁና ይችን ሾላ ተነስተሽ ወደዚህ ነይ ብትሏት ትመጣለች፤ ይህን ተራራ ከዚህ ሂድ ብትሉት ይሄዳል" እንዳለ አባታችን አባ ዘግሩምም ይህንን አደረጉ፡፡ ❤ ከአባታችን ይባረኩ፤ እጅ ይነሡም ዘንድ አርባ አራት ቅዱሳን በደመና ተጭነው አባታችን ካለበት ቦታ ወደ ዐደል መጡ፡፡ ሶምሶን ከአህያ መንጋጋ፤ ሙሴ ከዐለት ውሃ እንዳፈለቁ ሁሉ ለሚያስፈልጋቸው ነገር ይጠቀሙበት ዘንድ አባታችንም በጸሎቱ በአንድ ጊዜ አርባ አራት የውሃ ምንጮችን አፍልቆ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ይህን አይተው አደነቁ፤ ስምህ ዘግሩም ይሁን አሉት፤ ስለዚህም አባታችን አባ ዘግሩም ተባለ፤ ምንጮቹም ድውያንንና ሕሙማንን የሚፈውሱ ሆኑ፡፡ ❤ ዳግመኛም ለአባታችን የሚገለገልበት አንድ አህያ ነበረው፤ የሚጭነው ሰው ሳይከተለው ለሁለት ቀናት ሔዶ ወደ ጫነው ሰው ቤት ይመለስ ነበር፤ የአገሩ ሰዎችም ይህን አይተው ያላቸውን ሁሉ ይጭኑትና ብቻውን ሔዶ ወደ አባታችን ይመለስ ነበር፡፡ ❤ የአቡነ ብርሃነ መስቀልን ተአምራቱን ዜናውን በሰማ ጊዜ ከንጉሡ ባለሟሎች አንዱ መጣ፡፡ ሌላም በቤቱ አጠገብ የሚኖር አንድ ሰው መጣና "ጨው ጭኜ ወደ ገበያ እወስድበት ዘንድ አህያህን ስጠኝ" ብሎ ለመነው፡፡ የተቸገሩትን ለመርዳት የሚልከው አንድ አህያ ነበረውና አባ አብርሃምም "የጨው መጠን ምን ያህል ነው?" አለው፡፡ ያ ሰውም "በሰቅል ስሳ ይሆናል" አለው፡፡ አባታችን አብርሃምም "ውሰደው ከተናገርኸው በላይ ግን አትጫነው" አለው፡፡ ሰውየውም አህያውን ወስዶ አባታችን እንዳለው ጫነው፤ ለአባታችን ያልነገረውን በቤቱ የተረፈውን ግን ያ ሰውና ወንድሙ ተሸከሙት፡፡ እነርሱም ተካፍለው ተሸክመው መንገዳቸውን እየሄዱ ሳለ ከአገር ብዙ በራቁ ጊዜ ወንድሙን "ና አህያውን እንጫነውና እንደፈቀድነው እንሒድ የሚያየን የለምና" አለው፡፡ በዚህም ምክራ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፳፬ (24) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ጌታችን በደሃ ሰው ተመስሎ ተገልጦ ቁራሽ እንጀራ ለለመናትን በኋላም በጀርባዋ አዝላ ለሸኘችው ለታላቋ እናትን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተአራሚት ለመታሰቢያዋ በዓል፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ነድያንን ለሚወዱ ለአቡነ ብርሃነ መስቀል (አብርሃም) በሚያደርጉት ድንቅ ድንቅ ተአምራት አባ ዘግሩም ለተባሉት ሙሴ ጽላትን እንደተቀበለ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና የመድኃኔዓለምን ታቦት ለተሰጡበት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ቅድስት ጸበለ ማርያም፡- ትውልዷ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ቀሐ አካባቢ ነው፡፡ ወላጆቿ አባቷ እንድርያስና እናቷ መስቀል ክብራ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር ኮትኮተው አሳደጓት፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተከስተ ብርሃን የተባለ ደገኛ ባሕታዊ ወደ አባቷ ቤት መጥቶ ባደረበት መንፈስ ቅዱስ ኀይል የቅድስት ጸበለ ማርያምን ጸጋ አወቀ፡፡ ለወላጆቿም "ይኽቺ ልጅ ወደፊት ነፍሳት የሚድኑባት የከበረች ትሆናለች" ብሎ በእርሷ ላይ ትንቢት ተናገረ፡፡ ❤ ቅድስት ጸበለ ማርያም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ በጋብቻ ሕግ እንድትወሰን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ጸበለ ማርያም "ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር አጭቶኛልና ፈጣሪዬን በድንግልና ለማገልገል ተስያለሁ" በማለት ተቃወመቻቸው፡፡ ወደ አንድ ደገኛ ባሕታዊም ዘንድ ሄዳ በጸሎቱ ከዚህ ነገር እንዲያድናት ተማጸነችው፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ከጠየቀላት በኋላ ማድረግ የሚገባትንና ወደፊት የሚገጥማትን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ለዕጣን እንዲሆን ጌጧን ሁሉ አውጥታ ሸጠችና "መሥዋዕቴን አሳርግልኝ" ብላ ለባሕታዊው ሰጠችው፡፡ እርሱም ከጸለየላት በኋላ የጸሎቱን ምላሽ ነገራት፡፡ ❤ ወለጆቿም ያለፈቃዷ በሕግ ቢያጋቧትም ቅድስት ጸበለ ማርያም ግን በሌሊት ማንም ሳያያት ከጫጉላ ቤት ወጥታ ሄዳ በልዳው ፀሐይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች ቤተክርስቲያን ሄዳ እያለቀሰች ጸሎት አደረገች፡፡ እመቤታችንም ከሚካኤል ወገብርኤል እንዲሁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገለጠችላትና እንዲጠብቋት ነገረቻቸው፡፡ ቤተሰቦቿም እንዳያዝኑባት ፈርታ ተመልሳ ወደ ባሏ ዘንድ ብትገባም ባሏ በግብር እንዳያውቃት መላእክቱ ይጠብቋት ነበር፡፡ ባሏንም ሰውነቷ እንደእሳት ያቃጥለው ነበር፡፡ እርሱም አእምሮውን ከሳተ ከ3 ቀን በኋላ ሲነቃ የደረሰበትን ለቤተ ዘመዶቹ ባስዳቸው ጊዜ "ከገዳም የመጣች ከሆነች ለእኛ ልትሆን አይገባም" አሉና አስጊጠውና ሸልመው መልሰው ወደ ቤተሰቦቿ ላኳት፡፡ ❤ አባቷም ዳግመኛ ወደ ባሏ እንድትመለስ በማስገደድ ብዙ አሰቃቂ ግርፋት ቢገርፋትም በተአምራት ምንም እንዳላገኛት ሆነች፡፡ ከዚኽም በኋላ ወጥታ ወደ ምድረ በዳ ሄደች፡፡ ወደ ገዳምም ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ስትጸልይ አድራ አረፍ ስትል ነብር መጥቶ የእግሯን ትቢያ ይልሳት ነበር፡፡ ከዚያም ወጥታ ንህበት ወደሚባል ሀገር መጥታ ቶማስ ከሚባል መነኩሴ ጋር በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ቆማ ስትጸልይ እንባዋ መሬቱን ያርስ ነበር ነገር ግን ሰው እንዳያውቅባት አፈር በላዩ ትጨምርበታለች፡፡ በአንድ ዕለትም በቤተክርስቲያን ቆማ ስትጸልይ በሁለቱ ማዕዘን የተቀበሩ ምውታን ሲጮኹ ሰማቻቸው፣ እነርሱ ግን በሲኦል ነበሩ፡፡ ጩኸታቸውንም በሰማች ጊዜ በእንባዋ ላይ እንባን በጸሎቷም ላይ ጸሎትን ጨምራ ስለ እነርሱ ለመነች፡፡ ስለእነርሱም ሱባኤ ያዘች፡፡ በባሕርይው ቸርና ይቅርባይ የሆነ ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ እነዚያን ነፍሳት ማረላት፡፡ ❤ ቅድስት ጸበለ ማርያም በምግባርና በትሩፋት በጾም በጸሎት ጸንታ ከኖረች በኋላ የምንኵስና ቀንበርን ትሸከም (በምናኔ ትኖር) ዘንድ በብሕትውና ወደሚኖረው ታላቁ አባት ወደ አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር የደረሰው ነው፡፡ ❤ አቡነ ገብረ ማርያምም ካስተማራትና በኋላ አመነኰሳትና ስሟን "ጸበለ ማርያም" ብሎ ሰየማት፡፡ ከዚኽም በኋላ ተጋድሎዋን እጅግ በማብዛት ትሕርምትን ገንዘብ አደረገች፡፡ ከዕንጨት ፍሬዎች ውጭ የማትመገብ ሆነች፡፡ በተቀደሰችው የጌታችን ፵ ጾም ወራት ግን ከሰንበት በቀር እርሱንም ፈጽሞ አትቀምስም፣ እስከ ፋሲካም ድረስ ከበዓቷ ስለማትወጣ ማንም አያያትም ነበር፡፡ ከመነኰሰችም ጊዜ ጀምሮ በጎኗ ተኝታ አታውቅም፡፡ ባመማት ጊዜም ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፡፡ በውርጭ ቅዝቃዜ መከራን እየተቀበለች በባሕር ውስጥም ቆማ እየጸለየች ታድራለች፡፡ በስግደቷም በቀን እስከ 8 እልፍ ትሰግድ ነበር፡፡ ከወንድሟ ቶማስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማረች፡፡ የዮሐንስን ወንጌልና የራእዩን መጽሐፍ ዘወትር በማንበብ ትጸልያለች፡፡ የእመቤታችን በዓል በሆነ ጊዜ አርጋኖን ውዳሴዋን በቀን ሦስት ጊዜ ታነባለች፣ አንቀጸ ብርሃንንም በየሰባቱ ጊዜ ትጸልያለች፡፡ የዳዊትንም መዝሙር በፈጸመች ጊዜ የጌታችንን መከራ ግርፋት እያሰበች ራሷን ሺህ ጊዜ ትገርፋለች፡፡ ❤ ዳግመኛም አገዛዛቸው መልካም ይሆን ዘንድ ስለ ጳጳሱና ስለ ንጉሡ አንድ አንድ ሺህ ጊዜ፣ ስለ መነኰሳትም ሺህ ጊዜ፣ ስለኃጥአንም ሺህ ጊዜ ራሷን ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም ነጭ ዕጣን በእጇ ይዛ ሰባት ቀን እስኪሆን ድረስ ዕንባዋን ታፈስበታለች፣ ያም ነጭ ዕጣን ከዕንባዋ ብዛት የተነሣ ጥቁር ይሆናል፡፡ በዓል በሚሆንበት በሰባተኛው ቀን አስቀድማ ዐውቃ በመሠዊያ ያሳርገው ዘንድ ያን ዕጣን ለቄሱ ትሰጠዋለች፡፡ እግዚአብሔርም እንደሱራፌል የጽናሕ መዐዛና እንደኪሩቤል ዕጣን ሽታ አድርጎ ከቄሱ እጅ ሲቀበል በግልጽ ታያለች፡፡ ❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅድስት ጸበለ ማርያም እየጸለየች ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቆሰለ ችግረኛ ደሃ ሰው ተመስሎ ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገልጦ ወደ እርሷ በመምጣት ቁራሽ እንጀራ ለመናት፡፡ እርሷም ፈጥና ይዛ መጥታ ሰጠችው። እንጀራውንም ተቀብሎ ሲያበቃ "በመንገድ ብዛት ደክሜአለሁና በጀርባሽ አዝለሽ ትሸኚኝ ዘንድ እወዳለሁ" አላት፡፡ እርሷም ለድሆች አዛኝ ናትና አዝላው የድንጋይ መወርወሪያ ያህል እንደወሰደችው ቁስሉ ይድን ጀመር፡፡ ወዲያውም ቁስሉ ድኖ ምንም እንዳላገኘው ፍጹም ደህነኛ ሰው ሆነ፡፡ ያንጊዜም ፊቱ እንደፀሐይ አበራ፣ ሁለንተናውም ተለወጠ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ከጀርባዋ ወርዶ በፊት ለፊቷ ቆመና "የከበርሽ አገልጋዬ ጸበለ ማርያም ሆይ! ምን እንዳድርግልሽ ትወጃለሽ?" አላት፡፡ እርሷም ከድንጋጤዋ የተነሣ እንደበድን ሆና መሬት ላይ ወደቀች፡፡ ጌታችንም አበረታትና እጇን ይዞ አነሣትና "የልብሽን መሻት ለምኚኝ" አላት፡፡ እርሷም "አምላኬ ሆይ! በፊትህስ ሞገስ ካገኘሁ በሲኦል ያሉ ነፍሳትን ይቅር በላቸው" አለችው፡፡ በዚኽም ምክንያት በጌታችን ቸርነትና በእርሷም አማላጅነት ብዙ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቷት በክብር ዐረገ፡፡ ❤ ዳግመኛም ጌታችን ለቅድስት ጸበለ ማርያም ሦስት በትሮችን ሰጥቷት በእነርሱ እየተመረኮዘች እስከሲኦል ድረስ ትሄድና ነፍሳትን ታወጣና ታስምር እንደነበር ራሷ ተናገረች፡፡ ዳግመኛም ስትናገር "ሰማያውያን ብዙ ስሞች አወጡልኝ፣ 'የወይን ፍሬ' እያሉ ይጠሩኛል፣ 'የበረከት ፍሬ' የሚሉኝም አሉ፣ 'የገነት ፍሬም' ይሉኛል" አለች፡፡ ዳግመኛም ከልዑል ዘንድ ብዙ ጸጋዎች እንደተሰጣት በሕይወት

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 6:36-ፍ፡ም፡ "ወኩኑ መሐርያነ ከመ አቡክሙ" - "አባታችሁ፡ርኅሩኅ፡እንደ፡ሆነ፡ርኅሩሆች፡ሁኑ። አትፍረዱ፡አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ፡አትኰነኑምም። ይቅር፡በሉ፡ይቅርም፡ትባላላችሁ። ስጡ፡ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት፡መስፈሪያ፡ተመልሶ፡ይሰፈርላችኋልና፥የተጨቈነና፡የተነቀነቀ፡ የተትረፈረፈም፡መልካም፡መስፈሪያ፡በዕቅፋችሁ፡ይሰጣችኋል። ምሳሌም፡አላቸው፦ዕውር፡ዕውርን፡ሊመራ፡ይችላልን፧ሁለቱ፡በጕድጓድ፡አይወድቁምን፧ ደቀ፡መዝሙር፡ከመምህሩ፡አይበልጥም፤ፈጽሞ፡የተማረ፡ሁሉ፡ግን፡እንደ፡መምህሩ፡ይሆናል። በወንድምህም፡ዐይን፡ያለውን፡ጕድፍ፡ስለ፡ምን፡ታያለኽ፥በራስህ፡ዐይን፡ግን፡ያለውን፡ምሰሶ፡ስለ፡ ምን፡አትመለከትም? በዐይንህ፡ያለውን፡ምሰሶ፡ራስህ፡ሳታይ፥እንዴት፡ወንድምህን፦ወንድሜ፡ሆይ፥በዐይንህ፡ያለውን፡ጕድፍ፡ላውጣ፡ፍቀድልኝ፡ልትል፡ትችላለህ? አንተ፡ግብዝ፥አስቀድመህ፡ከዐይንህ፡ምሰሶውን፡አውጣ፡ከዚያም፡በኋላ፡በወንድምህ፡ዐይን፡ያለውን፡ጕድፍ፡ታወጣ፡ዘንድ፡አጥርተህ፡ታያለህ። ክፉ፡ፍሬ፡የሚያደርግ፡መልካም፡ዛፍ፡የለምና፥እንዲሁም፡መልካም፡ፍሬ፡የሚያደርግ፡ክፉ፡ዛፍ፡የለም። ዛፍ፡ሁሉ፡ከፍሬው፡ይታወቃልና፤ ከሾህ፡በለስ፡አይለቅሙም፥ከዐጣጥ፡ቍጥቋጦም፡ወይን፡አይቈርጡም። በልብ፡ሞልቶ፡ከተረፈው፡አፉ፡ይናገራልና፥መልካም፡ሰው፡ከልብ፡መልካም፡መዝገብ፡መልካሙን፡ያወጣል፥ክፉ፡ሰውም፡ከልብ፡ክፉ፡መዝገብ፡ክፉውን፡ያወጣል። ስለ፡ምን፦ጌታ፡ሆይ፥ጌታ፡ሆይ፥ትሉኛላችሁ፥የምለውንም፡አታደርጉም? ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፡ዅሉ፡ቃሌንም፡ሰምቶ፡የሚያደርገው፥ማንን፡እንዲመስል፡አሳያችኋለሁ። ቤት፡ሲሠራ፡አጥልቆ፡የቈፈረ፡በአለት፡ላይም፡የመሠረተ፡ሰውን፡ይመስላል፤ ጐርፍም፡በመጣ፡ጊዜ፡ወንዙ፡ያን፡ቤት፡ገፋው፥በአለት፡ላይም፡ስለ፡ተመሠረተ፡ሊያናውጠው፡አልቻለም። ሰምቶ፡የማያደርገው፡ግን፡ያለመሠረት፡በምድር፡ላይ፡ቤቱን፡የሠራ፡ሰውን፡ይመስላል፤ወንዙም፡ገፋው፡ወዲያውም፡ወደቀ፡የዚያ፡ቤት፡አወዳደቅም፡ታላቅ፡ሆነ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.54 KB

23/2/2015 ዓ.ም (፳፫/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን፡፡ መዝ. 83፥5 🕯 ትርጉም የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና። ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳል። የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 10:16-34 "ወናሁ አነ እፌንወክሙ ከመ አባግዕ" - "እንሆ፥እኔ፡እንደ፡በጎች፡በተኵላዎች፡መካከል፡እልካችኋለሁ፤ስለዚህ፥እንደ፡እባብ፡ልባሞች፡እንደ፡ርግብም፡የዋሆች፡ሁኑ። ነገር፡ግን፥ወደ፡ሸንጎ፡አሳልፈው፡ይሰጧችኋል፥በምኵራቦቻቸውም፡ይገርፏችኋልና፥ከሰዎች፡ተጠበቁ፤ ለእነርሱና፡ለአሕዛብም፡ምስክር፡እንዲሆን፥ስለ፡እኔ፡ወደ፡ገዢዎች፡ወደ፡ነገሥታትም፡ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም፡ሲሰጧችሁ፥የምትናገሩት፡በዚያች፡ሰዓት፡ይሰጣችኋልና፥እንዴት፡ወይስ፡ምን፡እንድትናገሩ፡አትጨነቁ፤ በእናንተ፡የሚናገር፡የአባታችሁ፡መንፈስ፡ነው፡እንጂ፥የምትናገሩ፡እናንተ፡አይደላችሁምና። ወንድምም፡ወንድሙን፥አባትም፡ልጁን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ይሰጣል፥ልጆችም፡በወላጆቻቸው፡ላይ፡ይነሣሉ፡ይገድሏቸውማል። በሁሉም፡ስለ፡ስሜ፡የተጠላችሁ፡ትሆናላችሁ፤እስከ፡መጨረሻ፡የሚጸና፡ግን፡እርሱ፡ይድናል። በአንዲቱ፡ከተማም፡መከራ፡ቢያሳይዋችሁ፡ወደ፡ሌላዪቱ፡ሽሹ፤እውነት፡እላችኋለሁና፥የሰው፡ልጅ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡የእስራኤልን፡ከተማዎች፡አትዘልቁም። ደቀ፡መዝሙር፡ከመምህሩ፥ባሪያም፡ከጌታው፡አይበልጥም። ደቀ፡መዝሙር፡እንደ፡መምህሩ፥ባሪያም፡እንደ፡ጌታው፡መሆኑ፡ይበቃዋል።ባለቤቱን፡ብዔል፡ዜቡል፡ካሉት፥ቤተ፡ሰዎቹንማ፡እንዴት፡አብዝተው፡አይሏቸው! እንግዲህ፡አትፍሯቸው፤የማይገለጥ፡የተከደነ፥የማይታወቅም፡የተሰወረ፡ምንም፡የለምና። በጨለማ፡የምነግራችሁን፡በብርሃን፡ተናገሩ፤በጆሮም፡የምትሰሙትን፡በሰገነት፡ላይ፡ስበኩ። ሥጋንም፡የሚገድሉትን፡ነፍስን፡ግን፡መግደል፡የማይቻላቸውን፡አትፍሩ፤ይልቅስ፡ነፍስንም፡ሥጋንም፡በገሃነም፡ሊያጠፋ፡የሚቻለውን፡ፍሩ። ሁለት፡ድንቢጦች፡በዐምስት፡ሳንቲም፡ይሸጡ፡የለምን፧ከእነርሱም፡አንዲቱ፡ያለአባታችሁ፡ፈቃድ፡በምድር፡ላይ፡አትወድቅም። የእናንተስ፡የራሳችሁ፡ጠጕር፡ሁሉ፡እንኳ፡ተቈጥሯል። እንግዲህ፡አትፍሩ፡ከብዙ፡ድንቢጦች፡እናንተ፡ትበልጣላችሁ። ስለዚህ፥በሰው፡ፊት፡ለሚመሰክርልኝ፡ሁሉ፥እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እመሰክርለታለሁ። በሰው፡ፊትም፡የሚክደኝን፡ሁሉ፡እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እክደዋለሁ። በምድር፡ላይ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡የመጣኹ፡አይምሰላችኹ፤ሰይፍን፡እንጂ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡አልመጣሁም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.50 KB

23/2/2015 ዓ.ም (፳፫/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን፡፡ መዝ 78:10 🕯 ትርጉም አሕዛብ አምላካቸው ወ ዴት ነው? እንዳይሉ። የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል። በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

#ምሥጢረ ሜሮንና አፈጻጸሙ ምሥጢረ ሜሮን ከሚሥጥረ ጥምቀት ቀጥሎ ወዲያውኑ የሚፈጸም ማኅተመ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በተጨማሪም የአጠቃቀም ሥርዓቱና ጸሎቱ የተለየ ሆኖ ቅብዓ ሜሮን ለምሥጢረ ክህነትና ለሚሥጢረ ተክሊል ማክበሪነት ያገለግላል፡፡ ሜሮን ማለት ቅብዐ ቅዱስ፣ የተባረከ ሽቱ፣ ብፁዓን ጳጳሳት ከበለሳንና ከዕፀወ ዕጣን ከአስጳዳቶስ ከሌላም ከብዙ ዓይነት ሽቱ፣ ተገቢውን ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው የሚያወጡት ነው፡፡ ምሥጢረ ሜሮን ከጥምቀት ጋር ተያይዞ ከጥምቀት ቀጥሎ የሚፈጸም፣ መንፈስ ቅዱስን የሚያሳድር፣ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃችንን፣ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለዳችንን የሚያረጋግጥልን ታላቅ ምሥጢር ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ፣ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ሲወጣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ባረፈ ጊዜ የአብ የባሕርይ ልጅነቱ በባሕርይ አባቱ ምስክርነት ተረጋግጧል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አማኞች ተጠምቀው ሲወጡ በቅዱስ ቅብዐት በሜሮን ከብረው የጸጋ ልጅነት ማግኘታቸው ይረጋገጣል፡፡ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ መወለዳቸው ይታወቃል፡፡ ምሥጢረ ሜሮንን የመሠረተልን ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “እኔ በንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል” (ማቴ 3፡ 11) በማለት እንደመሰከረለት በመንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቅ እሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ለሐዋርያትም ተስፋ እንዳደረገላቸው በበዓለ ሃምሳ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስን ላከላቸው፤ በደቀ መዛሙርቱ ላይ እፍ ባለባቸው ጊዜ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ከዕርገት በፊትም ደቀ መዛሙርቱን እስከ ቢታንያ አውጥቶ እጁን አንሥቶ በላያቸው ጭኖ ባርኳቸዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም ቅዱሳን ሐዋርት የተቀበሉትን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ለተከታዮቻቸው በአንብሮተ ዕድ ያድሉ ነበር፡፡ አዳዲስ ተጠማቂዎችም በሐዋርያትና በተከታዮቻቸው አንብሮተ እድ እየተደረገላቸው በልጅነት ይከብሩ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ተጠማቂዎች እየበዙ ሲመጡ ለአባቶቻችን እግዚአብሔር ገልጾላቸው ቅብዐ ሜሮኑን በአንብሮተ እድ እያከበሩ ለአብያተ ክርስቲያናት በማከፋፈል ምሥጢረ ሜሮን በአንብሮተ እድ ምትክ እንዲፈጸም ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይህንንም የቤተ ክርስቲያን አባቶች በሎዶቅያ ጉባኤ ወስነው አጸኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሐዲስ ኪዳን በቅብዐ ሜሮን የሚታደለውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በተመለከተ ሲያብራራ “እናንተስ ከቅዱሱ ያገኛችሁት ቅብዐት አላችሁ፤ ሁሉንም ታውቃላችሁ፡፡ እውነትን የምታውቁ ስለሆናችሁ፣ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን እንደማታውቁ አድርጌ አልጽፍላችኁም፡፡” (1ኛ ዮሐ 2፡20-22) በማለት አስተምሮናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ከዚህ አሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልእክት “ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፡፡ ደግሞም ያተመንና የመንፈስ ቅዱስን ፊርማ በልቦናችን የሰጠን እርሱ ነው፡፡” በማለት አስተላልፎልናል፡፡ (2 ቆሮ 1፡ 21-23) ቅብዐ ሜሮን ሦስት ዓይነት አገልግሎቶች አሉት 1ኛ. ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል፡- አዳዲስ አማንያን(ተጠማቂዎች) ከተጠመቁ በኋላ በሜሮን ተቀብተውና ከብረው ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርባቸው ያደርጋል፡፡ 2ኛ. የእግዚአብሔር አገልጋዮች (ካህናት) ለመሾም፡- ካህናት አባቶች የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ወይም ሕዝብ ለማገልገል የሚችሉበትን ሥልጣን (ሹመት)፣ ማስተዋል (ጥበብ)፣ ኃይል (ብርታት)፣ ትዕግሥትና ጽናት የሚያጎናጽፋቸውን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል እንዲችሉ በሚሾሙበት ጊዜ በሜሮን ይቀባሉ (ይከብራሉ)፡፡ 3ኛ. አዳዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲንና ለንዋየ ቅድሳት ማክበሪያ፡- አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ንዋየ ቅድሳቱ የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንዲሆኑ በሜሮን ተቀብተው እንዲከብሩ ይደረጋል፡፡ ከጽላቱ ጀምሮ መስቀሉ፣ ጽንሐው፣ ከበሮው፣ ሰኑ፣ ብርቱና የመሳሰለው ሁሉ በሜሮን ከከበረ በኋላ ለአገልግሎት ይውላል፡፡ ቅብዐ ሜሮን ለሁለት ምሥጢራት ማክበሪያነት (ማተሚያነት) ያገለግላል፡፡ ምሥጢረ ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው፡፡ ምሥጢረ ክህነት ካህናት ከቄሱ ጀምሮ ወደ ላይ ያሉት ማለትም ጳጳስና ቄስ በቅብዐ ሜሮን ከብረው ካህናተ እግዚአብሔር ይሆናሉ፡፡ ይህም በብሉይ ኪዳን “እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ የቅብዐትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈሰዋለህ፤ ትቀባዋለህ፡፡ ልጆቹንም ታቆርባቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፡፡ እንዲሁም የአሮንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ፡፡” (ዘፀ 29፡ 1-8) የተባለውን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ካህናትን በቅብዐ ሜሮን አክብሮ ሥልጣነ ሐዋርያትን ማስተላለፍ ጥንታዊ የተለመደና የከበረ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡ ምሥጢረ ተክሊልም ሙሽራውና ሙሽሪት በቅብዐ ሜሮን ታትመው ይከብራሉ፡፡ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆን የጀመርነው ከተጠመቅንበትና በሜሮን ከከበርንበት ዕለትና ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ በመቅደስ ሰውነታችን አድሮ የነበረውን አምላክ አሳዝነን አስወጣነው ወይስ አስደስተን እስካሁን ከእኛ ጋር አቆየነው? የእግዚአብሔርን የክብር ዕቃ፣ ማደሪያ መቅደሱንም በጥንቃቄ የማይዙና የሚያቃልሉ ሁሉ የሚቀጡ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የመቅደሱ ባለቤት እግዚአብሔር ለቤቱና ለሥርዓቱ ቀናዒ ነው፡፡ መቅደሱ የኃጢአት ሸቀጠጥ ማራገፊያና መነገጃ ሲሆን ዝም ብሎ አያይም፡፡ (ማቴ 21 ፡ 12 -18) ናቡከዳናፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ማርኮ በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት በክብር ያኖራቸውን ንዋያተ ቅድሳት አስመጥቶ በማቃለል ጣዖታትን እያመለኩ እንዲበሉባቸውና እንዲጠጡባቸው በማድረጉ በንዋየ ቅድሳቱ በተሳለቀባቸው ዕለትም ተገድሎ አደረ፡፡(ዳን 5፡1 እስከ ፍጻሜ) እግዚአብሔርንና የሱ የሆኑትን ሁሉ የማያከብሩ ሰዎች ለማይገባ አእምሮ ተላልፈው እንደሚሰጡ ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ (ሮሜ 1፡ 21) እግዚአብሔር ያከበራቸውን ማቃለል እግዚአብሔርን ማቃለል ነውና፡፡ (ሉቃ 10 -16) ሜሮን ከተፈላ (ከተዘጋጀ) በኋላ በየሀገረ ስብከቱ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይታደላል፡፡ ከዚህ ውጪ ከአታላዮች በስመ ሜሮን ወይም ቅብዐ ቅዱስ እየገዙ ለምሥጢረ ሜሮን መፈጸሚያነት መጠቀም ሕገ ወጥ ተግባር ነው፡፡ ምእመናን የአታላዮችን ድርጊት በመቃወምና ለካህናት ትክክለኛ አገልግሎት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን ሁሉ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ምንጭ፡- የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትና ሥርዓት (2011)

photo content
+6

photo content

photo content

ፈ ወርቅን ንግሥት አውዶክስያ እንዳሳደደችው በክፉዎች ሰዎች ምክር ንግሥቲቱ ሚስቴ ማሳደዷን የቀኖናውንም ትእዛዝ በመተላለፍ በፈቃዳቸው ሌላ ጳጳስ እንደሾሙ ነገሩኝ"። ❤ እርሱ አባ ዮሐንስም ከኢትዮጵያ በአሳደዱት ጊዜ ወደ አስቄጥስ በመሔድ አስቀድሞ በመነኰሰባት በአባ ሙሴ ጸሊም ገዳም በዚያ ተቀመጠ። የኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክትም ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ በደረሰች ጊዜ አነበባት ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ የሃይማኖት ጽናት እጅግ ደስ አለው ፈጥኖም ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ልኮ አባ ዮሐንስን ወደርሱ አስመጥቶ አረጋጋው አጽናናው ከዚያም በኋላ ከደጋጎች ሰዎች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው። ❤ አባ ዮሐንስም ወደ ኢትዮጵያ አገር በደረሰ ጊዜ ቸነፈር ተወገደ ዝናብም ዘነበ ንጉሡና መላው የኢትዮጵያ ሰዎች ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም ሥውር የሆነውን ተርጉሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥቅምት 23 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ። መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኲስና በፊት ሃያ አመት በምንኲስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የከሀዲ ዱድያኖስ ንጉሥ ሚስት ሰማዕቷ ቅድስት እለእስክንድርያ፦ ይኸውም ለጣዖቶቹ እንደሚሠዋ መስሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘበተበት ጊዜ ዝንጉዕ ዱድያኖስም ዕውነት መስሎት ራሱን ሊስም ተነሣ። ቅዱሱ ግን ለአማልክት ከመሠዋት አስቀድሞ አይሆንም ብሎ እንዳይስመው ከለከለው። ❤ ከዚህ በኋላም ዱድያኖስ ወደ ቤተ መንግሥቱ አዳራሽ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስገባው በዚያም በንግሥት እለእስክንድርያ ፊት የዳዊትን መዝሙር በማንበብ ጸለየ። በሰማችም ጊዜ ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው ያን ጊዜም ተረጐመላት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነቱን ገለጠላት ትምህርቱም በልቡዋ አድሮ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነች። ❤ ከዚህም በኋላ ሲነጋ ለአማልክት ወደሚሠዋበት ቅዱስ ጊዮርጊስን ወሰዱት እርሱም የረከሱ አማልክትን ትውጣቸው ዘንድ ምድርን አዘዛት ምድርም ዋጠቻቸው። ንጉሥ ዱድያኖስም አፈረ እየአዘነና እየተከዘ ወደ ሚስቱ ወደ እለእስክንድርያ ዘንድ ገባ። እርሷም "ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነው አላልኩህምን" አለችው። ይህንንም ሰምቶ በእርሷ ላይ ተቆጣ ያሠቃዩዋት ዘንድ ጡቶቿንም ሠንጥቀው ይሰቅሏት ዘንድ አዘዘ። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት እለእስክንድርያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። የሚያዝያ 15 ስንክሳር። + + + ❤ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ፦ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ተቀበለ። ይህንንም ቅዱስ በያዙት ጊዜ ብዙ ሥቃይን አሠቃዩት ማሠቃየቱንም በሰልቹ ጊዜ ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። የቅዱስ ዲዮናስዮስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 23 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለሊቀ ጳጳሳት ዮሴፍ። ዘእምሀገረ መኑፍ። ዘተውህበ ሎቱ አእምሮ መጽሐፍ። ወሰላም ካዕበ ለተልእኮቱ ዕስቁፍ። እንተ ክሣዶ መቲረ ዘኢይክል ሰይፍ"። ሊቀ አርከ ሥሉስ አርኬ የጥቅምት 23። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 1ጢሞ፥17-ፍ.ም፣ ያዕ 1፥12-19 እና የሐዋ ሥራ 15፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ6፥36-49። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ እጨጌ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩንይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክድርያ አገር ኀምሳ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ዮሴፍ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ ለቆሮንቶስ አገር ኤጺስቆጶስ ለቅዱስ ዲዮናስዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለከሀዲ ንጉሥ ለዱድያኖስ ለሚስት ለቅድስት እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ኢላርዮስ፣ ከጣንቅያቅ፣ ከቴዎደስዮስ፡ከቴዎላስ፣ ከዮሳብና ከገድላ ከሰማዕት እስክድርያም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ አገር ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ፦ ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው። ❤ አድጎ በጎለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ፃድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ። ❤ ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ የዚህን አባ ዮሴፍን በጎ ጠባዩንና የትሩፋቱን ዜና ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው በቤቱም አኖረው። ከብዙ ወራትም በኋላ አባ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ማርቆስን "ወደ አስቄጥስ ገዳም እሔድ ዘንድ ተወኝ" ብሎ ለመነው ያን ጊዜም ቅስና ሹሞ አሰናበተው ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖንም እስከ ዐረፈ ድረስ በዚያ በእስቄጥስ ገዳም ኖረ ከዚህም በኋላ የግብጽ አገር ያለ ሊቀ ጳጳሳት ብዙ ወራት ኖረች ። ❤ ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳቱ መማለጃ ስለተቀበሉ ከአንድ ሚስቱ ከሞተችበትና መዓስብ ከሆነ ጸሐፊ ጋር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተስማሙ እኩሌቶቹ ግን ተቃወሟቸው እንዲህም አሏቸው "የአባቶቻችን ቀኖና መማለጃ የሚቀበለውን ሁሉ ወይም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ የሚሰጠውን ያወግዛል። ይልቁንም ይህ ሰው ሚስት አግብቷል እንዴት ሊሾም ይችላል በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ የሚሾም ንጹሕ ድንግልም ነውና"። ይህንንም በአሏቸው ጊዜ ፈሩ ተመልሰውም ተስማሙ ለዚች ለከበረች ሹመት የሚሻለውን ይገልጽላቸው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በአንድ ምክር ሁነው ጸለዩ እግዚአብሔርም ሰምቷቸው ለዚች የከበረች ሹመት የሚሻል አባ ዮሴፍ እንደሆነ አሳሰባቸው። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ያመጡት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ላኩ መልክተኞችም "ይህን አባት ዮሴፍን የመረጥከው ከሆነ ምልክትን ትገልጥልን ዘንድ አቤቱ እንለምንሃለን የቤቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ ካገኘን ምልክት ይሁንልን" ብለው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ❤ በደረሱም ጊዜ አንዱን መነኰስ እየሸኘ የበዓቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ አባ ዮሴፍን አገኙት በአያቸውም ጊዜ መንፈሳዊ ሰላምታ በመስጠት እጅ ነሣቸውና በደስታ ተቀብሎ ወደ በዓቱ አስገባቸው በዚያንም ጊዜ "ለአባ ዮሴፍ ሊቀ ጵጵስና ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" እያሉ ይዘው አሠሩት። እርሱ ግን "እኔ ብዙ ኃጢአትን ሠርቻለሁና ይህ የከበረ ሹመት አይገባኝም" እያለ ይጮህ ነበር እነርሱም ወደ እስክንድርያ ከተማ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እንጂ ምንም ምክንያት አልተቀበሉትም። ❤ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ለአብያተ ክርስቲያን እጅግ የሚያስብ ሆነ ለርሱ የሆነውን የግብሩን ገቢ ወስዶ ምድሮችን በመግዛት ለአብያተ ክርስተያን መተዳደሪያ ሊሆኑ ጉልቶች ያደርጋቸው ነበርና። አዘውትሮም ሕዝቡን የሚያስተምራቸው ሆነ በምንም በምን ለየአንዳንዱ ቸለል አይልም ነገር ግን ሰይጣን ስለቀናበት ያለ ኀዘን አልተወውም። ይህም እንዲህ ነው በምስር አገር የተሾሙ ሁለት ኤጲስቆጶሳት በሕዝቡ ላይ ክፉ ነገር በማድረግ በማይገባ ሥራ አስጨነቋቸው እርሱም በርኅራኄና በፍቅር መንጎቻቸውን እንዲጠብቁ አዘዛቸው ለመናቸውም እነርሱ ግን ሰምተው ከክፋታቸው አልተመለሱም። ❤ በሕዝቡም ላይ ችግርን በአበዙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉም በጠቅላላ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መጡ በፊቱም እንዲህ ብለው ጮኹ "እሊህን ኤጲስቆጶሳት ከላያችን ካላነሣሃቸው እኛ ወደሌላ ሃይማኖት እንገባለን አባ ዮሴፍም በመካከላቸው ሰላምን ለማድረግ ብዙ ትግልን ታገለ ግን አልተቻለውም። ❤ ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ያሉትን ኤጲስቆጶሳት ለጉባኤ ሰበሰባቸውና ስለ እሊህ ሁለት ኤጲስቆጶሳት ነገራቸው አሁንም ከመንጋዎቻቸው ጋር ሊአስታርቅ ሽቶ እሊህን ኤጲስቆጶሳት ወደ ጉባኤው አስቀረባቸው እነርሱ ግን የጉባኤውንም የእርሱንም ቃል አልተቀበሉም ስለዚህም ያ ጉባኤ ከሹመታቸው ሻራቸው። እነርሱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሒደው በሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ ላይ በሐሰት ነገር ሠሩበት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍንም ያመጡት ዘንድ ንጉሡ ወንድሙን ከጭፍራ ጋር ላከው። ❤ የንጉሡም ወንድም ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ በደረሰ ጊዜ ተበሳጨ ሊገለውም ወዶ ሰይፉን መዞ ሊቀ ጳጳሳቱን ሊመታው ሰነዘረበት ግን እጁ ወደ ሌላ አዘንብሎ ምሰሶ መትቶ ሰይፉ ተሰበረ እጅግም ተቆጥቶ ሌላ ሰይፍን መዝዞ በመላ ኃይሉ መታው ያን ጊዜም ሰይፉ ከአንገቱ ወደ ወገቡ ተመልሶ ልብሱንና ቅናቱን ብቻ ቆረጠ የንጉሡም ወንድም ከክፋት ንጹሕ እንደሆነ ስለዚህም አምላካዊት ኃይል እንደምትጠብቀው አሰበ አስተዋለም። ወደ ንጉሡም በክብር አደረሰው ወንድሙ ለሆነ ንጉሥም በእርሱ በሊቀ ጳጳሳቱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገረው ንጉሡም ፈራው አከበረውም። ❤ ከዚህም በኋላ ስለከሰሱት ስለ ሁለቱ ኤጲስቆጶሳት ጠየቀው እርሱም ስለ ክፉ ሥራቸው በጉባኤ እንደተሻሩ እውነቱን ለንጉሡ አስረዳው ያን ጊዜም ሐሰተኞች እንደሆኑ ንጉሥ አወቀ ይገድሏቸውም ዘንድ አዘዘ። ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍም ንጉሡን እንዲህ ብሎ ማለደው "ጌታችን በክፉ ፈንታ በጎ እንድናደርግ እኛን አዞናልና ስለ እግዚአብሔር ብለህ እሊህን ማራቸው እንጂ አትግደላቸው" ንጉሡም ስለ የዋህነቱ አደነቀ ልመናውንም ተቀብሎ ማረለት። ❤ ከዚህም በኋላ በሹማምንቱና በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ የፈለገውን ያደረግ ዘንድ ቢፈልግ እንዲሾም ወይም እንዲሽር የሚቃወመው እንዳይኖር ደብዳቤ በመጻፍ ሥልጣንን ሰጠው። ❤ በዚህም አባት ዘመን የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደዚህ አባት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ እንዲህ ብሎ መልእክትን ላከ "ለወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ መንበርና በላዩ ለመቀመጥ ለተገባው ቅድስናህ እጅ እነሣለሁ በእኔና በመንግሥቴ ላይ በመላው ወገኖቼ በኢትዮጵያ ሰዎች ላይ ይቅርታ እንድታደርግና አባታችንን አባ ዮሐንስን እንድትልክልን እለምንሃለሁ ከሀገራችን ሰዎች ከእውነት መንገድ የወጡና የሳቱ ጳጳሳችንን አባ ዮሐንስን እኔ ሳልኖርና ሳላውቅ አባረውታልና ስለዚህም በሀገራችን ቸነፈርና ድርቅ ሁኖ ከሰዎችም ከእንስሶችም ብዙዎች አለቁ። አሁንም አባቴ ሆይ ስንፍናችንን ይቅር በል መሐሪና ይቅር ባይ ወደ ሆነ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልድልን ዘንድ በከበረች ጸሎቱም ከዚህ መከራ እንድን ዘንድ አባታችንን አባ ዮሐንስን ላክልን። አባቴ ሆይ የተባረረበትን ምክንያት እኔ አስረዳሃለሁ እኔ ልጅህ ከአባቴ ከጳጳስ አባ ዮሐንስ ቡራኬ ተቀብዬ እርሱ ከሠራዊቴ ጋር በፍቅር አሰናብቶኝ ወደ ጦር ሜዳ ሔድሁ ከጦር ሜዳም በተመለስኩ ጊዜ አባቴን አባ ዮሐንስ ጳጳሱን አጣሁት ስለርሱም በጠየቅሁ ጊዜ በቀድሞ ዘመን ዮሐንስ አ