cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Dire Dawa Administration Education Office communication

DDAEOc Telegram Channel

Больше
Рекламные посты
1 996
Подписчики
+324 часа
+327 дней
+21730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳሬክቶሬት አዘጋጅነት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የንባብ ክሂል ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡ በግንቦት ወር ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይደረግ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ውድድሩ ሊከናውን ችሏል:: በተማሪዎች የንባብ ክሂል ውድድር ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዕለቱ የክብር እንግዳዋ የም/ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ሰላማዊት አስፋው በንግግራቸዉ የንባብ ውድድሩ መካሄድ በተማሪዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ንባብ ማንኛውንም ትምህርት ለመማር መሠረት ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት አንደኛ እርከን ላይ ማንበብ የቻሉ ተማሪዎች ለወደፊቱ የትምህርት እና የህይወት ስኬታቸው አይነተኛ ሚና ያለው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የትምህርት ባለድርሻ አካላትና ወላጆች ለሕጻናት የንባብ ክህሎት መዳበር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል። በዕለቱም ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የንባብ ክሂል ውድድሩ ላይ በድምሩ 21/ ሃያ አንድ ተማሪዎች በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ ፣ በአፍ-ሶማሌ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለውድድሩ ቀርበዋል፡፡ በውድድሩ ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የንባብ ምዘና የተደረገላቸው ሲሆን በውድድሩ፡- በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 1ኛ. ሌንሳ ነሻድ ……………ከገንደ አዳ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,500 ብር ተሸላሚ ሆኗለች፡፡ 2ኛ. ሀምዲ አብዲ……ከኦከሰዴ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,250 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 3ኛ. አኑ አህመድ………………ከገንደ አዳ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በአማርኛ ቋንቋ 1ኛ. ያብስራ አሰፋ…………… ከምስለ እናት ት/ቤት በማሸነፍ የ1,500 ብር ተሸላሚ ሆኗለች፡፡ 2ኛ. ሀመዛ መሀመድ……ከአዲስ ከተማ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,250 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 3ኛ. ልኡል ሰንደቅ………………ከምስለ እናት ት/ቤት በማሸነፍ የ1,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በአፍ-ሶማሌ ቋንቋ 1ኛ. ነገድ መሐመድ……………ከኢፍቲን ት/ቤት በማሸነፍ የ1,500 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 2ኛ. ፋጡማ ዱሀር……ከመልካጀብዱ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,250 ብር ተሸላሚ ሆኗለች፡፡ 3ኛ. ሙስጠፋ አብዲ………………ከአፈተኢሳ ት/ቤት በማሸነፍ የ1,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በመጨረሻም የክብር እንግዳዋ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ይህ ውድድር ተሻለ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ለማፍራት የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚን የሚፈጥር ሲሆን በዛሬው ዕለት ውጤት ቀንቷችሁ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጣችሁ ተማሪዎችና ት/ቤቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ ይህንን ውጤት በማስቀጠል የንባብ ክህሎታቸውን በላቀ ደረጃ በማስረፅና የተሻለ አቅም መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ፕሮግራሙም በዚሁ ፍጻሜውን አግኝቷል።
Показать все...
ሰኔ 10/በ2016 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና የቅድመ ዝግጅት እና በፈተናዎች አሰጣጥ ሂደት ላይ ኦረንቴሽን ተሰጠ። ~~~ በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚሰጠዉ የ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ለርዕሰ መምህራን፣ የክላስተርና የወረዳ ትምህርት ማስተባበሪያ ኋላፊዎች እና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ኦረንቴሽን ተሰጥቷቸዋል። በኦረንቴሽኑ ላይ ሰነድ ያቀረቡት የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ እሸቱ ሹሜ እና የICT ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይርጋ ሙሉነህ ስለ አጠቃላይ የፈተና ስርዓት አስተዳደር ግንዛቤ የሚያሲዝ ፅሁፍ አቅርበዋል። በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት እና በግል ት/ቤቶች በመደበኛና በምሽት የሚማሩ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን በዚህም 7ሺ 527 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ተጠቁሟል። ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ መሰረት በአስተዳደር ደረጃ 6ኛ ክፍል ፈተና እንዲሰጥ በተወሰነዉ መሰረት ዘንድሮ የሚጀመር መሆኑ ይታወቃል። እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ፈተናዉ ተጀምሮ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እና በከፍተኛ ዲሲፒሊን በጥንቃቄ እንዲመራ ሃላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ በኦረንቴሽኑ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ አስገንዝበዋል። ፈተናውም ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
Показать все...
sticker.webp0.31 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የደስታ፣ የፍቅር እና የሠላም እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ Hordoftoota amantaa Islaamaa hundaan baga Ayyaana Eid Al-Adha(Arafaa) kan bara 1445ffaa nagaan geessan jechaa ayyaanni kan Gammachuu, Jaalalaa fii Nagaa akka isiniif ta’u hawwa. Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Diree Dhawaa
Показать все...
ሰኔ 8/2016ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኋላፊ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ መልቀቂያ ፈተና ሂደት ላይ የታዩ ጠንካራ ና ደካማ ጎኖችን የፈተሸ የአፈጻጸም ግምገማ ከፈተና አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ። በዚህ የመገምገሚያ መድረክ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኋላፊ የሆኑት አቶ ሱልጣን አሊይ ከዛሬው ከሚቀርበው ሪፖርት ተነስተን በቀጣይ ቀናት በአስተዳደር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው ቢሮው ከምንግዜውም በላቀ ሁኔታ የፈተና አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችለውን የአሰራር ስርዓት እየዘረጋን እንገኛለን ብለዋል። በውይይቱ ወቅት ባለፋት ቀናት በፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች የነበሩባቸውን ችግሮች ሪፖርት አቅርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በመጨረሻ በቢሮ ኋላፊ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ከመድረክ ምላሽ የሱጡ ሲሆን በቀጣይ ከነዚህ ችግሮች በመላቀቅ በ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ላይ ተሻሽሎ ሊስራ እንደሚገባ አሳስበው የቀጣይ የስራ መመሪያ ሰተው የውይይት መድረኩ ፍፃሜውን አግኝቷል።
Показать все...
01:23
Видео недоступноПоказать в Telegram
20240614_195608.mp4101.09 MB