cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተዋህዶ ሃይማኖቴ😇🙏🙏🙏

#ለተዋህዶ አማኝ ብቻ😇 #ለመንፈሳዊ አለም🙏 #ትምህርቶች💗 #መዝሙሮች💕 @tewahd0

Больше
Рекламные посты
206
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
🕊  መስከረም ፳፱    እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። " ሰማዕቷ ግን ፦ " ከሰማያትና ከምድር ንጉሥ ከእግዚአብሔር አምላኬ ትለየኝ ዘንድ የወደድክ ሰነፍ ንጉሥ ሆይ ! የሰይጣን መልአክተኛና የጥፋት ልጅ ፤ የይሁዳ ወገን ከእኔ ምን ትሻለህ ? ከወደድክስ በእጅህ ሰማዕት እሆን ዘንድ እወዳለሁ" አለችው፡፡ ......  እጅግ ስላፈረ አስገረፋት ፣ አሰቃያት ፣ ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት፡፡ "                             🕊 " ሰማዕታት የዚችን አለም ጣዕም ናቁ ፤ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ፤ ስለመንግስተ ሠማያት መራራ ሞትን ታገሡ፡፡ " [ ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ] የእናታችን የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ፤ የወንጌላዊውም የቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ ፣ ቃል ኪዳንና በረከት ከሁላችን ጋር ጸንቶ ይኑር፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለፅጌ ፆም (ዘመነ - ፅጌ) በሠላም አደረሰን/ አደረሳችሁ። ፆመ ፅጌ ☞ ፆመ ፅጌ በየአመቱ መስከረም ፳፮ ተጀምሮ ህዳር ፮ የሚጠናቀቅ ፆም ነው። ☞ ይህ ፆም የሚፆመውም ለ፵ቀናት ወይም ለ፩ወር ከ፲ቀን ነው። ☞ ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል ነው። ☞ ፅጌ ፆም የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል። ☞ ይህች ፆም የሚፆምባት ምክንያት እመቤታችን ስደቷን በማሰብ ነው።እመቤታች ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በመሳብ ነው። ☞ ይህች ፆም ምንም እንኳን ከ፯ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እንድፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች። ከመስከረም ፳፮ (26) ጀምሮ እስከ ሕዳር ፮ (6) ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም ማሕሌተ ጽጌ እና ጾመ ፅጌ (የፈቃድ ፆም ) ☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን፣ ☞ የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከ ሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ፣ ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን። ♥️♥️እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!! ♥️የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን !!! ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲዳረስ
Показать все...
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ ******** ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኅንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ቦታው በዓታ ለማርያም በተባለው ቦታ 1934 ዓ.ም ተወለዱ። ፊደልና ንባብና የቃል ትምሕርት በመማር ለግብረ ዲቁና የሚያበቃቸውን ትምሕርት ከየኔታ ክንፈ ገብርኤል በመማር ማዕረገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል። ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ዜማ ከየኔታ ተክለ ማርቆስ ማየ አንበሳ ገዳም ተንቤን፤ ቅኔ ከየኔታ ንጉሤ መነዌ ገዳም ተንቤን እንዲሁም ቅኔን ከየኔታ አክሊሉ ደበጋ ጎንደር ትርጓሜ መጻሕፍት፣ እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ማርያም ቀረፃ ማርያም ከምትባል ገዳም ፤ ቅኔና ትርጓሜ መጽሐፍት እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ልሣነ ወርቅ ጎጃም ፤ ቅኔ ከየኔታ ዲበኩሉ ጎጃም በሚገባ ከተማሩ በኋላ ለመምህርነት በቅተዋል፡፡ በተጨማሪም መዝገብ ቅዳን ከየኔታ ልዑል ቦረራ ሚካኤል ተምረዋል፡፡በወቅቱ የጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ የቅስናና የቁምስና ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡ብፁዕነታቸው በሊቀ ጵጵስና በአክሱም፣በምሥራቅ ሐረርጌና በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም አገልግለዋል። የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። ጸሎተኛው፣ ደጉ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት። የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን  የምናሳውቅ ይሆናል።   የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Показать все...
sticker.webp0.16 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
አቤቱ ያለፈውን አትቁጠርብን እንኳን ከ 2015 ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ ወደ 2016 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ! ❝ጌታችን ሆይ ስለ አንተ ቸርነት ምን እንበል ! ? ❝እንደ ክፉዎች በታሰበብን ሳይሆን እንደ አንተ በተፈቀደልን ስንቱን አለፍነው❞❝እንደ አመጸኞች በተሴረብን ሳይሆን እንደ አንተ ጥበቃ ስንቱን ተሻገርነው❞  አቤቱ ተመስገን ። አቤቱ ጌታችን ሆይ እኛ ሆዳሞች ንን ፍቅርህ አይገባንም።  ከምህረትህ ጀርባ አምጸናል ፣ ከፍቅርህ ጀርባ ክፋት ተማዘናል  አቤቱ ሆይ  ያለፈውን አትይብን ። ያለፈውን ዘመን ለይቅርታ ብትሰጠን እኛ አመጽንበት ፣ ለፍቅር ብትሰጠን እኛ ተከፋፈልንበት ፣ ለህብረት ብትሰጠን  እኛ ፈረስንበት ። የይቅርታ አምላክ ሆይ ይቅር በለን ። የፍቅር ጌታ ሆይ ልባችንን ፍቅር ዘይት አለስልሰው ። የሱታፌ አምላክ ህብረታችንን መልሰው ። አቤቱ ሆይ አቤቱ ያለፈውን አትቁጠርብን መጪውን ባርክልን ። በዚህም አዲስ ዘመን አንተን እሺ የሚል ልብ ፣ የሚበልጠውን ለአንተ የሚያሳይ እምነት ፣ ለቃል የሚታዘዝ ክርስትና ፣ አባቶችን የሚከብር ልጅነት ፣ ታላቆችን የሚሰማ ታናሽነት ፣ ሀገርን የሚወድ ወጣትነት እንድታድለን እንመጸንኸለን ። በእውነት ጌታዬ ሆይ አቤቱ ያለፈውን አትቁጠርብን  መጪውንም ባርክልን ።  ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ መስከረም 1 ቀን 2016 የምሕረት ዓመት
Показать все...
ዕንቁጣጣሽ በወርኃ መስከረም ስለመከበሩ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕይታ፡-   የዕንቁጣጣሽ በዓል በመስከረም ወር ላይ ለምን እንደሚከበር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ያብራራሉ፡፡ ብርሃናት (ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት) የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜን ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ይጀምራሉ፤ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ እንዳለ፤ (መጽሐፈ ሄኖክ ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድርገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ኩፋሌ ፯፥፩)   ዘመን ሲለወጥ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያልፋል፤ በዚህ መልኩም ከኬጂ እስከ ዩኒቨርስቲ ደረጃ ይደረሳል፡፡ ገበሬውም የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋ ወራት የልፋቱን ዋጋ የምድርን በረከት የሚያገኝበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሦ ከፀሐይ ወራት ይደርሳል፤ ክርስቲያንም ዓመት ሲለውጥ በኃጢአት የነበረ ሰው ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣  ከክፋት ወደ በጎነት፣ ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ ከመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ እስከ ዐሥረኛው ማዕረግ የሚደረስብትን እያቀደ መኖር ይገባዋል፡፡ ምን ጊዜም ዘመን በተለወጠ ጊዜ የዓመታት እና የወራት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የክርስቲኖችም የሕይወት ለውጥ የሚገባ መሆኑን ከተፈጥሮ ክስተት መረዳት ይቻላል፡፡ መጪውን አዲሱ ዓመት ዘመነ ዮሐንስን የቤተ ክርስቲያን ከፍታ የምናይበት፣ በክርስትናችን  የሕይወት ለውጥ የሚያድግበት፣ ሰላም፣ አንድነት፣  የምናይበት እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን፤ አሜን፡፡   ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Показать все...
✞ እግዚአብሔር ፈዋሽ ✞ እግዚአብሔር ፈዋሽ የስምህ ትርጉም ፈታሄ ማህጸን ሩፋኤል ግሩም ለአንተ አለኝ ምስጋና የመንገዴ መሪ ነህና(፪) ይውረድ ከሰማይ የምህረት ጠል ሩፋኤል አሳደገኝ ልበል ከልጅነቴ ያኖርከኝ በክብር ሩፋኤል ለአንተ ልዘምር(፪) አዝ= = = = = የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘህ ከንፋስ ይልቅ ትፈጥናለህ መራሄ ፍኖት ናልኝ ወደኔ ጦቢት ነኝ ይብራልኝ አይኔ(፪) አዝ= = = = = ተሾምክ በኃይላት አለቃ ሆነህ ሰሚነህ ሩፋኤል ላለህ ሲወልዱ እናቶች እንዳይጨንቃቸው ማህጸን ከፋች ሆንካቸው(፪) አዝ= = = = = እኔ ያንተ ልጅ ላንተ ልዘምር ስላየሁ ያንተን ልዩ ፍቅር በደረስኩበት የማትለየኝ ስላንተ ምለው ብዙ አለኝ ስላንተ ገና ብዙ አለኝ መዝሙር በዘማሪ ዲያቆን ሀብታሙ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Показать все...
እግዚአብሔር ፈዋሽ .mp34.34 MB
✞ ምን ብትወደኝ ነው ✞ ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ/2/ ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/ አዝ= = = = = አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ እቀኛለሁ ስለአዳኜ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/ አዝ= = = = = ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/ አዝ= = = = = ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት አዝማናቱ ስራህን እያሳየ ልሁንልህ ከዓለም የተለየ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/ አዝ= = = = = ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/        መዝሙር   ዲያቆን አቤል መክብብ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Показать все...
ምን ብትወደኝ ነው .mp37.98 MB