cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Infotainment

Information and Entertainment

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
179
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

እመን! "አንድ እምነት ያለው ሰው ፍላጎት ብቻ ካላቸው 99 ሰዎች እኩል አቅም አለው" ይለናል ጆን ስቱአርት ሚል። የእምነትን ፍሬ ሳትዘራኸው ማጨድ የለም፤ ምንም ነገር እንደማያቅትህ በሂደት ሁሉም ነገሮች እንደሚሳኩልህ ማመን አለብህ! ግሩም ማክሰኞ ተመኘንላችሁ🙏 @infotement
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብዙ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው ስልችት የሚላቸውና ባዶነት የሚሰማቸው ህይወትን እስከመስጠት ድረስ ከፍ የሚል ዋጋ ሊከፍሉለት የሚችል ራእይና ዓላማ የሌለው ሕይወትን ስለሚኖሩ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኑሯቸው ደስ የሚላቸውና ሙሉነት የሚሰማቸው ጊዜያቸውንም ሆነ ሕይወታቸውን እስከመክፈል ድረስ የሚኖሩለትን ነገር ስላገኙት ነው፡፡ “የምትሞትለት ዓላማ ከሌለህ የምትኖርለት ዓላማ የለህም ማለት ነው” ሕይወትን እስከመክፈል ድረስ ራሳችንን የምንሰጥለት ዓላማ፣ ዛሬ ሕይወትን እንድናጣጥማት የማድረግ ጉልበት አለው፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#የአእምሮህን_ፍሬ_ትበላለህ የሰው አእምሮ ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ኃይል የመጠቀምን ከንቱነት በተመለከተ የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ያህል ትልቅ ማሳያ ትቶ ያለፈ ታሪካዊ ክስተት የለም ማለት ይቻላል፡፡ ሃሳቡን ወደሚያሳዩ ዝርዝር ነገሮች መግባት ሳያስፈልግ የጀርመን ፍልስፍና ባለፉት አርባ ዓመታት ገደማ ያለፈበት መሰረቱ ኃይል የነበረ መሆኑን መረዳት ቀላል ነው፡፡ ነገሮችን በትክክል ለመከወን የሚያስችለው መመሪያ እና መርህ ለዓለም ሁሉ ተሰጥቶ ነበር፤ ግን ውጤት አላመጣም፡፡ የሰው አካል በአካላዊ ኃይል ቁጥጥር ስር ሊሆን ወይም ሊታሰር ይችላል፡፡ አእምሮ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ፈጣሪ የሰጠውን አእምሮውን የመቆጣጠር መብቱን ለመጠቀም የመረጠን የትኛውንም ጤነኛ ሰው በቁጥጥር ስር ሊያደርግ የሚችል ሰው ምድር ላይ የለም፡፡ ብዙ ሰዎች ይሄን መብታቸውን አይጠቀሙም፡፡ ምስጋና ለውዳቂው የትምህርት ሥርዓታችን ይሁንና በዓለም ውስጥ ሲኖሩ፣ በትምህርት ቤት ሕይወታቸው ውስጥ ሲያልፉም በአእምሯቸው ውስጥ ተደብቆ የተኛውን ድብቅ ኃይል እንዲያውቁ አይሆንም፡፡ በተደጋጋሚ በሚባል ደረጃ አጋጣሚ በሚመስል ሁኔታ ሰዎች ይሄን ኃይላቸውን ማወቅ እንደሚችሉ እና አግኝተውም እንዲጠቀሙበት የሚያነቁ ልዩ ልዩ ነገሮች ይፈጠራሉ፡፡ በውጤቱ ጀግና፣ ምጡቅ ይወለዳል! የሆነ ለየት ያለ ነገር ተፈጥሮ ወደ መሰናክሎች የሚወስደው ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የሰው ልጅ አእምሮ ማማተር እና ማደግ የሚያቆምበት የሆነ ነጥብ አለ፡፡ በአንዳንድ አእምሮዎች ውስጥ ይህ ዝቅተኛ፣ በሌሎች ውስጥ ደግሞ ከፍተኛ ነው፡፡ ሰው ሰራሽ በሆነ ሁኔታ በራሱ መንገድ አእምሮውን ከዚህ ነጥብ መቀስቀስ እና ማነሳሳት የቻለ የትኛውም ሰው ጥረቱ ገንቢ በሆነ አቅጣጫ ከሆነ ፍሬውን መብላቱ አስቀድሞ የተረጋገጠ ነው፡፡ #ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ
Показать все...
1. ሁለታችሁም በተመሳሳይ ጊዜ የንዴትን ስሜት አትግለጡ፡፡ 2. በቤታችሁ ድንገተኛ እሳት ተነስቶ አንዱ ሌላውን ለማንቃት ካልሆነ በስተቀር አንዱ በሌላው ላይ አይጩህ፡፡ 3. ጭቅጭቅ እንዲፈጠር የሁለት ሰዎችን ተሳትፎ እንደሚፈልግ አስታውሱ፡፡ አንዱ ሲረጋጋ ጭቅጭቁ ይረግባልና አጋራችሁ ሲጨቃጨቅ እናንተ ተረጋጉ፡፡ 4. አንደኛችሁ የሌላኛውን ፍላጎት ለማሟላት የተቻላችሁን አድርጉ፡፡ 5. በሌሎች ሰዎች ምልከታ መልካም ሆናችሁ ለመታየት ስትሉ አጋራችሁን አጋልጣችሁ አትስጡ፤ በቅድሚ እነሱ መልካም ሆነው እንዲታዩ የምትችሉትን አድርጉ፡፡ 6. አጋራችሁን በአንድ ሃሳብ መሞገት እንዳለባችሁ ስታምኑበት በታላቅ ትህትናና ፍቅር አድርጉት፡፡ 7. ያለፈ፣ የቆየና የተዘጋን ስህተት እንደገና ጎትታችሁ አታምጡ፡፡ 8. አጋራችሁን ችላ ከምትሉ በዙሪያችሁ ያለውን ሰውና ሁኔታ ችላ ብትሉና ለአጋራችሁ ቅድሚያ ብትሰጡ ይሻላል፡፡ 9. ለአጋራችሁ ቢያንስ አንዲት የምስጋና ወይም የአድናቆት ቃልን ሳታወጡ አንዲትም ቀን አትለፍ፡፡ 10. ሁለታችሁም ከነበራችሁ የቀን ውሎ ስትገናኙ ፍቅር የተሞላበትን ሰላምታ መለዋወጣችንና እንደገና ስለተገናኛችሁ ደስተኛ መሆናችሁን መግለጽን ተለማመዱ፡፡ 11. ስህተትን ስትሰሩ ስህተታችሁን በግልጽ በማመን ይቅርታን ጠይቁ፡፡ 12. በፍጹም በብስጭትና ባለመግባባት ወደ መኝታ አትሂዱ፡፡ (ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን ለተወጋዉ ጎንህ ለበትረ መስቀልህ ለፈሰሰዉ ደምህ ቀራንዮ ሞትህ ጎለጎታ ቤትህ ኪራላይሶን ማረን ለዛ ህማማትህ። አባ አባታችን በጥፊ ስመታህ እጆቼን ይዘሀኝ ልማርህ ብለሀል ዉሀ አልሠጥም ብዬ በከርቤ ኮምጣጤ ጉንጭህን ሞልተሀል ጠማኝ አባቴ ስል ይሄ አይጠቅምም ብለህ የዘላለም ዉሀ ለኔ አዘጋጅተሀል። ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን.......... መፃጉ ሆኜ ሳለሁ መዳኔን ሽተሀል አልጋህን ተሸከም ብለህ ምረሀኛል ሰንበት አፈረሰ እያልኩ መክሰሴን ጌታ አረሳሁትም ማራት ይህቺን ነፍሴን። ጎንህን ወጋሁት በጦሩ ጎርጉሬ አቤቱ ማዳንህ አይኖቼን አበራህ ትተህ መነወሬን። የሀጥያቴ መብዛቱን አይተህ ሳትጠየፍ ፈራሽ ሰዉነቴን አፈር ማንነቴን ተመልክተህ ሳታልፍ እኔ የከንቱ ከንቱ ፊትህን ተጠይፊ የማይፈርስ አካልህን ፍቅርህን ጠፍፌ ማረዉ ብለህ ስትል ሰዉነቴ ቀፎት ምራቅ ተፋዉብህ ለኔ መምጣትህን እኔነቴ ክዶት። ኪራላይሶን ማረን ስለናትህ ማረን................ ሸክማችሁን በኔ ጣሉት ብለህ ስትል ችግሬን ጥዬብህ እንቅልፍና እረፍትን ባንተ አገኘዉብህ ችግሬ አንሶብኝ መስቀል ማሸከሜን ጌታ አትይብኝ ከኃላ እንድትፈጥን እየገፈተርኩ ከፊት ቀስ እንድትል እየገፈተርኩ መሬት ስትወድቅ እያንቀለቀልኩ ስትነሳ ደግሞ እያወዛገብኩ መቼ ይረሳኛል እንዳንከራተትኩህ። ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን............... መዳፍህ ይታየኛል ጭቃ አበጃጅቶ እኔን የሰራልኝ ዳብሶ የፈወሰኝ እኔ የእፉኝት ልጅ አዴራ አላዶር ሳዳርና ዳናት በሚባል ችንካሮች መዳፍህን በሳዉ አለምን በያዙ በነዛ ድንቅ እጆች። እግርህን ቸነከርኩ ምድርና ሰማይ ሊችሉት ያልቻለ አልፋና ኦሜጋ በመስቀል ላይ ዋለ። ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን ❤❤❤❤❤❤❤❤ በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍ ♥♥♥♥♥♥♥♥ @infotement
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሀብታም መሆንና ገንዘብ ማግኘት ግዜ ይፈጃል..ያለፋል፣ ጤናማና ስፖርተኛ ሸንቀጥ ያለ የሰውነት አቋም መገንባት ግዜ ይፈጃል ፣ ያለፋል፣ ….መልካም የሆነ ዘላቂነት ያለው የትዳር ፣ የፍቅርና የማህበራዊ ህይወት ግዜ ይፈጃል ፣ ያለፋል ፣ ዋጋ ያስከፍላል ፡፤ በየትኛውም የህይወት መንገድ ለስኬት የምናደርገው ጉዞ ልጅ ወልዶ እንማሳደግ ነው፡፡ ምክንያቱም ልጅ ከተወለደ ጀምሮ ለመጀመሪያዎቹ ሶስተ አመታት እንቅልፍ ይነሳል.ሃያ አራት ሰአት ተንከባከቡኝ ፣ ጠብቁኝ ይላል …ትንሽ አድጎ ትምህርት ቤት ሲገባ ግን የተወሰነ ግዜ ስለምናገኝ ማረፍ እንጀምራለን ..እንረጋጋለን..… አድጎ፣ተምሮ ዩኒቨርስቲ እስኪገባና ራሱን እስኪችል ድረስ ጭንቀቱ እንደድሮው ባይሆንም የተወሰነ እየቀለለ ይሄዳል። ከዛም ስራ ሲይዝና ሙሉ ለሙሉ ራሱን ሲችል ደግሞ ከራሱ አልፎ ወላጁን መልሶ መጦርና መንከባከብ ይችላልማለት ነው፡፡ ስለዚህ ስኬትን ወይም ከህይወት የፈለግነውን ነገር ጥረታችንን ከጀመርን በሳምንታችን ታላቅ ውጤት መጠበቅ ገና ከእናቱ ማህፀን ከወጣ ወር ያልሆነውን ልጃችንን ጡረን ወይም አስተዳድረን ማለት ነው፡፤ የህይወት የስኬት ጉዞም እንደዛ ነው በራእያችንና በግባችን ዙረያ ስንቀሳቀስ የተወሰነ ለውጥ በሶስት ወር …ቀጥሎም በአንድ አመት ቀጥሎም በሶስት አመት…. በአምስት አመት…ቀጥሎም በአስር አመት እንጂ! ህይወታችን የሚቀይረው የምናውቀው ነገር ወይም ማረግ የምንፈልገው ነገር ብቻ ሳይሆን ያን ለመከወን የሚያስፈልገውን ውሳኔ፣ተግባር፣ መስዋእት ከፅናት ጋር እየከፈልን ቀን በቀን ራሳችንን እያሻሻልን እየተገበርን እየተንቀሳቀስን ፣ ስንወድቅ እየተነሳን፣ ስህተታችንን፣ጥፋታችንን ፣ አካሄዳችንን ፣ እውቀታችንን፣ስትራቴጂያችንን፣ድርጊታችንን እንደችግሩና እንደ ሁኔታው እያሻሻሽልና እየለዋወጥን ወደ ፊት ያለ ፍርሀት በድፍረት በመጉዋዝ ራሳችንን ወደ ህልማችንና ግቦቻችን መግፋት ስንችል ብቻ ለስኬት የተገባን ምርጥ ሰዎች መሆን የምንችለው። ጠንከረን ተስፋ ሳንቆርጥ እስከተጉዋዝን ድረስ ግን ያሰብነው ቦታ እንደርሳለን! (በቢፀ ተስፋዬ) @infotement