ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
​​ማርያም ፊደል ምንጭ፦መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ ፯ ቀን ክፍል ሁለት ❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጸሎት፣ የዝማሬና የተመስጦ ሕይወት ነበራት፡፡ ዘመዷ ኤልሳቤጥን በጐበኘቻት ጊዜ ያመሰገነችውን ምስጋና ስንመለከት ይኽን እውነት ፍንተው አድርጐ ያሳየናል፡፡ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሲበተኑ የእመቤታችን ተግባር እነርሱን በጸሎቷ መርዳት ነበር፡፡ ክንፍ የሌላት ወፍና የጸሎት ሕይወት የሌለው ክርስቲያን አንድ ናቸው፡፡ ክንፍ የሌላት ወፍ መብረር አትችልም፡፡ ጠላት በቀላሉ ያጠቃታል፡፡ ክርስቲያንም ያለ ጾምና ጸሎት አምላኩን ማግኘት አይችልም፡፡ ርኵሳን መናፍስትንም ከሕይወቱ ማራቅ አይችልም፡፡ እስኪ እውነት እንነጋገር! ስንቶቻችን ነን ከጧት እስከ ማታ በመጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ተተክለን ስንውል የማይደክመን፤ የጸሎት ሕይወታችን ግን ምንም የኾነብን? መጽሐፈ ገጽ አያያዙን አልቻልንበትም ማለት አይደል? ጸሎትና እመቤታችን ግን ለቅጽበት ስንኳ ተለያይተው የማያውቁ ወዳጆች ናቸው፡፡       የእመቤታችንን የተመስጦ ሕይወት ስናነብ ደግሞ እጃችንን በአፋችን እንጭናለን፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወለደችው ጊዜ፣ ሰብአ ሰገል ከአሕዛብ አገር መጥተው በልጇ ፊት ሰግደው እጅ መንሻ ባቀረቡ ጊዜ፣ መላዕክት "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ ሃሌ ሉያ - አምላክ ለኾነ ሥጋ ከሥላሴ ጋራ ባንድነት ምስጋና ይገባዋል፤ የሰው ግዕዛኑ ይሰጠው ዘንድ በምድርም ዕርቅ ተወጠነ፡፡ አንድም የሰው ፍቅር አገብሮት አምላክ ሰው ቢኾን ሰው አምላክ ኾነ" ብለው ባመሰገኑ ጊዜ፣ መላዕክት የነገሯቸው ኖሎት (እረኞች) ሰምተው በተደነቁ ጊዜ፣ ግዑዛኑ እንስሳት ጌታን በበረቱ ከብበው በትንፋሻቸው ባሞቁት ጊዜ "ማርያምሰ ተዓቅብ ዘንተ ኵሎ ነገረ ቀትወድዮ ውስተ ልባ - እመቤታችን ግን ይኽን ነገር ታስተውለው ነበር፤ በልቡናዋም ታኖረው ነበር" እንጂ ለሰው አታወራውም ነበር፡፡ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፡- "የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበርይላል፡፡ ❤️ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃለ እግዚአብሔርን ዕለት ዕለት የምታነብ ነበረች፡፡ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም" ተብሎ እንደተጻፈ ቃለ እግዚአብሔር የዕለት ተዕለት ምግቧና መጠጧ ነበር፡፡ በሉቃ ፩፥፵፯-፶፭ በምናነበው ድንቅና ጥልቅ ምስጋናዋ ላይ የምናስተውለው ነገር ቢኖር ምን ያኽል ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደምታነብና እንደምታውቅ ነው፡፡ ማወቅ ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ትጠቀምበት ነበር፡፡ መልዐኩ መጥቶ "ትፀንሲ" ሲላት "እም አይቴ ረከብከ ዘከመዝ ብሥራት ዘእንበለ ምት እም ድንግል ፅንሰት ወዘእንበለ ዘርዕ እምድር እትወት - ምድር ያለ ዘር ታፈራ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ትፀንስ ዘንድ እንዲኽ ያለ የምሥራች ከማን አገኘኸው?" ያለችው ተሰምቶም ታይቶም የማይታወቅ ስለኾነ ነው፡፡ አንድ እንግዳ ነገር በሕይወታችን ሲመጣ እውነትነቱን የምንመዝነው በቃሉ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ሲባል ከቃሉ ባለቤት ከእግዚአብሔር ጋር መጨዋወት መነጋገር ማለት ነውና፡፡ እግዚአብሔርም ለዚያ ቃሉን ለሚያነብ ሰው ፈቃዱ ምን እንደኾነ ይገልጥለታልና፡፡ ለዚኽም ነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲኽ በማለት የሚመክረን፦ "ዕለት ዕለት ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነብ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ መጻሕፍትን የማያነቡ ብዙ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርን ካለማወቅ የተነሣ ክሕደት የተባለ ክፉ ልጅን ወልደዋልና፡፡ ኃጢአት የተባለ ክፉ ዛፍም ዳግም በተወለደው ሰውነታቸው ላይ አብቅለዋልና፡፡ ደጋግመው ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡ ግን ቢወድቁ እንኳ ተመልሰው ይነሣሉ፡፡ ልጆቼ! እናንተም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብ ቸል አትበሉ፡፡ በጣም ተቸግራችኁ ለተከታታይ ዐሥር ቀናት ብቻ ይኽን ብትለማመዱት ከዚያ በኋላ ልምድ ይኾንላችኋል፡፡ በርግጥ ይኽ ልምምድ ለንባብ ብቻ ሳይኾን ለሌላ መንፈሳዊ ሕይወታችኁም ብትጠቀሙበት መልካም ነው፡፡" ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ከቤት ረስተነው ወደ ሥራ ቦታ ብንሔድ ምን ይሰማናል? ቃሉን ስንረሳውስ?  ❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እጅግ ትሑት ነበረች፡፡ ክፍል ሦስት ይቀጥላል https://t.me/Eotcw

​​ማርያም ፊደል ምንጭ፦መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ ፯ ቀን፣ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! እንኳን ለዓለም ኹሉ ደስታን ወዳመጣችው ዕለት አደረሳችኁ፤ አደረሰን፡፡ ነሐሴ ሰባት ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትኾን ንጽሕተ ንጹሐን፥ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነው፡፡ ይኽቺን ዕለት ያልናፈቀ ትውልድ የለም፡፡ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለኾነባቸው ቅዱሳን አበው ወእማት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከእግዚአብሔር ቀጥሎ እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚኹ ነው፡፡ ሊቃውንቱ፦ ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን  ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ብለው የሚዘምሩላትም ይኽን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው። አባ ጽጌ ድንግል፤ ማኅሌተ ጽጌ ቁ.፵፬  አነሣሣችን ግን ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ጽንሰት ለመናገር አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ለዛሬ እንድንማማር የወደድኩት ከእመቤታችን ሕይወት ምን እንማራለን? እመቤታችን "ታማልዳለች፤ አታማልድም" ከሚለው ክርክር በላይ ከሕይወቷ የምንማረው ነገር የለም ወይ?" የሚል መሠረተ ሐሳብን የያዘ ትምህርታዊ ስብከት ነው፡፡  ተወዳጆች ሆይ! ክርስትና የሚኖሩት ሕይወት እንጂ የሚተርኩት ታሪክ አይደለም፡፡ ጌታችን በተራራው ስብከቱ ላይ፡- "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ኹሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም"ያለን ስለዚኹ ምክንያት ነውና ማቴ.፯፡፳፩ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ለጊዜው በዛን ወቅት ለነበሩት ምዕመናን ለፍጻሜው ግን ለእኛ ለኹላችንም ከንግግሩና ከስብከቱ ጣዕም የተነሣ ሲያጨብጨቡለትና ሲያደንቁት ዐይቶ፦ ልጆቼ! ስለምናገረው ንግግር ብታደንቁኝ ምን ያደርግልኛል? ስለ አሰባበኬስ ብታጨበጭቡልኝ ምን እጠቀማለኹ? እኔ የምጠቀመው ደግሞም የምማጸናችኁ በጽሞና እንድታደምጡኝና የምነግራችኁን ቃለ እግዚአብሔር ለማድረግ እንድትጣጣሩ ብቻ ነው፡፡ እንዲኽ ስታደርጉ ነፍሴ ስለ እናንተ ሐሴት ታደርጋለች፡፡ የምናገረውን ሳታደርጉ ስለ ንግግሬና ስለ አሰባበኬ ብቻ የምታደንቁ ከኾነ ግን ጥቅም የለውምነበር ያላቸው፡፡ ስለዚኽ ስለ እመቤታችን ከመናገር በላይ እመቤታችንን ለመምሰል እንደ ዓቅሚቲ መጣጣር የተሻለ ዋጋ አለው ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ እንዳለን ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ከመተረክ በላይ ቅዱስ ጳውሎስን ለመምሰል ልንተጋ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዐለማየኹ በአንድ ጕባኤ ላይ እንዲኽ ብለው ሲያስተምሩ አድምጫለኹ፦ ቅዱሳን አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱሱን በአንድ ወገን፤ የትርጓሜ መጻሕፍትን በአንድ ወገን፤ የገድላትና የድርሳናት መጻሕፍትንም በሌላ ወገን አድርገው በብልት በብልት ከፋፍለው ያስቀመጡልን የድኅነት መንገድን ለማስረዘም አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን እንድናነበው፤ ቢጸንብን በትርጓሜአት እንድንረዳው፤ በገድላቱና በድርሳናቱ ደግሞ እንደምን ተግባራዊ እንደሚኾን እንድንገነዘበው እኛም በዚያ ሕይወት ለመመላለስ እንድንጣጣር ነው እንጂ፡፡ እውነት ነው!!! የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በአንድምታ ትርጓሜአትና በተለያዩ ድርሳናትና ተአምራት ተከፋፍሎ መቅረቡም ለዚኹ ዓላማ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንብበው የማይጨርሷት እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ናት፡፡ ከአዕምሮ በላይ የኾነ፥ ግን ደግሞ የተፈጸመ ሕይወቷን ስናነበው የእኛንም ሕይወት ስናየው፥"የእመቤታችን አምላክ ሌላ ነው እንዴ?" ያስብላል፡፡ እስኪ ለማንኛውም ምንም እንደ ርሷ ባንኾንም የዓቅማችንን ያኽል ክርስቲያን እንኾን ዘንድ እመቤታችንን እናንብባት፤ እንማርባትም፡፡ ❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚያክል ንጹሕ ፍጥረት በሰማይም በምድርም ፈጽሞ የለም። እግዚአብሔር አብ በሰማያት ኾኖ ምሥራቁንና ምዕራቡን፣ ሰሜኑንና ደቡቡን ቢመለከት እንደ እመቤታችን ያለ ንጹሕ ፍጥረት አላገኘም፡፡ ንጽሕናዋ ልዩ ነው፡፡ "ወኢረኵሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ" ከፈጠራት ዠምሮ በምንም በምንም ከድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አልተለወጠችም (አልበደለችም) ሃይ.አበ. ዘቴዎዶጦስ ፶፫፡፳፪ ምንም ኀጢአት በሌለበት በሰማይ ለመላዕክት ያልተቻላቸውን ንጽሕናና ቅድስና፥ እመቤታችን እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በደል በበዛበት ዓለም ኾና ኑሯለች፡፡ እመቤታችን በዚኽ ምድር በቆየችባቸው ፷፬ ዓመታት አንድም ቀን አልበደለችም፡፡ እኛ ከፈቀድን በኃጢአት ሥራ በተከበበ ቦታ፣ ክፋት በተንሰራፋበት መሥሪያ ቤት ወይም ትምህርት ቤት ብንኾንም ከእግዚአብሔር ጋር የማይቻል የለም ማለት ነው፡፡ እኛ የተቸገርነው ፈቃዳችንን እንደ እመቤታችን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው፡፡ መለወጥ እንፈልጋለን፤ ፈቃዳችን ግን ከእኛ ጋር ነው፡፡ እመቤታችን ግን ፈቃዷን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ያስረከበች ብጽዕት ናት፡፡  ❤️እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጸሎት፣ የዝማሬና የተመስጦ ሕይወት ነበራት፡፡ ክፍል ሁለት ይቀጥላል

+1
#ነሐሴ_፯ #ዘነግህ መዝ ፹፮፥፩ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን እምኲሉ ተዓይኒሁ ያዕቆብ #ትርጉም መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለሐዋርያት አለቃ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሕያው እግዚብሔር ልጅ ብሎ ለመሰከረበትና ሥልጣነ ክህነት (የመንግሥተ ሰማያትን ምክፈቻ ቊልፍ) ለተቀበለበት በዓልና እግዚአብሔር ለሚወድ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለቅዱስ ናዖድ ለዕረፍት በዓል (8ሺህ ዘመን አታሳየኝ ብሎ ሲፀልዩ 8ሺህ ሳይገባ 1500ዓ.ም ያረፉት)፣ ለራኄል ልጅ ለቅዱስ ዮሴፍ ልደትና ለእስክድርያ ሃያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ጢሞቴዎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ በዚችም ቀን የሐዋርያት አለቃ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ በዓል ነው። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና። ❤ በከበረ ወንጌል እንተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊሊጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል" ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኵላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን። ❤ ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ሰለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጪ አወጣቸው። ከእርሷቸውም ኤልያስ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ። ቅዱስ ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ "ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ" አላቸው። ስዚህም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጪ አወጣቸው። ❤ እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ "ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ" በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ በእውነት ምስክ ሆነ። ❤ ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት፣ የኤጲስቆጶሳት፣ የቀሳውስትና ዲያቆናት ሹመት ተሰጠ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለሁላችን ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ጢሞቴዎስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ለእስክንድርያ ሃያ ስድስተኛ ነው። ይህም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መርጦት ተጋዳይ የነበረ አባ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ ከዐረፈ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ። ❤ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል ንጉሥ መርቅያን በእስክንድርያ አገር ሌላ መናፍቅ ሊቀ ጳጳሳት ሾሞ አባት ጢሞቴዎስን አስቀድሞ አባ የዲዮስቆሮስ ተሰዶባት ወደ ነበረች ደሴተ ጋግራ አጋዘው። መርቅያንም ከሞተ በኋላ የእስክንድርያ ሰዎች ተነስተው መርቅያን የሾመውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት አባ የዲዮስቆሮስ እንደ አዘዘ አባ ጢሞቴዎስ መልሰው ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ የመርቅያን ልጅ ሊዮን ነገሠ ያን ጊዜ አባ ጢሞቴዎስ ሁለተኛ ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ዐሥር ዓመት ኖረ ሊዮን እስከ ሞተ ድረስ ከእርሱም ኋላ ዘይኑን ነገሰ። ያን ጊዜም አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበረ ሲመቱ በታላቅ ክብር መለሰው ሕዝቡንም እያስተማራቸውና እየመከራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ኖረ። ❤ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ መንበር ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ እግዘብሔርንም አገልግሎ ነሐሴ 7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮሴፍ ዘተሠይጠ ወኮነ ገብረ ወተሞቅሐ ሠለስተ ዓመተ"። ትርጉም፦ በወንድሞቹ ተሸጦ አገልጋይ ለኾነ፤ ሦስት ዓመታት ለታሰረ ለዮሴፍ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለጴጥሮስ ሥዩም። ላዕለ ሐዋርያት ኄራን ካህናተ ኵሉ ዓለም። ሶበ ለክርስቶስ አምኖ ከመ ወልደ አምላክ ዮም። ኢከሠተ ለከ ይቤሎ ዘሥጋ ወደም። እንበለ አቡየ ዘሀሎ እምቅድም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 7። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለፅንሰቷ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ"። ትርጉም፦ ድንግል ሆይ በኃጥያት ፍትወት የተፀነሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄብ ተወለድሽ እንጂ። ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ። + + + ❤ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንሰቷን ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው። ❤ ይህም ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤልም ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደረጉ ስለትን ተሳሉ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎች ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላቸውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች። ❤ በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት አመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ በቅዱስ ኢያቄምና በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ለምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ"። መዝ86፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1፥1-17። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13 ወይም መዝ 84፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 9፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 2፥6-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የእመቤታችን የፅንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ላወጣላት ከ36 ቅዱሳት አንስት አንዷ ለሆነችው ለእናታች ለቅድስት መግደላዊት ማርያም ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነች ለከበረች ለቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ ከአባ ሲኖዳ ረድእ ከቅዱስ አባት ከአባ ዊፃ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለማርያም እንተ ቀብዐቶ ለእግዚእነ ዕረፍተ፤ በአንብዓ ዘረከበት ሥርየተ ዘአርኀወት ለኃጥኣን ዘንሥሐ ፍኖተ"። ትርጉም፦ ለኃጥኣን የንሥሐ ጎዳናን የከፈተች በዕንባዋ ይቅርታን ያገኘች፤ ጌታችንን ሽቱን የቀባችው ለኾነች ለማርያም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ቅድስት መግደላዊት ማርያም፦ ይችም ቅድስት ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች። ❤ በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም "እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል" አላቸው ። ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት "ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው" አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው። ❤ ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች። ❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በቅድስት መግደላዊት ማርያም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ከቂሳርያና ከቀጰዶቅያ አገር የሆነች ቅድስት ኢየሉጣ፦ ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብ ወረሰች ከታጋዮችንም አንዱ በግፍ ተነስቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿን ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት። ❤ ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት። በልቧም እንዲህ አለች "የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም"። ❤ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች "እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ"። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም ነሐሴ 6 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ❤ ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን። + + + ❤ በዚችም ቀን የአባ ሲኖዳ ረድእ ቅዱስ አባ ዊፃ ዐረፈ። እርሱም ከእግዚአብሔር ብዙ ምሥጢራትን የሰማ የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደ አየና እደንሰማ የጻፈ ነው። መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ እግዚአብሔርም አገልግሎ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም ዐረፈ። እግዚአብሔር በአባ ዊፃ ጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 6 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለኢየሉጣ እንበይነ ምግባር ሠናይ። በውስተ እቶን ዘእብዋእ በውዴተ ብእሲ እኩይ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ ነሐሴ 6። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን"። መዝ 44፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥10-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓሣ ከሰማይ ለሚዘንብላቸው ለመናኔ መንግሥት አቡነ ኢዮስያስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ መናኔ መንግሥት አቡነ ኢዮስያስ፡- ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጥር 6 ቀን ሲወለዱ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በመመነን በመጀመሪያ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ገቡ፡፡ አቡነ ኢዮስያስ በሐይቅ ገዳም ለ14 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኰሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አጠናቀው ተምረዋል፡፡ በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ትግራይ ደብረ በንኰል ገዳም ሄዱ፡፡ በደብረ በንኰልም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ መነኰሱ፡፡ ቆብ የተቀበሉት ግን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡ ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩአቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ወደ አዱዋ አውራጃ ዛሬ በስማቸው ወደተጠራው ገዳም ሄደው በቦታው ላይ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ገዳሙንም ከገደሙት በኋላ በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ ያፈለቁት ጠበል በፈዋሽነቱ የታወቀ ነው፡፡ በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ነሐሴ 6 ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ በየዓመቱ ነሐሴ 6 ቀን በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡ ❤ አቡነ ኢዮስያስን ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን ቢያስቸግሯቸው ጻድቁም በጸሎት ቢያመለክቱ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ የንብ መንጋ መጥቶ አረማውያኑን አንጥፍቶላቸዋል፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡ ❤ ጻድቁን እንደ ረድእ ሆኖ የሚያገለግላቸው አንበሳ ነበራቸው፡፡ ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የሰየመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከአቡነ ኢዮስያስ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ነሐሴ ፭ በቅዳሴ ጊዜ #ምንባባት ፪ ቆሮ ም ፲፪ቊ፲-፲፯ ፩ዮሐ ም፭ ቊ ፲፬-ፍጻ ግብ ሐዋ ም ፲፭ቊ ፩-፲፫ #ምስባክ መዝ ፲፯ ቊ፵፫-፵፬ ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስምዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ። #ትርጉም ከሕዝብ ክርክር አድነኝ፣ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፣ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛኛል፣ #ወንጌል የሉቃስ ወንጌል ም፲፭ቊ፩-፲፩ #ቅዳሴ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)

photo content