cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፈለገ ምሕረት ሰ/ት/ቤት felege mihret sunday school

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ይህ ቻናል #የወልድያ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የፈለገ ምህረት ሰ/ት/ቤት ቻናል ነው ቻናሉን join ሼር ያድርጉ በዚህ ቻናል #መዝሙሮች#ትምህርቶች#ስነ ፁሑፍ #የፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት እንቅስቃሴዎች መንፈሳዊ የኪነ ጥበባት ስራዎች ይቀርባሉ ቻናሉን share በማድረግ ይተባበሩን https://youtu.bpe/25ZvKhbpaY0

Больше
Рекламные посты
407
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት 36ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉአን በድምቀት አከበረች በመላው አለም የምትገኙ የፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት ልጆች እንኳን አደረሳችሁ አዲሱ አመት የሰላም እና የጤና ያድርግልን ፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት 06/12/2015 ወልድያ
Показать все...
ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ የአምላክ ሰው መሆንና ተወልዶ የማደጉ ዜና ሲነገር ሁልጊዜም የሚዘነጋ ክብሩ ግን ከብዙ ቅዱሳን ክብር የሚበልጥ አንድ ታላቅ ሰው ዛሬ በልቡናዬ ውል አለ፡፡ መቼም ከፀሐይ አጠገብ ያለ ኮከብ በፀሐይ ብርሃን ምክንያት መሸፈኑ አይቀርምና በተወለደው የጽድቅ ፀሐይ ፣ የሰላም ንጉሥ በልደቱ ደስታ ተውጠን ፣ በገብርኤል ብሥራት ፣ በድንግል ምስጋና ፣ በመላእክት ዝማሬ ተስበን የዘነጋነውን ፣ ድምቀት ሳያንሰው የተሸፈነውን ኮከብ የቅዱስ ዮሴፍን ነገር ባሰብኩኝ ጊዜ ክብሩን ለመናገር ልቡናዬ ተጨነቀ፡፡ በቅድስናው እያመንን ፣ ውለታውንም እያወቅን የምንዘነጋውን ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች የድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለማቃለል ስሙን በክፉ ማስረጃነት ሲያነሱብን ከእነርሱ ሸሸን ብለን ሳናውቅ ከበረከቱ የሸሸነውን ጻድቅ ዛሬ ልዘክረው ብል ልቤ በጥፋተኝነት ስሜት ተጨነቀብኝ፡፡ ስለ እርሱ ብዙ ያልዘመርንበትን ፣ ብዙ ያልተቀኘንበትን ዘመን ሳስብ ‘ላዕከ ማርያም ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ስለረሳንህ ቀኛችን ትርሳን ፣ ስላላሰብንህም ምላሳችን ከትናጋችን ይጣበቅ’ ብዬ ይቅርታውን ለመለመን ተመኘሁ፡፡ ቅዱስ ዮሴፍን ማን ብለን እንጥራው? እርሱ እንደሆን እንደ አብርሃም ዘመዶቹን የተወ አማኝ ፣ እንደ ይስሐቅ የታዘዘውን ብቻ ያደረገ ትሑት ፣ እንደ ያዕቆብ በእምነት ግብጽ የወረደ ስደተኛ ነውና እርሱን ለመግለፅ እንደምን ያለ ቋንቋ እንጠቀም ይሆን? እስቲ ንገሩኝ? ‘መልካሙን እረኛ’ ክርስቶስን የጠበቀውን እረኛ ቅዱስ ዮሴፍን ከቶ በምን ቃል እንገልጸዋለን? የአብን ልጅ ያሳደገውን (ሐፃኔ ወልደ አብ) ቅዱስ ዮሴፍን በምን ቅኔ እናወድሰው? ሕዝቅኤል ያያትን የእስራኤል አምላክ ገብቶባት ለዘላለም የተዘጋችውን ደጅ የጠበቀውን ታማኝ ዘብ ፤ ‘ከበሩ ደጀ ሰላም መንገድ በዚያ ይገባል በዚያም ይወጣል’ ተብሎ የተነገረለትን የተዘጋችው በር ደጀ ጠኚ ፣ ከታላቅዋ ተራራ ከድንግል ማርያም ያለ ሰው እጅ ድንጋይ ተፈንቅሎ ሲወርድ ቆሞ የተመለከተውን የሐዲስ ኪዳኑን ዳንኤል ከቶ እንዴት ባለ ቃል እንገልጸዋለን? በቤተ ልሔም ግርግም ውስጥ በላምና አህያ መካከል የተኛውን ሕፃን የተመለከተውንና እንደ ነቢዩ ዕንባቆም ‘በማዕከለ ክልዔ እንስሳ ርኢኩከ’ /በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ/ ሊል የሚቻለውን የቅዱስ ዮሴፍን ክብር በምን አቅማችን እንግለጸው? ወደ ግብጽ ወርዶ ለወገኖቹና ለዓለም ሁሉ ምግብን እንዳቆየው የብሉይ ኪዳኑ ዮሴፍ ወደ ግብጽ በመከራ ተሰድዶ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስን ለሁላችን ላቆየልን ጻድቅ እንዴት ያለ የምስጋና ቃል እናዋጣ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ለቅዱስ ዮሴፍ ዝክር ሐምሌ 26 ከብርሃን እናት ገፆች የተቆረሰ (ወተዘከረኒ ለኃጥእ ገብርከ ተክለ ማርያም )
Показать все...
Repost from @ነቅዐጥበብ
#ጸሎት_በእንተ_ክረምት <<ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ>> ማር 13፡18 ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ የክረምት ወቅት ነው #ክረምት የብሉይ ኪዳን ዘመን ምሳሌ ነው የክረምት ገበሬ ጠዋት ጾሙን ይወጣል ቀን ከላይ ዝናም እየወረደበት ከታች ጭቃ እየሆነበት ሲሠራ ውሎ ማታ እራት ጎመን ይቀርብለታል ድካምና ረኃብ ፍርሃትና ስቃይ ይፈራረቁበታል! ነቢያት በዘመነ ብሉይ እንዲሁ ነበሩ። ያለ ልጅነት ወጥተው ያስተምራሉ ፤ትንቢት ይናገራሉ ሲመሽ ማታ (ሲሞቱ) በሥጋ ወደ መቃብር በነፍስ ወደሲኦል ይወርዳሉ(የጎመን እራት)! #ክረምት የቃል ኪዳን መገለጫ ነው ክረምት በብሉይም በሐዲስም ከተደረጉ ኪዳናት ጋር ተያይዞ ይገለጻል በተለይም ቅዱስ ያሬድ ክረምትን ከኖኅ ኪዳን ጋር እያነጻጸረ የገለጸው የዜማ ድርሰት አስደናቂ ነው "ያከርም በበዓመት ተዘኪሮ ዘመሐለ ለኖኅ ገብሩ" የሚያስደንቀኝ ገለጻ ነው! (ዘፍ 8፥22) #በክረምት፦ መብረቅ ነጎድጓድ በረድ (በረዶ) ማዕበል ሞገድ አለ ሰማዩ ይጠቁራል ደመናው ይከብዳል መሬቱ ይላላል ወንዙ ይሞላል ዘመድ ከዘመድ ሳይጠያየቅ ይከርማል ስለዚህም በዚህ ወቅት ወርኀ ክረምቱን በሰላም እንዲያሳልፍልን ጸሎት/አስተምሕሮ ይደረጋል ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው የአስተምህሮ ጊዜው የዚሁ አካል ነው። ዝናሙ ዝናመ ምሕረት ጠሉ ጠለ በረከት ነፋሱ ነፋስ ምሕረት እንዲሆን አስተብቁዖት(ምልጃ) ሊደረግ ይገባል። #ክረምት የምጽአተ እግዚእ ምሳሌ ነው ማቴ 24፥27 ክረምት የጌታ መምጣት የዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ሆኖም ይነገራል በክረምት ከሚሰማው ነጎድጓድ በላይ የሆነ ነጎድጎድ በዕለተ ምጽአት ይሰማል ጌታም እንደ መብረቅ ብልጭታ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ያለ ወሰን በምልዓት በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ይገለጣል ይህን እያሰብን በጎ እንድንሠራ ክረምት አስፈሪ ምልክቶች ይታዩበታል! ምልክቶቹም አቅማችንን አውቀን፣ ተፈጥሮ ከእኛ አቅም በላይ መሆኑን ተገንዝበን ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ የሚያሳስቡ ናቸው! #በዚህ ክረምት መርከብ መሥራት በመርከቡ መቀመጥ ያስፈልጋል #መርከቡም፦ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ንስሐ በጎ ሥራ ነው! "ግበር ታቦተ በዘትድኅን" የምትድንበትን መርከብ ሥራ! አምላካችን እግዚአብሔር ክረምቱን በሰላምና በጤና ያሳልፈን!!! አሜን! በቴሌግራም ያግኙን! https://t.me/joinchat/Z1hTW-X4CDI3MDVk ነቅዐ-ጥበብ
Показать все...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

# በዘባነ ኪሩብ በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ የተከበረነው በሰማይ በምድሩ/2/ ኢሳያስ ሲያየው እጅግ አፈረ የተፈራ ነው የተከበረ የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ ለቅዱስ ስሙ ክበርን ሲሰጡ ያልተቀደሰ ለምፅ ያነደደው እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምስጋና ዙፋንህ ታየኝ ትምክቴ ሆይ ስትመሰገን በሰማይ ላይ ሲያመሰግንህ የተደሰተ ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ ቅኔ ሞላበት ያንን ሰገነት ልቀላቀለው ተመኘው በዕውነት ልዘምርልህ ባይገባኝም ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም
Показать все...
file_309214.opus6.93 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዘማሪት እስከዳር አማረ በ2015 ዓ.ም በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመረቃችሁ ውድ የፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት አባላት እንኳን ደስ አላችሁ በተጨማሪም በወልዲያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጂ ለተከታታይ ሶስት አመት እና አራት በትምህርት ላይ የነበራችሁ አሁን ላይ የኮሌጃችን ተመረቂዎች እንኳን ደስ አለችሁ::ከነዚህም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የዛሬ 22/11/2015 ዓ.ም ተመራቂዎች መካከል 1/ሃብተ ማርያም ሲሲይ የሰንበት ትምህርት ቤቷ ሰብሰቢ 2/ብኒያም አሻግሬ  የሰንበት ትምህርት ቤቷ ምክትል ሰብሳቢ 3 /ወርቄ ተስፋ 4/ቃል ኪዳን በለጠ 5/ዲያቆን ቢሆነኝ እሽቴ 6/ሰምረ ኪዳን ተፈራ እግዚአብሔር የእስከ ዛሬዉን ልፋታችሁን በመልካም ፍሬ ይባርክላችሁ፡፡በሙያችሁ ለራሳችሁ: ለቤተሰቦቻችሁ እና ለቤተ -ክርሰቲያናችሁብሎም ለሀገራችሁ አገልጋይ እንድትሆኑ የቅዱሳን ፀሎት የእመቤታችን ምልጃ የእግዚአብሔር ቸርነቱ አይለያችሁ፡፡ እንኳን ደሰ አላችሁ!!! የሰንበት ትምህርት ቤቷ ግኑኝነት ክፍል፡፡
Показать все...
በፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ መርሐ ግብር ተካሄደ በዕለቱ መዝሙር ስነ ፁሑፍ ትምህርት .ትምህርት በአካላዊ ምሳሌ(ድራማ). መነባንብ ቀርቧል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
36 የአገልግሎት ዓመታትን በመቃብር ቤት የወልድያ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት ባለፉት 36 የአገልግሎት ዓመታት በመቃብር ቤት በርካታ ወጣቶችን በመንፈሳዊ ሕይወት በማነጽ የድርሻውን ሲወጣ ቆይቷል። አሁንም አየሠራ ይገኛል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል። አሁን የአባላቱ ቁጥር እያደገ በመምጣቱና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለማስፋፋት አዲስ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በግንባታ ላይ ይገኛል። የግንባታው ኮለን በመጠናቀቅ ላይ ነው። ቀሪ ሥራዎችን ለመሥራት የእናንተ ድጋፍ እጅግ አስፈላጊ ነውና የምትችሉትን ድጋፍ ያድርጉልን ብለዋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ደ/ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ሕንፃ አሰሪ 1000150496563 #ወልድያ_ቅዱስ_ሚካኤል_ፈለገ_ምሕረት_ሰንበት ት/ቤት
Показать все...