cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቤተ መጻሕፍት

ይህ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ቀዳሚ የሆነው የጥንታዊው የመልዕልተ አድባራት ቀራንዮ መድኃኔዓለምና የሙት አንሣው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ተዋሕዶ ሰንበት ትምህርት ቤት የአቡነ ኢየሱስ ሞዓ ቤተ መጻሕፍት የቴሌግራም ቻናል ነው።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
306
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ቀራንዮ መድኃኔዓለም አዲስ አበባ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኝ ደብር ነው ከአዲስ አበባ አድባራት ሁሉ ቀዳሚው ነው የተተከለው በ1826 ዓ.ም. በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዘመን ነው። በዚያን ጊዜ ፊንፊኔ በእቲሳ ተክለ ሃይማኖት አለቃ በአባ ዘወልደ ማርያም ሥልጣን ሥር ነበረች። በአካባቢው ያልተጠመቁትን ማጥመቅና ክርስትናን ማስፋፋት ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ለአባ ዘወልደ ማርያም የተሰጠ ተልእኮ ነበረ። የዚህ ተልእኮ መጀመሪያ ያደረጉትም ቀራንዮ መድኃኔዓለምን መትከል ነበር ሲተከል በእቲሳ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ሥር ነበር ደብሩን ይጠብቁት የነበሩት 300 ወታደሮች በአንድ ሌሊት በአካባቢው ጦረኞች ተገድለው አደሩ በዚህ ምክንያት የንጉሡ ታላቅ ልጅ ደጃዝማች መሸሻ ሠይፉ ታዝዘው አካባቢውን አሠሡት። በ1901 ዐፄ ምኒልክ ደብሩ ከእቲሳ ተክለ ሃይማኖት አስተዳደር ወጥቶ ራሱን እንዲችል በማድረግ ስሙን ቀራንዮ ብለው ሰየሙት። 15 ጋሻ መሬት ለደብሩ 2 ጋሻ መሬት ለአለቃው ተሰጥቶ ነበር። ምንጭ፦ከበደ ተሰማ ፣ የታሪክ ማስታወሻ / 1962/ ገጽ 39 ፤ የኢትዮጵያ ብራና መጻሕፍት መጽሔት ፣ ቅጽ 1 ቁጥር 1 /1967/ ፤ Haile Gabriel Dagne, oral information on the Establishment of churches in Addis ababa, International symposium on the centenary of Addis ababa(24 -25,Nov, 1986).IES library, page 275. ( ከሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት, የቤተክርስቲያን መረጃ መጽሐፍ የተወሰደ) 💚 @AbuneEyesus💚 💛 @AbuneEyesus💛 ❤️ @AbuneEyesus❤️
Показать все...
ጸሎተ_ሃይማኖት_ትርጓሜ.mp338.69 MB
የአቤል ደግነት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአቤል የየዋሃቱን ዋጋ ያሰጠችው መኾኗ በአባ ሕርያቆስ ተመስክሮላታል። ይኸውም አባታችን አዳም ሔዋንን በግብር ካወቃት በኋላ ቃየልንና ሉድን ወልዳለች ፤ ኋላም ቃየልንና ሉድን ካሳደገች በኋላ ወንድሙን አቤልንና አቅሌማን ወለደች( ዘፍ 4+1, ኩፋ5+8 ) ፤ ስለኹለቱ ወንድማማቾች ታሪክ የሚናገረው የአዳም ገድልና ትርጓሜ ኦሪት ቃየል ከልጅነቱ ጀምሮ ክፉ እንደነበር ያስረዳል ። ይኸውም አዳም መሥዋዕት ለማቅረብ እንኺድ እንኳ ሲለው አይሆንም እያለ ይቀር ነበር። '' ወኮነ ብዙኅ ጊዜ ሶበ ያዐርግ ቁርባነ አቡሁ ይተርፍ ወኢየዐርግ ምስሌሆሙ '' ይለዋል ትርጓሜ ኦሪት። ወንድሙ አቤል ግን ከሕፃንነቱ ዠምሮ ደግ ስለነበር ለአባቱና ለእናቱ ይታዘዝ ደስ ያሰኛቸው ነበር ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ ያተጋቸው ነበር ፤ ወአቤልሰ ኮነ ሎቱ ልብ ጥዑም ወኮነ ይደነግፅ ለአቡሁ ወለእሙ ወየሀውኮሙ በእንተ ቁርባን ብዙኅ ጊዜ እስመ ውእቱ ኮነ ያፈቅር ቁርባነ '' ይለዋል። ኹለቱ ወንድማማቾች እንዲህ ኾነው ካደጉ በኋላ አቤል በግ ጠባቂ ሲሆን ቃየል ገበሬ ኾነ፤ አባታቸው አዳምም ትውልድን ለማራራቅ ሲል የቃየልን መንትያ ሉድን አቤል ፤ የአቤልን መንትያ አቅሌማን ቃየል ያግባ አለ ፤ ቃየል ግን በአባቱ ሐሳብ አልተስማማምና ፤ በዚኽ ምክንያት አዳም መሥዋዕት ሠውና መሥዋዕቱን የተቀበለለት ሉድን ያግባ አላቸው። አቤልም ንጹሐ ባሕርይ እግዚአብሔር ንጹሕ ነገር ቢያቀርቡለት ይወዳል ብሎ ከበጎቹ በኩራት ጸጒሩ ያላረረውን ፣ ቀንዱ ያልከረከረውን ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረውን ፣ ዓመት የኾነውን ጠቦት አቀረበ። እግዚአብሔርም የልቡናውን ቅንነት የመሥዋዕቱን መበጀት አይቶ መሥዋዕቱን ተቀብሎታል( ዘፍ 4 + 4) ። ቃየል ግን አባር የመታውን ስንዴ እንክርዳዱን ሳይለቅም አቀረበ ፤ ጌታም የመሥዋዕቱን አለመበጀት ፣ የልቡናውን ጥመት አይቶ መሥዋዕቱን አልተቀበለለትም ፤ በዚኽም ምክንያት ቀንቶ ወንድሙ አቤልን በግፍ ገድሎታል ( ዘፍ 4 + 2- 8, ዕብ 11 +4 )። '' አቤልሰ አሥረጸ ጽድቀ እምነፍሱ '' እንዲል የአቤል ወላጆች አዳምና ሔዋን እንዳያስተምሩት ሕግ አፍራሾች ኾነው ፤ ወንድሙ ቃየል እንዳያስተምረው በክፉ ምኞት እየተጓዘ ፤ ከሌላ እንዳይማር ሌላ አስተማሪ ባልነበረበት ጊዜ ፤ ጽጌያት ከአዕፁቃቸው እንዲፈነዱ እርሱም እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነው ማለትና ከኀሊናው አፍልቆ በደግነቱ በጎ መሥዋዕትን ሲያቀርብ በየዋህነቱም ለሞት በቅቷል። ታላቁ ሊቅ አባ ሕርያቆስም የዚህ የአቤል የደግነቱን ዋጋ ነገትን የሰጠው ክርስቶስን ወልዳ ያስገኘችልን ቅድስት ድንግል ማርያምን ናትና በቅዳሴው በቁጥር ፴፩ '' የዋሃቱ ለአቤል ዘተቀትለ በዓመፃ '' ( በግፍ የተገደለ የአቤል የዋሃቱ አንቺ ነሽ በማለት የየዋህነቱም ዋጋ ያሰጠችው መኾኗን በመጥቀስ እመቤታችንን አመስግኗታል። ምክንያቱም አቤል ይኽንን የየዋህነትና የጽድቅ ሥራን ቢሠራም ፤ ደግነቱ በእደ እግዚአብሔር ለመጠበቅ አበቃው እንጂ ሲኦል ከመውረድ ግን ሊያድነው አልቻለም ፤ የደግነቱን የየዋህነቱን ዋጋው ገነትን ማግኘቱ ክብር ይግባውና ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ካዳነ ወዲኽ ነውና። ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ ላይ ይኽንን የድኅነት ምሥጢር ሲያብራራ '' በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ ፤ ያለ አንቺ ከአንቺ በቀር እንደምን ያለ ፈውስ እንደምን ያለ ይቅርታ ተደረገ ፤ አንቺ ሳትወለጂ ከመወለድሽ አስቀድሞ እንደምን ያለ መድኃኒት እንደምን ያለ ረድኤት ተደረገ ? ኾነ ? አቤል በቃየል በግፍ ተገደለ ፤ ደሙ ማነንም ማነን አላዳነም ፤ የማኅፀንሽ ፍሬ የክርስቶስ ደም ግን አዳምንና ልጆቹን አዳናቸው '' በማለት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ መላውን ዓለምን ያዳነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልዳ ያስገኘችልን መኾኗን መስክሯል ።
Показать все...
የአቤል ደግነት ከአባታቸው ከአዳም ባገኙት ትውፊት መሠረት አቤልና ቃየል መሥዋዕት ማቅረባቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ዘፍ 4 + 3 ። ቃየን አሰስ ገሰስ የበዛበትን መሥዋዕት ከምድር ፍሬ አቀረበ አቤል ደግሞ ከበጎቹ በኩራትና ከስቡ የተመረጠ መሥዋዕት አቀረበ ። በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የአቤል መሥዋዕት ነበር ። እግዚአብሔር ከመሥዋዕቱ በፊት የመሥዋዕት አቅራቢውን ልቡና ይመለከታልና ። '' እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ፤ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግም አልተመለከተም ። '' (ዘፍ 4 +4 ) ቃየን ተናደደ ወንድሙ አቤልንም ገደለው ። የአቤል ደግነቱ ንጹሕ መሥዋዕት በማቅረቡ ብቻ አይደለም የሚታወቀው በደግነቱ ፣ በቅንነቱና በየዋህነቱ እስከ ሞት ደርሶአልና። እግዚአብሔር የመረጣት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በአቤል ደግነት ትመሰላለች ። እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት የተቀበለው ደግነቱን ተመልክቶ ነውና። እመቤታችንም የአምላክ እናት ለመሆን የተመረጠችው በደግነቷ ነው አባ ሕርያቆስም የአቤል የዋሃቱ አንቺ ነሽ በማለት መስክሮአል ።
Показать все...
አባ ሕርያቆስ ሕርያቆስ ማለት ኅሩይ ማለት ነው፡፡ ለሹመት መርጠውታልና አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን ይናገራልና፡፡ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥላሴን የማይናገር የለም ቢሉ ከሁሉ ይልቅ እርሱ አምልቶ አስፍቶ ይናገራልና አንድም ፀሐይ ማለት ነው። አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ እያለ ጽፏልና፡፡ አንድም ብርሃን ማለት ነው የምዕመናንን ልቡና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና፡፡ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል፡፡አንድም ንሀብ ማለት ነው ንሀብ የማይቀስመው አበባ የለም እሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለምና፡፡ይህስ እንደምን ነው ቢሉ ሐዋርያት የተማረ ግብረ ገብ ይሾም ብለው ሥርዓት ሠርተዋልና ይህስ አይደለም ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ አይገኝም ብሎ የተማረ ከሆነ ይሾም ብለዋል በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ብለው ግብረገብ ከሆነ ብለዋል፡፡በጸሎቱ ይጠብቃል በትሩፋቱ ያጸድቃል ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋልና ብለው ፤ ይህም አባ ሕርያቆስ ያልተማረ ግብረ ገብ ነው ቢማርም ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ነበር በብህንሳ በ፼ መነኮሳት በ፼ መነኮሳይያት ተሹሟል በብዙም መሾም ልማድ ነው፡፡ አባ ሆርና አባ ኤስድሮስ በሺህ በሺህ አባ አሞን በሶስት ሺህ አባ ጳኩሚስ በስድስት ሺህ አባ ሰራብዮን በ፼ እንደ ተሾሙ ይህችም ብህንሳ ቅድመ ትሰመይ አርጋድያ ወድኀረ መኑፍ ይላል። ብዙ ጊዜ ስመ ተፋልሶ አግኝቷታል፡፡በፊት አርጋድያ ኋላም መኑፍ ተብላለች ዛሬም ብህንሳ ትባላለች ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ናት እንደ ዘጌ እንደ ቆራጣ እንደ ቀንጠፋሜ እርሱም ግብረ ገብ ነውና ሥርዓት ቢያጸናባቸው ይጣሉታል ያልተማረ ነውና ይንቁታል ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ ከመሾም መማር አይቀድምምን እያሉ፡፡ እርሱ ግን ወእቀውም ዮም በትሕትና ወፍቅር ብሎ እንዲያመጣው እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር በትሕትና ጸንቶ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዳቸው በምን ምክንያት እንሻረው አሉ ወዲያው ቀድሰህ አቁርበን ብለን በዚህ ምክንያት እንሻረው ብለው መከሩ የሱ ግን ተምኔቱ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤቴ ምስጋና እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደ ምግብ ተመግቤው እንደ መጠጥ ጠጥቼው እንደ ልብስ ለብሼው እያለ ይመኝ ነበር ፡ ሥርዓቱን ጨርሶ ከፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ የለመንዋትን የማትነሳ የነገሯትን የማትረሳ እመቤት ገልጻለት ከሊቃውንት ቅዳሴ የሚያስቸግር ማነን እናውጣለት እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ወይእዜኒ ንሰብሖ እስኪል ድረስ ሰተት አድርጎ ተናግሮታል፡፡የሚንቁት የሚጠሉት ይህ የነገሩትን ቀለምስ ስንኳ አከናውኖ መናገር የማይቻለው ዛሬስ እንግዳ ድርሰት እደርሳለሁ ብሎ አገኝ አጣውን ይቀባጥራል ሆነ ብለው አደነቁበት የሚወዱት የሚያከብሩት ከመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እንዲህ ያለ ምሥጢር ከእሩቅ ብእሲ ይገኛል ብለው አደነቁለት፡፡ ወዲያው የሚወዱት የሚያከብሩት ጽፈን ደጉሰን አንይዘውምን አሉ የሚንቁት የሚጠሉት ማን ተናገረ ብለን እንይዘዋለን አሉ እንደልማዱ አድርገን አንይዘውም አሉ በሀገራቸው ለልማዱ እንግዳ ድርሰት የተደረሰ እንደሆነ ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ይጥሉታል ከእሳት ደኅና የወጣ እንደሆነ ከውሃ ይጥሉታል ከውሃ ደኅና የወጣ እንደሆነ ከሕሙም ላይ ይጥሉታል ድውይ የፈወሰ እንደሆነ ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ይይዙታል፡፡ ይህንንም ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ላይ ጣሉት ከእሳት ደኅና ወጣ፡፡ከውሃ ጣሉት ከውሃ ደኅና ወጣ፡ ፡ከሕሙም ላይ ጣሉት ድውይ ፈወሰ ይልቁንም ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ጽፈው ደጉሰው ይዘውታል፡፡ በጥራዝም ዐሥራ አራተኛ አድርገው ጠርዘውታል፡፡ ከዐሥራ አራቱም ቅዳሴ ተአምራት ያልተደረገበት የለም፡፡ የቀደሰበትስ ምን ቀን ነው ቢሉ ከእመቤታችን ከሠላሳ ሦስቱ በዓላት ባንዱ ቀን ነው። አንድ ባሕታዊ ከባለሟልነት የተነሳ ከሠላሳ ሦስቱ በዓላት ማነን ትወጃለሽ ብሎ ጠየቃት ኪዳነምህረትን ልደታን አስተርእዮን ፍልሰታን አለችው፡፡ ከሊህስ ከአራቱ ማንን ትወጃለሽ አላት ከጸባብ ወደ ሰፊ ከጨለማ ወደ ብርሃን የወጣሁበት ነውና ልደቴን እወዳለሁ አለችው። ቀድሞ እኔ ሳልወለድ አባት እናቴን መባችሁን አንቀበልም ብለዋቸው አዝነው ነበር የሳቸው ኃዘን ኃዘኔ ነውና፡፡ እኔን ከወለዱ በኋላ መባቸውን ተቀብለዋቸው ደስ ብለዋቸዋል የነሱ ደስታ ደስታዬ ነውና እንዳለችው የልደታ ለት ነው፡፡ እሱስ ማንን ሊቀድስ ኑሩዋል ቢሉ ከቅዳሴ ሐዋርያት በቀር ሌላ አያውቅም ነበርና ቅዳሴ ሐዋርያትን፡፡ ይህስ አይደለም ሐዋርያት ለእመቤታችን ምንዋ ነው ምን ቢቸግር ተበድሮ ጋሬዳ እንዲሉ ቅዳሴ እግዚእ ሊቀድስ ነበር ምንም ባያነሳ እምድንግል ተወሊዶ ከመ ፈቃደከ ይፈጽም ብሎ በምሥጢር ያነሳታልና። ከባሕር ወዲህስ ማን አምጥቶታል ቢሉ ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ መደበይ ታብር በሚባል ቦታ ይኖር ነበር እመቤታችን ኤፍሬምን ከሶርያ አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ በደመና ጠቅሳ ያሬድ ካለበት አድርሳ አንተ ውዳሴዬን አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ ብላ ነግረውት በዜማ አድርሶታል ከዚህ ዓያይዞ ዐሥራ ሦስቱን ቅዳሴ ሁሉ በዜማ ደርሷል ይህም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡ ከተከዜስ ወዲህ ማን አምጥቶልናል ቢሉ ሳሙኤል ትውልደ ጌዲዎን ዘገበዘ አክሱም ይለዋል እሱ አምጥቶልናልና እሱም ይህን እየደገመ ሲሄድ ክንድ ከስንዝር ከመሬት መጥቆ ይሄድ ነበር ከዕለታትም ባንዳቸው ይህን ደግሞ ውኃውን ቢባርከው ኅብስት ሁኖለት ተመግቦ ምዕመናንን መግቧቸዋል፡፡ ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፡፡ ረስዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፡፡ ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ ሥረዪ ኃጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ እስመ ኩሉ ገቢረ ማርያም ትክሊ እንዳለ ደራሲ የፍቅር ምልክት ሁለት ንዋያት ሰጥታዋለች ይኸውም ነጭ ዕጣን ዕንቁ ነው ሊቀ ካህናት ሳሙኤል እንዘ ይጼሊ በቅዳሴሃ ፡፡ማርያምሂ እኂዛ በእዴሃ አምጽአት ሎቱ ክልኤተ አምኃ እንዲል፡፡ ከዚህ አያይዛ ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ ጋር አንድ አድርጎ ሚደግመውን ሰው አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አገባዋለው ብላ ተስፋውን ነግራዋለች ይኸውም ሊታወቅ ዛሬ በዋልድባ ያጠና በቃሉ ያላጠና በመጽሐፍ ቅዳሴ ማርያምን ሳይደግም የሚውል የለም ይህም ተስፋ ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ ጋር አንድ አድርጎ ለሚደግም ሰው ሁሉ ነው እንጂ ለሱ ብቻ አይደለም ፡፡ አንድ ባሕታዊ ከምስጋናሽ ሁሉ ማነን ትወጃለሽ ብሎ ቢጠይቃት ልጄ ዳዊትን አቡነ ዘበሰማያትን ቢደግሙለት እንዲወድ እኔም ውዳሴዬን ቅዳሴዬን ቢደግሙልኝ እወዳለሁ ብላዋለች እሱ ተሹሞ ሳለ ብዙ ድርሳን ደርሷል ብዙ ተግሣጽ ጽፏል። ከብዙውም አንዱ ይህ ቅዳሴ ነው፡፡ዕረፍቱ በጥቅምት ሁለት ነው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ። ምንጭ ፦ የ14ቱ ቅዳሴያት አንድምታ
Показать все...
እንኳን ለጾመ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ <<ፍልሰታ>> የሚለው ቃል የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው። (ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ ገጽ 88) የእመቤታችን ትንሣኤ እንደ አንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ከነቢያት አንዱ ክቡር ዳዊት " ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦትም " ይላል መዝ 131÷10። በዚህም ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳፍርበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሣ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደሪያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች ። ንጉሥ ሰሎሞንም "ያውሥእ ወልድ እኁየ ወይብለኒ ተንሥኢ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ልጅ ወንድሜ ወልድ (እግዚአብሔር ) ርግቤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ ፣ ውበቴ ሆይ ነይ አለኝ "ብሏል።መኃ2፥10።እዚህ ላይ"ወዳጄ-ዉበቴ"የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ምክንያቱም የሰው ዘር በሙሉ በሰይጣን ባርነት ተይዞ በጨለማ በነበረበት ጊዜ ብርሃን ክርስቶስን ያስገኘች ሙጻእ ፀሐይ በመሆኗ " ወዳጄ " ይላታልና። እመቤታችን በውስጥ በአፍአ፣በነቢብ ፣ በገቢር ፣በሐልዮ ፍጹም ነቅዕ በሌለባት ፤ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ድንጋሌ ሕሊና የተባበሩላት፤በነፍስ በሥጋ በልቡና ንጽሕት ቅድስት ልዩ በመሆኗ " ውበቴ ይላታል። እንዲህ ሆና በመገኘቷም ለእናትነት መርጧታል። መርገመ ሔዋን ያልወደቀባት ለአምላክ እናት የተጋባች መሆኗን ሲገልጽም እንዲህ ይላል፦"ኵለንታኪ ሠናይት እንተ ኀቤየ አልብኪ ነውር በኢምንትኒ ላዕሌኪ-በእኔ ዘንድ ሁለንተናሽ ያማረ ነው፣ ምንም ምን ነውር ነቀፋ የለብሽም።"እመቤታችንን በእኔ ዘንድ ሁለንተናሽ ያማረ ነው፣ገቢረ ኃጢአት የለብሽም፣ነቢብ የለብሽም፣ሐልዮ ከነትንታው ስንኳ የለብሽም እንዳላት መናገር ነው።መኃ4፥7። እንግዲህ ክቡር ዳዊት "በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች "እንዲል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የክርስትናን ፍሬ ማፍራት ካየች በኋላ በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ "ተነሽ ነይ" አላት። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ፈርሶ በስብሶ እስከ ትንሣኤ ዘጉባኤ በከርሠ መቃብር ይቆይ ዘንድ የማይገባ ስለሆነ በልጇ ፈቃድ እንደተነሣች ቅዱስ ያሬድ ሲያስረዳ :-"ተለዐለት እምድር ወበህየ ነበረት ዘምስለ ወልዳ በየማነ አብ ወመንፈስ ቅዱስ ከምድር እስከ ሰማይ ዐረገች በሰማይም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች" ብሏል። ስለዚህ ይህንና ይህን የመሰለውን ሁሉ ይዘን ልደቷን ÷ ዕድገቷን ÷ መጽነስ መውለዷን÷ስደቷን÷ዕረፍቷን ÷ ትንሣኤዋን እንዘክራለን እንመሰክርማለን። የፍልሰታ ጾም ከነሐሴ አንድ እስከ አስራ አምስት ያሉትን ቀናት የያዘ ነው። ታሪኩም በነገረ ማርያም እንዲህ ተጽፏል። እመቤታችን ጥር 21 ቀን በግምት በ39 ዓ.ም ዐርፋ ሐዋርያት ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ የመቃብር ቦታ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇን ሞተ ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያሳድሙ እንደኖሩ እሷን ዛሬ እንዲሁ ሊያደርጉ አይደለምን በማለት "ቅዱስ ሥጋዋን ያቃጥሉት ዘንድ ተማከሩ ። ታውፋንያ የተባለ የጎበዝ አለቃ ቀድሞ ደርሶ የአልጋውን ሸንኮር በመያዝ ከመሬት ሊጥላት ሲሞክር መልአከ እግዚአብሔር ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው። ሥጋዋንም ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወደ ገነት ዐሳረገ። በዚያም ዳዊት በበገና ዕዝራ በመሰንቆ እንዳመሰገኗት ሰማዕታት እየዘመሩላት ቆየች። ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በዐረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ እስከ 14 ቀን ሁለት ሱባዔ ይዘው በዐሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምሕላ በፍጹም ደስታ በጌቴሴማኒ አሳረፏት ። በሦስተኛውም ቀን ተነሥታ ስታርግ ጥሪው ከሰዱቃውያን ወገን የሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ጊዜ አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ሕንድ ስለሆነ ሊያስተምር ወደዚያው ሔዶ ነበርና በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል ትንሳኤዋን ከእርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ብሎ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ አሰበ። እመቤታችንም ትንሣኤዋን ከእርሱ በቀር ማንም እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለዐሥራ አንዱ ሐዋርያት እንዲነግራቸው ለምልክትም (ለምስክርም) እንዲሆነው ሰበኗን (መግነዟን) ሰጥታው ዐረገች ። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን "የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?" ሲል ቢጠይቅ "አግኝተን ቀበርናት እኮ" አሉት እርሱም ምሥጢሩን ዐውቆ ደብቆ "ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር " አንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳምኑት ሽተው መቃብር ሲከፍቱ አጧት። አርሱም "አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች" በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኗን ተከፋፍለው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሔዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ በመጾር ላይ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው። በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባኤ ቢይዙ ልመናቸውን ሰምቶ መላውን ሐዋርያት ወደ ገነት አውጥቶ በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረው መቃብር እመቤታችንን ነፍሷን ከሥጋዋ አዋሕዶ አንሥቶ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አሳይቶ ይህንንም ለዓለም እንዲያስተምሩ አዘዛቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያናችን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ምእመናን ልጆቿ ይጾሙ ዘንድ ታዛለች። ምእመናንም የእመቤታችንን በዓል ለማክበር ይጾሙታል። ይልቁንም ጽሙዳን መነኮሳት የሚጾሙት ነው። በጸናው መናገር ነው እንጂ ሕፃናት ሳይቀሩ የሚጾሙት ነው። በፍልሰታ ጾም በቁጥር የበዙ ሕጻናት ጾመው ይቆርባሉ። ብዙዎችም ቤታቸውን እየዘጉ በመቃብር ቤት ተከተው በጾምና በጸሎት ይሰነብታሉ። ይህን ጾም የማይጾም ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን አይኖርም። ምንጭ:-"ጾምና ምጽዋት" በዲያቆን ቃኘው ወልዴ ገጽ45
Показать все...
ሐምሌ 19 በዓሉ ለቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ገብርኤል ማለት እግዚእ ወገብር / አምላክ እና ሰው ማለት ነው። በዕለተ እሑድ መላእክት መኑ ፈጠረነ ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ ፈጥሮ ለማሳየት እጁን ከእሳት ከትቶ አቃጥሎት መላእክት በተረበሹ ጊዜ በያለንበት እንቁም ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው ። በዚህም ምክንያት ጌታ '' ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም '' እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል ። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል። በዚህም ዕለት የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑትን ሕፃኑን ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን አድኗቸዋል። ቅዱስ ቂርቆስ አገሩ ሮም አንጌቤን ነው አባቱ ቆዝሞስ ይባላል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገሥት ነች። ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በ20 ዓመት በአባ ባጋግዮስ ምክንያት '' አብያተ ጣዖታት ይትራኀዋ ወአብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ '' / የጣዖትታት ቤቶች ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ / ብሎ አወጀ /በ303 ዓ.ም. / በዚህ ጊዜ እኩሎቹ ተሰደዱ ቅድስት ኢየሉጣም ልጇ የ3 ዓመት ሕፃን ነበርና ለርሱ ብላ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች ። መስፍነ ብሔሩ ( የአገሩ ገዢ) እለእስክንድሮስ ክርስቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ አላት ፤ ዓይን እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች። አይሆንም ካልሽማ በሰይፍ ትቀጪያለሽ ብሎ አስፈራራት። እስኪ ይህን ሕፃን ጠይቀው አለችው። አንተ ሕፃን ወርቅ እሰጥሀለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ አለው መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና አንሰ ኢይሰግድ ለአማልክቲከ ርኩሳን ዘኢይክሉ አድኅኖ ርእሶሙ/ ራሳቸውን እንኳ ማዳን ለማይችሉ ርኩሳን ጣዖታትህ አልሰግድም አለው ተበሳጨ በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሏቸው አለ ዝፍት ተይ ጨምረው አንድደው በብረት ጋን ውኃ አፈሉ ። ድምጻ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት ይላል የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ 42 ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር ። ሊከቷቸው ሲወስዷቸው ኢየሉጣ ልቧ በፍርሀት ታወከ እሱ ግን ፍርሃቷን አርቅላት እያለ ይጸልይላት እሷንም ጥብዒኬ እምየ እምዝ ዳግመ ኢይረክበነ ሞት ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ በርቺ ጨክኚ በዚያውስ ላይ ዘአድኀኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ እኛንስ ያድነን የለምን እያለ እያጽናናት ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ ከዚህ በኋላ እሷም ጨክና በፍጹም ልብ ሆነው ተያይዘው ከእሳቱ ከውኃው ገብተዋል ። በዚህ ጊዜም ከዐላውያን ነገሥታት ከዐላውያን መሳፍንት ገብተው የመሰከሩለት በስሙ መከራ የተቀበሉለት ጌታ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል ። ይህም የኾነው በሐምሌ 19 ቀን ነው ፤ በወጡም ጊዜ ልብሳቸው ሳይለበለብ ሰውነታቸው ሳይሸበሸብ ቢያዩ ከአሕዛብ ብዙዎቹ አምነው አንገታቸውን ለስለት ሥጋቸውን ለእሳት ሰጥተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል። ከዚህም በኋላ እለእስክንድሮስ መከራውን ፈርተው ይመለሳሉ ብሎ በሀብለ ሰናስል እያሰረ በችንካር እየቸነከረ ሲያሰቃያቸው ቆየ ። የማይሆንለት ቢሆን እጅ እግራቸውን አስሮ ከዝግ ቤት አስቀመጣቸው ። ጌታም የመከራቸውን ጽናት የትዕግሥታቸውን ብዛት አይቶ በጥር 15 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስን በጥር 16 ቀን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን በሰማዕትነት ከመከራው አሳርፏቸዋል ። ምንጭ ፦ መዝገበ ታሪክ ክፍል አንድ እና ሁለት ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር
Показать все...
ለካልኣይ ተማሪዎች እሑድ 10/11/2014 ካልኣይ ተማሪዎች ትምህርት ስለማይኖር ከወዲሁ እንድታውቁ እና 12 ሰዓት ላይ መምጣት የምትችሉ ተማሪዎች በጥያቄ እና መልሱ መርሐ ግብር ላይ ተገኝታችሁ ብዙ ዕውቀት እንድታተርፉ ተጋብዛችኋል ።
Показать все...
ሐምሌ 7 -- በዓለ አጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ሥላሴ የሚለው ሠለሰ - ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት (ሦስትነት ) ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም / አንድነት ሦስትነት ተብሎ ይተረጎማል ። ሦስትነታቸው በስም ፣በአካል፣ በግብር አንድነታቸው በባሕርይ ፣ በህልውና በመለኮት ፣ በሥልጣን በፈቃድ ነው ። ሀ,የስም ሦስትነት - አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ነው ማቴ 28 ፣ 19 ለ, የአካል ሦስትነት - ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው። አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው ። ገጽ ፊት ነው መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለ ነው አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ መዝ 33 ፥ 15, መዝ 118+73 ኢሳይያስም '' ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ '' ብሏል (ኢሳ 66 + 1 ) ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ። ዘፍ 18+ 1-4, ማቴ 3+16 ሐ, የግብር ሦስትነት፦ የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው ። አብን ወላዲ ፣ ወልድን ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስንም ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደለም አንድ ናቸው ። እንዲህም ማለት ሦስት አማልክት ማለት አይደለም ። አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ የአንድነታቸውስ ነገር እንደምን ነው ? ቢሉ በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ አንድ ናቸው የህልውና አንድነታቸው በአብ ልቡናነት ወልድ መንፈስ ቅዱስም ያስቡበታል፤ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስም ይናገሩበታል ። በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ ወልድም ህልዋን ናቸው ይተነፍሱበታል ። ቅድስት ሥላሴ የሚል የሴት ቅጽል የተቀጸለላቸው ባሕርያቸውን አይቶ ነው ። ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንዲገኝ ይህም ዓለም ከሥላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና ፤ እናት ለልጅዋ የሚያሻውን አስባ እንድታቀርብለት ሥላሴም ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈለገውን ሁሉ አስቀድመው ያዘጋጁለታል። ማቴ 6 +32 አንድም እናት ልጅዋ ቢያስቀይማት ፈጽማ እንዳትጥለው ሥላሴም ሰርቀው አመንዝረው ቢበድሏቸው ንስሐ ገብተው ቀኖና ይዘው ቢለምኗቸው ይቅር ይላሉና ። ማቴ 6 +32 ይህን የሥላሴ አንድነት ሦስትነት ካልተማሩ ሥርየተ ኃጢአት ተስፋ መንግሥተ ሰማያት አይገኝምና ፤ ይህንንም ምሥጢር ያፋለሰ ለየራሳቸው ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ አላቸው ዘጠኝ አማልከት ናቸው ። እንዳለው እንደ ዮሐንስ ተዐቃቢ ፍዳን ይቀበላልና ፈጽሞ ጠንቅቆ መረዳት ይገባል ። ሥላሴ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ካለ መኖር ወደ መኖር አምጥተው የፈጠሩ ድካም የማይሰማቸው በሞት የማይለወጡ ገዥ ፈጣሪ ናቸው ። ሥላሴ እንደዛሬ ሁሉ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ባሕርያቸው ባሕርያቸውን ሲያመሰግን ይኖር ነበር ኋላ ግን ሰውና መላእክትን ስማቸውን ለመቀደስ ክብራቸውን ለመውረስ ፈጠሩ። ሌላውን ገን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ፈጥረውታል። የበዓሉ ታሪክ አብርሃም ቤቱን ከተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን እንግድነት ሲቀበል ይኖር ነበር ። ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ራሱን ገምሶ አጥንቱን ከስክሶ ከመንገድ ቆይቶ እንግዶቹን ወዴት ትሄዳለችሁ ? ይላቸዋል ። ርቦን ሊያበላን ጠምቶን ሊያጠጣን ከአብርሃም ዘንድ ይሉታል ፤ የወትሮው አብርሃም መሰላችሁን እኔም እንደ እናንተ ርቦኝ ያበላኛል ጠምቶኝ ያጠጣኛል ብዬ ብሄድ ራሴን ገምሶ አጥንቴን ከስክሶ ሰደደኝ ይላቸዋል ፤ እያዘኑ በመጡበት ይመለሳሉ ። እንዲህ አድርጎ 3 ቀን ሙሉ እንግዳ ከለከለበት እሱም ያለምስክር ግብር አላገባም ብሎ ሳይመገብ ቆይቷል ። በሦስተኛው ቀን በቀትር ከድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ ሥላሴ በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ተቀምጠው ታዪት። ( ዘፍ 13 + 18 ) '' ገሀሡ አጋዕዝትየ ቤተ ገብርክሙ አብርሃም '' ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፉ አላቸው ። ደክሞናልና እዘለን አሉት ። አንዱን አዝሎ ቢገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ ገብተው ተገኝተዋል ። እሱም ሦስት እንደሆኑ አውቆ ሣራን 3 መስፈሪያ ዱቄት ወስደሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ ጋግሪው አላት ፤ ጋግራ አቀረበች ፤ እርሱም ወይፈን አርዶላቸው ወተት እርጎ ጨምሮ አቅርቦላቸው ተመግበዋል / አቅረበ ሎሙ ሐሊበ ዕቋነ ወዕጉለ ላሕም / እንዲል ። መብላቸው ግን አሳት ቅቤ በላ እንደ ማለት ነው ። ይህንንም ሲያጠይቅ አርዶ አወራርዶ ያቀረበው ወይፈን ተነሥቶ '' ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ '' ብሎ አመስግኗል ። '' ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤ ዘበኃይልክሙ ሐይወ ላሕም ፤ ሥላሴ ክቡራነ ስም '' እንዳለ ደራሲ። በሚሄዱም ጊዜ ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ቃል አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ ፤ የዛሬ ዓመት እንደዛሬ ወዳንተ እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ብሎ ለጊዜው ልደተ ይስሐቅን ፍጻሜው ግን ሰው ሆኖ የሚያድነው መሆኑን ነግሮታል ። ዘፍ 18 + 1- 14 ምንጭ ፦ መዝገበ ታሪክ 1 & 2
Показать все...