ሰዋስው ☘☘☘☘
Открыть в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Больше1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
1 161
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጳጒሜን ቅዱስ ሩፋኤል
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️
❣❣❣ሥርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCWW
❣መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለመታክፍቲክሙ መሠረተ ዓለም እለ ፆሩ: ኖትያተ ኖኅ ሥላሴ ወዕፀወ ዐባይ ሐመሩ: ዲበ መንበርክሙ ሰብአ ሶበ አምላክ ነጸሩ: ኪሩቤል ወሱራፌል ታህተ እገሪሁ ገረሩ: እስመ ለሊሁ አዘዘ ወእሉ ተፈጥሩ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
እሉ ኪሩቤል ወሱራፌል የዐርጉ ሎቱ ስብሐተ እንዘ ይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ነግሥ
ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል: ሱራፌል ወኪሩቤል ዑራኤል ወሩፋኤል ሱርያል ወፋኑኤል: አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል: ሊቃናተ ነድ ዘሰማያዊት ማኅፈድ: በእንተ በግዑ ዕቀብዋ ለዛቲ አፀድ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ለዛቲ አፀድ በእንተ በግዑ ዕቀብዋ ለዛቲ አፀድ/፪/
ሊቃናተ ነድ ሊቃናተ ነድ ነድ ሊቃናተ ነድ/፪/
@EOTCWW
❣ዚቅ
መላእክተ ምሕረት እለ ድልዋን ለሣህል: ሰአሉ አስተምሕሩ ለነ እስመ በጸሎተ ትንብልናክሙ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለአእናፊከ መዓዛ አርያም እለ ተመልዑ: ሱራፌል ምስሌከ አመ ይሠውዑ: ሚካኤል አንተ ለያዕቆብ ኖላዌ ዘርዑ: በሎሙ ለአብያጺከ ለሐውፆ አርክየ ንዑ: እስመ በአሐዱ ፍቁር ይሰሐብ ካልዑ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
እኲት ወስቡሕ: ዕቀብ ኩልነ ኖላዊ ትጉህ: ሐውፀነ በምህረት ብዙኅ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ኖላዊ ትጉህ ኖላዊ ትጉህ/፪/
ሐውፀነ በምህረት ብዙኅ/፬/
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
መላእክት በልሳነ እሳት ይሴብሑኪ: መላእክት በአክናፈ ብርሃን ይኬልሉኪ: ማርያም እምነ: ወእሙ ለእግዚእነ: መላእክት በቀለመ ወርቅ ይጽሕፉ ውዳሴኪ: እስከ ዳግም ምጽአቱ ለበኲርኪ።
@EOTCWW
❣መልክአ ሩፋኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ተጸውዖ ዘቀደመ: በአፈ አምላክ አዳም እንበለ ይሰመይ ስመ: ሩፋኤል ምልዓኒ ወወስከኒ ዳግመ: መንፈስ ቅዱሳዌ አዕምሮ እንተ ይፈሪ ሰላመ: ወአምላካዌ ጥበበ ዘየአዱ አቅመ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አእምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ: ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ሀበነ እግዚኦ አዕምሮ አዕይንተ አእምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ/፪/
ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ/፪/
@EOTCWW
❣መልክአ ሩፋኤል
ሰላም ለቃልከ ዘይደምፅ እመብረቅ:
ለእስትንፋስከኒ እስትንፋሰ መንፈስ ረቂቅ: ሩፋኤል ሐዋርያ ወመልአከ ጽድቅ: ይጸንሑከ እግዚኦ ዕሡራነ በዓል በጻሕቅ: ነዓ ነዓ እምሕላዌከ ምጡቅ ውስተ ቤትከ ዛቲ ክርስቶሳዊት ምርፋቅ፡፡
@EOTCWW
❣አመላለስ
ሩፋኤል ሐዋርያ/፪/
ወመልአከ ጽድቅ/፪/
@EOTCWW
❣ዚቅ
ሩፋኤል ግሩም: በመንፈስ ቅዱስ ሕቱም: መዓዛ ቅዳሴከ ጥዑም: ከመ ጽጌ ገዳም: ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም: በበዓልከ ባርከነ ዮም።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ነዐ ነዐ ማዕከሌነ ቁም/፪/
በበዓልከ ባርከነ ዮም/፪/
@EOTCWW
❣መልክዓ ሩፋኤል
ሰላም ለመዛርዒከ ለአህጒሎ አርዌ ዘጸንዓ: ለኲርናዕከኒ እንበለ ተፈልጦ ዘጸብአ: ሩፋኤል መዋኢ እንተ ትትአጸፍ መዊአ: እምደዌ ኃጢአት ትትፈወስ አባልየ እምርጢንከ ቅብዓ: ለዓይነ ጦቢት ከመ ፈወስኮ ከዊነከ ሰብአ።
@EOTCWW
❣ዚቅ
መልአከ ፍሥሐ ዘይትአጸፍ ነደ: ኀበ ጦብያ ሩፋኤል ወረደ: እምከርሠ ዓሣ ነሢዖ ስብሐ ዘምስለ ዓሣ ዘምስለ ሐሞት ከብደ: አዕይንተ ጦቢት ከሠተ ወአጋንንተ ሰደደ።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣መልክአ ሩፋኤል
ሰላም ለገበዋቲከ ስርግዋነ ምንትው አክናፍ: ለከርሥከሂ ሕሩመ ሲሲት ዘዘልፍ: ሩፋኤል አሐዱ ሊቀ አዕላፍ: አብሥረኒ ነገረ ሣህል ለወልደ ላሜህ ፍልሱፍ: ከመ ሕጸተ ማይ አብሠረቶ የዋሂት ዖፍ፡፡
@EOTCWW
❣አመላለስ
ሩፋኤል አሐዱ/፪/
ሊቀ አዕላፍ/፪/
@EOTCWW
❣ዚቅ
ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ: ሩፋኤል ስሙ: ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
"ሐመልማለ ወርቅ"/፪/ ልብሱ ዘመብረቅ/፪/
ዓይኑ ዘርግብ/፬/
@EOTCWW
❣መልክአ ሩፋኤል
ተወኪፈከ እግዚኦ ዘንተ አምኃየ: ዘአቅረብኩ ለከ መጠነ ክሂል ዘብየ: ሩፋኤል ባዕል እንተ ታብዕል ነዳየ: ዕስየኒ ለፍቁርከ ዕሤተ ሠናየ: ዘዕዝነ መዋቲ ኢሰምዐ ወዘዐይን ኢርእየ፡፡
@EOTCWW
❣ዚቅ
ወሰሚአ ሀገር ከልሃት ሎቱ ወትቤ ተወከፈኒ አንተ መልአክ ቅዱስ ገብረ እግዚአብሔር።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር/፪/
ገብረ እግዚአብሔር ተወከፈኒ አንተ መልአክ/፪/
@EOTCWW
❣❣አንገርጋሪ
ሃሌ ሉያ
ይሰግዱ በብረኪሆሙ፡ ወያሌዕሉ ኅሊናሆሙ፡ በጥንቃቄ ወበኃሢሥ፡ ኀበ እግዚኦሙ ንጉሥ፡ ቀዋምያን ለነፍሳት፡ እሙንቱ ሊቃናት፡ ዑራኤል ወሩፋኤል፡ ይትፌነዉ ለሣህል: እምኀበ ልዑል።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት ዑራኤል ወሩፋኤል/፪/
"ይትፌነዉ ለሣህል"/፪/እምኀበ ልዑል/፪/
@EOTCWW
❣እስመ ለዓለም
ዑራኤል ወሩፋኤል: አስተምሕሩ ለነ በስኢል: ወበትህትና ኀበ ውእቱ ነበልባለ ኃይል አመ ይመጽእ በክብር: ምስለ ብዙኅ ስብሐት ወኃይል: ንርከብ ድኅነተ በዘአሜሃ ቀመር: በዐውዱ ፍጹም ዘኢይትነገር፣ ንዕርር ፍሥሐ በሐዳስ ምድር።
@EOTCWW
❣አመላለስ፦
በዐውዱ ፍጹም ዘኢይትነገር፣
ንዕርር ፍሥሐ በሐዳስ ምድር
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ዑራኤል ወሩፋኤል/፬/
አስተምሕሩ ለነ በስኢል ወበትህትና ኀበ ውእቱ ነበልባል/፪/
https://t.me/Eotcw
@EOTCWW
# Join & share
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
አመ ሠሉሱ ለጳጉሜን በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል ሥርዓተ ዋዜማ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሃሌ ሉያ ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ፤ ሱራፌል በግርማሆሙ፤ ወኪሩቤል በውዳሴሆሙ፤ ኪያከ አበ ይሴብሑ፤ ኪያከ ረዳዔ ኪያከ መጋቤ፤ ስቡሕ በውስተ ቅዱሳን
@EOTCWW
❄️አመላለስ፦
ኪያከ ረዳዔ ኪያከ መጋቤ/2/
ስቡዕ በውስተ ቅዱሳን/4/
@EOTCWW
@EOTCWW
ለእግዚአብሔር ምድር በምላዕ፦
ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ ትጉሃን እለ ኢይነውሙ
@EOTCWW
@EOTCWW
❄️እግዚአብሔር ነግሰ፦
ይቤሎ ለጦቢያ አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሀዱ እም ተስአቱ ሊቃነ መላእክት ዘተፈኖኩ ኀበ ጦቢት
@EOTCWW
@EOTCWW
❄️ይትባረክ፦
ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ ኪያከ አበ ይሴብሑ
@EOTCWW
@EOTCWW
❄️ሰለስት፦
ትጉሃን እለ ኢይነውሙ መላእክት በበስርአቶሙ፤ ሱራፌል በግርማሆሙ፤ ወኪሩቤል በውዳሴሆሙ፤ ኪያከ አበ ይሴብሑ
@EOTCWW
@EOTCWW
❄️ሰላም፦
በ 4 ሃሌታ-
ጥበበ ኩሉ ኃይል ለኩሉ ወብዙኃ ሣህል ንስእል ወናስተበቁዕ ኪያከ መጋቤ ኩሉ ከመ ተሀበነ ተምኔተነ በሰላም ንፈጽም ንብረተነ ንጉሠ ሠራዊተ ሰማያት ዘዲቤሆሙ የዓርፍ በበማኅበሮሙ ኪያከ ይሴብሑ ስብሐት ለከ የዓርጉ
@EOTCWW
@EOTCWW
❄️አመላለስ፦
በበማኅበሮሙ ኪያከ ይሴብሑ/2/
ስብሐት ለከ የዓርጉ/4/
@EOTCWW
# Join & share
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጳጒሜን ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ለጻፈለት ለከበረ ለሐዋርያው ለቅዱስ ቲቶ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ፦ የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ቀርጤስ ከሚባል አገር ነው። እርሱም ለዮናናውያን ወገን ለሆነ ለአገረ ገዥው እኅት ልጅዋ ነው። ከታናሽነቱም የዮናናውያንን ትምህርትና ፍልስፍና ተምሮ እጅግ አዋቂ ሆነ በጠባዩም ቅን ሥራው ያማረ ለድኆችና ለችግረኞች መራራት የሚወድ ነው። ከሌሊቶችም በአንዲቱ "ቲቶ ሆይ ስለ ነፍስህ ድህነት ተጋደል ይህ ዓለም አይጠቅምህምና" የሚለውን በሕልሙ አየ። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ደነገጠ ምን እንደሚሠራም አላወቀም።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ሰዎችም ተአምራቱን እርስበርሳቸው ተነጋገሩ የአክራጥስ መኰንንም ሰምቶ አደነቀ ዕውነት እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ወይም የሥራይ እንደሆነ ሊያውቅ ሽቶ የሚልከው ብልህ ሰው ፈለገ የእኅቱንም ልጅ ቲቶንን መረጠው ከእርሱ የሚሻል የለምና። ሲልከውም ታላቅና ጥልቅ የሆነ ምርመራ እንዲመረምር አዘዘው።
❤ ቲቶም ከይሁዳ ምድር በደረሰ ጊዜ የመድኃኒታችንን ድንቆች የሆኑ ተአምራቶቹን አየ ሕይወትነት ያላቸው ትምህርቶቹንም ሰማ። ከዮናናውያንም በትምህርታቸውና በሥራቸው መካከል ታላቅ የሆነ መራራቅን አግኝቶ የዮናናውያን ሃይማኖታቸው የቀናች እንዳልሆነች ለይቶ ዐወቀ።
❤ ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ አመነ፤ ደቀ መዝሙሩም ሁኖ ተከተለው። ወደ እናቱ ወንድም ወደ አገረ ገዥውም መልእክትን ላከ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምረውና የሚሠራው ዕውነት እንደሆነ ነገረው።
❤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ውስጥ የተቆጠረ አደረገው ከዕርገቱም በኋላ ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀብሎ ከእሳቸው ጋር በሀገሮች ሁሉ ዙሮ አስተማረ። ጌታችንም ጳውሎስን ጠርቶ ሐዋርያው በአደረገው ጊዜ ያን ጊዜ ሐዋርያ ጳውሎስን ተከተለው በብዙ አገሮችም ወንጌልን ሰበከ።
የከበረ ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜ ከተማ ምስክር ሆኖ ከሞተ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ወደ ሀገረ አክራጥስ ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በዙሪያቸው ላሉ አገሮችም እንዲሁ አደረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ጳጒሜን 2 ቀን ሔደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ቲቶ መስተሳልም። ለእከ ጳውሎስ ዘኮንከ እንበለ ድካም። ከመ ገሠጸከ በቃል ወይቤለከ በሕልም። ተጋደል በእንተ ነፍስከ በገድለ ሃይማኖት ፍጹም። ኢይበቊዓከ ዝንቱ ኃላፊ ዓለም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጳጒሜን 2።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር። ምክር ሠናይት ለኵሉ ዘይገብራ። ወስብሐቲሁኒ ይነብር ለዓለም"። መዝ 110፥10። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥1-11፣ 2ኛ ጴጥ 3፥7-14 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-36። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ቲቶ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የተባረከ የጳጒሜን ወር ባተ።
❤ ጳጒሜን ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን ለጾመ ዮዲት (የፈቃድ ጾም) በሰላም አደረሰን።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የተባረከ የጳጒሜን ወር ባተ።
❤ ጳጒሜን ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን ለወንጌላዊው ለቅዱስ ዮሐንስ ረድእ ለሐዋርያውና ለሰማዕቱ ለከበረ ዑቲኮስ ለዕረፍት በዓል፣ ለአባ ሖር ወንድም ለሰማዕቱ ለቀሲስ ቅዱስ ብሶይ ለዕረፍት በዓል አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ከአባ ጳኩሚስና ከአባ ሰራብዮን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚች ቀን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድምህን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ማግባት የለብህም ብሎ ይገስጸው ስለነበር በሳምንቱ በልደቱ ቀን መስከረም 2 እስኪገለው በዛሬው ዕለት ወደ እስር ቤት ያስገባበት ነው።
+ + +
❤ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ረድእ ቅዱስ ዑቲኮስ፦ ይህም ቅዱስ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስን ሲያገለግለውና ሲታዘዘው ኖረ። ከዚያም ከሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ጋራ ሔደ እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲሰብክ አዘዘው በአረማውያንና በዮናናውያንም መካከል ሰበከ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ወደማወቅ ብዙዎችን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው።
❤ የጣዖታት ቤቶችን አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። ከሀድያንም ብዙ መከራ ደረሰበት መታሠርና ብዙ ቀኖች ግርፋቶችን በመቀበል የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ እሥር ቤት ከምግብ ጋር መጥቶ ይመግበዋል።
❤ ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጣሉት እሳቱም ከቶ አልነካውም ሁለተኛም ለአንበሶች ጣሉት እነርሱም እንደ በጎች ሆኑለት።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ሔደ ሲሔድም የእግዚአብሔር መልአክ ይመራውና ያጸናናው ነበር ተጋድሎውንም ፈጽሞ በበጎ ሽምግልና ጳጉሜን 1 ቀን ወደ እግዚአብሔር ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ዑቱኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የአባ ሖር ወንድም ቀሲስ ቅዱስ ብሶይ፦ ይህም ቅዱስ ከአንጾኪያ አገር ክብር ካላቸው ወገኖች ውስጥ ነው ስለ ዕውቀቱና ስለ ሃይማኖቱ ጽናት ቅስና ተሾመ።
❤ ወንድሙ አባ ሖርና እናቱ ወደ ግብጽ አገር ሒደው በሰማዕትነት ከሞቱ በኋላ እርሱም ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሥጋቸውን ያይ ዘንድ ሔደ። ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጠ ከሦስት እንጀራና ከሚመረጐዛት ከአንዲት የሰኔል በትር በቀር ምንም አልያዘም ነበር።
❤ ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰ ጊዜ የዘመዶቹ በድን ወዳለበት ሰዎች መርተው አደረሱት የእናቱንና የወንድሙንም ሥጋ በአየ ጊዜ ከእርሳቸው ስለ መለየቱ መሪር ልቅሶን አለቀሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ መነኰንኑ ሒዶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ለመኰንኑም የአባ ሖር ወንድም እንደሆነ ነገሩት መኰንኑም ታላቅ የደንጊያ ምሰሶ በሆዱ ላይ እንዲአቆሙበት አዘዘ ይህንንም በአደረጉበት ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ሥጋውን ከወንድሙና ከእናቱ ሥጋ ደግሞ ቊጥራቸው ሰማንያ ስምንት ከሆነ ከሌሎች ሰማዕታት ሥጋ ጋር በአንድነት ያቃጥሉ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ወደ እሳት በጨመሩአቸውም ጊዜ ከቶ እሳቱ አልነካቸውም።
❤ ምዕመናን ሰዎችም መጥተው የከበሩ የአባ ሖርና የወንድሙ የአባ ብሶይን የእናታቸውንም ሥጋ ወሰዱ። አገርዋ ዲብቅያ የሚባል የቅድስት ዳሞንንም ሥጋ አገሩ በረሞን ከሚባል የቅዱስ ቢማኮስም ሥጋ ጡልያ ከሚባል አገር የመጣ የውርሱኑፋን ሥጋም አብስላሲ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሷቸው በመርከብ ጫኗቸው። የስደቱ ወራት እስከሚፈጸም አክብረው ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው።
❤ ከዚህም በኋላ አብያተ ክርስቲያን ተሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጣቸው አኖሩ ከእርሳቸውም ተአምራት ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆኑ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳግሜን 1 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለዑቲኮስ ዘተሰምየ ሱታፎ። ለወንጌላዊ ዮሐንስ ለንጹሐ መላእክት ዘተዐጽፎ። መኰንን ዕልው አመ ውስተ እሳት ገደፎ። ካዕበኒ እምህየ ለአናብስት አኅለፎ። በአናብስት ስእኑ ይግሥሥዎ ወእሳት ይልክፎ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጳጒሜን 1።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ጽድቀ ወምጽዋተ ያበድር እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ይሁብ ክብረ ወሞገሰ። እግዚአብሔር ኢያስተፄንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየዋሃት"። መዝ 83፥11። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 1፥12-25፣ 1ኛ ዮሐ 5፥1-6 እና የሐዋ ሥራ 18፥21-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 14፥1-7። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም፡ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊቷ ጻድቅ ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት በማሰብ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) ትመመገብ ለነበረች ለታላቋ እናት ለቅድስት ዜና ማርያም ለዕለፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም፦ ከአባቷ ከቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ከእናቷ ከቅድስት አመተ ማርያም በ11 መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30 ቀን የተወለደች ሲሆን ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንፅህ ድንግልና በምድረ ሂንፍራንስ ጣራ ገዳም አካባቢ በሚገኘው በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25 ዓመት በጾም በፀሎት ምንም አይነት የላመ የጣፈጠ እህል ሳትቀምስ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋህዳ) በመዘፍዘፍ ከ3 ቀን በኃላ በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ላይ የቀመሰውን መራራ ሐሞትን በማሰብ ሙሉ ሕይወቶን እየተመገበች ታላቅ ተጋድሎዋን ፈፅማለች፡፡ ከዚህ የተነሳ ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜ ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ ተብሎ እስከ አሁን ድረስ በስሞ እየተጠራ ይገኛል፡፡
❤ ከአቡነ እድርያስ ዋሻ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ተነስተን ስንጓዝ አዲስ ዘመን ከተማ በስተቀኝ በኩል ተገንጥለን 15 ኪሜ ያክል የጥርጊያ መንገድ እንደተጓዝን በስሟ የተሰየመውን ደሪጣ ጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ገዳም ላይ ቀሪ ሕይወቶን ምንም አይነት ዋሻ ባልነበረበት በከፍተኛ ተራራ ላይ እጅግ አስቸጋሪ ቀዝቃዛ አየር ባለበት ብርዱን፣ ፀሐዩን፣ ቁሩን፣ ረኃቡንና ጥሙን በመቋቋም ራቁቶን በመሆን መራራ ምግቦችን አዋህዳ በመመገብ በጾም በፀሎት በመትጋት አስቸጋሪ የሆነውን ተጋድሎዋን በመፈፀም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን በታላቅ ክብር አርፋለች፡፡
❤ በዚህም ወቅት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አላፋት ቅዱሳ መላዕክት ጋር እንዲሁም ከሐዋርያት ፣ ከሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከደናግል ጋር በመሆን ከሰማይ በመውረድ በታላቅ ክብር ዕረፍቷን አክብሮላታል ታላቅ ኪዳንም ገብቶላታል፡፡
❤ በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ላይ ወይንም በአሁኑ ሰዓት መቃብሯ በሚገኝበት ዋሻ ቤተመቅደስ አካባቢ በተጋድሎዋ ጊዜ ራቁቷን በሆነች ሰዓት መላ ገላዋን የሸፈነላት ፀጉር በእየ ዛፎቹ ላይ እስከ አሁን ድረስ አለ፡፡ ይህም የጸጉር አምሳያ ከገዳሙ በመውሰድ ብዙ ሰዎች በቤታቸው በመታጠን ከአስም እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች እየተፈወሱና እየዳኑ ሲሆን ታላላቅ ታምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡
❤ በዚህ ገዳም ከሌሎች ገዳማት ለየት የሚያደርገው ታሪክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ በመውረድ ራሱ የባረከው ልዩ ታሪክ ያለው ጠበል የሚገኝ ሲሆን ይህም ጠበል በቦታው ላይ ሆኖ የተጠመቀ ፣ የጠጣ ፣ አልያም በአለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀመ እስከ አሁን ድረስ መካን የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ልጅ የሚያገኙ ከመሆናቸው ባሻገር ከማንኛውም ከተለያዩ በሽታዎች በመፈወስ ታላላቅ ታምራትን እየሰራ ይገኛል፡፡
❤ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ላሊበላ በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሰረት ወደዚሁ ታላቅ ስፍራ በመምጣት የጻድቋ ማረፈያ መታሰቢያ ዋሻ ቤተ መቅደስ በመፈልፈል የሰራላት ሲሆን በመቀጠል አፄ ይስሐቅ በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህን ገዳም በስሟ በመገደም በዚሁ ዋሻ ውስጥም የጻድቋ የቅድስት ዜና ማርያም መቃብሯ እንዲሁም የመታሰቢያዋ ፅላት የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢው ያሉት ሕዝበ ክርስትያን ከካህናት ጋር በመሆን ሥርዓተ አምልኮ በመፈፀም እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡
❤ ይህ ዋሻም አስቀድሞ ሦስቱ ቅዱሳን ማለትም አቡነ እንድርያስ ዘጣራ ገዳም ፣አቡነ ተክለኃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፣ ጻድቋ ቅድስት ዜናማርያም ዘደሪጣ ውስጥ ለውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በፀጋ እግዚአብሔር ይገናኙበት የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓትም እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ይመላለሱበታል፡፡
❤ ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ስፍራ ተነስቶ የጻድቋ ደጃን የረገጠ ለ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ የሚል ቃል ኪዳን ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም ተሰቶታል። ከእናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ማኅበረ ዜማ ማርያም ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት የተወረደ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
