cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

Рекламные посты
483
Подписчики
Нет данных24 часа
+77 дней
+730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ድምፅ በዝቶናል ብዙ መገለጥ አለ፣ ጠቢብ በርክቷል ዕውቀት ለኹሉ ታደለ። ኹሉ መካሪ ኹሉ አስተካካይ፣ ግንድ ይዞ የሚዞር ጒድፍ ገላጋይ። ከፍቅር ያልኾነ ማቅናት ያልገራው፣ ግብ ለማስቈጠር ነው የሚለፋው። አንተ ግን ከፍቅር እውነት ተናግረኽ፣ የጠፋውን ነፍስ ትመልሳለኽ። አንተ ተናገር፤ ዝም ይበል ኹሉ! ጌታ ተናገር፤ ዝም ይበል ኹሉ! ልብ ተይዞ በዚኽ ዓለም ከንቱ፣ ሥጋ በዛብን ባዶ ጩኸቱ። ምን ፊደል ቢያምር ቃል ከጥሩ ቃል ቢሳካ፣ በምድር ውሃ ነፍስ ፈጽማ አትረካ። ቀሚስ ቢረዝም ጸሎት ቢያስገርም፣ የጠቢባን ቃል ነፍስ አያክምም። ሕይወት የሚሰጥ ሕይወት የኾነ፣ መንፈስ የሚሰርቅ ቃልኽ ብቻ ነው። አንተ ተናገር፤ ዝም ይበል ኹሉ! ጌታ ተናገር፤ ዝም ይበል ኹሉ! https://youtu.be/AUGfLCtoq6s?si=YuRIDazlxrig3YT2
Показать все...
ዝም ይበል ሁሉ Zim Yibel

ዝም ይበል ሁሉ Zim Yibel: Track 03 of the live recorded gospel album “Silante”.

👍 1
THE HOLY SPIRIT DOES NOT BELONG TO YOU. ARE YOU CHARISMATIC? He is bigger than your signs and wonders events. Are you Reformed? He will not be limited by your theology. The Lord Jesus said of the Holy Spirit, “He blows where he will. R.T. Kendall
Показать все...
3
የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ወደ ኤፌሶን ሰዎች ለክርስቲያኖች ጥልቅና መሠረታዊ እውነቶችን የያዘ መጽሐፍ ነው። ይህን መጽሐፍ በግልም ኾነ በጋራ ማጥናት እንዲያመች አድርገን አዘጋጅተነዋል። መጽሐፉን የምትፈልጒ ከዛሬ ጀምሮ በAmazon ላይ ይገኛል። https://a.co/d/gu9HYu3
Показать все...
የኤፌሶን መጽሐፍ ማጥኛ Ephesians Bible Study - Amharic

4
ጥበብን የሚያገኛት፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤ ርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና። ከቀይ ዕንቊ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም። (ምሳሌ 3፥13-15)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ በቺካጎ የሚገኘው ሙዲ ቤተ ክርስቲያን ታዋቂ መጋቢ የነበረው ሃሪ ኤ. አይረንሳይድ በአንድ ወቅት በሳች ብዛት ወደ ተጨናነቀ ምግብ ቤት ገባ። በዚያም ማንም ያልተቀመጠበት አንድ ወንበር ነበረ፡፡ በወንበሩ አጠገብ የነበረውንም ሰው ወንበሩ በማንም እንዳልተያዘ ለማወቅና ዐብሮት መቀመጥ ይችል እንደሆነ ጠየቀው። ከዚያም ምግቡ ሲመጣለት አይረንሳይድ አንገቱን አቀርቅሮ ጸለየ። ሰውየውም ምነው ችግር አለ እንዴ? ሲል ጠየቀው። ርሱም “አይ እግዚአብሔርን እያመሰገንኹ ነበር” ብሎ መለሰለት። ሰውየውም “ኦ! ከእነዚያ ሰዎች አንዱ ነህ ማለት ነው” አለው። “ምግቤ ከቀረበልኝ ወዲያው ነው የምበላው እንጂ እኔ በፍጹም አላመሰግንም” አለ። መጋቢ አይረንሳይድም እንዲህ ሲል መለሰለት “አዎ፣ አንተ ማለት ልክ እንደ ውሻዬ ነህ፤ ውሻዬም ምግብ ሲቀርብለት ልክ እንዳንተው ነው የሚያደርገው!”
Показать все...
ቃል በበዛ ቍጥር፤ ከንቱነት ይበዛል፤ ይህ ታዲያ ለሰው ምን ይጠቅማል? - መክብብ 6፥11
Показать все...
ስደት፣ መፈናቀል፣ የተሻለ ኑሮና ቦታ ፍለጋ የሚደረግ መኳተን ከዓለማችን ወትሯዊ እንቅስቃሴዎች መካከል ናቸው። ክርስቲያኖችም በዚህ ዓለም ውስጥ ባዳነት የሚሰማቸው መጻተኛና ግዩራን ናቸው። ታዲያ በመንፈሳዊ ስደት ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች እንዴት ይኑሩ? ምን ያድርጉ? ምንን ተስፋ ያድርጉ? ሐዋርያት ለዚህ መልስ አላቸው። ጴጥሮስና ይሁዳ ክርስቲያኖች በመጻተኛነት እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባቸው ጠንካራ የኾኑ ተግባራዊ ምክሮችን በመልእክታቸው ጽፈዋል። በእነዚህን መልእክታት ዳራ ላይ የሚያጠነጥነውን ይህን ዐጭር ቪድዮ እንድትመለከቱ እጋብዛችኋለኹ። https://youtu.be/4_P9nVJ-7V4?si=wqitIXnABZUNqo2I
Показать все...
የ1ጴጥሮስ፣ 2ጴጥሮስ እና ይሁዳ ታሪካዊ ዳራ

የ1ጴጥሮስን፣ 2ጴጥሮስን እና የይሁዳ መልእክታትን በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቪድዮ በዐዲስ መንገድ ይመልከቱ፡፡ ስለ እነዚህ መልእክታት ታሪካዊ ዳራ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያግኙ፡፡ መልእክቶቻቸውንም ዛሬውኑ በሕይወትዎና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ተግባራዊ ያድርጉ፡፡ 1ጴጥሮስ፣ 2ጴጥሮስ እና ይሁዳን በጸሐፊዎቹ እና በቀዳሚ ተደራሲያኑ መነፅር ማንበብ፣ ተቃውሞ ቢገጥመንም እንኳ በኢየሱስ ላይ ያለንን እምነት ሳናላለ አጽንተን እንድንቆም ያበረታታናል፡፡ ሥነ ጽሑፋዊና ታሪካዊ ዐውዶችን በመረዳት መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪኩንና በሕይወታችን ያለውን ተጽዕኖ በተሻለ ለማወቅ በምናደርገው በዚህ ጉዞ ይቀላቀሉን፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዋናው ክፍል ሲኾን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና ኑሮ እንዲኖራችኹ ያግዛችኋል፡፡ ቪድዮዎቻችን በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙና በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኹሉ የሚኾኑ ናቸው፡፡ http://www.thebibleeffect.com FACEBOOK:

https://www.facebook.com/experiencethebibleeffect

INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/thebibleeffect

ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት http://www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ Chapters 0፡00 መግቢያ የመንፈሳዊ መጻተኛነት ስሜት 0፡46 1ጴጥሮስ፡- ተመሳስሎ የመኖርን ግፊት መቋቋም 3:43 2ጴጥሮስ፡- ከሐሰተኛ መምህራን ተጠንቀቁ 4:42 ይሁዳ፡- ለእምነት መጋደል 5:38 የሕይወት ተዛምዶ፡- ቤታችን ከክርስቶስ ጋራ ነው #1ጴጥሮስ #2ጴጥሮስ #ይሁዳ

Фото недоступноПоказать в Telegram
ብዙ ክርስቲያኖች በሰዎች ጕዳይ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍጹም መግቦት መቀበል የሚቸግራቸው ጊዜ አለ፡፡ ቻርለስ ስፐርጀን በዚህ ጕዳይ ላይ የሰጠው አስተያየት ዐይን ከፋች ነው፣ “እግዚአብሔር ከዙፋኑ ውጪ በየትኛውም ቦታ እንዲገኝ ሰዎች ይፈቅዳሉ፡፡ በመሥሪያ ቦታው ሆኖ ከዋክብትን እንዲያበጅና ዓለማትን እንዲያስውብ ይፈቅዱለታል፡፡ በምጽዋት መስጫው ሥፍራ ሆኖ ምጽዋቱን እንዲሰጥና፣ ቸርነቱንና ልግስናውን እንዲያሳይ ይፈቅዱለታል፡፡ ምድርን ደግፎ እንዲያቆማትና ምሰሶዎቿንም እንዲያጸና፣ ወይም የሰማይን መብራቶች እንዲያበራ፣ ወይም ዘወትር የሚናወጡትን የውቅያኖሱን ማዕበሎች እንዲቈጣጠር ይፈቅዱለታል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ፣ ፍጥረታቱ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፡፡ እኛም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና በራሱ ፈቃድ ምክር ሁሉን የማድረግ መብት ያለውን፣ ፍጡራኑን ሳያማክራቸው በራሱ መልካም መስሎ የታየውን የሚያደርገውን እግዚአብሔር ስናውጅ፤ የዚያን ጊዜ በሰዎች ዘንድ እንጠላለን፣ እንወገዛለን፣ እንገፋለን፤ የዚያን ጊዜ ሰዎች ጆሯቸውን ይነፍጕናል፤ ምክንያቱም፣ እነርሱ የሚወዱት እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ያለውን እግዚአብሔር አይደለምና፡፡”
Показать все...
6
Фото недоступноПоказать в Telegram
በጥንት ማኅበረ ሰቦች ዘንድ (አይኹድ፣ ግብጻውያን፣ ግሪካውያን፣ ሮማውያን) ዘንድ የትኛው ነገር ውድነቱና ክቡርነቱ የሚለካው ባስቈጠረው ዕድሜ ብዛት ነው። ለዚህም፣ ምን ያኽል ዓመታት አስቈጠረ? የማን ትውልድ ነው? የመሳሰሉ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ። ያለንበት ዘመን ደግሞ የአንድ ነገር ውድነት፣ ክቡርነትና ምርጥነት የሚለካው ምን ያኽል ዐዲስ ነው? የቅርብ ጊዜ ነው ወይ? በሚል መመዘኛ ነው። C.S. Lewis በአንድ መጽሐፉ እንደተናገረው ግን ለየትኛውም ነገር መለኪያችን ዘላለማዊ አስሚታው መኾን አለበት በማለት "ዘላለማዊ ያልኾነ ነገር ኹሉ ለዘላለም ከንቱ ነው" ይላል። ወዳጆቼ፣ በዚኽ ምድር ላይ አንድም ዘላለማዊ የኾነ ነገር የለም። ዕውቀት ጊዜያዊ ነው፤ ዝናም አላፊ ነው፤ ድሎት ቶሎ ይጠፋል፤ ሀብትም እንደ ጢስ ነው። ዘላለም ዘላቂ ኢየሱስ ብቻ ነው። ርሱን ፈልጒ፣ በርሱም ታርፋላችኹ።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.