cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

✞✟ ኦርቶዶክሳዉያን ✞✟

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣቹ ይህ ቻናል የተከፈተው ለኦርቶዶክሳውያን እና ማወቅ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ነው ✞መዝሙር ✟ግጥም ✞ኦርቶዶክሳዊ ፎቶ ያገኙበታል

Больше
Рекламные посты
501
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

[ + ሥላሴን አመስግኑ + ] .mp31.35 MB
[ + ኃይልየ ሥላሴ + ] .mp33.24 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
† 🕊         ቅድስት ሥላሴ      🕊 " የቅድስት ሥላሴ ዕምነት የሃይማኖት መጨረሻ ናት፡፡ የሥላሴ ዕምነት መግቢያ በር ወልድ ዋህድ ብሎ ማመን ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሥርዓት በዚህ የሥላሴ አርአያ ተመሠረተ፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም ለታመኑ የሕይወት መታወቂያ ማኅተም ነው ለዝንጉዎች ግን የጥፋታቸው ቁልፍ ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የሕሙማን መፈወሻ የክፉዎች አጋንንት ማባረሪያ ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የአስማተኞችን ወይም የጠንቋዮችን ጥበብ የሚያጠፋና የሟርተኞችን መርዝ የሚያበርስ [ የሚያከሽፍ ] ነው፡፡ ይህ ግሩም የሥላሴ ስም የበሽተኞች መድኃኒት የሙታን ትንሣኤያቸው ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም አሸናፊ የሆኑ የሰማዕታት የገድላቸው ሞገስ የብሩካን ጻድቃን የጸሎታቸው የመልካም መዓዛ ሽታ ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የረከሱትን የሚቀድሳቸው የተዳደፉትን የሚያነጻቸው ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም እንደ መጎናጸፊያ እጎናጸፈዋለሁ ከእንቁ እንደተሰራ እንደ እራስ ወርቅም እቀዳጀዋለሁ፡፡ በዚህ ግሩም በሆነ የሥላሴ ስም እታመናለሁ በመጎንበስም እሰግድለታለሁ፡፡ ለዚህ ግሩም አስፈሪና አስደንጋጭ ለሆነ የሥላሴ ስም በፊቱ ተንበርክኬ በደስታ እሰግዳለሁ፡፡" [  ሰይፈ ሥላሴ  ] 🕊 ኃይልየ ሥላሴ ! [  ኃይሌ ሥላሴ ነው ! ] ወጸወንየ ሥላሴ ! [  አምባ መጠጊያየም ሥላሴ ነው !  ] በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ ! [ በሥላሴ ስምም ጠላትን /ዘንዶውን/ እቀጠቅጠዋለሁ ! ] የአብርሃምን ድንኳን የጎበኙ ሥላሴ : የእኛንም ቤት በቸርነታቸው ይጎብኙልን . . . አሜን ! [       🕊   ክብርት ሰንበት   🕊        ] 💖               🕊                💖
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🕊 [ †  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ] 🕊   †  ሥሉስ ቅዱስ   †   🕊 በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና:: ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ:: ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል:: አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው:: ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና:: 🕊   †  ታላቁ አባ ሲኖዳ  †   🕊 የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :- ¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ ¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ ¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት ¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት ¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ ¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ ¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ ¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው:: ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ ¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ ¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ ¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ ¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ ¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና ¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው:: በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::] ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው:: 🕊   † አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ  †  🕊   [GIYORGIS_OF_SEGLA] ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ:: ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር ፵፩ [41] ድርሰቶችን ደረሰ:: [መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ] ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች :- ፩. ሊቀ_ሊቃውንት ፪. በላዔ_መጻሕፍት ፫. ዓምደ_ሃይማኖት ፬. ዳግማዊ_ቄርሎስ ፭. ጠቢብ_ወማዕምር ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ፷ [60] ዓመቱ በ፲፻፬፻፲፰ [1418] ዓ/ም  በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ ፯ [7] ቀን ነው:: የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: 🕊 [ †  ሐምሌ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ [ሥላሴን ያስተናገዱ] ፪. ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ ፫. ታላቁ አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን ሁሉ አለቃ] ፬. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ [ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ የሃይማኖት ምሰሶ] ፭.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ [ምጥው ለአንበሳ] ፮. አባ መቃቢስ ፯. አባ አግራጥስ [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፪. አባ ባውላ ገዳማዊ ፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ " እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ :- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: " [ዕብ.፮፥፲፫] (6:13) " የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [ቆሮ.፲፫፥፲፬]  (13:14) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
[ ስንክሳር ሐምሌ - ፯ - ] .mp32.92 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
                        †                              †      🕊    ዘላለም ሥላሴ    🕊     † †  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ  ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † 🕊                        💖                       🕊 " በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ፤ ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል ፣ እርሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም። " [  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ] †      🕊    እንኳን  አደረሰን    🕊     † 🕊                        💖                       🕊
Показать все...
01 Track 1.mp37.15 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.