cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Masa Farm Journal (ማሳ)

Masa was founded to support commercial farmers. We do this by sharing relevant agricultural information like the latest news, weather info, interesting studies, price info, subsidies etc. https://masaeth.com/

Больше
Рекламные посты
445
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
+1030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የግብርና ኬሚካሎች በኢትዮጵያ 🌾 የግብርና ኬሚካሎች በዘመናዊ የግብርና ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ አላቸው። በአንድ በኩል ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድጉ ሲሆን በሊላ መልኩ በግብአት ላይ ጥገኛነትን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ከ2017 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ከውጪ ሀገራት ገቢ የተደረጉት የግብርና ኬሚካሎች እንደሚከተለው የቀረቡ ሲሆን የቀረበው መረጃ አሃዛዊ እውነታውን በኬሚካል አይነቶች እና በክብደት ያሳያል። #ግብርና_ግንዛቤዎች #ዘላቂ_እርሻ #የኢትዮጵያ_ግብርና
Показать все...
ከመጋቢት ወር ጀምሮ እስከ ሰኔ ድረስ በጋምቤላ ክልል በሚገኙ እርሻዎች ላይ በእርሻ ሪፖርት የተደገፈ ጥናት ስንዳስስ ቆይተናል። ጥናታችን የሰሊጥ እርሻዎችን ምርት ለማሳደግ የሚረዳ የእርሻ መመሪያ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ምርታማነትን ለማረጋገጥ የአየር ሁኔታን፣ የተባይ ስጋትን እና የእርሻ አስተዳደር እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጥናታችን ለጥሩ ምርታማነት ጊዜውን ጠብቆ ዘር መዝራት፣ በሽታ እና ተባይ የሚቋቋሙ ምርጥ ዘሮች መጠቀም እንዲሁም በየጊዜው እርሻችን ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ በተገቢው ጊዜ መውሰድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳላቸው ማሳየት ችሏል። #sesame #sesame_production #ethiopia #farm_management #phenology
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
"The session gave a wider view of how agricultural investors can access loans." Ato Dereje was one of the participants in the first "agricultural-financing" training session. Much like Ato Dereje, most of the session participants found the session insightful. The second session is going to be held on October 6, 2023. Make sure to register and reserve your spot! For more details follow the link http://bit.ly/3ZFyk7e #agriculture #investment #finance #training #Ethiopia
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀጣዩ የሁለተኛ ዙር ስልጠና በሚመጣው ቅዳሜ መስከረም 12 ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት የሚዘጋጅ ሲሆን አሁኑኑ በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ ! Make sure not to miss the next session to be held this coming Saturday on September 23, 2023. 📅 ቀን: መስከረም 12 2016 🕒 ጊዜ፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ረፋዱ 6 ሰዓት 📍 ቦታ፡ 22 ጫካ ቡና ፊት ለፊት #agri_financing #የግብርና_ፋይናንስ #DBE #ኔትወርክ #network
Показать все...
ቀጣዩ የሁለተኛ ዙር ስልጠና በሚመጣው ቅዳሜ የሚዘጋጅ ሲሆን አሁኑኑ በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ ! Make sure not to miss the next session to be held this coming Saturday on September 23, 2023.
Показать все...
00:58
Видео недоступноПоказать в Telegram
የመጀመሪያውን የግብርና ፋይናንሲንግ ዙር ስልጠና የግብርና ኢንቨስትመንት ባላቸው እና የግብርና ኢንቨስትመንት መጀመር የሚፈልጉ ባለሃብቶች ታድመውን ነበር። በስልጠናውም ከኢትዮጵያ ልማት የመጣው ከፍተኛ ባለሙያ ታዳሚዎቹ የነበራቸውን ጥያቄዎች ግልፅ ያደረገላቸው ሲሆን በስልጠናውም ይዘት መደሰታቸውን ታዳሚዎቹ አጋርተውናል። #agriculture #investment #finance #training #Ethiopia
Показать все...
Testimonial 1.mp48.77 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
በግብርና ፋይናንስ ሂደት ላይ በነበረን የመጀመሪያ መርሀ-ግብር ባገኘነው አስደሳች የተሳታፊ ምላሽ መሠረት ሁለተኛ መርሀ-ግብር እንዳዘጋጀን ስንገልፅ በደስታ ነው። 🌟🌾 ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር በመውሰድ የግብርና ፕሮጀክትዎን ለማሳደግ ወይም ግብርና መጀመር የሚፈልጉ ከሆኑ ይህ ስልጠና ለእርስዎ ተዘጋጅቷል። የልማት ባንክ የብድር ሂደት፣ ብድር በመውሰድ ሂደት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች፣ መሟላት ያለባቸው ዶክመንቶች እና የመሳሰሉትን ብድር ነክ ጥያቄዎችን በጥልቀት እንመረምራለን። 💡 📈 📅 ቀን: መስከረም 12 2016 🕒 ጊዜ፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ረፋዱ 6 ሰዓት 📍 ቦታ፡ 22 ጫካ ቡና ፊት ለፊት #agri_financing #የግብርና_ፋይናንስ #DBE #ኔትወርክ #network
Показать все...
👍 4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምን አይነት የብድር አማራጮችን ይሰጣል? የብድር ጥያቄ ካስገባን ጀምሮ ብድሩን እስከምናገኝ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? የግብርና ብድር ለመውሰድ ምን አይነት መስፈርቶችን ማሟላት አለብን? እነዚህን እና የመሳሰሉትን ከግብርና ብድር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከመጣው ከፍተኛ ባለሙያ ጋር ውይይት አድርገናል። በተጨማሪም ማሳ ምን አይነት አገልግሎት እንደሚሰጥም ማሳየት ችለናል። እርስዎስ ከልማት ባንክ ብድር ለመውሰድ አስበዋል? ግብርና ለመጀመር እና ብድር ለማግኘት ምን አይነት መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባችሁ ያውቃሉ? እነዚህን እና ሌሎችም እንዲመለስላችሁ የሚፈልጉትን ብድር ነክ ጥያቄዎች በሁለተኛው የስልጠና መርሀ ግብራችን ላይ በመታደም መጠየቅ እና ማማከር ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ LinkedIn እና Telegram ገፆቻችንን ላይ ይከታተሉን!
Показать все...
የመጨረሻው የእድገት ሳምንት፡ #የመድረቅ_ደረጃ በመጨረሻው የመድረቅ ደረጃዎች ላይ ሰብላችን ጥሩ ፀሀይ እና ንፋስ መጠን የሚያገኝ ከሆነ የመድረቅ ሂደቱ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል። ሰሊጥ ከእርሻ ላይ መሰብሰብ ያለበት የእርጥበት መጠኑ ከ8% እስከ 12% ሲደርስ ሲሆን በመድረቅ ደረጃው ወቅት የፍሬ ከረጢቶቹን መክፈት ይጀምራል። በዚህም ምክንያት የሰብላችንን የእርጥበት መጠን መከታተል፣ ሰብላችንን ለመሰብሰብ በቂ ዝግጅት ማድረግ እና የፍሬ ከረጢቶቹ ተከፍተው የምርት ብክነት ስጋት በማይኖርበት ጊዜ ምርታችንን መሰብሰብ አለብን። #late_drying_stage #harvest #sesame #ethiopia #agriculture
Показать все...