cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Voa Amharic

መረጃዎችን ለመላክ @Voa_News_Amharic_bot

Больше
Рекламные посты
17 578
Подписчики
+1224 часа
+1117 дней
+50430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ስጋት የገባቸው ዴሞክራቶች ጆ ባይደንን ለመተካት እየመከሩ ነው ተባለ!! በሀሙሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ክርክር ጆ ባይደን ባሳዩት አቋም የተጨነቁ ዴሞክራቶች ባይደንን ከእጩነት ለማንሳት እየመከሩ መሆኑ ተሰምቷል። ሁለቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን ባደረጉት ተጠባቂ ክርክር የስደተኞች ጉዳይ ፣ ኢኮኖሚ ፣ የዩክሬን እና ጋዛ ጦርነት እንዲሁም በእጩዎቹ የመምራት አቅም ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር። በክርክሩ ላይ ጉልበት ባነሰው በለሆሳስ ድምጽ ንግግር ሲያደርጉ የነበሩት ጆ ባይደን በትራምፕ ብልጫ እንደተወሰደባቸው ተነግሯል፡፡ ከክርክሩ በኋላ ሲኤንኤን ያሰባሰበው የህዝብ ድምጽ እንደሚያመላክተው 67 በመቶ የተመዘገቡ መራጮች ትራምፕ በክርክሩ እንዳሸነፉ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን ክርክሩ የ81 አመቱ ፕሬዝዳንት የሚገኙበት ሁኔታ ሀገሪቷን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በግልጽ ያሳየ ምሽት ብለውታል፡፡ የሪፐብሊክን ፓርቲ አባል የሆኑት ጆንሰን እኔ የዴሞክራት ፓርቲ አባል ብሆን ኖሮ ባይደን በሌለ እጩ እንዲተኩ ለማድረግ አላቅማማም ነበር ነው ያሉት፡፡ በአሁኑ ሰአት ዴሞክራቶች ባይደንን መተካት በሚኖረው ጠቀሜታ እና ኪሳራ ላይ እየመከሩ ሲሆን የፓርቲው ደጋፊዎች ወጣት እጩ እንዲያቀርቡ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው ሊደረግ ከአራት ወራት ያነሱ ግዚያት በቀሩ ጊዜ አዲስ እጩ አስተዋውቆ እና በአዲስ መልክ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጎ የማሸነፍ አድሎ ጠባብ ነው ያሉ የፓርቲው አባላት ጆ ባይደን እንዲቀጥሉ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢትዮ-ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ. ማ. ለፋብሪካው ተከላ ከGenoyed Machine Ltd. ኩባንያ ጋር ኮንትራት ተፈራረመ። "ቀዩን ዝሆን መመለስ" በሚል መሪ ቃል የቀድሞውን የወንጂ ስኳር ትዝታ እውን ለማድረግ በ24 ሰዎች የተጠነሰሰው የስኳር ፋብሪካን የማቋቋም ህልም አሁን ወደ መሬት ወርዶ እውን ሊሆን ተቃርቧል። ኢትዮ-ስኳር አክሲዮን ማህበር ከ5000 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን አሁን ላይ የፋብሪካው መሣሪያዎች እየተመረቱ እና የተከላ ቦታው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመት ይህ ፋብሪካ እውን ይሆናል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ! መቻል ስፖርት ክለብ "መቻል ለኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።ምስረታውን አስመልክቶ ነገ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ ይካሄዳል። ሩጫው የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልል ሲሆን፡- .  ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ . ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ . ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ . ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት .ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ . ከሀራምቤ መብራት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚገኙ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ አንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
<< ከፋኖ ሃይሎች ጋር ለመደራደር አንድ አለመሆናቸው አስቸግሮኛል >> - መንግስት ከባህርዳሩ << የሰላም ኮንፈረንስ >> በኋላ የተቋቋመው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ይፋዊ የድርድር ጥሪ ለፋኖ ሃይሎች አቀረበ። < ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም > በሚል ለሁለት ቀናት ተካሂዷል ከተባለው < የሰላም ኮንፈረንስ > በኋላ የተቋቋመውና 15 አባላት ያሉት የክልሉ የሰላም ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የመጀመሪያ መግለጫውን በአዲስ አበባ ከተማ ሰጥቷል። በመግለጫው ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ደረጃ ፣ በየትኛውም ቦታ፣በየትኛውም አደራዳሪ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች [ የመንግስት ሃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ] ቢያንስ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ መወሰኑን አመልክቷል።የመንግስት ጸጥታ ሃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች ጦርነት በንግግር በውይይት በድርድር ይፈታ የሚል ድምዳሜ እንደተደረሰ የገለፀው የካውንስሉ መግለጫ ድርድሩ በክልል እንዲሁም በሀገር ደረጃ አልያም በየትኛውም መንገድ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁሟል። መንግስት ይህ አሸናፊና ተሸናፊ የሌለው አውዳሚ የእርስ በእርስ ጦርነት በንግግርና በድርድር ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኑን ነግሮኛል ያለው ምክር ቤቱ << ነገር ግን ፋኖ አደረጃጀቱና መሪው ብዙ ነው፤ ለመደራደር አንድ መሆን አለባቸው ብሏል ሲል አትቷል።የድርድሩ ደረጃ ፤ጊዜና ቦታ ተደራዳሪዎች ተለይተው ሁለቱን ወገኖች እያነጋገረ ለንግግርና ለድርድር ጥረት የሚያደርግ 15 አባላት ያሉት አመቻች የሰላም ካውንስል መመረጡን በመጥቀስ ካውንስሉ የተቋቋመበትን አመከንዮ አስገንዝቧል።በርካታ ሃላፊነትና ተግባራት አሉኝ የሚለው ካውንስሉ በዋናነት ግን ተከታዮቹን ጉዳዮች ዘርዝሯል። ካውንስሉ በሁለቱም ወገኖች እስካልተመረጠ ድረስ አመቻች እንጂ አደራዳሪ እንዳልሆነ ያስታወሰው የምክር ቤቱ መግለጫ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይላት እኩል ድርድርና ንግግር እንዲቀበሉ፣ አደራዳሪና ተደራዳሪ እንዲመርጡ፣ ቦታና ጊዜ እንዲወስኑ፣ ተኩስ አቁመው እንዲገቡ የማግባባትና የማመቻቸት ስራ እሰራለሁ ብሏል።በተከታይነት ካውንስሉ እከናውነዋለሁ ያለው ተግባር ለየትኛውም ወገን ማዳላት ሳያሳይ፣ በየትኛውም ወገን ጫና ሳይደረግበት፣ ሁለቱም ወገኖች በቅንነት እንዲቀራረቡና እንዲደራደሩ የአመቻችነት ሚናዬን እወጣለሁ ብሏል።አክሎም ከየትኛውም ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማያስተናግድ የጉባዔውን መደምደሚያ መሠረት አድርጎ እንደሚሰራ አስታውቋል። መግለጫው በመቋጫው የሰላም ጥሪውን ለተለያዩ አካላት አስተላልፏል። ከእነርሱ ውስጥ የፌዴራልና የአማራ ክልል መንግስታት፣ የፋኖ ሃይሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይገኙበታል።በመግለጫው የተገኘችው አሻም ይህ የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ከመንግስትና ከ1ዐ በላይ የፋኖ አመራሮች ጋር መወያየቱን ሲገልጽ አድምጣለች።ይሁንና ከየትኛኞቹ የፋኖ አመራሮች ጋር እንደተነጋገረ በይፋ የገለፀው ነገር የለም። ይህ መግለጫ ከመውጣቱ አስቀድሞ የአማራ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድርና የወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ከካውንስሉ መግለጫ ጋር ተቀራራቢነት ያለው መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።ለነዚህ 15 የምክር ቤት አባላት ዋስትና የሰጣቸው/የሚሰጣቸው አካልን በተመለከተ ከአሻም በኩል ጥያቄ የቀረበለት ምክር ቤቱ በህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እያቸው ተሻለ ለአማራ ክልል ህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጠ መሆኑን በመጥቀስ ማንም አካል ዋስትና እንዳልሰጣቸው በማስገንዘብ ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኤፍ ኤንደ ቲ (F & T) ኬብል ማኑፋክቸሪንግ  የተባለ የቻይና ካኩባንያ  በሃገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ገመዶችን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ። የድርጅቱ ባለቤት  ሚር ፎ እና ሚር ፍራንክ  እደገለፁት ይህ አምራች ካምፓኒ የሚገኘዉ  በሰበታ በተለምዶ ዲማ እየተባለ በሚጠራዉ  አከባቢ ነዉ ። ወደሃገር ዉስጥ ከገባ አንድ አመት የሞላዉ ሲሆን፤ የጥራት ማረጋገጫ ወስዶ የኤሌክትሪክ ፓዎር  ገመድ ወይንም ኬብል በአሁን ሰዓት  በማምረት ላይ ይገኛል ብለዉናል ፡፡ ኤፍ ኤንደ ቲ የተሰኘዉ ድርጅት በ5 ሚሊዮን ዶላር  ወደ ገበያዉ መግባቱንም ባዘጋጁት ሴሚናር ላይ  ነግረዉናል ፡፡ ድርጀቱ  ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ እንደ ገለፀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ያለ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ጥራቱ የተረጋገጠ የኤለክትሪክ ኬብሎች ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑ በዚህ ዘርፍ ላይ በትኛዉም ሃገርና ቦታ ላይ የሚሰሙና የሚታዩ የኤሌክትሪክ ኬብል ጥራት ችግር ለመፍታት አቅደን ነዉ ወደ ገበያዉ ለመቀላቀል የወሰነዉ ብለዋል ፡፡ ከኤሌክትሪክ ኬብል በተጨማሪ ከኤሌክትሪክ ጋር የሚገናኙ ሌሎች ምርቶችን እያመረተ ለገበያው የማቅረብ ፍላጎት አለው ነው የተባለው። በተጨማሪም ይህ ካንፓኒ በገበያዉ እንዳለዉ የኮፐር መጠን በወር 3 መቶ ቶን ያህል  ኮፐር የማምረት አቅም አለዉ ብለዉናል ። በመጨረሻም ይህ ኤፍ ኤንደ ቲ ኬብል ማኑፋክቸሪንግ በቻይና ውስጥ የታወቀ እና ባለቤቶቹ ከዚህ ቀደም በቻይና ዉስጥ ለ 15 ዓመት በዘርፉ ላይ መስራታቸዉን ሰምተናል፡፡ https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ። ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et/remedial/result ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት። ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ። ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 984 ኢትዮጵያውያን በትናንትናው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። በዕለቱ የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ 20ዎቹ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሆኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል። ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ51 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት መመለስ መቻሉ ተገልጿል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በኦክላሆማ ግዛት በህዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት ታዘዘ የአሜሪካዋ የኦክላሆማ ግዛት ከፍተኛ የትምህርት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች ሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው ውስጥ በአስቸኳይ እንዲያካትቱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ለትምህርት ቤቶች የተላለፈው መመሪያ አስገዳጅነት ያለውና “አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን” የሚጠይቅ ደንብ ያካተተ ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል። በመመሪያው መሰረት በሁሉም የግዛቷ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ እና ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ለሆኑ ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት እኩል መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይሰጣል ነው የተባለው። ይሁን እንጅ ይህ አዲሱ መመሪያ ከሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ከሚሉ ቡድኖች ትችት ቀርቦበታል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ወመዘክር ሰነዶችን በሕገወጥ መንገድ የሚያስወግዱ ተቋማትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ አሳወቀ! አስፈላጊ ሰነዶችን በሕገወጥ መንገድ በራሳቸው አልያም በጨረታ የሚያስወግዱ ተቋማትን በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስታወቀ፡፡የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ይኩኖአምላክ መዝገቡ ተቋሙ በትናንትናው እለት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትንና የሙገር ሲሚንቶ ሰነዶችን በሕጋዊ መንገድ ማስወገዱን ገልጸዋል፡፡ ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የተቋማት የተለያዩ ሰነዶችን ለይቶ የሚያስወግድ ቢሆንም ተቋማት ሕገወጥ በሆነ መልኩ ሰነዶችን በእራሳቸው አሊያም በጨረታ በማቅረብ እያስወገዶ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ ተቋሙ እነዚህ ተቋማትን የማስተማር ሥራ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ ችግሩን ለማስተካከል ፍቃደኛ ያልሆኑ ተቋማት በሕግ አግባብ እንደሚጠየቁ ማመላከታቸውን ኢፕድ ዘግቧል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቆጵሮስ ኒኮሲያ ከሚገኘው የህክምና ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው። ዋና ዳይሬክተሩ ለሽልማቱ አድናቆታቸውን ገልጸው "የጤና ባለሙያዎች በቅንነት የሚያገለግሉ ከሆነ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ ከማምጣት የሚያግዳቸው ነገር የለም" ብለዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.