Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Открыть в Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite
Больше3 594
Подписчики
Нет данных24 часа
+47 дней
-2030 дней
Архив постов
የሐምሌ_ወር_2015_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ.PDF3.39 MB
*ማስታወቂያ*
የነባር እና የአዳዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት ምዘገባ ለ 5 የስራ ቀናት መራዘሙን የሚገልፅ ማስታወቂያ፡-
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቤት ልማቱ ጎን ለጎን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር በኢኮኖሚው ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየና እያደረገም ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚኖረው የግንባታ ፕሮጀክቶች በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት ያሰበና ለዚህም ይረዳው ዘንድ በከተማችን ያሉትን የስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን በመመዝገብ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ እና መመልመል አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱን በቅርቡ በተቋሙ ማህበራዊ ድረ-ገጽ ምዝገባ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
ይሁንና ምዝገባው በተለያየ ምክንያት ያለፋቸው እና ያልሰሙ በመኖራቸው እና ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት ለነባር እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎች ከቀን 06/11/2015 - 11/11/2015 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰአት ድረስ ለለተከታታይ አምስት የስራ ቀናት online ምዝገባው መራዘሙን እየገለጽን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) http://aahdc.gov.et በመጫን እና የሚጠይቀውን መረጃ በአግባቡ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
በነባር፡-
በተቋማችንና በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ትስስር ተደርጎላችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ ስራ ተቋራጮችና ማህበራት ነባር በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማድረግ ያለባችሁ ሲሆን፤
በአዲስ፡-
ከዚህ በፊት በተቋማችንም ሆነ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ምንም ዓይነት የስራ ትስስር ያልተደረገላችሁ አዲስ በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማካሄድ ትችላላችሁ፡፡
ለምዝገባ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በድጋሚ ለማስታወስ ያህል፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የግበር መክፈያ መለያ ቁጥር( Tax
Identification Number- TIN.)
- የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
- የስራ ልምድ ከ1-2 ገፅ በማይበልጥ
በዝርዝር ይጠቀስ
- የስራ ልምድ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር
የሚያሳዩ መረጃዎች
- እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና
ማህበራቱን የሚገልጹ ሰነዶችን ናቸው
ማሳሰቢያ፡-
ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከሚመለከተው አካል በሚላከው መረጃ መሠረትና በተቋማችን ባለው መረጃ መሠረት ወደ ስራ ሲገባ በነባር መመዝገብ እያለባችሁ በአዲስ ተመዝግባችሁ የተገኛችሁት ላይ እንዲሁም በሁለቱም (በነባርም፣በአዲስም) ተመዝግቦ የሚገኝ ስራ ተቋራጭም ሆነ ማህበራት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ከዚህ በፊት በነበረው ምዝገባ ማለትም እስከሰኔ 27/2015 ለተከታታይ 15 ቀን ሲደረግ በነበረው ምዝገባ የተመዘገባችሁ በዚህ ምዝገባ ማድረግ የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እንዲሁም
አንድ ተቋራጭ ወይም ማህበር ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ የሌለበት መሆኑን እያሳወቅን ማንኛውም ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፎ የተገኘ ተመዝጋቢ ከምዝገባው የሚሠረዝ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነው
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ የድህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች ግዥ
ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/PG-57/2015
‹
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የየተለያዩ የድህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርቲፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
2. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ /በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማረኛ ቋንቋ ነው ፡፡
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይንም በባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ቀን ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ
አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ
አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት
ስልክ ቁጥር 0118-13 45 27 / 0118-72 29 47
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ማስታወቂያ-ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!
ጂ.አይ.ዜድ. ኢትዮጵያ ኢንተግሬሽን በሚባል ኩባንያ በኩል ከፍ ያለ ደረጃ ያለውና ለ 10 ቀናት የሚሰጥ የአመራር (Leadership) ሥልጠና ለመስጠት አቅዶ በዚህ ሥልጠና ላይ ለመካፈል ፍላጎቱ ያላቸውን በፆታቸው ሴት የሆኑና በአመራርነት እየሠሩ የሚገኙ ሠልጣኞችን መርጠን እንድልክለት ጠይቆናል፡፡
ለሥልጠናው ብቁ የሚሆኑ ሠልጣኞችን ለመምረጥ የሚስችል መሥፈርትም አዘጋጅቶ የላከልን በመሆኑ ይኽው መሥፈርት ከዚህ ማስታወሻ ጋር ተያይዞ እንዲደርሳችሁ ተደርጓል፡፡ ሥልጠናው የሚጀምረው እ.ኤ.አ. በኦገስት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ነው፡፡
ስለሆነም በዚህ ሥልጠና ላይ ለመካፈል ፍላጎቱ ያላቸውና መሥፈርቱን የሚያሟሉ ሠልጣኞችን እስከ መጪው ረቡዕ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በዚሁ ገፅ ላይ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር
የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ለመንገድ ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ።
መንገዶች ላይ ጉዳት በሚያስከትል ሁኔታ ጭነት በሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን ግንባታ ማሽነሪ ኦፕሬተሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ።
በከተማችን በተለያዩ ስፍራዎች ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል። ከግንባታዎቹ ጋር ተያይዞ ሲሚንቶ የሚያቦኩ ተሽከርካሪዎች የተቦካ ሲሚንቶ መንገድ ላይ በማፍሰስ እንዲሁም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ከጭነት አቅም በላይ አፈርና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን መንገዶች ላይ በማፍሰስ እና ጭቃ በጎማቸው ይዘው ወደ ጎዳና የሚወጡ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ለመንገዶች ደህንነት ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ መንገዶች ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሸገር ለትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
ፖሊስ አጥፊዎቹ ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ መቆየቱን አስተውሷል።
በጥፋቱ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከለካል የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ እንደሚወስድ አሰጠንቅቋል።
የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ጭነት በሚጭኑበት ወቅት የመንገድ ደህንነት ህጉ በሚያዘው መሰረት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበቸው እንዲሁም መንገዶቹን በጭቃ የሚያበላሹ፤ የተሽከርካሪዎችንም የጎማ ፅዳት የመጠበቅ ግዴታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ያለው ፖሊስ ይህንን መልእክት በመተላለፍ ጥፋት ላይ በሚገኙ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
💥
ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
⚡ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን
ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
*ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
*ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
*አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።💥መሰረት /Foundation/
1) ቁፋሮ እና አፈር ሙሌት
⏺መሰረት ሁልጊዜ የተረጋጋ መሬት ላይ ሊቀመጥ ይገባል።
ጥሩ አፈር ካልሆነ በተመረጠ እና ከሌላ ቦታ በመጣ አፈር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እና ተደልድሎ ሊቀመጥ ይገባል።
⏺የተመረጠው አፈር ንብርብር/layer/ በየ 25 ሴ᎐ሜ በሚገባ
ሊጠቀጠቅ ወይም ሊደለደል/compact/ ሊደረግ ይገባል።
⏺በሚደለደልበት ወቅት በተወሰነ ረገድ እያንዳንዱን ንብርብር ለተሻለ ጥቅጠቃ እንዲያመች እርጥበት እነዲያገኝ ውሀ ማርከፍከፍ ያስፈልጋል
2) አርማታ ሙሌት እና የብረት ስራ
⏺ቀጭን አርማታ/lean Concrete/ ከተመረጠው አፈር ሙሌት በላይ ሊደረግ ይገባል እንደ አስፈላጊነቱም እርጥበተ መከላከያ/water proof/ ሊደረግ ይችላል።
⏺አርማታ ሙሌት ለመሰረት፣ ቢም፣ ኮለን እና ወለል ስራ የአርማታ ጥንካሬ በትንሹ C25 ሊኖረው ይገባል በተጨማሪ እንደ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ሊለያይ ይችላል።
⏺የቢም ብረት የላይኛው ብረት መሀል ላይ የታችኛው ደግሞ ኮለን ድጋፍ/support/ ላይ ሊሆን ይገባል እንዲሁም ማት ፋውንዴሽን ላይ የዚህ ተቃራኒ ይሆናል።
⏺ብረት 4D የብረቱን ውፍረት በአራት በማባዛት የሚሰጠንን ርዝመት በመደረብ መተላለፍ ይተበቅበታል።
⏺ዲዛይን ላይ በተቆራረጠ መስመር /hidden line የሚቀመጡ ብረቶች ሁልጊዜ የታች ብረት ሆነው ይቀመጣሉ።
⏺የአርማታ ሽፋን/concrete cover/አብዛኛውን ግዜ 5ሴ᎐ሜ ይሆናል ከመሬት በላይ ግን በ 2᎐5ሴ.ሜ ይሰራል።
⏺በአርማታ ወይም በብረት የሚሰራ ክፍተት መስጫ spacer/ ልንጠቀም ይገባል።
#Foundation
ማስታወቂያ: ለነባር እና ለአዳዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት በሙሉ ፡-
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቤት ልማቱ ጎን ለጎን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር በኢኮኖሚው ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየና እያደረገም ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚኖረው የግንባታ ፕሮጀክቶች በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት ያሰበና ለዚህም ይረዳው ዘንድ በከተማችን ያሉትን የስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን በመመዝገብ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ እና መመልመል አስፈላጊ ሆኖ ማግኘቱን በቅርቡ በተቋሙ ማህበራዊ ድረ-ገጽ አሳውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ለነባር እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎች ከቀን 13/10/2015 - 27/10/2015 ዓ.ም ድረስ ለለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት online ምዝገባ ማካሄድ እንደሚጀመር እየገለጽን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) https://www.aahdc.gov.et
በመጫን እና የሚጠይቀውን መረጃ በአግባቡ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
በነባር፡-
በተቋማችንና በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ትስስር ተደርጎላችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ ስራ ተቋራጮችና ማህበራት ነባር በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማድረግ ያለባችሁ ሲሆን፤
በአዲስ፡-
ከዚህ በፊት በተቋማችንም ሆነ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ምንም ዓይነት የስራ ትስስር ያልተደረገላችሁ አዲስ በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማካሄድ ትችላላችሁ፡፡
ለምዝገባ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በድጋሚ ለማስታወስ ያህል፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የግበር መክፈያ መለያ ቁጥር( Tax
Identification Number- TIN.)
- የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
- የስራ ልምድ ከ1-2 ገፅ በማይበልጥ
በዝርዝር ይጠቀስ
- የስራ ልምድ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር
የሚያሳዩ መረጃዎች
- እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና
ማህበራቱን የሚገልጹ ሰነዶችን ናቸው
ማሳሰቢያ፡-
ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከሚመለከተው አካል በሚላከው መረጃ መሠረትና በተቋማችን ባለው መረጃ መሠረት ወደ ስራ ሲገባ በነባር መመዝገብ እያለባችሁ በአዲስ ተመዝግባችሁ የተገኛችሁት ላይ እንዲሁም በሁለቱም (በነባርም፣በአዲስም) ተመዝግቦ የሚገኝ ስራ ተቋራጭም ሆነ ማህበራት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን t.me/unityconsupply
ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/ By: Gubaie A.
--------- --------------- ----
በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
.
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡
እንኳን ለኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ: የሰላም የፍቅር የደስታ የመረዳዳት የመከባበር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
ድርጅትዎን" እና አገልግሎትዎን" ከ85,000ሺ ቤተሰብ በላይ ባለው ድረ-ገፃችን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ? በቀላሉ ተደራሽነትዎን' ያሥፉ.. .) ያሳውቁ! ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
📞+251-989-999-001 | +251-
707-999-001 | 09-12-815619
ቴሌግራም ላይ ጥያቄ ሆነ ሀሳብ
ካለችሁ በቀጥታ ከስር /ያለውን:
t.me/UnitySupplydbot ☜|]
ለመልዕክት ይጠቀሙ, ይደርሰናል
ዩኒቲ ኮንስትራክሽን ስራ ኦፊሻሎች
http://t.me/unitysupplydb1
በቋሚነት ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን
ለርስዎና ለወዳጅ ዘመድዎ' በሙሉ
መልካም በዓል እንዲሆን እንመኛለን!
"ዒድ ሙባረክ!
ዩ ኒ ቲ´ | Official
