ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
ገደላቸው፡፡ የሮም ንጉሥ ሕርቃልም የፋርሱ ንጉሥ ክስራ ያደረገውን በሰማ ጊዜ ሠራዊቱን ሰብስቦ መጥቶ ንጉሥ ክስራን ከነሠራዊቱ ሀገሩንም ጭምር አጠፋቸው፡፡ ❤ የዚህ አባት እንድራኒቆስ ገድሉ ግን እጅግ ያማረ ነበር እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር8 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ከዓመተ ሰማዕታት ሦስት መቶ አርባ ሰባት እስላሞች በግብጽ ከመንገሣቸው በፊት በመንበረ ሢመቱ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር8 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ በእደ ብንያሚን ዘኮነ። የማነ አምላክ ምስሌሁ እንዘ ይቀብዕ ሜሮነ። ውሳጤ መቅደስከ ዛቲ መቃርዮስ አቡነ። ኢይባእ በትእግት ኪሩብ ወሰነ። ዘቦ ትዕቢተ ወዘቦ ህልያነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥር 8። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ። ወረከብናሁ ውስተ ኦመ ገዳም። ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር"። መዝ131፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥19-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም ነቢዩ የቅዱስ ሚኪያስ የመታሰቢያ በዓልና ዕለተ ሰንበት። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት ለሆነው ለአንዱ ለቅዱስ ሚክያስ ለመታሰቢያ በዓል፣ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በከበረና በተመሰገነ በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት በአባ ብንያሚን እጅ ለከበረችበትና ለእስክድርያ ሠላሳ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ብንያሚን ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ፦ከእስክንድርያ ሠላሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ ከአባ እንድራኒቆስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ንጉሥኪ ጽዮን ለትውልደ ትውልደ ትውድ መጽአ ኀቤነ ዘኪያሁ ይሴፈው ሰማያት ወምድር ዕበይ ለነገሥት ብርሃኖሙ ለእለ ይፀመድዎ አክሊለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት ዐምዳ ወድዳ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቤተ ልሔም ተወልደ ወበናዝሬት ተሐፅነ፣ ኢተዘኪሮ አበሳ አኃደገነ ፍሥሓ ኮነ ዘውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ። ትርጉም፦ ጽዮን ሆይ ንጉሥሽ ለልጅሽ ልጅ ወደ እኛ መጣ፣ ሰማያትና ምድር እርሱን ተስፋ የሚያደርጉ፣ የነገሥታት ልዕልና ከእርሱ ጋር ለሚጠመዱ ብርሃናቸው የሆነ የሰማዕታት አክሊላቸው የካህናት ሹመታቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምዷና መሠረቷ የሆነ ክርስቶስ በቤተ ልሔም ተወለደ በናዝሬት አደገ። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሚክያስ፦ የዚህም ነቢይ ከታናሽነቱ ጀምሮ አካሔዱ መልካም ሆነ ስለ ሥራው ማማርና ስለ ጽድቁ ሕዝቡ ሁሉ ያደንቁታል ያከበሩታል ሚክያስም ይሉታል ትርጓሜውም መልአክ ነው ማለት መልኩ እጅግ ያማረ ነውና የሚናገረውም ትንቢት እንደተናገረው ይሆናል የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጾለት ያነጋገረው ነበር ሕዝቡ ግን ያንን መልአክ እያዩትም ድምፁን ግን ይሰማሉ ከእርሳቸውም ያደላቸው የሚያዩት አሉ በመሳፍንት መጽሐፍ እንደተጻፈ። በጎልማሳነቱም አርፎ በአባቶቹ ቦታ ተቀበረ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሆን አሜን። + + + ❤ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በአባ ብንያሚን እጅ መክበር፦ ከዚህም በኋላ መቆቅዝ ከሚባል ዐላዊ መለካዊ በአባ ብንያሚን ላይ መከራ ደረሰበት አባ ቢንያሚንም ሸሽቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ ዐሥር ዓመትም እስኪፈጸም በዚያ ኖረ ከዚህም በኋላ ያን ዓላዊ መቆቅዝን እግዚአብሔር አጠፋው ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ጸጥታ ሰላም ሁኖ አባ ቢንያሚንም ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ የአስቆጥስ ገዳም ሽማግሎችና መምህራን ወደርሱ መጡ ወደርሳቸውም ሒዶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እንዲአከብርላቸው ለመኑት እርሷም የከበረ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ናት። በታላቅ ደስታም ተነሥቶ ከእርሳቸው ጋር ሔደ የቤተ ክርስቲያኒቱንም መባረኪያ ጸሎት ጀመረ። ❤ መሠዊያውንም በሜሮን ሊቀባ በጀመረ ጊዜ የክብር ባለቤት የጌታችን እጅ ከእርሱ ጋር ስትቀባ አየ ከታላቅ ፍርሀት የተነሣ በግምባሩ ፍግም ብሎ ወደቀ። ከኪሩቤልም አንዱ አነሣው እንዲህም አለው "ተነሣ አትፍራ ልዩ የሆነውን ሥርዓት ለዚህ ቦታ ጻፍ ይህ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚፈጸምበት ነውና ማንም በትዕቢት ወይም መማለጃ በመስጠት እንዳይገባ በውስጡ በሚገባ ከሚሾም በቀር የሚደፍርና በውስጡ ከንቱ ነገርን የሚናገር አይኑር የእግዚአብሔር መመስገኛ ቤቱ ነውና ይህም ሥርዓት በዚህ ቦታ እስከ ዘላለሙ የተሠራ ይሆናል። እነሆ ዘመን ይመጣል የአባቶችንም ትእዛዝና ሥርዓት ያፈርሳሉ ይህም የከበረ ቦታ እንደ መሣለቂያ ቦታ ይሆናል"። ❤ አባ ብንያሚንም "ይህች የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ናት" አለ ይህንንም ከኪሩብ ጋር ሲነናገር ከቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምሥራቅ ተመለከተ አንድ መልኩ የሚያምር ጽሕሙ የረዘመ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት የሚያበራ ሽማግሌ አየ። ለአባ ብንያሚንም ደስ አሰኘውና በልቡ እንዲህ አለ "ከኤጲሰሰቆጶሳት አንዱ ቢሞት በርሱ ፈንታ ይህን ሽማግሌ እሾመዋለሁ"። ኪሩብም እንዲህ አለው "ብንያሚን ሆይ ይህን አባት መቃርዮስን ኤጲስቆጵስን ታደርገዋለህ?"። እርሱ "የሊቃነ ጳጳሳት አባታቸው ነውና ዛሬ ከልጆቹ ጋር ደስ ይለው ዘንድ መጥቷልና ከልጆቹም መንፈሳዊ ሹመት የሚሾም ወይም አለቃ የሚሆን አይታጣም ከገዳማቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ አይታጣም"። ❤ አባ ብንያሚንም "ልጆቹ ብፁዓን ናቸው" አለ ኪሩብም እንዲህ አለ "ብፁዓንስ የሚባሉ ትእዛዞቹን ጠብቀው ፍለጋውን ቢከተሉ እነርሱ ከእርሱ ጋር አሁን በአለበት ክብር ውስጥ ይሆናሉ ትእዛዞቹን ቢተላለፋ ግን ከእርሱ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖራቸውም"። አባ ብንያሚንም ኪሩብን እንዲህ አለው "ጌታዬ ሆይ በዚህ ነገር በልጆቼ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አትናገር ነገር ግን በሰብል ውስጥ አንዲት ቅንጣት የተረፈች እንደሆነ እግዚአብሔር በውስጥዋ በረከቱን ያደርጋል። እንዲሁም የፍቅር ቅንጣት በውስጣቸው የተገኘ እንደሆነ እግዚአብሔር ከመንግሥቱ እንደማያርቃቸው እኔ አምናለሁ"። ❤ ከአረጋዊው አባ መቃርስ ርኅራኄ የተነሣ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን አደነቀ መልአኩ ኪሩብ እንዳዘዘውም ያንን ሥርዓት ጽፎ ለዘወትር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። ዕድሜው በደረሰ ጊዜ ዕረፍቱ በዚች ቀን ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እንዲሁም ሆነለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቢንያሚን በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ እንድራኒቆስ፡- ይኽም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሰባተኛ የሆነ ነው። ይህ አባት የሚራራ አዋቂ ሆነ እርሱ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ተምሮአልና እርሱም ለእስክንድር ገዥ የአጎቱ ልጅ ነውና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሊቃነጳጳሳት እንደሚያደርጉት በገዳም አልኖረም፤ ይልቁንም ስለቤቱና ስለክብሩ ታላቅነት በእስክንድርያ ባለው ቤቱ የሚኖር ሆነ፡፡ እርሱም የተሾመው ሕርቃል በነገሠ በ10 ዓመት ከእስክንድር ዘመነ መንግሥት በ933 ዓመት ነው፡፡ በሹመቱም ወራት ፀሐይን የሚያመልክ የፋርስ ንጉሥ ክስራ ተነሣና የሶርያንና የፍልስጤምን ከተሞች ወርሮ ዘረፋቸው፡፡ ወደ ግብጽም መጥቶ እስክንድድርያ ከተማ ደረሰ፡፡ በዙሪዋ በመነኮሳት የተሞሉ ሰባት መቶ ገዳማት ነበሩ፡፡ እነርሱም ገንዘብ ያላቸው በተድላ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሰጥቶት ገዳማቱን አፈረሰ፡፡ እነርሱንም ሸሽተው ካመለጡት በቀር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ሁሉ ማረከ፡፡ ❤ የእስክንድርያ ሰዎችም ንጉሥ ክስራ ያደረገውን ባዩ ጊዜ የከተማውን በር ከፈቱለት፡፡ እርሱም "ይህችን አገር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ አታፍርሳት፣ በውስጧ ያሉትን ብርቱዎች ግደላቸው-ዐመፀኞች ናቸውና" እንደሚለው በሕልሙ አየ፡፡ በዚህም ጊዜ የሀገሩን ንጉሥ ይዞ ካሠረው በኋላ ለሀገሩ ሰዎች "በጦር ሠራዊት አደራጃቸዋለሁና ከ18 ዓመት ጀምሮ ያሉትን ብርታት ያላቸውንም ሁሉ ሰበስቡልኝ፣ ለእያንዳንዳቸው ደመወዛቸውን 20 የወርቅ ዲናር እከፍላለሁ" አላቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ እውነት ወርቅ የሚቀበሉ መስሏቸው 8 ሺህ ብርቱዎችን ቆጥረውና መዝግበው በሰጡት ጊዜ ንጉሡ ክስራ ሁሉንም በሰይፍ ገደላቸው፡፡ ወደላይኛው ግብጽ በመሄድም ኒቅዮስ ደርሶ ሰባት መቶ በሥራቸው ክፉ የሆኑ መነኮሳትን በሰይፍ

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ንስግድ ለአብ ንስግድ ለወልድ ንስግድ ለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋሕድ ለዘአሐዱ ሠለስቱ ወለዘሠለስቱ አሐዱ በአሐዱ ስግደት"። ትርጉም፦ በአንድነት በሦስነት ላለ ለአብ እንስገድ፤ ለወልድ እንስገድ፤ ለመንፈስ ቅዱስም እንስገድ፤ አንድነት ላለው ሦስትነት፤ ሦስትነት ላለው አንድነት አንድ ስግደት እንስገድ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

photo content
+1

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ለቅድስት ሥላሴ የሰናዖር (የባቢሎንን) ቋንቋቸው ለደባለቁበትና የሰሩት ግንብ ላፈረሱበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፍ11፥1-9)፣ ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀት ላጠመቀው ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት ለአቡነ ሶል ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለመታሰቢያው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰሎሞን፣ ከጎርጎርዮስ፣ ከማርቆስ ከአትያኖስ፣ ከሉያ፣ ከመልይን፣ ከሱስዮስና ከማርትይ እግዚአብሔር አምላክ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ኵሉ ይሰግድ ለሥላሴ ወይትቀነይ ኵሉ ለመንግሥተ ሥላሴ እስመ ኮነ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ወበዓይኑ ይኔጽር ቀላያተ"። ትርጉም፦ ሁሉ ለሥላሴ ይስገድ፤ ለሥላሴም መንግሥት ይገዛ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በዐይኑ ጥልቆችን የሚያይ ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ አባ ሶል ጴጥሮስ፦ ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከዐረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ አገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሊኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ሠራላቸው። ❤ የዚህም አባት ሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጒሞ ያስገነዘባቸው። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ። እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። ❤ በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሶል ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር7 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለኤፍሬም ደራሲ ዘጽሩይ ልሳኑ፤ አብያተ ክርስቲያናት ይሰርገዉ በድርሳኑ"። ትርጉም፦ አብያተ ክርስቲያናት በድርሳኑ ያጌጡ ዘንድ አንደበቱ የጠራና ደራሲ ለኾነ ለኤፍሬም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለከ ጴጥሮስ ሶል። መጥምቀ ቈስጠንጢኖስ ንጉሥ ከሣቴ መስቀል። መዋዕለ ዕብሬትከ ኮነ ዕብሬተ ርትዕ ወሣህል። እስመ ተቀጥቀጠ ዳጎል ወወድቀ ቤል። በከመ ቀዳሜ ኢሳይያስ ይብል"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥር7። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ። ወበቃለ ለእግዚአብሔር ፀንዐ ሰማያት። ወእስትንፋሰ አፉሁ ኵሉ ኃይሎሙ"። መዝ32፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 28፥16-20። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 2፥10-16፣ 1ኛ ዮሐ 2፥25-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 22፥7-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥21-ፍ.ሜ። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅድስት ሥላሴ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ሥርዓተ ማኅሌት ዘቃና ዘገሊላ 🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። @EOTCW መልክአ ሥላሴ ሥላሴክሙ ሥላሴ ይረስየኒ መካነ፤ ድኅረ ተዋሃድኩሰ ዘሥላሴሁ ብርሃነ፤ ዮርዳኖስክሙ ዝየ እስመ ኲለንታየ ኮነ፤ ኢየኃሥሥ እምዮርዳኖስ ሰማዕተክሙ ምዕመነ፣ ወኢይትሜነዮ ለታቦር እስመ ታቦር አነ። @EOTCW ዚቅ ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ፤ ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ፤ እማርያም ዘተወልደ አፍቂሮ ኪያነ፤ መጽአ ኀቤነ ዘነቢያት ሰበኩ ለነ፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይፌጽም ኲሎ ሕገ፤ ወአስተርአየ ገሃደ። @EOTCW መልክአ ሚካኤል ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ፤ ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ፤ ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ፤ ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ፤ አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ። @EOTCW ዚቅ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ ዘበተዋሕዶ ይሤለስ፤ እምኀበ ትጉሃን ይትቄደስ፤ እሳተ ሕይወት ዘኢይትገሠሥ፤ ወዘኢይጤየቅ ለዓይን ረቂቅ መንፈስ፤ ንሰግድ ለትሥልስቱ አሐተ ስግደተ፤ ወሎቱ ናቄርብ ስብሐታተ። @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሃላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቌጸል በርእሱ፤ አሕጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ። @EOTCW ዚቅ ወዘምሩ ለስሙ፤ ሀቡ አኮቴተ ለስብሐቲሁ፤ በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ። @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለክሣድክ ግብረ መንፈስ ቅዱስ ኬንያ፤ አዳም ስና ወመንክር ላህያ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ ወሐዋርያ፤ አመ ወጽአ ስሙዓቲከ በአድያመ ኲሉ ሶርያ፤ ብጹአት አእይንት ኪያከ ዘርእያ። @EOTCW ዚቅ ምድረ ዛብሎን ወንፍታሌም፤ ፍኖተ ባሕር ማዕዶተ ሦርያ ዘገሊላ፤ ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእዩ ብርሃነ፤ እስመ ብርሃን ሠረቀ ሎሙ፤ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር፤ እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም፤ ንዑ ናንሶሱ በብርሃኑ። @EOTCW ወረብ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም/፪/ በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ/፬/ @EOTCW መልክአ ኢየሱስ ሰላም ለመከየድከ አሐዱ አሐዱ፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ለምሕሮ እለ ገይሠ ለመዱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመዓዛ ፍቅርከ ዕቊረ ናርዱ፤ አኃዊከ ሰማዕታት ቆላተ ህማማት ወረዱ፤ ወጻድቃኒከ ገዳማተ ዖዱ። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔዓለም፤ ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔዓለም፤ ወይኬልልዎ ለመድኃኔዓለም፤ ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔዓለም፤ ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔዓለም፤ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲአሁ። @EOTCW ወረብ ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔዓለም ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔዓለም/፪/ በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ/፪/ @EOTCW @EOTCW አንገርጋሪ እንዘ ሥውር እምኔነ ይእዜሰ፤ ክሡተ ኮነ ማየ ረሰየ ወይነ፤ ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ፤ በቃና፤ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ። @EOTCW አመላለስ በቃና ዘገሊላ/፪/ ዘገሊላ ከብካብ ኮነ/፬/ @EOTCW ወረብ ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ/፪/ በቃና 'ዘገሊላ'/፪/ ከብካብ ኮነ/፪/ @EOTCW እስመ ለዓለም ዘበዳዊት ተነበየ፤ ወበዮሐንስ ጥምቀት ኃርየ፤ በቃና ዘገሊላ ማየ ወይነ ረሰየ፤ መዓዛ ቃልከ ይትወከፍ ጸሎትየ። @EOTCW አመላለስ፦ በቃና ዘገሊላ ማየ ወይነ ረሰየ፤ መዓዛ ቃልከ ይትወከፍ ጸሎትየ። @EOTCW ዕዝል፦ አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፤ ኮነ እሙነ አስተርዮቱ ለመድኃኒነ ክርስቶስ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW ምልጣን፦ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW አመላለስ፦ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ወለማይኒ ረስዮ ወይነ @EOTCW አቡን፦ በ፭ ወእንዘ ሀለው ውስተ ከብካብ፤ ቅረቡ ኃቤሁ ኩሎሙ አርዳኢሁ ፤አንክርዎ ለማይ አእኰትዎ ለኢየሱስ፤ በእንተ ማይ ዘኮነ ወይን @EOTCW @EOTCW ምልጣን፦ አንክርዎ ለማይ አንክርዎ አእኰትዎ ለኢየሱስ፤ አንክርዎ ማይ አንክርዎ @EOTCW አመላለስ፦ አንክርዎ ለማይ አንክርዎ፤ አእኰትዎ ለኢየሱስ አእኰትዎ ለኢየሱስ። ዓራራይ፦ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ ለመድኃኒነ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራጽዮን፤ ፆፍ ፀዓዳ፤ ንጉስ አንበሳ እምዘርዓ ዘመጽአ @EOTCW ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW @EOTCW ምልጣን ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም። @EOTCW ወረብ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/ ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/ 👇👇👇👇👇 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👆👆👆👆👆 @EOTCW #Join & share # መልካም አገልግሎት

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ሥርዓተ ዋዜማ ዘቃና ዘገሊላ 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 ዋዜማ ሃሌ ሉያ እንዘ ሥውር እምኔነ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ፤ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ፤ አርአዮሙ ስብሐቲሁ፤ አምኑ ቦቱ አርዳኢሁ፤ ወርኢነ፤ ብዕለ ስብሐቲሁ። @EOTCW ምልጣን፦ እንዘ ሥውር እምኔነ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ፤ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ... @EOTCW @EOTCW አመላለስ፦ እንዘ ሥውር እምኔነ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ፤(2) ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ፤ (4) @EOTCW በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦ ማይ ኮነ ወይነ፤ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ፤ ማይ ኮነ ወይነ። @EOTCW እግዚአብሔር ነግሠ፦ ከብካብ ኮነ ከብካብ ኮነ፤ ወኮነ እሙነ በቃና ዘገሊላ፤ በቃና ዘገሊላ፤ ተፀውዓ ኢየሱስ ውስተ ከብካብ፤ ወሖረ ምስለ አርዳኢሁ። @EOTCW ይትባረክ፦ ገብረ መንክረ ገብረ ተአምረ፤ በቃና ዘገሊላ፤ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ። @EOTCW ሰላም ሃሌ ሉያ፤ ቀዳሚሁ ቃል፤ ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ማየ ረሰየ ወይነ፤ ገብረ ሰላመ ማዕከሌነ፤ አናህስዮ አበሳነ። @EOTCW አመላለስ፦ ገብረ ሰላመ ማዕከሌነ፤ አናህስዮ አበሳነ አናህስዮ አበሳነ 👇👇👇👇👇 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👆👆👆👆👆👆 @EOTCW #Join & share

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለኖኅ ዘተካየደ ምስለ እግዚአብሔር ከመ ኢይሥርዋ ለምድር በአይኅ፤ ዘረሰየ ዘርዖ ከመ ኆፃ ብዙኅ"። ትርጉም፦ ምድርን በንፍር የጥፋት ውሃ እንዳያጠፋት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳንን የተገባባ፤ ዘሩንም እንደ አሸዋ ብዙ ያደረገለት ለኾነ ለኖኅ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ለጎርጎርዮስ ወለባስልዮስ ዘተናገሮሙ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ ዘከመ ቀተሎ ለዑልያኖስ"። ትርጉም፦ ዑልያኖስን እንዴት እንደገደለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕሉ የተናገራቸው ለኾነ ለጎርጎርዮስና ለባስልዮስ ሰላምታ ይገባል"። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

❤ ወንድሙ የስብስጥያ ኤጲስቆጶስ ከሚስቱ ጋር በድንግልና ሲኖር ሕዝቡ ግን ያሙት ነበርና ቅዱስ ባስልዮስ መላእክት ሲጠብቋቸው እንደተመለከተ ለሕዝቡ ገልጦላቸው ሕዝቡ ከሐሜት ርቀው ንስሓ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ በተመለከተ ጊዜ "ይህ የቂሳርያው የባስልዮስ ነው" የሚል ቃልን ሰምቷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ወደ ቂሳርያ ሄዶ ከቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ዲቁናና ቅስና ተቀብሏል፡፡ ቅዱስ ባልዩስም በቅዱስ ኤፍሬም በላዩ ጸልዮለት የማያውቀውን አዲስ የዮናኒን ቋንቋን እንዲናገር አድርጎታል፡፡ ❤ ቅዱስ ባስልዮስ ሰው ሁሉ የሚያምንበትና በአቆጣጠሩም የሚታወቀውን ጠንቋይም በተአምሩ አሳምኖታል፡፡ ይኸውም ቅዱስ ባስልዮስ በታመመ ጊዜ የሚሞትበትን ጊዜ ዐውቆ ይህን ጠንቋይ ጠርቶ "ንገረኝ እስቲ መቼ እሞታለሁ?" አለው፡፡ ጠንቋዩም "ማታ ነፍስህ ከሥጋህ ትለያለች" አለው፡፡ እርሱም "እስከ ጠዋት ካልሞትኩ ክርስቲያን ትሆናለህ?" በማለት ቃል አስገባው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ወደ ጌታችን በመጸለይ በዕድሜው ላይ ሦስት ቀናት አስጨመረ፡፡ ያም ጠንቋይ ሥራው ከንቱ እንደሆነ ታወቀበትና እርሱም አምኖ ከነቤተሰቦቹ ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነ፡፡ ❤ ሌላው ተአምር ለቅዱስ ባስልዮስ እመቤታችን ስለ ሥዕሏ የነገረችው ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ባስልዮስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ከሠራ በኋላ በውስጧ የሚያኖረውን የእመቤታችንን ሥዕል ሊያሠራ መሳያ ሠሌዳ ፈለገ፡፡ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ቤት ጥሩ ሠሌዳ እንዳለ ነገሩትና ሄዶ ባለጸጋውን ሠሌዳውን እንዲሰጠው ለመነው፡፡ ባለጸጋውም የልጆቼ ነው አልሰጥም አለው፡፡ በትዕቢትም ሆኖ በታነጸቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብን ነገር ተናገረ፡፡ ወዲያውም ወድቆ ክፉ አሟሟት ሞተና ልጆቹ ፈርተው ሠሌዳውን አምጥተው ለባስልዮስ ሰጡት፡፡ እርሱም ያንን ሠሌዳ የእመቤታችንን ሥዕል አሳምሮ ይስልበት ዘንድ ለሰዓሊ ወስዶ ሰጠው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን በራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጠችለትና ከአመፀኛ ሰው የተገኘ ነውና በዚያ ሰው ሠሌዳ ሥዕሏን እንዳያስል ከለከለችው፡፡ ሥዕሏ የተሳለበትን ሠሌዳም የት እንደሚገኝ ነገረችውና ሄዶ በታላቅ ክብር አምጥቶ በቤተ ክርስቲያኑ አስቀመጠው፡፡ ከሥዕሉም ሥር ድውያንን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስ ጀመረ፡፡ በዚህም ብዙዎች ድንቅ የሆነ ፈውስን አገኙ፡፡ ይህም የተፈጸመው ሰኔ 21 ቀን ነው፡፡ ❤ ሌላም እንዲሁ ቅዱስ ባስልዮስ ያደረገው ተአምር የሰይጣንን የጽሕፈት ደብዳቤ በጸሎቱ የደመሰሰ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ጎልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ሥራይኛ ዘንድ ሄደ፡፡ ሥራይኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠውና ወደ አረሚ መቃብር ሄዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ በመቃብሩ እንዲቆ ላይ አዘዘው፡፡ ወጣቱም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ከሰይጣናትም አንዱ መጥቶ ወደ ወደ አለቃቸው አደረሰው፡፡ ያችንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰዳት፡፡ ሰይጣንም "የፈለከውን አደርግልሃለሁ ነገር ግን አምላክህን ክርስቶስን ትክደዋለህ ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላም ወደ እርሱ አትምለስም" ሲለው ወጣቱም በልጅቷ ፍቅር አብዶ ነበርና "አዎን ጌታዬ ያዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው፡፡ ሰይጣኑም "ይህን ልታደርግ በእጅህ ጻፍልኝ" አለውና አጻፈው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰይጣን በጌታው ሴት ልጅ ልብ ውስጥ አደረና ያንን ወጣት እጅግ ወደደችው፡፡ የፍትወት እሳትንም በልቧ ላይ ስላነደደባት መታገስ አልቻለችምና ወደ አባቷ ቀርባ ልጁን አጋባኝ አለችው፡፡ የልጁም ፍቅር በየዕለቱ ይጨምርባት ነበርና ራሷን እንዳታጠፋ ቤተሰቦቿ አጋቧት፡፡ ከእርሱ ጋር መኖር ከጀመረች በኋላ ሲያማትብ እንኳን አይታው አታውቅም ነበርና ስትመረምረው ክርስቲያን አለመሆኑንና ያደረገውንም ሁሉ ነገራት፡፡ ይህንንም ስትሰማ እጅግ ደንግጣ ወደ አገሯ ሊቀ ጳጳስ ወደ ባስልዮስ ዘንድ ሄዳ ከእግሩ ሥር በመውደቅ የደረሰባትን በመንገር ከሰይጣን እጅ እንዲያድናት ለመነችው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም በሏ የሆነውን የአባቷን ባርያ አስመጣውና በንስሓ ተመልሶ ክርስቲያን መሆን እንደሚፈልግ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ፈቃደኝነቱን ሲገልጥለት በአንድ ቦታ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበትና ከላይ በመስቀል ምልክት አተመበት፡፡ እንዲጸልይም አዘዘው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ስለ ወጣቱ ብዙ ጸለየ፡፡ ከሦስት ቀንም በኋላ ጎበኘውና በ3ቱ ቀን የደሰበትን ጠየቀው፡፡ ወጣቱም በላዩ በመጮህ ሰይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲያሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም "ከሰይጣናቱ ቁጣ የተነሣ አትፍራ አይዞህ እግዚአብሔር ይረዳናል" ብሎ ጥቂት ከመገበው በኋላ መልሶ ዘጋበትና ሄዶ ይጸልይለት ጀመር፡፡ ❤ ዳግመኛም ከ3 ቀን በኋላ መጥቶ ጠየቀው፡፡ ወጣቱም "የአጋንንቱን ጩኸታቸውን እሰማዋለሁ ነገር ግን አላያቸውም" አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ አሁንም ጥቂት ከመገበው በኋላ መልሶ ዘጋበትና እስከ 40 ቀን ድረስ እንዲሁ አደረገ፡፡ ከ40 ቀንም በኋላ መልሶ ሲጠይቀው ወጣቱ "ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ሲሰማ እጅግ ደስ አለው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንም ጠርቶ እግዚኦታ አደረሱና ከእግዚኦታው በኋላ ያ ወጣት ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ ተወስዶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ፡፡ ሁሉም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ይኸውም የተደረገው መስከረም 13 ቀን ነው፡፡ ❤ አንዲት ሴት ኃጢአቷን ሁሉ በዝርዝር ጽፋ በክርስታስ አሽጋ እንዲጸልይላት ቅዱስ ባስልዮስን ለመነችው፡፡ እርሱም ከአንዲት ኃጢአቷ በቀር ሁሉንም በጸሎቱ ደመሰሰላት፡፡ ስለ አንዲቱም ኃጢአቷ ወደ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲትሄድ አዘዛት፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም "ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሳይሞት ፈጥነሽ ተመለሽ የካህናት ሁሉ አለቃ ስለሆነ የቀረች ኃጢአትሽን የሚደመስስልሽ እርሱ ነው" ብሎ መለሳት፡፡ በተመለሰችም ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ዐርፎ ሊቀብሩት ሲወስዱት አገኘችው፡፡ እርሷም መሪር ልቅሶን ካለቀሰች በኋላ በእምነት ሆና ያንን ክርስታስ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችው፡፡ ስለ እምነቷም ጽናት ያች የቀረች በደሏ ተደመሰሰችላት፡፡ ❤ ይህም የከበረ ቅዱስ ባስልዮስ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከጻፍነው ሌላ ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶችን አድርጓል ብዙዎችንም ተግሣጻትንና ድርሳናትንና ለመነኰሳትም ትምህርቶችን ደርሷል፡፡ ከብሉይና ከሐዲስም አምላካውያን የሆኑ ብዙ መጻሕፍቶችን ተርጒሟል ሥርዓቶችንም ሠራ እነርሱም በሁሉ ቦታ ይገኛሉ ከዚህም በኋላ ጥር6 በሰላም ዐረፈ በክብር በብዙ ምስጋና ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ባስልዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 6 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለኖኅ በሕቁ። ምስለ ብእሲቱ ወደቂቁ። በገቢረ ታቦት ላዕሌሁ እለ ተሣለቁ። በዝናመ ድምሳሴ ወበማየ አይኅ ኀልቁ። ውእቱሰ እምሠጠ በጽድቁ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥር 6። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ይጫኑት @Eotcw @Eotcw @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥር ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ከአዳም ዐሥረኛ ትውልድ ለሆነው ለታላቁ አባት ለጻድቁ ለቅዱስ ኖኅ ለዕረፍቱ መታሰቢያ፣ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤልያስ በሕይወት ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ለዐረገበት (ከሞት ለተሰወረበት) በዓል፣ ለታላቋ ሰማዕት ለቅድስት አርሴማ ለልደቷ በዓልና ለከበረና ለታላቁ አባት ለቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ለአቡነ ባስልዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ ከአባ ወርክያኖስ ዕረፍትና በበረሀ ስልሳ ዘመናት ከኖረ ከአባ ሙሴ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለኤልያስ ነቢይ ቴስብያዊ ኮሬባዊ ታቦራዊ ሰማየ ዘለጐመ ወከልአ ዝናመ፤ ቃለ ጸሎቱ ዘተሰምዐ ውስተ ዕዝኑ ለአዶናይ ወአውረደ እሳት እምሰማይ እስከ በልዖ ለማይ፤ ዘዐደወ ብሔረ ተድላ ተጽኢኖ ዘእሳት ሠረገላ። ትርጉም፦ ቴስቢያዊ (የቴስቢያ ሰው)፤ ኮሬባዊ (ወደ ኮሬብ ተራራ የወጣ)፤ ታቦራዊ (በታቦር ተራራ የተገኘ) ፤ ዝናብ እን ዳይዘንብ ሰማይን የለጐመ ለኾነ፤ የጸሎቱ ቃልም በአዶናይ ዦሮ ውስጥ ለተሰማ፤ ውሃውን እስካበላ ደርሶ እሳትን ከሰማይ ያወረደ ለኾነ፤ በእሳት ሠረገላ ተጭኖ ወደ ተድላ ደስታ ቦታ ለገባ ለነቢዩ ለኤልያስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ ዕረገት፦ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስን ወደ ሰማይ በሚወጣባት ጊዜ ኤልሳና ኤልያስ ከገልገላ ተነሥተው ሔደወሰ ወደ ዮርዳኖስ ደረሱ ኤልያስም መጠምጠሚያውን አውርዶ ጠቅሎ የዮርድያኖስ ውኃ መታበት ውኃውም ተከፍሎ ወዲያና ወዲህ ቆመ ሁለቱም ሁሉ በደረቅ ተሻገሩ ወጥተውም በምድረ በዳ ቆመ። ❤ ኤልያስ ኤልሳን "ካንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ" አለው ኤልሳዕም ኤልያስን "በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ዕጥፍ ሁኖ ይደርብኝ" አለው። ኤልያስም ኤልሳን "ድንቅ ነገርን ለመንከኝ ነገር ግን ካንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳርግ ብታየኝ ይሁንልህ ባታየኝ ግን አይሆንልህ" አለው። በዚያንም ጊዜ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረስ መጣ ወደ መካከላቸውም ገብቶ አራራቃቸው ኤልያስም እንደዚህ በንውጽውጽታና በጥቅል ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ። ኤልሳዕም አይቶ "የእስራኤል ኃይላቸውና ጽናታቸው አባ አባ ብሎ ጮኸ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ አላየውም ልብሶቹንም ለሁለት አድርጎ ከፈላቸው ኤልያስም ለኤልሳዕ መጠምጠሚያውን ጣለለት በኤልሳዕም ራስ ላይ ወረደ የኤልያስም ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በኤልሳዕ ላይ ዕጥፍ ሁኖ አደረ ኤልያስም የሠራውን ተአምራት ኤልሳዕ ዕጥፍ አድርጎ ሠራ። ❤ ይህም ኤልያስ በኋላ ዘመን ከኄኖክ ጋር ይመጣ ዘንድ አለው ሐሳዊ መሢሕንም ይቃወሙታል እርሱም ይገድላቸዋል በድናቸውም በአደባባይ ተጥሎ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ይቆያል ከዚህም በኋላ ይነሣሉ የሙታን ትንሣኤም ይሆናል ይህም ኤልያስ እውነተኛ ነቢይ አስቀድሞ የነበረ በኋላም የሚገለጽ ነው በብሉይ ዘመንም ኑሮው በበረሃ ውስጥ ነበር። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢይ በቅዱስ ኤልያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባታችን ጻድቁ ቅዱስ ኖኅ፦ እርሱም ከአባታችን አዳም ዐሥረኛ ትውልድ ነው። እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛ ክፋትም እንደሚመላ ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሁኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር። ❤ አምስት ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ጻድቁ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፡፡ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፡፡ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፡፡ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ኖኅም ከልጆቹና ከሚስቶቻቸው ጋራ ወደ መርከቡ ገባ፡፡ ንጹሐን የሆኑት እንስሳትና አእዋፋት ሴትና ወንድ ሰባት ሰባት፣ ንጹሐን ካልሆኑት ደግሞ ሁለት ሁለት ሴትና ወንድ አስገባ፡፡ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፡፡ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡ ❤ ከመቶ ሃምሳ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፡፡ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፡፡ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፡፡ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፡፡ ❤ ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍራም ጀመር፡፡ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፡፡ "ከነዓን የተረገመ ይሁን፣ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን" ብሎ ከረገመው በኋላ "የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ፣ በሴም ቤትም ይደር ከነአንም አገልጋይ ይሁን"። ❤ አባታችን ቅዱስ ኖኅም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሦስት መቶ ኅምሳ ዓመት ኖረ የኖኅም መላ ዕድሜው ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሆነ በሰላምም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን በጻድቁ ኖኅ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ኤስድሮስ ይባላል እርሱም ከአንጾኪያ አገር ሰዎች ንጹሕና ቅዱስ የሆነ ቄስ ነው አምስት ልጆችንም ወልዶአል እነርሱም ባስልዮስ፣ ጎርጎርዮስ፣ ጴጥሮስ፣ ኬርዮን፣ መክርዮን ናቸው ሁሉም ከፍጹማንነት የደረሱ ቅዱሳን ናቸው። ❤ በዚህም በከበረ ባስልዮስ ላይ መንፈስ ቅዱስ መልቶበት በሁሉ ዘንድ የታወቀች ቅዳሴውን ደረሰ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊሠርቁ የመጡትን ሌቦች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በጸሎቱ በሩን ዘግቶባቸዋል፡፡ በኋላም ምእመናን ሲመጡ በሩን ከፍቶላቸዋል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ መሆኑን ነው፡፡ የታላቁ አባት የቅዱስ ኤፍሬምም መምህሩ ነው፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ያደረጋቸው ተአምራት ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡

photo content