cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ATC NEWS

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Больше
Рекламные посты
116 411
Подписчики
Нет данных24 часа
+767 дней
+35830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡ ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ስምንት የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ ክህሎት እና ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ተይዘዋል፡፡ ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫም ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራው ሂደት መረጋገጡንም ከየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛ እና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች ገንዘብ በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች ሶስት ሰዎችን ፖሊስ አግኝቷል፡፡ መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡ ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ከባህልም ከስነ ምግባርም ያፈነገጡ የፈጠራ ወሬዎችን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በሚመለከትበት ወቅት ገፆቹን ከመከተል እንዲቆጠብ እና የሌሎች መረጃዎችንም ትክክለኛነት በማረጋገጥ ራሱን ከአላስፈላጊ መደናገር እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Показать все...
ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
Показать все...
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘና ተሰጠ፡፡ የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ15 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ ምዘናው በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች በ36 የትምህርት አይነቶች የተሰጠ ሲሆን፤ በምዘና ሒደቱ ከአንድ ሺህ በላይ ፈታኞች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና አስተባባሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡ የመምህራኑን ፍቃደኝነት መሰረት በማድረግ የተሰጠው የጽሁፍ ምዘናው፤ የመምህራንን የሙያ ብቃት በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ የጽሁፍ ምዘናው ከ80 በመቶ የሚያዝና ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የማህደረ ተግባር ምዘናን መሰረት እንደሚያደርግ ምዘናውን በጋራ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገልፀዋል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Показать все...
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች Entrance Hubን ስጠቀሙ 👌የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ1972-2015ዓ/ም 👌የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1996-2010ዓ/ም 📒 አጫጭር Note ከ9-12ኛ 🔹በየቀኑ መጠናከሪያ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለ2016 Online ፈተና  ልምምድ እንድታደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ መተግበሪያውን ለማውረድ ይህን ይጫኑ👇https://bitly.yt/olan7 🔹ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ @EntranceHubEthiopia
Показать все...
#አሳዛኝ_ዜና ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል። ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው። በጣም የቅርብ ቤተሰቤና ዘመዴ የሆነው እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር። የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Показать все...
የግል ዋይፋያችን #WiFi እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን? ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ላሰብነዉ አገልግሎት እየሰጠ ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ትኩረት ስንሰጥ አይስተዋልም፡፡ ይህም በአንድ በኩል ከቸልተኝነት ወይም የሚያስከትለውን ጉዳት በውል ካለመገንዘብ ሲሆን፤ በሌላም በኩል የግል ዋይፋያችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል እውቀትና ግንዛቤ በአግባቡ ካለመያዝም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አኳያ ለዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡፡ 1. ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ “default username” በመቀየር ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ 2. የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /service set identifier - SSID/ እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡ 3. አውታረ-መረባችንን መመስጠር የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡ 4. ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging) ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) ስናደርግ የዋይፋይ ኔትወርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡ 5. የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ ለመጠቀም የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡ 6. የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ስጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ 7. የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት የራውተራችንን ፋየርዎል /firewall/ ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር ጥቃቶች እራሳችንን መከላከል ያስችለናል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Показать все...
ATC NEWS

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች Entrance Hubን ስጠቀሙ 👌የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ1972-2015ዓ/ም 👌የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1996-2010ዓ/ም 📒 አጫጭር Note ከ9-12ኛ 🔹በየቀኑ መጠናከሪያ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለ2016 Online ፈተና  ልምምድ እንድታደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ መተግበሪያውን ለማውረድ ይህን ይጫኑ👇https://bitly.yt/olan7 🔹ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ @EntranceHubEthiopia
Показать все...
FULLY FUNDED - Fellowship Program in the USA 2025-26 Host Country: United States Host Institute: Harvard Radcliffe Institute Benefits: Fellows receive a stipend of $78,000 plus an additional $5,000 to cover project expenses. Fellows may also be eligible to receive relocation, housing, and childcare funds to aid them in making a smooth transition to Radcliffe. Health care support is made available as needed. Application Deadline: Humanities, Social Sciences, Creative Arts: September 12, 2024 Science, Engineering, Mathematics: October 3, 2023 For more information, Join @scholarshipsFESl
Показать все...