cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

Рекламные посты
274
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የጸሎት ጥሪ! ትናንት ዕረቡ ሰኔ 27/2016 የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዓመቱን የዩኒቨርስቲ ትምህርት አጠናቀው በኮንትራት ትራንስፖርት ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያሉ ደብረ ጉራቻ አካባቢ ተማሪዎች የያዙ ሁለት መኪና  እና አንድ የህዝብ ማመላለሻ በታጣቂዎች መታገታቸውን ሰምተናል። ጥቂት ተማሪ ያመለጡ ቢሆንም ብዙዎች ግን በታጣቂዎች እንደተያዙ ናቸው፤ መደወል የቻሉ እንደነገሩን ወደየ ቤተሰቦቻቸው በመደወል ብር እንዲከፍሏቸው እና እንደሚለቋቸው ካልሆነ ግን ሌላ እርምጃ እንደሚወስዱ በመዛት እያስፈራሩ ይገኛሉ። ከሁለት አመት በፊት በተመሳሳይ መንገድ የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩ ሴቶችን በዚህ መንገድ ታግተው ከተወሰዱት መካከል እስካሁን ያሉበት የማይታወቁ አሉ። ምድራችን ላይ እየተበራከተ የመታውን ይህ ሰዎችን የማገት ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ሆኗል። ሁላቸንም በያለንበት አጥብቀን እንጸልይ፥ እግዚአብሔር በብዙ ጭንቅ ውስጥ ስላሉ ወንድና ሴቶቹ፥ ለቤተሰብ እና ለወዳጁ እንባ እና ለቅሶ ጣልቃ ይግባ! በምድራችን ላይ እየተፈጠሩ ያሉትን ስርዓት አልበኝነቶች ላይ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲባ አጥብቀን እንጸልይ። ጌታ ሆይ እጅህ በዚህ ሰዓት በምጥ እፈለጉህ ስላሉ ጣልቃ ትግባ ! ©️ Ermiyas
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 3 🙏🏽ለሻቦ ሕዝብ ክፍል 🙏🏽 እንጸልይ የሻቦ ሕዝብ የሚተሉት የጎሳ እምነትን ነው። የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸውን አማልክት ያመልካሉ፤ አማልክቱን ያስደስታል የሚሉትን መስዕዋት። የአምላኪ እና ተመላኪ ስርዓት ይፈጸማል። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏾 የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ለሻቦ ሕዝቦች የእግዚአብሔር የርህራሄ ልብ እንዲኖራቸው እና የወንጌሉን ሠራተኞች እንዲልኩ ወንጌልን እንዲሰብኩላቸው እንማልድ፡፡ 👉🏾 በሻቦ ሕዝብ መካከል የሚሰራውን የክፉ ሃይል፥ በክፋት የሚሰራውን መንፈስ ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲጠራረግ እንጸልይ! 👉🏾በሚቀጥሉት አምስት አመት የሻቦ ሕዝብ በወንጌል ተጥለቅልቀው የደቀመዝሙር ንቅናቄን እንድናይ እንጸልይ!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 2 🙏🏽ለሻቦ የሕዝብ ክፍል 🙏🏽 እንጸልይ የሻቦ ሕዝቦች በተለያዩ ሕዝቦች መካከል በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው፤ በዚህም በአንድ አካባቢ ሰፍረው የምናገኛቸው አይደሉም። የሻቦ ሕዝቦች በአደን እና በንብ  ማነብ የሚኖሩ ከዚህ ባሻገር ደግሞ አሳ በማጥመድ ፣የዱር አትክልቶችን እና ፍራፈሬዎችን በመሰብሰብ ገቢ ቢፈጥሩም  መተዳደሪያቸው ግን በዋናነት በእርሻ ላይ የተመሰረተ ነው። የጸሎት ርዕሶች 🙏🏾 👉🏾 የሻቦ ሕዝቦችን እግዚአብሔርን ወደ መፈለግ የሚያመጣ መንፈሳዊ ረሃብ እንዲያገኛቸው  እንጸልይ! 👉🏾 የእግዚአብሔር ቃል አዲስ ኪዳን በቋንቋቸው ተተርጉሞ ይገኛል። ይህን አቅርቦት በመጠቀም ለማስተማር፣ እና ትምህርቶች ለመካፈል ፈቃደኛ የሆኑ ክርስትያኖች እንዲነሱ እንጸልይ! 👉🏾እግዚአብሔር በግብርና የመተዳደር ህይወታቸው በመጠቀም ከብዙ የክርስትያን የንግድ ሰዎች ጋር እንዲያገናኛቸው፣ ወደ ከተማ እና ቤተክርስትያን ወዳለበት ስፍራዎች እንዲመጡ፣ ይህም እውነትን ወደማወቅ መንገድ እንዲመራቸው እንጸልይ!
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 1 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ለሻቦ የሕዝብ ክፍል • የህዝብ ብዛት፡- 500 • ዋነኛ ቋንቋ፡- ማጃንግ • ብዙ ተከታይ ያለው ሐይማኖት፡ - የጎሳ እምነት • ክርስትና ፡- 2.00% • ወንጌላዊያን አማኞች ፡ 0.00% • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፡- አዲስ ኪዳን ተተርጉሟል • ኢየሱስ ፊልም፡ አለ • ወንጌል ተኮር ቅጂዎች ፡- አሉ የውጭ ሰዎች የሰጡዋቸውን "መቄየር" የሚለውን ስም አይወዱትም። ሻቦ የሚለውን ስም ይመርጣሉ፡፡ ሻቦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ የሕዝብ ክፍል ነው። የቋንቋቸውን ምድብ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይቻልም ከኒሎ-ሳሃራን በተለይም ከኮማን ቋንቋዎች ጋር አንዳንድ ተመሳሳይነቶችን ያሳያል። የሻቦ ተወላጆች በጋምቤላ ክልል እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሚገኙት በማጃንጊር እና በሸካቾ ብሔረሰቦች የተከበቡ በርካታ የተበታተኑ ሰፈሮች ውስጥ ይኖራሉ። ማጃንጊር በሻቦ ባህል ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል፡፡ ሻቦ ከማጃንጊር ብዙ የቁሳቁስ ባህል (የሸክላ ስራን ጨምሮ) ልማዶችን እና ስርዓቶችን ተቀብለዋል። የጸሎት ርዕሶች 🙏🏾 👉🏾 እግዚአብሔር ለኃይሉ እና ፍቅሩ ምስክር እንዲሆን የሻቦ ሕዝብን እንዲባርክ እንጸልይ! 👉🏾አማኞች በሸቦ ህዝብ መካከል ወንጌልን ለመስማት እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ ልቦችን እንዲያዩ ጸልዩ (ዮሐንስ 4፡35) 👉🏾እግዚአብሔር ወደዚህ ህዝብ ሰራተኞችን እንዲልክ እንጸልይ!
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለጋብራ የሕዝብ ክፍል እንጸልይ! በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ 9፡ 37 - 38 ሰላም  የሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ ቤተሰቦች! ዛሬ አርብ ምሽት ከ3:30 ጀምሮ በቴልግራም ላይቭ ለጋብራ የሕዝብ ክፍል በህብረት የምንፀልይበት ጊዜ ስለሚኖረን ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናል ሊንክ በመግባት አብራችሁን እንድትጸልዩ እንጋብዛችኋለን። https://t.me/MobilizationEthiopia
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 4 ለጋብራ ኦሮሞ ሕዝብ ክፍል 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 የጋብራ ሕዝቦችን ታሪክ ስናጠና ወደ እስልምና እምነት የመጡት በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ መዛግብት ያሳያሉ፡፡ ሆኖም ግን እስልምናን እምነት ብቻ ሆኖ የረ ሳይሆን ከባህልና ቀደምት ሃይማኖታቸው ጋር ተቀላቀለ፡፡ ዛሬ እስልምና እና ባህላዊ እምነቶች ማህበረሱ ሚከተላቸው ዋና እምነቶች ሆነው ይገኛሉ። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏾የእግዚአብሔር ከተለማመዱት ጥልቅ የክፉ መናፍስት አምልኮ ነፃ እንዲያወጣቸው እየተቃወምን እንጸልይ! 👉🏾የጋብራ ኦሮሞ ህዝብን ምድር እስከነ የምታፈራው ፍሬ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች  ፣ ልጆችና ወጣት እናም እናቶች በክርስቶስ ደም ከሞት፣ ከሃጥያት መንፈስ እንዲከለሉ እንዲያመልጡ እየሸፈናቸው  -እግዚአብሔር ራሱን በክብር እና ባለጠግነት እንዲገልጽላቸው እንማልድ። 👉🏾 በዚህ ህዝብ መካከል -ለጋብራ ኦሮሞ ደቀመዝሙሮች ከመካከላቸው እንዲነሱ እነርሱ ደግሞ ሌላ ደቀመዝሙሮች ማፍራት እንዲችሉ እንጸልይ፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 3 ለጋብራ ኦሮሞ ህዝብ 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 አብዛኛዎቹ የጋብራ ኦሮሞ ሕዝቦች ኑሯቸውን በገጠር ያደረጉ ናቸው ይህም መተዳደርያቸው ከብት ማርባት ስለሆነ መጠነኛ በሆነም መንገድ በእርሻ ላይ የተሰማሩ ስለሆኑ ነው፡፡ ለምግብነት ዱራ(የእህል ዘር)፣ በቆሎ፣ ባቄላ፣ ሩዝ፣ ወተት፣ ስጋ እና የጫካ ፍራፍሬ ይጠቀማሉ፤ ቡና እና ሻይ በማህበረሱ ዘንድ ታዋቂ ናቸው፡፡ የጸሎት ርዕስ 🤲🏽 👉🏾የእግዚአብሔር መንፈስ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እንዲያፈሩ ይረዳቸው ዘንድ እንማልድ። 👉🏾የጋብራ ህዝብን ለመድረስ የእግዚአብሄር ልጆች፣ ቤተክርስትያን የተሰጣትን ሃብት በመታዘዠ ለተልዕኮው መስጠት ይጠበቅብናል። በልማት፣ የወደቁትን በማንሳት እና መሰል ፕሮጀክቶች ህዝብን ለመድረስ የገንዘብ አቅም እንዲያድግ እንጸልይ! 👉🏾 በዚህ ህዝብ መካከል የሃይማኖት መሪዎች ህዝቡን ለመድረስ ቁልፍ ሰዎች ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸውንም ጨምሮ የእግዚአብሔርን የማዳን እቅድ እንዲገለጥላቸው፣ እውነትን አውቀው ደግሞ በአውዳዊ መልኩ እውነትን እንዲናገሩ እና እንዲያመልኩ፣ ደቀመዝሙር የሚያደረጉዋቸው እንዲላኩ እንጸልይ!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰላም ለእናንት ይሁን ሁለተኛ ዙር የኦንላይን የሚሽን ስልጠናችንን የተልእኮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት በሚል ርዕስ ላይ የፊታችን አርብ ሰኔ 21 ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 5 ምናደርግ ይሆናል፤ በዚህ ስልጠና ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከታች ባለው ሊንክ በመመዝገብ ተሳታፊ ይሁን። ለበለጠ መረጃ ከታች ባሉት የቴሌግራም አድራሻዎች ያናግሩን ፡ https://t.me/FEVIREVIVALIST https://t.me/Amangeze https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdEWApwVGYPt6q27fDzHshr3VHpfHPnWpdjUg0AZO09uQRfDA/viewform?usp=sf_link
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 2 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ለጋብራ ኦሮሞ ሕዝብ ክፍል የጋብራ ኦሮሞ ሕዝቦ እንደ ሌሎች የአካባቢዎቻቸው ሕዝቦች በዋነኛነት ከብቶችን በማርባት የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። ከዚህ በዘለለ ጦረኛ የሚባሉ ጀግንነታቸውን የሚያቀነቅኑ ሕዝቦች ናቸው፡፡ የአንድ ሰው የኑሮ ደረጃ የሚወሰነው ባሉት ከብቶች ብዛትና መጠን ነው፡፡ የወንድ አንዱ ተፈላጊ ስእና እና መለኪየዓ ተደርጎ የሚወሰደው የጦረኝነት ጥበቡና ጀግንነቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ጋብራ ኦሮሞ በኢትዯጵያ ሞያሌ አካባቢ ከዚያም ባለፈ ደግሞ በኬንያ እና ሶማሊም የሚገኙ ሕዝቦች እንደሆኑ ታሪካቸው ያሳያል። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏾ለጋብራ ሕዝብ በመንፈስ የተሞሉ ብርቱ የወንጌል ሰራተኞች እንዲላኩ እንጸልይ! 👉🏾እግዚአብሔርን ስለእነዚህ ህዝብ፣ ስለስራቸው፣ በዚያ ለሚሰሩት ሁሉ በበረከቱ እንዲጎበኛቸው ጥበቃ እንዲሆንላቸው እንጸልይ! 👉🏾 ይህ ህዝብ በኬንያ እና በሶማሊም ይገኛል፣ በኬንያ የሚኖሩ በዚያ ያሉ ክርስትያኖች የማግኝት እድላቸው ሰፊ ስለሆነ፣ ይህ መልካም ገጠመኝ ለብዙዎች ማመን እንዲሆን ፥ በኬኒያ ያለች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንድትንቀሳቀስ እንጸልይ ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀን 1 🙏🏽 እንጸልይ🙏🏽 ለጋብራ ኦሮሞ ሕዝብ ክፍል የሕዝብ ብዛት:- 55,000 ዋነኛ ቋንቋ :- የቦረና-ጉጂ ኦሮምኛ ብዙ ተከታይ ያለው ሐይማኖት፡- እስልምና (100.00%) ክርስትና:- (0.00%) ወንጌላዊያን አማኞች:- (0.000%) የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም:- ሙሉ ተተርጉሟል የኢየሱስ ፊልም : አለ ወንጌል ተኮር ቅጂዎች:- አሉ የጋብራ ሕዝቦች ከራሳቸው አልፈው አስር ከሚሆኑ ተመሳሳይ ጎሳዎች ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የጋብራ ሕዝቦች ለመግባባት በሚነጋገሩበት ዘይቤ”ቦራና ኦሮሞ-አርሲ-ጉጂ” በሚባለው ቋንቋ ነው፡፡ምንም እንኳን በማህበራዊ ነገራቸው ተመሳስለው ቢኖሩም በእምነታቸው፣ በኑሮና በፖለቲካ ድርጅቶቻቸው ይለያያሉ፡፡ የጋብራዎችን ታሪክ ስንመለከት አሻሚነት ቢኖረውም በአስረኛው ክፍለ ዘመን በሶማሊዎች ከአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወደ ምእራቡ ሳይገፉ እንዳልቀሩ ይነገራል በምእራቡ አካባቢ ካሉ ባህሎችም ጋር መዛመድኑን ከዚያ የተነሳ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ የጸሎት ርዕሶች 🙏🏾 👉🏾 የጋብራ ኦሮሞ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ ለህይወታቸው ፍጽም ፈውስ እንዲሆን በመማለድ እንጸልይ! 👉🏾 የወንጌል መልዕክትን የያዙ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና መሳሪያዎች እያሉ ዛሬም ግን የሚያምኑ በመካከላቸው የሉም፣ ዛሬ በጋብራዎች ላይ ታላቅ መንፈሳዊ ጥማት እንዲያድር እንጸልይ። 👉🏾የእስልምና እምነት ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ነው፤ በመልካም ስራቸው ወደ ጀነት ይኬዳል የሚል እምነት አላቸው፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነሱ ላይ እንዲወርድ፣ በመጣም ጊዜ በህልም እና ራዕይ በክርስቶስ ስራ ለእነሱ መዳን እንዲሆን እንጸልይ!
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.