cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ahmed Habib Alzarkawi

Hello World

Больше
Рекламные посты
20 488
Подписчики
-924 часа
-627 дней
-26130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ከትናንት በስቲያ ከጅማ እስከ ወለጋ እንዲሁም እስከ ወላይታ የተሰማው ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ምንድን ነበር? የከባድ ጦር መሳርያ ድምፅ ነው፣ መብረቅ ነው፣ ከሌላ አለም የመጣ ባዕድ ነገር ነው ወዘተ የሚሉ በርካታ መላምቶችን ተመልክቻለሁ። በጠፈር ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የአስትሮፊዚክስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን በላይ ይህን መረጃ ሰጥተውኛል: - ከተመለከትኳቸው ምስሎች መረዳት የቻልኩት ወደቁ የተባሉት አካላት የሚቲዮራይት ስብርባሪ መሆናቸውን ነው - የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ዲፓርትመንትን በዚህ ዙርያ አነጋግሬ ያገኘሁት ምላሽ ተመሳሳይ ነው፣ ወድቆ የተገኘው አካል ወደ ዩኒቨርስቲው ለምርመራ እንዲወሰድ ሀሳብ አቅርቤያለሁ - ይህ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማው ከደቡብ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ነው፣ አጋሮ አካባቢ አንዳንድ ስብርባሪ ተገኝቷል ሚቲዮራይት ከሌላ ጠፈር (outer space) በመነሳት ምድር ላይ የሚያርፍ ድንጋይ/አለት ሲሆን ወደ ምድር ከባቢ አየር ሲገባ በሰበቃ (friction)፣ ሀይለኛ ግፊት እና በኬሚካል ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ድምፅ እና ብርሀን ይፈጥራል። Credit: ዶ/ር ሰለሞን በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፈ አስትሮኖሚካል ህብረት ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ለሙያዊ አስተያየታቸው አመሰግናለሁ። ሙሉ መረጃው ኢትዮጵያ ቼክ ላይ ይገኛል: https://t.me/ethiopiacheck/2379 Image: Social Media Elyas Meseret
Показать все...
👍 22🙏 4 1😍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ፓስፖርት ለማውጣት መንከራተት ሊቀር ነው...🇪🇹👌 ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሰዎች ላይ ጥላው የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳች በኢትዮጵያ ፓስፖርት ቤት ለቤት ማደል ሊጀመር ነው ተባለ በኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች ፓስፖርት መሰጠቱ ተገልጿል። አል ዐይን
Показать все...
👍 50😁 22 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ማስተካከያ ተደረገ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። በዓለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠነኛ የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህም መሠረት ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ ላይ የሚውለው የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ይሆናል፡- ቤንዚን …………………………… ብር 82.60 በሊትር ነጭ ናፍጣ……………………… ብር 83.74 በሊትር ኬሮሲን ……………………………. ብር 83.74 በሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ ………………… ብር 70.83 በሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ………………… ብር 65.48 በሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 64.22 በሊትር መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
Показать все...
👍 21 1
የጭካኔ ጥግ…😭😭😭😭 ከሰዓታት በፊት NBC4 Washington እንደዘገበው ፋሲል ተክለ/ማሪያም የተባለ የ53 አመት ጎልማሳ በአሰቃቂ ሁኔታ በWashington DC ተ*ገ*ደ*ለ የ22 አመት እና የ19 አመት አሜሪካዊ ሴቶች በተለያየ ጊዜ ቤቱ እየመጡ የፍቅር ጊዜ ያሳልፉ ነበር ። እነሱ (Sugar Daddy )እያሉ ይጠሩታል ። ታሪኩን ለማሳጠር ያክል በመጨረሻም ቤቱ ውስጥ ገ*ድ*ለውት አውራ ጣቱን ቆርጠው በመውሰድ አሻራውን በመጠቀም በተደጋጋሚ ከCash app ገንዘብ ይወስዱ ነበር ። የዚህ ግለሰብ አስክሬን ቤት ውስጥ 4 ቀን ሲቆይ እነሱ ግን ገንዘብ እያወጡ ይዝናኑ ነበር ። እጅግ በጣም ያሳዝናል 😭
Показать все...
👍 22 1
👍 38🥰 9 2😍 1
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሆኑት ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀርና ማሊ ተዋሃዱ ይህ ለመላው አፍሪካ በተለይ ለኛ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ምሳሌ ይሆናል የተባለው ውህደት የተፈፀመው በትላንትናው እለት በኒያሚ ሲሆን የሶሱቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች በይፋ ተፈራርመዋል። የቀኝ ገዢ ሀገራት የሆኑትን እነ ፈረንሳይን ከሀገራቸው ሙልጭ አርጎ በማባረር የጀመረው ይህ የውህደት ጉዞ እነኚህን የሳህል ቀጠና ሀገራት በመጨረሻም በኮንፌዴሬሽን አዋህዷል። እነኚህ ሀገራት በተለምዶ ኢክዋስ የሚባለውን ምዕራባዊያን ለጥቅማቸው የመሰረቱትን ማህበር በይፋ የተፋቱ መሆኑንም በትላንትናው እለት ይፋ አርገዋል። በዚህም መሰረት ውህደቱ " Confederation of Sahal State / AES" የሚል የጋራ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን የጋራ መገበያያ ገንዘብ፣ የጋራ ህገ መንግስት ፣ የጋራ የመከላከያ ጦር ፣ የጋራ ኤምባሲ፣ የጋራ ፓስፖርት ወዘተ የመሳሰሉትን የሚኖራቸው ሲሆን የ72 ሚሊየን የህዝብ ብዛት በማቀፍ ገዝፈው ተመስርተዋል። ሀገራቱ በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የበለፀጉና በነ ፈንሳይ ሲበዘበዙ የኖሩ ሲሆን በተለይም ለኒውክሌር ሀይል ሚውለው የዩራኒየም ክምችትና ወርቅን የመሳሰሉ ማዕድናት በከፍተኛ ሁኔታ በመሬታቸው ይዘው ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ከባህር ለማራቅ ሲሉ ድህነትና መከራን የመረጡት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከዚህ ምን ይማሩ ይሆን ? ኢትዮጵያስ እንዲህ ያለውን መንገድ ለመከተል ምን ይጠበቅባታል ? መልሱን ለናንተ ትተናል ! ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet
Показать все...
👍 63😍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 15
በኢራን አስቸኳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለዘብተኛው መሱድ ፔዝሽኪያን አሸነፉ።መሱድ የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም ናቸው። የ69 አመቱ የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም ከ30 ሚሊየን መራጭ የ16 ሚሊየኖን ድጋፍ ማግኘታቸውን የሀገሪቱ የምርጫ አስተዳደር ቃል አቀባይ ሞህሰን ኢስላሚ ተናግረዋል። ወግ አጥባቂው ሳኢድ ጃሊሊ በበኩላቸው 13 ሚሊየን ድምጽ ማግኘታቸው ተጠቁሟል። ፔዝሽኪያን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ምርጫ ቢያሸንፉም አብላጫ ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው በትናንትናው እለት ከፍተኛ ድምጽ ካገኙት ጃሊሊ ጋር ዳግም ተፎካክረው ነው ያሸነፉት። የቀድሞው የኢራን የጤና ሚኒስትር በቀጥታ በቴሌቪዥን በተላለፈ መልዕክታቸው ድጋፍ የሰጧቸውን ኢራናውያን አመስግነዋል። “ሁላችንም በወንድማማችነት መንፈስ ለጋራ ሀገራችን እድገት እንድንሰራ ጥሪ አቀርባለሁ” ሲሉም ተደምጠዋል። በህዝብ ዘንድ እምብዛም የማይታወቁትና ለዘብተኛ አቋም የያዙት ፔዝሽኪያን ኢራን ወደ 2015ቱ የኒዩክሌር ስምምነት እንድትመለስና ከምዕራባውያን ጋር ግንኙነቷን እንድታድስ እንደሚያደርጉ ተናግረው ነበር። ይህም በአያቶላህ አሊ ሃሚኒ ጭምር መነቀፉ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን ኢብራሂም ራይሲ ለመተካት በሚደረገው ምርጫ ውጤታማ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል የሚል ስጋት ፈጥሮ እንደነበር ፍራንስ 24 አስታውሷል። የኢራን የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ሃሰን ሮሃኒ እና ሞሀመድ ካታሚ የሰጧቸው ድጋፍ ግን ያልተጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ አድርጓቸዋል። ከዚህም ባሻገር በኢራን ያለውን የኢንተርኔት ገደብ እንደሚያላሉና ፖሊሶች ጸጉራቸውን የማይሸፍኑ ሴቶች ላይ የሚወስደውን ያልተገባ እርምጃ እንደሚቃወሙ መናገራቸውም የመራጮችን ድምጽ እንዲያገኙ ሳያግዛቸው አልቀረም። በኢራን በምርጫ መሳተፍ ከሚችለው 61 ሚሊየን ህዝብ በአሁኑ ምርጫ የተሳተፈው 40 በመቶው ብቻ ነው። ይህም ከ1979ኙ አቢዮት ወዲህ ዝቅተኛው የመራጭ ቁጥር የተመዘገበበት ነው የተባለ ሲሆን፥ ኢራናውያን በምዕራባውያን ማዕቀብ በተዳከመው ኢኮኖሚ እና በሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ቁጣቸውን ለመግለጽ ድምጻቸውን ከመስጠት ተቆጥበው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። የኢራን ሃይማኖታዊ መሪው አያቶላህ አሊ ሃሚኒ ግን የመራጮቹ ቁጥር ከተጠበቀው በታች ቢሆንም “ስርአቱ ላይ ተቃውሞን ማሳያ አይደለም” ብለዋል።(አልዓይን)
Показать все...
👍 25 3
ሰበር ዜና.!!! ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ኢኮኖሚዬን በከፍተኛ ሆኔታ ይጎዳል ያለችው ጂቡቲ የኢትዮ-ሶማሊላንድ ስምምነት ለማክሸፍ እየሰራች ነው ስትል ሶማሊላንድ ገለፀች። የሶማሊላንድ የመረጃ ሚኒስትር አሊ መሐመድ ሀሰን በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያና እና በሶማሊላንድ መሃከል የተደረገውን ስምምነት ለማክሸፍ በሚስጥር እየሰራች እንደሆነና ሴራ እየጠነሰሰች እንደሆነ ገልጸዋል።የመረጃ ሚኒስትሩ አያይዞ ጎረቤታችን ጂቡቲ የአውደል ግዛት ንቅናቄ በመባል የሚታወቀውን የሶማሊላንድ ከፋፋይ አጀንዳ የያዘ ቡደን በሀገርዋ በመጋበዝ በሶማሊላንድ ግጭት እንዲፈጠር እየሰራች ነው ብለዋል። ከዚህ ባለፈም የጂቡቲ መንግስት በኢትዮጵያ በጂቡቲና በሶማሊላንድ ድንበር አከባቢ ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራች ነው ይሄም በጣም አደገኛ ነው በማለት ማስጠንቀቃቸው ሆርን ኦብዘርቨር ዘግቧል። መግለጫውን ተከትሎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። ጠላት ከሩቅ አይመጣም አይደል የሚባለው🤔🤔 Ahmed Habib Alzarkawi
Показать все...
👍 82🕊 4 3🙏 2👏 1
የኔ ቻናል ቤተሰብ ሰው ሲጠፋ ለምንድነው የማትጠይቁት 😍
Показать все...
👍 104🙏 23😁 7👏 3🕊 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.