cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🎖🎖ሰው ሁን ከሰውም ሰው🎖🎖

For Any Comment Inbox Me @umbeya

Больше
Эфиопия1 661Амхарский1 328Категория не указана
Рекламные посты
12 739
Подписчики
-1124 часа
-957 дней
-45330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡ በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡ ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡ አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን? መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች … • ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት  ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡ • ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡   • አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡ እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ? dr eyob mamo ✍ታዚ
Показать все...
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡ በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡ ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡ ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡ አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን? መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች … • ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡ • ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ • አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡ እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показать все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”
Показать все...
7ቱ የሴቶች ውሸት / ለፈገግታ 1 "አንተኮ በጣም መልካም ሰዉ ነህ፡፡ አሪፍ ጓደኛህ እሆናለሁ" ትርጉም፡- ከጓደኝነት ዉጪ እኔን ፍቅረኛህ ለማድረግ እንዳትሞክረዉ! 2 "ፔሬድ ላይ ነኝ ራሴን አሞኛል" ትርጉም፡- ፔሬድ ላይ አይደለሁም... ራሴንም አላመመኝም፡፡ ግን ወሲብ መፈፀም ስለማልፈልግ እባክህን ተወኝ! 3 "አንተኮ ከኔ የተሻለ ሰው ይገባሃል!... እኔ ላንተ ምርቃት ነገር ነኝ!" ትርጉም፡-በል አርፈህ ተቀመጥ፡፡ ደባሪ ነህ ! ባይገርምህ አትመጥነኝም! 4 "ከ 5 ደቂቃ በኋላ እወጣለሁ፡፡" ትርጉም፡- በል 30 ደቂቃ ጨምርበት፡፡ ደፋር!   5 "እሺ በቃ ይቅር ብዬሃለሁ የኔ ዉድ!" ትርጉም፡-የእጅህን ካልሰጠዉህ እኔ ሰዉ አይደለሁም! ያደረከዉን የምረሳ አሻንጉሊትህ አይደለሁም! 6 "ደህና ነኝ" ትርጉም፡- ኤጭ ምን ይጨቀጭቀኛል...ገና መከራህን ትበላታለህ!   7 "ክብደቴን ለመቀነስ እራት አልበላም" ትርጉም፡- ለእናንተ ተውኩት.. ... እስኪ የተረሳ ካለ ጨምሩበት ✍ታዚ
Показать все...
👏 1
# መናገር ወይስ ማሰብ የቱ ይቅደም? በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል፤ ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡ 1. አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣ 2. አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣ 3. አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡ ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡ ከቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ጊዜ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡ ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም ፤ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡ «እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡ «አልቻልኩም» አላቸው፡፡ «ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡ «በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡ «ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት ይባላል። # ከመናገር ይልቅ ማሰብ ይቅደም!!! ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እውነት ነው የብዙዎቻችን ችግር ሳናስብ መናገር መልካም ቀን❤ https://t.me/gates5gatesjo https://t.me/gates5gates
Показать все...
👍 4👏 1
የአእምሮ ህክምና እርዳታ እንዴት ማግኘት እንችላለን? በአዲስ አበባ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች  የአዕምሮ ህክምና ባለሙያዎች አሉ:: እነዚህ ባለሙያዎች፣ ታካሚዎችን ከመረመሩ በኋላ እንደየአስፈላጊነቱ የተሻለ ህክምና ካስፈለገ ወደ ሆስፒታሎች ሊልኳቸው ይችላሉ:: የአዕምሮ ህክምና ከአማኑኤል ሆስፒታል በተጨማሪ በኤካ ኮተቤ፣ በጥቁር አንበሳ፣ ቅ/ጳውሎስ፣ ዘውዲቱ፣ በራስ ደስታ እና በአለርት ይገኛሉ።  እንዲሁም በክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ይሰጣል። የአእምሮ ህክምና በግል ተቋማትም ይሰጣል። ""ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!!"  ከEthio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ) ✍ታዚ
Показать все...
👍 4
#ማማዬ ሁሉንም ነገር ትክክል ለማድረግ አትጨነቂ። ሱፐር እናት ሱፐር ሚስት ሱፐር የቢሮሰራተኛ ሱፐር ሱፐር ሱፐር ለመሆን አትሞክሪ ምክንያቱም ሰውነትሽና አይምሮሽ ሲደክም ሁሉንም ነገር ፐርፌክት ማድረግ እንደማትችይ ይገባሻል እናም ቤቱን ለትንሽ ጊዜ ተይው እስቲ። ወጣ በይ ዎክ አድርጊ፣ ከጓደኞችሽ ጋር ሻይቡና በይ፣ ወደሀይማኖት ቦታ ሂጂ፣ እስፖርትሽን ስሪ፣ ፀጉር ቤት ሂጂ፣ ባጭሩ ለራስሽ ጊዜ ስጪ የሚያስደስትሽን ነገር አድርጊ ልጆችም ያድጋሉ አንዳንዴም ባልሽም ጥሎሽ ሊሄድ ይችላል ስራቦታሽም በሌላ ሰራተኛ ሊተካሽ ይችላል ቤቱም ተመልሶ ሊቆሽሽ ይችላል ነገር ግን አንቺ ዳግም ለመኖር ሁለተኛ እድል የለሽም አራት ነጥብ❗️ሩጫና ጭንቀትሽን ቀንሺና ለራስሽ ጊዜ ስጪ ራስሽን አክብሪ ራስሽን ውደጂ ©️kiya Bekele #እናትነት #እረፍት #mindthemind
Показать все...
🙏 6
Father complex or daddy issue and childhood trauma ያለባቸው ሴቶች በrelationship ላይ ያላቸው attachment በተወሰነ መልኩ ይህን ይመስላል። ከዝርዝሩ በፊት ግን ማንኛዋም ሴት ከመጠን በላይ የምታፈቅር ልትሆን አትችልም።በዚህ ማህበረሰብና ቤተሰብ ውስጥ ሆኖ ማደግ የተወሰኑ የሚከተሉት ሊተነበዩ የሚችሉ ሁኔታዎችን መፍጠር ይችላል። ለአንቺም ሊሆን ይችላል። 1/ ከሀሉ በፊት፣ ያደግሽው ስሜታዊ ፍላጎቶችሽ በማይሟሉበት ቤተሰብ ውስጥ ነው። 2/ አንቺ ያገኘሽው እንክብካቤ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ፣ በተለይም እንክብካቤን ለሚሹ ወንዶች ክብካቤን ለመስጠት ይህንን ያልተሟላ ፍላጎትሽን ለመሙላት ትፈልጊያለሽ። 3/ወላጆችሽን specialy አባትሽን ወደምትፈልጊው አፍቃሪና ተንከባካቢነት ልትለውጪ ሳይቻልሽ በመቅረቱ፣ ይህን ፍላጎትሽን በስሜት የራቀሽን ያንን ወንድ ለመለወጥ ፍቅርሽን መጠቀም ትጀምሪያለሽ። 4/ብቻሽን መቅረት ስለሚያስፈራሽ፣ አንድ ግንኙንት እንዳይከስም የማታደርጊው ነገር የለም። 5/አብሮሽ ያለውን ወንድ  ለመርዳት ምንም ችግር አይገብሽም፣ ጊዜ ይወስዳል አትይም፣ ዋጋው ውድ ነው ብለሽ አታስቢም (ብዙ ሱስ ያለበት፣ ተደባደቢና ተሳዳቢ ቢሆንም……) 6/በግል ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነቶች ፍቅርን ማጣትን የተለማመድሽ በመሆንሽም ግለሰቡን ለማስደሰት ለመታገስ፣ ተስፋ ለማድረግና የበለጠ ለመሞከር ፈቃደኛ ነሽ። 7/ከሀላፊነቱ፣ ከጥፋተኝነቱና ከማንኛውም የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ከሚፈጠረው ፀፀት መሀል ከግማሽ የሚበለጠውን ድርሻ ለመቀበል ዝግጁ ነሽ ( even ጥፋቱ የሱ ብቻ ቢሆንም እንኳ) 8/ ለራስ ያለሽ ግምት በጣም ዝቅተኛ ነው፣ ውስጥሽም ደስታ ላንቺ እንደማይገባሽ ያምናል። በዚህ ፈንታ፣ ህይወትን በደስታ የመኖር መብትሽን በልፋት ማግኘት እንዳለብሽ ታምኛለሽ። 9/ በልጅነትሽ ከምታውቂው አነስተኛ ደህንነት የተነሳ ወንዶችሽንና ከእነሱ ጋር ያለሽን ግንኙ ነት ለመቆጣጠር አጥብቀሽ ትፈልጊያለሽ። 10/ አንድ ግንኘነት ውስጥ ስትሆኚ፣ ከግንኙነቱ እዉነታ ይልቅ ግንኙነቱ እንዲሆንልሽ በምትፈልጊው ህልምሽ ውስጥ ትኖሪያለሽ። 11/ የወንዶችና የስሜት ስቃይ ሱስ ይኖርብሻል። 12/ ለአደንዛዥ ዕፆች፣ ለአልኮል እና ወይም ለተለዩ ምግቦች በተለይም ስኳርነት ላላቸው ሱስ የተጋለጠ ስሜትና አካላዊ ቅንብር አለሽ። 13/ መፍትሔን የሚሻ ችግር ወዳለባቸው ሰዎች በመሳብ ወይንም ውጥንቅጥ፣ እርግጠኝነት የጎደላቸውና ስሜትን የሚጎዱ ሁኔታዎች ውስጥ በመግባት ከራስሽ ኃላፊነቶች ትሸሻለሽ። 14/ ለተከታታይ ጭንቀቶች የተጋለጥሽ ልትሆኚ ትችያለሽ፣ ይህንንም ዘለቄታ ከሌላቸው የፍቅር ግንኙነቶችሽ በምታገኚው ደስታ ለማስታገስ ትሞክሪያለሽ። 15/ሩህሩህ፣ ጠንካራ፣ አስተማማኝና በአንቺ የተማረኩ ወንዶች አይስቡሽም።    ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት አይነት ባህሪና ስሜቶች ያላችሁ ሴቶች እራሳችሁን ወደኋላ መለስ ብሎ መፈተሽ አስፈላጊ ነው። በዚህ አመት እራሳችሁን ከtoxic relationship እንደምታወጡ ተስፋ አደርጋለው። ✍ በኃይሉ( ታዚ)
Показать все...
8
🌓"ለምንድነው_መኖር_የደከመህ?? ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? እሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ፡ ☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡ ☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡" አዎ አሁንም ታስፈልጊናለሽና በርቺልን እህቴ ✍ታዚ
Показать все...
🙏 3😢 2 1
Repost from Five(5)Gates Center
🌓"ለምንድነው_መኖር_የደከመህ?? ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? እሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ፡ ☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡ ☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡ ☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡"
Показать все...