የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
Открыть в Telegram
1 411
Подписчики
+224 часа
+257 дней
+8530 дней
Архив постов
1 411
ለኤክስፖርት ስጋ ምርመራ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቆ ተመረቁ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን UNIDO ከተሰኘ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ለኤክስፖርት ስጋ ምርመራ ባለሙያዎች በ ISO ስታንዳርድ ላይ በተከታታይ ዙሮች በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቆ ተመረቁ፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ የስጋ ምርቷን ወደ ውጭ በመላክ የተቀባይ አገራትን ስታንዳርድ ያሟላ እንዲሆን የሚደረገውን የቁጥጥር ስራ አቅም የሚያጠናክርና የተቀባይ አገራትን ቁጥር እንዲጨምር ለማስቻል ያለመ በመሆኑ ይህን ስልጠና አጠናቃችሁ ለዛሬዋ የምረቃ ዕለት በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡
አያይዘውም በቅርቡ አገራችን ኢትዮጵያ የስጋ ምርቷን ወደ ቻይና ለመላክ በዝግጅት ላይ በመሆኗ ለዚህ ትልቅ መደላድል እንደሚፈጥር አብራርተዋል፡፡በመጨረሻም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታችሁ ወቅት ያገኛችሁትን እውቀት በተግባር ላይ እንደምታውሉት እምነቴ የፀና ስለሆነ ለዛሬዋ የምረቃ ስነስርዓት በመብቃታችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ለተመራቂዎቹ ሰርተፊኬት የመስጠት ስነስርዓት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
1 411
ለእንስሳት ጤና ሐኪሞችና መለስተኛ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማሳጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ጣቢያዎች ለመጡ የእንስሳት ጤና ሐኪሞችና መለስተኛ ባለሙያዎች በደረጃ እድገት መሰላል መመሪያ ላይ በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማሳጨበጫ ስልጠና ተሰጠስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ እሳቸውም ምንም እንኳን ይህ የደረጃ እድገት መሰላል መመሪያ በተለያዩ ምክንያቶች ለረጅም ጊዚያት ሳይፀድቅ በመቆየቱ በባለሙያዎቹ ላይ የስራ ተነሳሽነትን ሊቀንስ እንደሚችል ቢታመንም አሁን ግን በኢፌዴሪ ግብርና ሚ/ርና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቅንጅት ጭምር ተሰርቶና ፀድቆ በመምጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡አያይዘውም ይህ መመሪያ አንዱ ከአንዱ ጋር የሚወዳደርበት ሳይሆን የተቀመጡ መስፈርቶችን ያሟሉ ባለሙያዎች ሁሉ ወደሚቀጥለው ደረጃ የሚያድጉበት በመሆኑ ተጠቃሚነታችሁና የስራ ተነሳሽነታችሁ እንደሚጨምር እምነታቸውን ገልፀው ይህን መመሪያ ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ እናንተን የሚወክሉ የኮሚቴ አባላት ተመርጠው ወደ ስራ መግባታቸውን እና የዛሬው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም በእነሱ የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል፡፡በመቀጠል ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ የአደረጃጀትና ምዘና አናሊስት ባለሙያዎች በአቶ ገረመው ቀናቴ እና በአቶ ተገኝ አንሙት ፀድቆ የመጣው የእንስሳት ጤና ሐኪሞችና መለስተኛ ባለሙያዎች የደረጃ እድገት መመሪያ ላይ ሰፊ ገለፃ ካደረጉ በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ የግልፅነት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም እያንዳንዱ ባለሙያ የደረጃ እድገት መሰላል ማመልከቻ ቅፁን እንዲሞላ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
1 411
የኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን መ/ቤት ተገኝተው የስራ ጉብኝት አደረጉ
****
የኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ ከስራ አማካሪዎቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን መ/ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከማኔጅመንት አባሎቻቸው ጋር በመሆን የእንኳን ደሀና መጣችሁ አቀባበል አድርገው ክቡር ሚኒስቴሩ የስራ አማካሪዎቻቸውን ጭምር ይዘው ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሰጠውን ትልቅ ሀገራዊ ተልእኮ ለመረዳትና አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ እዚህ ድረስ በመምጣት ላደረጉት የስራ ጉብኝት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የባለስልጣኑን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 509/2014 መሰረት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እንዲያስችለው በተቋሙ የተፈጠረውን መዋቅራዊ አደረጃጀት ምን እንደሚመስል እና የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ሲል ያጋጠሙትን ችግሮች፤ ችግሮችን ለመፍታት የተሄደበትን ርቀት በተመለከተ ገለፃ ቀርቦላቸዋል፡፡
አምባሳደር ድሪባ ኩማ አያይዘውም ባለስልጣን መ/ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አብራርተው ነገር ግን በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው ደንብ ቁጥር 509/2014 መሰረት ከተሰጠው ተግባርና ኋላፊነት አኳያ እንዲሁም ተቋሙ እንደ አዲስ የተቋቋመ በመሆኑ ስራዎችን ለማከናወን የተለያዩ ችግሮች እንዳጋጠሟቸው አብራርተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የበጀት ዕጥረት፤ የተሸከርካሪ እጥረት፤ የራሱ የሆነ ቋሚ ቢሮ ያለመኖር፤ ከስራችን ጋር አግባብነት ያላቸው ረጂ ድርጅቶች ያለመምጣት ተጠቃሾች እንደሆኑና ለወደፊት እነዚህ ችግሮች ተቀርፈው ዘመኑ የሚዋጀውን ጠንካራ የቁጥጥር ተቋም ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊያግዘን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በስራ ጉብኝታቸው ሁሉንም የስራ ክፍሎች ተዟዙረው ከጎበኙ በኃላ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ እሰካሁን ድረስ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታና የሚደነቅ ነው በማለት መስሪያ ቤቱ ግዙፍ እና በግብርናው ዘርፍ በርካታ የቁጥጥር ስራዎችን የሚሰራና እየሰራ ያለ ተቋም በመሆኑ በተለይም አገሪቱ በግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባትን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንድታገኝ ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ ይህንንም ለማሳካትና በታቀደው ልክ ለመሄድ ከሌሎች ተቋማት እና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለዉም የተነሱ ችግሮች እንደ ክብደታቸውና አንገብጋቢነታቸው በቅደም ተከተል እየታዩ መፍታት እንደሚገባ አብራርተው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም የጀመረውን ድጋፍና እገዛ አጠናክሮ በመቀጠል ሀገራዊ ሀላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡
1 411
“የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ ብሐራዊ እንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና”
***
16ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ‹‹የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው፡፡›› በሚል መሪ ቃል በኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የተገኙ ሲሆን ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራችን ክብርና ነጻነት መገለጫ ፣ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ፣ የአብሮነታችንና የሉዓላዊነታችን ዓርማ እና የነጻነታችን ኩራት ምልክት ሲሆን ለሰንደቅ አላማችን ሁላችንም ክብር በመስጠትና በተሰማራንበት የስራ መስክ በቅንነት ፣ በታማኝነትና በታታሪነት የተቋማችንን ተልዕኮ ለማሳካት በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በሌላ በኩል የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች መንግስት የሰጠንን ሀላፊነትና ግደታ ለመወጣት ተቋሙን ፈልገው የሚመጡ ተገልጋይ ደንበኞቻችንን ከአድሎና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል እንድሁም በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚሰራጩ ሀገርና ህዝብን ከሚጎዱ የተሳሳቱ መረጃዎች ራስን በማራቅና ለእውነትና ለሰላም ለመስራት በኢትዮጲያ ሰንደቅ አላማ ፊት ቃል እንገባለን በማለት ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል ፡፡
በመጨረሻም ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀል ስነ-ሥርዓት በብሔራዊ የሰንደቅ አላማ መዝሙር ታጅቦ ሰንደቅ አላማ በመስቀል የበዓሉ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ 674/2002ን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ፤
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በደንብ ቁጥር 509/2014 ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል የጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር ማካሄድ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሥራ ላይ ያለውን የጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ 674/2002 ን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ላይ በአደማ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ዋነኛ ዓላማ ፍቱንነቱና ጥራቱ ከፍተኛ የሆነ እና በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ስጋት አነስተኛ የሆነ ጸረ ተባይ በመመዝገብ የገብያ ፍቃድ መስጠት መሆኑን ገልጸዋል።
አምባሳደር ድሪባ አክለውም ባለፉት ጊዜያት ጠንካራ የጸረ ተባይ ምዝገባ እና ቁጥጥር ሥርዓት ባለመኖሩ ምክንያት በተለይም ወደ ውጭ በሚላኩ የሰብል ምርቶች ላይ ከጸረ-ተባይ ቅሪት መብዛት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ስጋት ፈጥሯል። በቀጣይም ተቀባይ አገራት ያላቸውን መስፈርቶች በማጥበቅ ላይ በመሆናቸው እና አሁን በሥራ ላይ ያለው የጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ 674/2002 ይኼን ለማስፈጸም ክፍተት ያለበት መሆኑን ተናግረዋል።
በአዋጅ 674/2002 ውስጥ በተግባር የታዩ ክፍተቶችን የሚሞሉና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ ማሻሻያዎች በማድረግ የዘመነ አገራዊ የጸረ ተባይ አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት ከባለሥልጣን መ/ቤቱ፣ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተውጣጡ ተመራማሪዎች፣ የሥራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ማዘጋጀታቸውን የተናገሩት አምባሳደር ድሪባ የምክክር መድረኩም ዓላማ በተዘጋጀው ረቂቅ የማሻሽያ ሃሳብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ሃሳብና ግብዓት በማሰባሰብ ረቂቅ አዋጁን ማዳበር መሆኑን ገልጸዋል።
አዋጁን ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በባለሥልጣኑ የፀረተባይና ማዳበሪያ ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር በየነ ንጋቱ እንዲሁም የፀረ ተባይ ኢንስፔክተር ባለሙያ በሆኑት በአቶ ኃይሉ መካ የተሻሻለውን ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ በምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች አዋጁ ላይ የሠራተኞችን የሥራ ላይ ደህንነትና ጤንነት፣ የጸረ ተባይ ንግድንና አወጋገድን በተመለከተ ታሳቢ አድርጎ ሌሎች ቢጨመሩና ቢቀነሱ ያሏቸውን ኃሳቦች አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በተነሱ ኃሳቦች ላይ ማጠቃልያ የሰጡት በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው የማሻሻያ አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ያለ በመሆኑ በምክክር መድረኩ የተነሱ ኃሳቦችን ታሳቢ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
አቶ መሰሉ አክለውም በጸረ ተባይ ምዝገባና ቁጥጥር ውጤታማ ሥራ ለመስራት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አውስተው ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ተቀራርቦ መሥራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።
1 411
እንኳን ለደማቁ የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!
ኢሬቻ የዝናብ ወቅት አልፎ ፀሀይ ሲገለጥ ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረቢያ ታላቅ በዓል ነው፣
መልካም በአል
Baga Ayyaana Irreechaatiin Isin Gahe!
