cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

HabeshaStudent

www.habeshastudent.com engaging telegram channel. Share to all your youth friends!

Больше
Рекламные посты
202
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ውጤታማ ፀሎት መርህ አለው! "አባት ሆይ" ብሎ መፀለይ ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማረን የፀሎት መርህ አንዱ ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ ሲፀልይ ሁል ጊዜም አባት ሆይ ብሎ ሲፀልይ እናገኛለን:: ዮሐንስ ወንጌል 17 ምን ብለን እንደምንፀልይ ፣ ማን ብለን እንደምንፀልይ ፣ ፀሎታችንን የምናቀርብለት ማን እንደሆነ ማወቅ የፀሎታችን መልስ የያዘ ትልቅ ቁልፍ ነው! “እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፤ አባታችን ሆይ...” ሉቃስ 11:2 “ቅዱስ አባት" ዮሐንስ ወንጌል 17:11 "ጻድቅ አባት" ዮሐንስ ወንጌል 17:25 የበለጠ ለማንበብ... https://www.habeshastudent.com/a/prayers.html
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በዚህ ዓለም እጅግ አሰቃቂ ስቃይና መከራ የመኖሩ ነገር አጠያያቂ አይደለም፡፡ አንዳንዱ የሚደርሰው በራስ ወዳድና ጥላቻ በተሞሉ ሰዎች ምክንያት ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ በዚህ ሕይወት ውስጥ ማለፍ አስፈራኝ በማለት የሚመጣ ነው፡፡ እግዚአብሐየር ግን እራሱን ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን በመሰለው መከራ ውስጥ ማለፍን የቀመሰው መሆኑን እንድናውቅ አድርጓል ስለዚህም ስቃያችንንና መሻታችንን ያውቃል፡፡ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ”ሰላምን እተውላችኃለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኃለሁ፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም፡፡ ልባችሁ አይጨነቅ አይፍራም፡፡” እንድንፈራ እንድንጨነቅ የሚያደርገን ከበቂ በላይ የሆነ ምክንያት አለን እግዚአብሔር በፊታችን ካለው ችግር የሚበልጥ ሰላምን ይሰጠናል፡፡ እርሱ እኮ ፈጣሪ የሆነ እግዚአብሔ(አምላክ) ነው፡፡ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ፍጥረተ አለምን ሁሉ የፈጠረ ከሁሉ ነገር ጀርባ ሆኖ የሚቆጣጠር እርሱ ነው፡፡ የበለጠ ለማንበብ... https://www.habeshastudent.com/a/why.html
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እግዚአብሔር ማነው? ሊታወቅ ይችላል? ታላቁንና በፈጠራ ችሎታው ተደናቂ የሆነውን የሥነ-ፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔርን ልናውቀው እንችላለን፡፡ በግል እንድናውቀው ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንድንፈጥር ይጋብዘናል፡፡ ስለ እርሱ ማወቅ ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱን በቅርብ ልናውቀው እንችላለን፡፡ “እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው” (መዝ 145፡18) እግዚአብሔርን የበለጠ እንድታውቁት እናበረታታለን፡፡ ስለዚህ ነገር የበለጠ ሊያብራሩ የሚችሉ አማካሪዎች ስላሉ በዉስጥ መስመር እንዲያገኙን እናበረታታለን። የበለጠ ለማንበብ...https://www.habeshastudent.com/a/whois.html
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከዚህም የሚበልጥ ነገር መኖር አለበት ብላችሁ ያሰባችሁበት ጊዜ የለም? እንደው በቀላሉ ከሕይወት ባሻገር (ከመኖር በላይ) አንድ ነገር መኖር እንዳለበት አስባችሁ አታውቁም ? ሕይወት የራሷ ውጣ ውረድ አላት። በትገልም የተሞላችም ናት። ግን የሕይወትን ትርጉም ማወቅና የሚያረካትን መምረጥ ብቻ ሰላምና ደስታን ይሰጣል። ይህንንም የምናቅውቀው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ነው። ስለዚህ ነገር የበለጠ ሊያብራሩ የሚችሉ አማካሪዎች ስላሉ በዉስጥ መስመር እንዲያገኙን እናበረታታለን። የበለጠ ለማንበብ...https://www.habeshastudent.com/a/reallife.html Join our telegram group https://t.me/habeshastudent
Показать все...
Repost from Tesfa
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ምስክር_ነኝ በጸጋ የዳንነው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ነው እንጂ በራሳችን ጥረት ወይም ሥራ አይደለም። በጸጋ ብቻ፤ በእምነት ብቻ ነው። እግዚአብሔር የወደደን ፣ይቅር ያለን እና ያዳነን በማንነታችን ወይም በምንሰራው ነገር ሳይሆን በልጁ በክርስቶስ ስራ ነው። ለአንተም በጸጋው የመዳን ስጦታ ተሰጥቶሀል። እርሱም የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት፣ አዲስ ሕይወት እና በሰማይ ያለውን የዘላለም ሕይወት ማግኘት ነው። በማመን ብቻ የሚገኘውን ይሄን ህይወት ልትኖር ትወዳለህ? ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2:8-9 ለጓደኛዎ ያጋሩ! #tesfa #acts1120 #GCME #kalehiwot #Antsokiya
Показать все...
Connect to Mentor
Repost from Tesfa
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ምስክር_ነኝ ኢየሱስም ወደ እግዚአብሔር መድረሻ ብቸኛ  መንገድ ነው፤ እርሱ ከብዙዎች አንዱ ሳይሆን አንድ እና አንድ መንገድ ነው።  ኢየሱስ የእውነት ሁሉ ምንጭ ነው።   ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር  ያለውን እውነት ሁሉ አሳይቶናል። ዓለምና ሕይወት ሁሉ የተፈጠሩት በክርስቶስ ነው። ኢየሱስ የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖርህ ነው የመጣው። በአዳም ኃጢአት ምክንያት ለመጣው የሞት ችግር ኢየሱስ  ክርስቶስ ብቻ መልስ ነው።መንገድ ኢየሱስ ነው ከሱ ውጪ ያለው ሁሉ ገደል፤ እውነት ኢየሱስ ነው ከእርሱ ውጪ ያለው ሁሉ ሀሰት፤ ህይወት ኢየሱስ ነው ከእርሱ ውጪ ያለ ሁሉ ሞት ነው። አንተስ ወንድሜ ወደአብ ምትደርስበት ብቸኛውን መንገድ ልትከተል ትወዳለህ? ልንረዳህ ዝግጁ ነን። ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐንስ 14፥6 #tesfa #acts1120 #GCME #kalehiwot #Antsokiya
Показать все...
Connect to Mentor
Repost from Tesfa
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ምስክር_ነኝ የእግዚአብሔር ሀሳብ እጅግ የተለየ ነው፤ የመዳንና የሕይወት ተስፋ  በራሳችን ማግኘት ስለማንችል ፤በራሳችን ልንደርስበት ስላልቻልን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ በመገለጥ ወደ እኛ አቅርቦልናል።    ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት እንዳስነሳው በልብህ ማመን እውነትን መቀበል  ነው።  ህይወትህን እንደሚለውጥ እና ለዘለአለም ደስታ እንደሚሰጥህ እርግጠኛ መሆን ማለት ነው። አምነህ የምትጸድቅው በልብህ እና በአፍህ መናገር  ነው። በማመን ብቻ ወዳለህ ዘላለም ህይወት ልትገባ ትወዳለህ? ልንረዳህ ዝግጁ ነን። “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤”   — ሮሜ 10፥9  #tesfa #acts1120 #GCME #kalehiwot #Antsokiya
Показать все...
Connect to Mentor
Repost from Tesfa
https://bit.ly/ሃጢያተኛነኝ1 👆#ምስክር_ነኝ
Показать все...
ሃጢያተኛ ነኝ!?

ይህንን አጭር ቪዲዮውን ይመልከቱ

Connect to Mentor
Repost from Tesfa
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ምስክር_ነኝ አዳም በእግዚአብሔር በተሰጠው ተእዛዝ ላይ ባመፀ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የመቤዠት እቅድ አመጣ ዕቅዱም ከዳዊት ዘር የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ወደ እርሱ ሊመጣ የሚወድ ይድናል። መዳን በእርሱ ነውና። በምሕረቱ ባለ ጠጋ የሆነው እግዚአብሔር " በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ይሄን ወስኖለታል፤ መዳን በማንም የለም። ይሄን ህይወት እግዚአብሔር ላንተም ወስኖልሀል ወደዚህ ህይወት ልትቀርብ ትወዳለህ? ልንረዳህ ዝግጁ ነን። መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። — ሐዋርያት 4፥12 #tesfa #acts1120 #GCME #kalehiwot #Antsokiya
Показать все...
Connect to Mentor
Repost from Tesfa
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ምስክር_ነኝ የዘላለም ሕይወት በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው እንጂ ለሥራህ ሽልማት አይደለም።  የዘላለም ሕይወት በክርስቶስ ውስጥ ነው፤የዘላለም ሕይወት ከእርሱ ዘንድ እና  በእርሱ አለ፤ ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ግን ሕይወት የለውም፤ " እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠ ምስክሩ ይህ ነው።   ሕይወት በልጁ በአየሱስ ክርስቶስ መሆኑ:: እኔ ምስክር ነኝ ቃሉ ታማኝ እና እውነት ለዘላለምም ፀንቶ የሚኖር ነው። በኃጢአት ለወደቀው ከእግዚአብሔር የተሰጠው ዋስትና የዘላለም ህይወት ነው። ይሄም ህይወት የሚገኘው  በልጁ በኩል ነው። ዘላለማዊነትን የመስጠት ስልጣን ያለው፤ ድህነትን ፈልገው ወደእርሱ ለሚመጡ ሁሉ ህይወትን የሚሰጠው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንተስ ልትድን፣ የዘላለም ህይወትን ልታገኝ ትወዳለህ? ልንረዳህ ዝግጁ ነን። እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። – 1ኛ ዮሐንስ 5: 11-12 ለጓደኛዎ ያጋሩ! #tesfa #acts1120 #GCME #kalehiwot #Antsokiya
Показать все...
Connect to Mentor
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.