ru
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Открыть в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Больше
1 161
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ። ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ። ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ። ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ። ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ"። ትርጉም፦ የጌታ አገሩ ናዝሬት በጌታ ላይ ክፋን የመከሩ፣ ጠላቶቹም የሆኑ የሄሮድስ ሠራዊት ይሸሹም፣ ይተፋፈሩም ዘንድ የግብፅ ጣዖታትን በብትሩ (በሥልጣኑ) አጥፍቶ ከዙፋኑ ማርያም ጋር ንጉሥሽ ተመልሷልና ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ። ሰቆቃወ ድንግል። + + + ❤ የዕለቱ እግ ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "በከመ ይቤ ኢሳይያስ ነቢይ ናሁ ይወርድ ውስተ ምድረ ግብፅ ተፅዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ድንግል ዘሀዘለቶ በዘባና ለአማኑኤል"። ትርጉም፦ ኢሳይያስ ነቢይ እንዳለ እነሆ ወደ ምድረ ግብጽ ይወርዳል በቀላል ደመና ተጭኖ ደመናስ የሚለው አማኑኤልን በጀርባው ያዘለችውን ድንግልን ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ለታላቁ አባት ለአቡነ ዳንኤል ዘገርዓልታ ለዕፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ዳንኤል ዘገርዓልታ፦ የአባታቸው ስም መልክአ ሥላሴ የእናታቸው ስም ዓመተ ጽዮን ሲባሉ የትውልድ አገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው። በሰባት ዓመታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምረው አጠናቀው በዓሥራ ሦስት ዓመታቸው መነኰሱ። ሊቃውንቱ "ማኅቶተ ገዳም" እያሉ የሚጠሯቸው ታላቅ ገድለኛ አባት ናቸው። ባለ አራት ዓምዱና አርባ ያሸበረቁ ሥዕላት ያሉት አስደናቂው ገድላቸው የት እንዳለ አይታወቅም፣ እኛ አገር ገድላቸው የለም። 2ኛውን ገድላቸውን ፖርቹጋሎች ከጠባቂው ገዝተው ወስደው አገራቸው አሳትመውታል። ገድሉን የሸጠው ጠባቂም ሆዱ ተነፍቶ በስብሶ ተልቶ ከቤተ ክርስቲያኑ በራፍ ላይ ወድቆ ሞቷል። የጻድቁ የዕረፍታቸው ዕለት ኅዳር 6 ቀን ትግራይ ገርዓልታ በሚገኝ ገዳማቸው በደማቅ ሁኔታ የከበራል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም ላአረፉበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት ለአባ ፊልክስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን በስክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ከአባ ፍሞስ፣ ከቅዱሳን ለንዲዎስ፣ ከይላጥስ፣ ከማርትሮስ፣ ከኢላስዎስ፣ ከቆርናልዮስ፣ ከሱኪሮስ ከናውኔኖስ ከሊባዲቆ ከሲላስዮስና ከሰማዕት ኢስድሮስ ማኅበር ከሆኑ ከሁለት መቶ ሰባ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልደ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም አማን ወበምድር ሰላም"። ትርጉም፦ ዛሬ መላእክት በማርያምና በልጇ ክርስቶስ ዙሪያ ላይ በቍስቋም ተራራ ረበቡ (ረበው ታዩ)። በእውነት በሰማይ ምስጋና በምድርም ሰላም እያሉ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገባ በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም ዐረፉ። ❤ ዳግመኛም በኋላ ዘመን በዚህ ደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው። ለዚህም የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮችን ሆኑ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊልክስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው። ❤ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ፊልክስን መረጡት በእግዚአብሔርም ፈቃድ በሮሜ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የክርስቶስንም መንጋዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። ❤ ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር ነገሠ። እርሱም በምዕመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት። ስርሱም ወደ እግዚአብሔር ማለደ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህንን ከሀዲ በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው። ❤ ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አብዝቶ ማሠቃየትን ጀመረ ይህም አባት ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያይ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዲዮቅልጥያኖስም በመጀመሪያው ዘመነ መንግሥት ኅዳር 6 ቀን ዐረፈ። ❤ ይህም አባት ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጾችን ደርሶአል ከእርሳቸውም ስለ ውግዘትና ስለ ቀናች ሃይማኖት የተመላለሰብት አለ እሊህም ለክርስቲያን ወገን እጅግ የሚጠቅሙ በጎዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ፊልክስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 6 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌቱ ምስባክ፦ "ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ። ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር ዕጐሊሃ። ምሥዋዒከ እግዚኦ እግዚአ ኃያላን"። መዝ 83፥3 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ22፥14-24። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ። ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ። ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ"። መዝ 36፥35። የሚበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 8፥1-16፣ 2ኛ ዮሐ 1፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ማቴ 2፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የደብረ ቊስቋም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 19:31-ፍ፡ም፡ "ወአይሁድሰ እስመ ዐርብ ውእቱ" - "አይሁድም፡የማዘጋጀት፡ቀን፡ስለ፡ሆነ፡ያ፡ሰንበት፡ትልቅ፡ነበረና፡ሥጋቸው፡በሰንበት፡በመስቀል፡ላይ፡እንዳይኖር፥ጭናቸውን፡ሰብረው፡እንዲያወርዷቸው፡ጲላጦስን፡ለመኑት። ጭፍራዎችም፡መጥተው፡የፊተኛውን፡ጭን፡ከእርሱም፡ጋራ፡የተሰቀለውን፡የሌላውን፡ጭን፡ሰበሩ፤ ወደ፡ኢየሱስ፡በመጡ፡ጊዜ፡ግን፡እርሱ፡ፈጽሞ፡እንደ፡ሞተ፡አይተው፡ጭኑን፡አልሰበሩም፤ ነገር፡ግን፥ከጭፍራዎች፡አንዱ፡ጐኑን፡በጦር፡ወጋው፤ወዲያውም፡ደምና፡ውሃ፡ወጣ። ያየውም፡መስክሯል፤ምስክሩም፡እውነት፡ነው፤እናንተም፡ደግሞ፡ታምኑ፡ዘንድ፡እርሱ፡እውነት፡እንዲናገር፡ያውቃል። ይህ፡የሆነ፦ከእርሱ፡አጥንት፡አይሰበርም፡የሚል፡የመጽሐፉ፡ቃል፡እንዲፈጸም፡ነው። ደግሞም፡ሌላው፡መጽሐፍ፦የወጉትን፡ያዩታል፡ይላል። ከዚህም፡በኋላ፡አይሁድን፡ስለ፡ፈራ፡በስውር፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡የነበረ፡የአርማትያስ፡ዮሴፍ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ሊወስድ፡ጲላጦስን፡ለመነ፤ጲላጦስም፡ፈቀደለት።ስለዚህም፡መጥቶ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ወሰደ። ከዚህም፡በዃላ፡አይሁድን፡ስለ፡ፈራ፡በስውር፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡የነበረ፡የአርማትያስ፡ዮሴፍ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ሊወስድ፡ጲላጦስን፡ለመነ፤ጲላጦስም፡ፈቀደለት።ስለዚህም፡መጥቶ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ወሰደ። ደግሞም፡አስቀድሞ፡በሌሊት፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጥቶ፡የነበረ፡ኒቆዲሞስ፡መቶ፡ንጥር፡የሚያህል፡የከርቤና፡የሬት፡ቅልቅል፡ይዞ፡መጣ። የኢየሱስንም፡ሥጋ፡ወስደው፥እንደ፡አይሁድ፡አገናነዝ፡ልማድ፥ከሽቱ፡ጋራ፡በተልባ፡እግር፡ልብስ፡ከፈኑት። በተሰቀለበትም፡ስፍራ፡አትክልት፡ነበረ፥በአትክልቱም፡ማንም፡ገና፡ያልተቀበረበት፡አዲስ፡መቃብር፡ነበረ። ስለዚህ፥መቃብሩ፡ቅርብ፡ነበረና፥ስለ፡አይሁድ፡ማዘጋጀት፡ቀን፡ኢየሱስን፡በዚያ፡አኖሩት።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.81 KB

05/3/2015 ዓ.ም (፭/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ኃጢአትየ ዘበንዕስየ ወእበድዕየ ኢትዝክር ሊተ። ወበከመ ሣህልከ ተዘከረኒ። በእንተ ምህረትከ እግዚኦ። መዝ. 24፥7 🕯 ትርጉም የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ። አቤቱ ስለቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 19:3-12፡ "ወይቤልዎ አርዳኢሁ እመሰ ከመዝ" - "ፈሪሳውያንም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፡ሲፈትኑት፦ሰው፡በሆነው፡ምክንያት፡ሁሉ፡ሚስቱን፡ሊፈታ፡ተፈቅዶለታልን? አሉት። እርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ፈጣሪ፡በመጀመሪያ፡ወንድና፡ሴት፡አደረጋቸው፥ አለም፦ስለዚህ፡ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥ከሚስቱም፡ጋራ፡ይተባበራል፥ሁለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡ይሆናሉ፡የሚለውን፡ቃል፡አላነበባችኹምን? ስለዚህ፥አንድ፡ሥጋ፡ናቸው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ሁለት፡አይደሉም።እግዚአብሔር፡ያጣመረውን፡እንግዲህ፡ሰው፡አይለየው። እነርሱም፦እንኪያስ፡ሙሴ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ሰጥተው፡እንዲፈቷት፡ስለ፡ምን፡አዘዘ፧አሉት። እርሱም፦ሙሴስ፡ስለልባችሁ፡ጥንካሬ፡ሚስቶቻችሁን፡ትፈቱ፡ዘንድ፡ፈቀደላችሁ፤ከጥንት፡ግን፡እንዲህ፡አልነበረም።እኔ፡ግን፡እላችኋለሀ፥ያለዝሙት፡ምክንያት፡ሚስቱን፡ፈቶ፟፡ሌላዪቱን፡የሚያገባ፡ሁሉ፡ያመነዝራል፥የተፈታችውንም፡የሚያገባ፡ያመነዝራል፡አላቸው። ደቀ፡መዛሙርቱም፦የባልና፡የሚስት፡ሥርዐት፡እንዲህ፡ከሆውነ፡መጋባት፡አይጠቅምም፡አሉት። እርሱ፡ግን፦ይህ፡ነገር፡ለተሰጣቸው፡ነው፡እንጂ፡ለሁሉ፡አይደለም፤ በእናት፡ማሕፀን፡ጃን፡ደረባዎች፡ሆነው፡የተወለዱ፡አሉ፥ሰውም፡የሰለባቸው፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፥ስለ፡መንግሥተ፡ሰማያትም፡ራሳቸውን፡የሰለቡ፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፦ሊቀበለው፡የሚችል፡ይቀበለው፡አላቸው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

05/3/2015 ዓ.ም (፭/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወአንሰ ብከ ተወከልኩ እግዚኦ። ወእቤለከ አምላኪየ አንተ። ውስተ እዴከ ርስትየ። መዝ. 30፥14 🕯 ትርጉም አቤቱ፥ እኔ ግን ባንተ ታመንኹ፤ አንተ አምላኬ ነኽ አልኹ። ርስቴ በእጅኽ ነው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

፭ኛ ወረብ ዮም ጸለሉ @EOTCW

፬ኛ ወረብ ናዝሬት ሀገሩ @EOTCW

፫ኛ ወረብ አልቦ እንበለ ሰሎሜ @EOTCW

፪ኛ ወረብ ከማሃ ኃዘን @EOTCW

አመ ፮ለሕ ቁስቋም ፩ኛ ወረብ ፀምር ፀዓዳ @EOTCW

ከአንገርጋሪ እስከ እስመ ለዓለም ዘሰ @EOTCW

አመ ፮ለሕ ቁስቋም ዚቅ በዜማ @EOTCW

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ስረዓተ ማኅሌት 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ✨መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። @EOTCW 🌱ዚቅ ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት። @EOTCW @EOTCW 🔸ነግስ/ለልሳንከ/ @EOTCW ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። @EOTCW 🌱ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። @EOTCW @EOTCW 🌱🌱ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW 🌱ዚቅ ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት። @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ/2/ በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ/2/ @EOTCW @EOTCW ✨ሰቆቃወ ድንግል @EOTCW በስመ እግዚአብሔር @EOTCW በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤ ሰቆቃወ ድንግል እጽህፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤ ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤ ርእዮ ለይብኪ አይነ ልብ ዘቦ። @EOTCW ❣❣ወረብ ከማሃ ኃዘን ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን/2/ ሶበ በኲለሄ ረከቦ ከማሃ ኃዘን/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ ምንዳቤ ወኃዘነ ወኲሎ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ። @EOTCW ❣❣ወረብ ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ/2/ ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል/2/ @EOTCW ምዕረ በዘባንኪ @EOTCW ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤ ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ። @EOTCW ❣❣ወረብ አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ/2/ ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስዕን ሕፃንኪ ያንቀዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ እስከ ትፀውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ። አብርሂአብርሂ አብርሂአብሂ ናዝሬት ሀገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ምስለ ማርያም መፆሩ፤ ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤ ይጒየዩ ወይኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤ ዘበላዕሌሁ እኩ መከሩ። @EOTCW 🌱ዚቅ አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ አብርሂ ጽዮን በጽሐ ብርሃንኪ ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል በሰላም ቦአ ኀቤኪ። @EOTCW ❣❣ወረብ አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም/2/ በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም (ደብረ ... እከሌ)/2/ @EOTCW @EOTCW ❄️ምልጣን ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤ እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤ አማን፤ ወበምድር ሰላም። @EOTCW @EOTCW 🔹እስመ ለዓለም፦ ይቤ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፤ ሶበ ዕኩ ውስተ ዝ ንቱ ቤት፤ አዕረፈት ነፍስየ እምፃማ ዘረከበኒ በፍኖ ት፤ ኀበ ኀደረት ቅድስት ድንግል፤ ምስለ ፍቁር ወ ልዳ ኢየሱስ ክርስቶስ። @EOTCW @EOTCW 🔸🔹እስመ ለዓለም ዓዲ (ወይም)፦ መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም፤ ወልደ ቅ ድስት ማርያም፤ ኃሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉ ሥ ዘለዓለም፤ ግሩም እምግሩማን፤ ብርሃነ ሕይ ወት ዘኢይጸልም ኃደረ ደብረ ቍስቋም፤ ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም። https://t.me/Eotcw # Join & share #

አመ ፮ለሕ ቁስቋም ከዋዜማ-ሰላም @EOTCW

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ዋዜማ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እም ርእሰ ሳኔር ወኤርምን እምግበበ አናብስት ፤ወእም አድባር አናምርት ወጻእኪ፤ እትፌሣህ ብኪ፤ ርግብየ ሠናይት @EOTCW 🔹አመላለስ፦ እትፌሣህ ብኪ ርግብየ ሠናይት/2/ እትፌሣህ ብኪ ርግብየ ሠናይት/4/ @EOTCW ለእግዚአብሔር ምድር በመላ፦ ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኃረያ ሰአሊ ለነ ማርያም @EOTCW 🔹እግዚአብሔር ነግሠ፦ በከመ ይቤ ኢሣይያስ ነቢይ ናሁ ይወርድ እግዚአብሔር ውስተ ምድር ግብፅ ተፅዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል ደመናሰ ዘይቤ ይእትኬ ድንግል ዘሀዘልቶ ለአማኑኤል @EOTCW 🔹በ፫ት፦ ማርያምሰ እሙኒ ዐመቱኒ በትረ አሮን እንተ ሠረጸት እንበለ ተክል @EOTCW 🔸ይትባረክ፦ እግእዝትየ እብለኪ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኃደረ ላዕሌኪ @EOTCW ✴️ሰላም፦ ወኩሉ ነገራ በሰላም ፡ወኩሉ ነገራ በሰላም ሰላማዊት ይብልዋ ለቅድስተ ቅዱሳን ፣ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ጥዕምት በቃላ ወሰናይ ምግባራ ፡ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ንፅህት ይእቲ በድንግልና አልባቲ ሙስና ዕራቁ ደመና፤ ወኩሉ ነገራ በሰላም ወኩሉ ነገራ በሰላም ማርያም ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ https://t.me/Eotcw # Join & share #