cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቀጥተኛ እምነት

“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” ዮሐ 8፥32 ። Follow the Orthodoxy channel on WhatsApp:https://whatsapp.com/channel/0029VagYU4E7IUYWqK9aJk0r

Больше
Рекламные посты
1 834
Подписчики
+624 часа
+187 дней
+3730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ከዚህ በፊት መጻሕፍትን የለገሱልኝ ብዙ ወዳጆች አሉ። ወንድም ዮን ገጡ; የአግዛዘቸውን ደቂቅ አስትፋኖስና ..፣ እህት ሜሮን ተፈራ; የቴዎድሮስ ደመላሽን እንታደስን፣ እህት ልያ ;የዶክተር ተስፋዬ ሮቤል መጻሕፍትን ፣ ... ።አኹን ደግሞም ወንድም ተስፋዬ ስዩም[https://www.facebook.com/tilahun.seyoum.35 ]፥ ከታች በፎቶ የሚትመለከቱትን መጽሐፍ አበርክቶልኛል። ኹሌም በልቤ አመሰግናለሁ ክበሩልኝ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ወንጌልና_የሥጋ_ፈውስ! የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5ን በተደጋጋሚ ተምረናል ። ታርኩ በኹላችንም ዘንድ የሚታወቅ ነው፤ ለ 38 ዓመታት የአልጋ ቊረኛ ስለነበረው ሰው። ይኽ ሰው "በውኃ ውስጥ ገብቶ ለመዳን" ለ38 ዓመታት በትዕግስት ጠብቋል ። በርሱ ላይ የመጡና የሄዱ ታማሚዎች እልፍ ናቸው ። ጌታ ግን ይኽንን ሰው ከለመዱት ልዩ በኾነ መንገድ ልፈውስ ወድዷል፤ ሰውየውን በቃሉ ብቻ ከፈወሰው በኋላ፣ ሌሎችን ግን [በሥጋ] አልፈወሰም። ታርኩ በዚህ ጽኑ ተማሚ ተመርኩዞ መሢሑ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ ማስተማር ስኾን፣ በርሱ አለማመን "የከፋ ኃጢአት መሥራት" እንደኾነ የሚያስገነዝብ ነው። የተፈወሰውን  “.. ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ #ከዚህ_የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።'' [ዮሐ 5፥14]።ይኽ የኢየሱስ ንግግርም ለሌሎች ሕሙማን ጭምር መልእክት ነበር። በፈዋሹ እንዲያምኑ የሚያሳስብ ። ጌታ ከሕሙማን መሃል አንዱን ብቻ ፈውሶ መተው፣ ሌሎች ታማሚዎች ለነፍሳቸው ድኅነትን የመንግስቱን ወንጌል እንደሰበከ ያስረዳል ። *ይኽም የሥጋ ፈውስ ዓላማ ወደ መንግስቱ መጥራትና ማንነቱን መግለጥ እንደኾነ ያረጋግጣል ። አስቡት እስኪ; ጌታ ሆስፒታል ሄዶ አንዱን ታማሚ ብቻ ፈውሶ ስወጣ?! የወንጌሉ ዓላማ የሥጋ ፈውስ መስጠት አይደለም ። በሥጋ ፈውስ እግዚአብሔርን መግለጥ እንጂ። ምክንያቱም በሥጋ የተፈወሰ ኹሉ በነፍስም የተፈወሰ ነው ማለት አይደለም። ከሥጋ ፈውስ ይልቅ የነፍስ ፈውስ ይልቃል። ስለዚህም ምክንያት ፈውስ ለነፍስም ጭምር እንዲኾን፣ ለሚያድን ትምህርት እንትጋ!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ወንጌልና_የሥጋ_ፈውስ! የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5ን በተደጋጋሚ ተምረናል ። ታርኩ በኹላችንም ዘንድ የሚታወቅ ነው፤ ለ 38 ዓመታት የአልጋ ቊረኛ ስለነበረው ሰው። ይኽ ሰው "በውኃ ውስጥ ገብቶ ለመዳን" ለ38 ዓመታት በትዕግስት ጠብቋል ። በርሱ ላይ የመጡና የሄዱ ታማሚዎች እልፍ ናቸው ። ጌታ ግን ይኽንን ሰው ከለመዱት ልዩ በኾነ መንገድ ልፈውስ ወድዷል፤ ሰውየውን በቃሉ ብቻ ከፈወሰው በኋላ፣ ሌሎችን ግን [በሥጋ] አልፈወሰም። ታርኩ በዚህ ጽኑ ተማሚ ተመርኩዞ መሢሑ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ ማስተማር ስኾን፣ በርሱ አለማመን "የከፋ ኃጢአት መሥራት" እንደኾነ የሚያስገነዝብ ነው። የተፈወሰውን  “.. ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ #ከዚህ_የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።'' [ዮሐ 5፥14]።ይኽ የኢየሱስ ንግግርም ለሌሎች ሕሙማን ጭምር መልእክት ነበር። በፈዋሹ እንዲያምኑ የሚያሳስብ ። ጌታ ከሕሙማን መሃል አንዱን ብቻ ፈውሶ መተው፣ ሌሎች ታማሚዎች ለነፍሳቸው ድኅነትን የመንግስቱን ወንጌል እንደሰበከ ያስረዳል ። *ይኽም የሥጋ ፈውስ ዓላማ ወደ መንግስቱ መጥራትና ማንነቱን መግለጥ እንደኾነ ያረጋግጣል ። አስቡት እስኪ; ጌታ ሆስፒታል ሄዶ አንዱን ታማሚ ብቻ ፈውሶ ስወጣ?! የወንጌሉ ዓላማ የሥጋ ፈውስ መስጠት አይደለም ። በሥጋ ፈውስ እግዚአብሔርን መግለጥ እንጂ። ምክንያቱም በሥጋ የተፈወሰ ኹሉ በነፍስም የተፈወሰ ነው ማለት አይደለም። ከሥጋ ፈውስ ይልቅ የነፍስ ፈውስ ይልቃል። ስለዚህም ምክንያት ፈውስ ለነፍስም ጭምር እንዲኾን፣ ለሚያድን ትምህርት እንትጋ! [በኢየሱስ ካለማመን; ከ38 ዓመታትም በላይ በሥጋ መታመም ይሻላል!]
Показать все...
ከማቴዎስ ወንጌል ጥናቴ [30] “ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።” ማቴ 6፥13 ። የኢየሱስ አስተምህሮ የሚገልጽልን መከራን እንዳንጣራ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን "ጌታ ኾይ የሚገፉትን አብዛልኝ ፣ፈተና ኾይ "ና" ብለው መጸለይ ይፈልጋሉ ። በዚህም ከኢየሱስ አስተምህሮ ጋር በቀጥታ ይቃረናሉ ። እንዲያ ያለ ጸሎት; በሰው ዘንድ እምነት ያለው የሚያስብል ይመስላል ። ግን አይደለም ፤ትዕቢትን የሚገልጽ እንጂ። አማኝ; ወደ ሕይወቱ ፈተና ካልመጣ እራሱን ይፈትሽ እንጂ ፈተናን በጸሎት መልክ መጥራት አይገባም፤ ሥጋዊ ጸሎትን አያድርግ። የፈተና ውጤት ያማሬ ስለኾነ ፈተናን በራስ ፈቃድ መጥራት ትክክል አይደለም ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ነቀፌታ ያላቸውን አማኞችን መለኮታዊ ፈተና አይፈትንም። አስቀድመው ከገቡበት አዘቅት እንዲወጡ ይፈልጋል እንጂ። ለዚያ ነው ሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ለመከራ የተጠራችው። ራእ 2። ጤናማ ስለኾነች። ለዚህ እንደ ማሳያ; የኢየሱስን ጸሎት መመልከት እንችላለን ። ስጸልይ "መከራ ና" አላለም ። እንዲሁም መከራው ይለፈኝ ብሏል። ነገርግን የአባቱን ፈቃድ አስቀደሜ ። ሰው ግን በሰው ዘንድ ልመጻደቅ ዘንድ "መከራ ኾይ ና፣ ጌታ ኾይ ገፊዎችን አብዛልኝ" በማለት የትዕቢት ጸሎትን ያደርጋል ። ጌታን እየመሰለ መኖር የሚወድ መከራ መቀበል አይቀርምና ከኛ የሚጠብቀውን ብቻ እንኹን፤ እናድርግም ። በጤናማ መሠረት ላይ እንቁም ፤ ሃሰትን በግልጽ እንቃወም መከራ እራሱ እያንበለበለ ይመጣል ። ከወዳጅም ከወገንም 'ከአማኝም'። ስለዚህም ባለማወቅ በትዕቢት ሥጋዊ ጸሎት እንዳናደርግ ። እንጠንቀቅ ።ይኽንንም እንወቅ ። ጸሎቱን ስንጀምር "መንግስት ትምጣ" በማለት ጸለይን ፣ "መንግስትህ ትምጣ" ማለታችን በኛ መካከል በሚሉአት ይገለጥ ዘንድ መለመናችን ስኾን፣ እግዚአብሔር የሚነግስበት ጊዜ አለው ማለት ግን አይደለም ።ምክንያቱም መንግስት የርሱ ናትና ።ለዘለዓለም ። እግዚአብሔር ንጉሥ የኾነበት ጅማሮ የለውም። እርሱ ነግሶ ያለ ነው። ከኹሉ በላይ። እንደ ምዲራዊ ንጉሥ "በንግስና ቆይልን" አይባልለትም። ሺህ ዓመት ንገስልን በማለት ማንም መልካም ምኞቱን አይገልጸውለትም። ወይም እንኳን ለዚህ ንግስና አበቃይ አይባልለትም።ነግሶ የሚኖር። ያለ ነው። መንግስቱ፣ ግዛቱ፣ ንግስናው ጅማሮ ኾነ ፍጻሜ የለውም። ይገርማል እግዚአብሔር ከጊዜ ወደጊዜ ኃይሉ እየገነነ የሄደበት አይደለም ። እርሱ ኃያል ነው። የማይደፈር። ፍጥረታት ከመፍጠራቸውም በፊትም ። ከኹሉ በላይ ነው። እርሱ ክብሩ ከፍ ከፍ እያለ የሄደበት ጊዜ የለውም። ከብሮ ያለ ነው። ይኽ የሚያሳየው በፍጥረታት መፈጠር ለጌታ የተጨመረ ነገር እንደሌለው ነው። እርሱ ያው ነውና። ጉድለት የለበትም። ለዚህም ነው ብናመሰግነው ጥቅሙ ለኛ የሚኾነው ። ተባረኩ። ቊ.29 https://t.me/FistumTehadiso/1235
Показать все...
#ሰላም_ለናንተ_ይኹን_ወዳጆቼ|| ያስፈልግሃል የሚትሉትን መንፈሳዊ መጻሕፍትን [pdf ብኾንም እንኳ] ብትልኩልኝ በብዙ ትረዱኛላችኹ 👐፤ በተለይ በአኹኑ ሰዓት ከዘመን ፍጻሜ ጋር ፣ ከራእይ ዮሐንስ መጽሐፍ ጋር፣ ከዳንኤል መጽሐፍ ጋር ወ.ዘ.ተ ተቀራራቢ ኾኖ ፥ የኔን ሃሳብ የሚደግፍም የሚቃወምም ብኾንም እኲል ይጠቅመኛልና እንዲትልኩልኝ አሳስባለሁ! ✅ @ediluyohannes16
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተማሪዎች፥ "ልጁ ኢየሱስ ስላይደለ ሴቲቱም ቤተክርስቲያን አይደለችም" የሚል ደካማ ሙግት ያነሳሉ። የሴቱቲ ቤተክርስቲያን መኾን በልጇ ላይ የተሞረኮዘ እንዳልኾነ ብረዱ መልካም ነበር። ራእይ 12 ። ካስተዋላችኹ; ሴቲቱ የፍላድልፊያ ቤተክርስቲያን የድል ነሺዎች ተስፋ ቃል ወራሽ ስትኾን፣ ልጁ ደግሞ የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ተስፋ ቃል ወራሽ ነው። ራእይ 2፤3 ይመልከቱ። በብረት በትር አሕዛብን መቀጥቀጥ የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ ኃይሉም የእርሱ ነው፤ እግዚአብሔርም ለኢየሱስ ይኽንን ስልጣን ሰጠ ፤ ኢየሱስም ለድል ነሺ አማኞች "እንደራሱ ያለውን ሥልጣንን" ሰጠ ፤ ስለዚህም "አሕዛብን ይቀጠቅጣል" ስለተባለ ልጁ ኢየሱስ ነው ማለት አይደለም። ለድል ነሺ አማኞች የተሰጠ የተስፋ ቃል ጭምር እንጂ። ደግሞም ልጁ ኢየሱስ እንዳልኾነ እንደገናም እንናገራለን; ኢየሱስ እንደገናም፣ ብቻውም አይነጠቅምና። በስፋት እነዚህ ነገሮች ተብራርተዋል፣ pdf ያነብቡ። አለማወቅ ወይም ለማወቅም አለመፈለግ፥ አማኝነት አይደለም!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በፎቶ የምትመለከቷቸው ቤተእምነቶች የተመሠረቱበትን አስተምህሮ፣ ዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ << ያለ እውነት፣ "የእውነት ቃል" አገልግሎት !? >> በሚል ርዕሰ ባዘጋጀው መጽሐፉ ፦ስለ ትምህርቱ አጀማመር ታርካዊ ዳራ፣ ለዚህ አስተምህሮ ይመች ዘንድ ያዘጋጁትን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ይገመግማል፣እንዲሁም በአምልኮ፣ በጸጋና በመንግሥቱ ወንጌል ያላቸውን ስሁት አስተምህሮአቸውን በስፋት ይዳስሳል።ደግሞም የጸጋ ስጦታ ቆሟል ስለማለታቸው በቃሉን እውነት በአስረጂ ነጥቦች ይሟገታል። *መጽሐፏ ተሐሶዊያን ስታደስ እንዳይፈርስ ትጮኻለች! *ጆን ኔልሰን ደርቢ (1800-1882 ዓ.እ) የወንድማማቾች ቤተክርስቲያን መሥራች..ስኾን የእስራኤልና የቤተክርስቲያን ትስስር በሐዲስ ኪዳን ምንደኾነ ለመግለጥ እያጠነጠነ፣ << በመጨረሻም የደረሰበት ድምዳሜ ፦ *"መጀመሪያ የክርስቶስ አመጣጥ ለክርስቲያኖች ነው፤በኋላ ላይ ግን በልዩ ክብር ንግሥናቸውን ይመልስላቸዋል፤ አይሁድም ደግሞ ብቻቸውን ምድራዊ ንግሥናንና ባለጠግነት ከመሢሑ ጋር በምድር ላይ "ይቋደሳሉ፤ *እነዚህ ኹለት ክሥተቶች በእግዚአብሔር ጊዜ ተለያይተው ከተፈጸሙ በኋላ የእግዚአብሔር ቊጣ በምድር ላይ ይፈስሳል፤ በዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያን ከዓለሙ ተለይታ ልዩ ደስታን በሰማይ ከክርስቶስ ጋር ታደርጋለች። >> [1] *ምን ልላችሁ ነው? የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጠቀት አስተምህሮ ፥በመጽሐፍ ቅዱስም ኾነ በጥንት አባቶችም እንዲሁም [በሉተርም] ዘንድ የማይታወቅ እንግዳ ትምህርት ነው። ሃሰተኛ አስተማሪዎች የሠሩት ስሁት አስተምህሮ ነው። [1] ዲያቆን አቤንኤዘር፣ ያለ እውነት፣ የእውነት ቃል አገልግሎት !?፣ 2013 ዓ.ም ፣ገጽ 24፣
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተማሪዎች ''ዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 4 ጀምሮ ቤተክርስቲያን የሚል ስም ስላልተጠቀሰ፣ መልእክቱ ቤተክርስቲያንን አይመለከትም''  ማለታቸው፣ በስሙ ደብዳቤ ተጽፎ የተላከለት ግለሰብ፥ "በደብዳቤው መሃል ስሜ አልተጠቀሰምና አይመለከተኝም" የሚልን ሰውን ይመስላሉ። ልምሰላቸው ብዬ እንጂ እንዲያ የሚል ሰውስ እንኳ አይኖርም ። ለ7ቱ አብያተክርስቲያናት የተላከውን መልእክት [ራእ1፥11]፣ለዚያውም ለአሕዛብ አብያተክርስቲያናት የተሰጠውን ደብዳቤ እንዴት ለቤተክርስቲያን አይደለም ይላሉ?! እያስተዋልን ወገን!
Показать все...
እንዴትስ ያለ ውብ ዝማሬ ነው 👐፤ ተባረክ።ቀን ሙሉ ሳሰላስለው 😓፤ስሰማው ❤ ።ጸጋ ይብዛልህ ። ___ https://youtu.be/TZ3W9ANoS0M?si=4bg0lFFTH_Amj4gQ
Показать все...
ኢየሱስ ደግ ነህ - ቢኒያም ደሳለኝ | Eyesus Deg neh - Biniyam Desalegn[Official Visualizer] @faithstudioEthiopia

ደግ ነህ (የመዝሙር ግጥም) -------------------------------------- 1 ከአባትነትህ መርጦ ድሎት ደክርቶ ሲመለስ ከሸፈተበት እየሮጠክ ሄደህ አንገቱን ሳምከው ስታየው ራርተህ አንጀትህ ተላውሶ ምህረትን ሰጠኸው እንደወደድከኝ ቀርቶ አንተን ላፈቅር እንዲያው ተችሎ ቦታ እንቀያየር አትጠራጠር ሀሳብ ሳልቀይር እንኳን ልምርህ ገድዬህ ነበር አዝማች አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ ኢየሱስ ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ 2 ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቀህ እንዳዳንከኝ የጭንቅ ቀን ጩኸቴን እንደሰማኸኝ ልቤ አስታውስ ስላለፈው ሊያመሰግን ሲል እምባ ቀደመው ወደህ ወደህ መች ሰለቸህ ሰተህ ሰተህ አልደከመህ የሰው መውደድ ዛሬ ቢያበቃ ባንተ ፍቅር ግን ልቤ አይሰጋ አዝማች አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ ኢየሱስ ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ 3 ለሚወዱህ ለጠሉህም ለቀረቡህ ለራቁህም ቢፈለግ ቢፈለግ | እንደእግዚአብሔር የታል ደግ |×2 አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ ኢየሱስ ደግ ነህ ደግ ነህ አንተ ግን ደግ ነህ ደግ ነህ -------------------------------- #Biniyam_Desalegn #ደግ_ነህ

#ከዮሐንስ_ራእይ ምዕራፍ 4 ጀምሮ ቤተክርስቲያን ተነጥቃለችና ለቤተክርስቲያን የተጻፈ አይደለም የሚለው አስተምህሮ በቃሉ ስፈተሽ|| "ወደዚህ ውጣና #ከዚህ_በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።” ራእይ 4፥1። <<ዮሐንስ መጀመሪያ ድምጹን ሰምቶ ደንግጦ እንደሞተ ሰው የኾነለት [ራዕ1፥12]፣ "ያ" የፊተኛው ድምጽ ኢየሱስ ክርስቶስ"ከዚህ በኋላ ሊኾን የሚያስፈልገውን አሳያለሁ" አለው። ‘’ ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ’’ ማለቱ #ዮሐንስ_ከተመለከተ_በኃላ_ጀምሮ_የሚፈጸሙ ትንብቶችን እንደ ሆነ እንጂ የመጨረሻ መጨረሻው ፍጻሜ ላይ ያለውን ብቻ የሚያመላክት አይደለም፡፡ ከዚህ መባሉ አሁን ጀምሮ ያለውን እንጂ የወደፊቱን ብቻ አያሳይም፡፡ ደግሞም መጽሐፍ� “እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።” ራእይ 1፥19/፤ ስል ̋ከዚህም ̋ መባሉ አሁን ጀምሮ ተፈጻምነት ያለውን ትንቢት መገለጡን ያስረዳል ፡፡ ስለዚህም ከዚህ ክፍል ተነስተው ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኃላ ያለውን የመጨረሻ ጊዜ ላይ ያለውን መልእክት /ብቻ/ ያመለክታል መባሉ አያስኬድም እልለሁ፡፡� >> *የቤተክርስቲያን ቅድሜ መከራ ንጥቀት አስተምህሮ በቃለ እግዚአብሔር ስመዘን፣ ገጽ 30-31። መጽሐፏን ታነቡትና ታተርፏት ዘንድ ጸሎተ ነው።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.