cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ ይህ channel ለመልካም ስራ የሚውል በመልካም አላማ የተቀናጀ ነው

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
138
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
የጳውሎስ ምርጫ        ጳውሎስ ጌታን በማገልገል ታማኝ ነበር። ወንጌልን በማገልገል ብዙ መስዋዕትነትን ከፍሏል ሕይወቱንም ሰጥቷል። የዓለም ህዝብ ሁሉ እርሱ ያመነውን ጌታ ያምኑና የዘላለም ሕይወት ይሆንላቸው ዘንድ አጥብቆ ይመኝና ይተጋ ነበር። አንድ ቀን ግን ራሱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገባ። እግሮቹ በእግር ብረት ከግንድ ጋር ታሰሩ፣ እጆቹ ሰንሰለት ጠለቀባቸው።          ጳውሎስ መልካም ለማድረግ ነፃ ፍቃድ የለውም ታስሯል፣ እንደልቡ ለመሆን ምቾት የለውም ታስሯል። በዚህ ምክንያት ተስፋ ሊቆርጥ፣ ሊያጉረመርም፣ ተሸናፊ የሚሆንበት አሉታዊ ስሜት እንዲቆጣጠረው አልፈቀደም። በደረሰበት ችግር ምክንያት እግዚአብሔርን መውቀስ ይችል ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ ግን በሕይወቱ ውስጥ ባሉ መልካም ነገሮች፣ በረከቶች ላይ ማተኮር መረጠ።       ጳውሎስ እጅ እግሩ ቢታሰርም አዕምሮው በተሸናፊነት እንዲታሰር አልፈቀደም። ከአሉታዊ ነገር በላይ የሆነውን ማሰብ ጀመረ። አዎንታዊ ነገርን ማሰብ አሉታዊውን መዋጥ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አሰበ፦       " በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።" (ፊልጵ 4:8-9)          ዛሬም የጳውሎስ ምርጫ አለን። አሉታዊ ነገሮች ሲከቡን ትዳራችሁ ተናውጦ ግጭት ውስጥ ሲገባ፣ በስራችሁ ቦታ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥማችሁ፣ ልጆቻችሁ ላይ ጉዳት ሲደርስ፣ ገንዘብ አጥታችሁ ስትቸገሩ፣ ተስፋ አስቆራጭ ነገር ሲገጥማችሁ ሕይወት ኢ- ፍትሐዊ ናት ልትሉ ትችላላችሁ። በዚህ የተነሳ ስሜታችሁን ላትቆጣጠሩ፣ ችግሩን መለወጥ ላትችሉ፣ ሀዘን ሊሰማዎት፣ ከችግሩ ለመሸሽ ትጥሩ ይሆናል። እንዲህ የምትወስኑት ትኩረታችሁ በጉዳዩ ላይ ሲሆን ነው።          በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ ላይ አተኩሩ፤ ጌታ በሰጣችሁ ነገር ሁሉ ላይ ተደሰቱ። በዚህ ጊዜ የደስታና የሰላም ስሜት ይሆንላችኋል። አዎንታዊ ስሜቶች ወደምትባረኩበትና ወዳምትበረቱበት ድርጊት ይመራችኋል። እግዚአብሔር በሕይወታችሁ ውስጥ መኖሩ ብቻ ሳይሆን ዳይሬክተራችሁም አድርጉት። እንዲመራችሁ እንዲቆጣጠራችሁ ፍቀዱለት። ያረጀውን አመት አሳልፎ አዲስ አመትን እንደሚሰጥ የከበባችሁን የከረመ ችግርና ተግዳሮት አሳልፎ ሰላሙና ደስታውን ይሰጣችኋል።
Показать все...
Add a comment
“በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።” (መዝሙር 37፥3)         ብዙ ሰው በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር ሊያደርግ ይችላል ያደረገበት መነሻ ሃሳብ ግን በእግዚአብሔር ስለታመነ ላይሆን ይችላል። ሰጠ እንዲባል ሲወጣ ሲገባ ይቸራል፣ ባለጠግነቱን በምስኪኖች ጉድለት ላይ ለማሳየት ይለግሳል፣  ሰጥቶ በመቀበል ስሌት መልካም ነገር ሊያደርግ ይችላል። መልካምነት ሽታው የሚያውደው፣ ስጦታው የሚማርከው፣ የህሊና ዕረፍት ያለው እግዚአብሔርን ከመታመን ውስጥ ሲወጣ ነው።         ከእግዚአብሔር በቀር መታመኛ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የጎንዮሽ ጉዳት አሏቸው። በገንዘብ የሚታመን ሰው መልካም ነገር ቢያደርግ መታበይ በሕይወቱ ይገለጣል። በእግዚአብሔር የምንታመነው ከእርሱ በቀር ታማኝ፣ ከእርሱ በቀር ስለኛ የተሻለ የሚያስብልን የሚንከባከበን፣ ከእርሱ በቀር በመልካም የሚያሰማራን ደግሞም የሚቆጣጠረን ስለሌለ ነው።          መልካምነታችሁ ጠልፎ እንዳይጥላችሁ በቅድሚያ በእግዚአብሔር ታመኑ። በሕይወታችን ውስጥ ፍቅር የሰጠናቸው ሰዎች ጥላቻን፣ ያጎረስናቸው የሚተፉብን፣ ያቀፍናቸው የሚገፈትሩን ጊዜ ይኖራል። በዚህ ጊዜ ለእነዚህ ሰዎች መልካም መሆን የለብኝም የሚል መራርነት ውስጥ እንዳንገባ በእግዚአብሔር መታመናችን ከጉዳትና ልባችንን ከጥላቻ ያድነናል።          ብዙ ፊቶች ቢጠቁሩ የእግዚአብሔር ፊት ግን ለኛ ሁሌም ብሩህ ነው። የሰዎች ግንባር ቢታጠፍብን የእግዚአብሔር ገጽ ግን ዛሬም በፈገግታ ነው። የኔ ያልናቸው ሲፀየፉን እግዚአብሔር ብቻ ሊያቅፈን ዝግጁ ነው። እግዚአብሔር ይህን ነው ያደረገልን። እኛ ለከፉብን ሰዎች መልካም መሆን ሲያቅተን የተደረገልንን እናስብ። ራሳችንን መቀበል ሲያቅተን፣ ሰዎችን መቀበል ሲቸግረን፣ ሰዎችም አልቀበል ሲሉን የተቀበለን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።         አንዳንድ ሰዎች ለመውደድ እና መልካም ለማድረግ ይቸገራሉ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ለናንተ እንዴት መልካም እንደነበረ አስቡ አሰላስሉ።         ታዲያ እስከ መቼ መልካም ልሁን ካላችሁ እግዚአብሔር ለናንተ መልካም መሆኑን እስኪያቆም ድረስ!
Показать все...
Add a comment
ትግስት እየተሸነፍክ የምታሸነፍበት ጥበብ ሲሆን ፡ትዕቢት ግን እያሸነፍክ የምተሸነፍበት ውድቀት ነው።
Показать все...
Comments – 1
መጥቶ ያሳርፋችሁ "ታንኳይቱም አሁን በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና በማዕበል ትጨነቅ ነበር። ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ።" (ማቴ 14:24-25)         ጀልባዋን የተነሳው ማዕበል ካናወጣት በላይ የሐዋርያቱ መንቀጥቀጥ፣ መፍራትና መጮህ ይበልጥ አናውጧት ነበር። ጀልባዋ ላይ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ድረስ ተሳፍረዋል እምነት ግን አብሯቸው አልተሳፈረም።        ምሽት ላይ አምስት ሺህ ህዝብ በርሃብ ሆዱ ሲናወጥ ጌታ ኢየሱስ ለአንድ ጎረምሳ ጥሩ ምሳ በማይሆን ሁለት አሳና አምስት እንጀራ አምስት ሺህ ሰዎችን አጥግቦ ሲመግብ ተመልክተዋል ለሊት ላይ ግን ሆዳቸው ሳይሆን ጀልባዋ ስትናወጥ ለህዝቡ ርሃብ ወደብ እንዳበጀለት ለማዕበሉ ወደብ ያበጅለታል ብለው ማመን ረስተው በፍርሃት ተዋጡ።       ኢየሱስ እስኪደርስ ድረስ ችግሮች የማታውን ተዓምር ለሌሊት  ሊያስረሱን፣ እምነታችንን አጥፍተው ፍርሀት ሊጭኑብን፣ አንደበታችን ከመፀለይ ይልቅ ጩኸት ሊያበዛ ይችላል። ኢየሱስ ግን ባለንበት አስጨናቂ ሁኔታ ሲመጣ ችግራችሁን ብቻዬን ሳይሆን ኮሚቴ አዋቅሬ ልፍታላችሁ፣ ፎቶ አንስቼ ፖስት ላርግላችሁ፣ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ላቋቁምላችሁ ሳይል የልባችንን ማዕበል ፀጥ ያደርገዋል። ልባችን ሰላም ሲሆን ዙሪያችን የሚተራመሰውን ማዕበል መድረክ ላድርገው ልረማመድበት ትሉታላችሁ። ጌታም ያስጨነቃችሁን ከእግራችሁ በታች ጥሎ ያስረግጣችኋል።         ሁሌም እግዚአብሔር በህይወታችሁ ይሰራል የሚሰራው ሰው እሚሰራውን ያህል ሳይሆን አምላካዊ ክንዱ የሚሰራውን ያህል ነው። በህይወታችሁ ይሰራል ግን ድንቅን ይሰራል። ለነጴጥሮስ ማዕበሉ አስጨናቂ መከራ ነበር። ጌታ ግን በመከራው ድንቅን ሰራ ባስጨነቀው ማዕበል ላይ አረማምዶ ድንቅን ሰራ። ዛሬ በህይወታችሁ የሚያፏጭ የሚያገሳ ማዕበል፣ የሚያስጨንቅ የሚንቀጠቅጥ መከራ ቢኖር በመከራችሁ ድንቅን አድርጎ የሚያወጣችሁ ጌታ ኢየሱስ አለ። በየትኛውም የሕይወታችሁ ቀጠና ላይ ና በሉት ይመጣል። የችግራችሁን ምንጭ ደፍኖ ያሳርፋችኋል።
Показать все...
አዲስ መዝሙር 😍 @mizan_amann
Показать все...
መድረስ ስንል ወዳቀደልን ወዳለመልንና ፈቃዱ ወዳለበት መድረስ ማለታችን ነው። አምና ብዙ ድንቅና ተዓምራት ይሆናል እንዳለን አድርጓልና አይተነዋል። ዘንድሮም ትልቅ በሆነው ፍቅሩ፣ በልዩ ልዩ መንገድ መድረስ እንድንችል ቃሉን ሰጥቶናል። ዘንድሮ አፍ ለአፍ ምስክርነት በመስጠት፣ በጎዳና ስብከቶች፣ በአደባባይና በመቅደስ ጀማዎች በሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች መድረስ ይሆንልናል። በሚሊዮኖች ጓዳ ደግሞ በቴሌቭዥን መስኮትነት እንደርሳለን። ዘንድሮም ፣ የምንበላው፣ የምንለብሰውና መኖሪያ ሣናጣ ለሺህዎች ባሉበት በእርሱ በእግዚአብሔር አቅም በምግብና መጠለያ እንደርሳለን። ሥራውን ሁሉን አቀፍ በሆነ መልክ እየሠራን ራዕያችንን ወደምንውንበት አቀበት በመውጣት ዓምባው ላይ እንደርሳለን፤ ታላቁን ፕሮጀክታችንን በመከወን ለትውልድ ጥቅም ለጌታችን ደስታ ወደሆነው ከፍታ እንደርሳለን!! የእርሱን ስራ በተሠጠ ልብ ስንሰራ እርሱ አዝመራችንን ከነጣቂ ጠብቆ፣ ከእቅፍ የሚተርፍ ነዶ ያሣቅፈናል። ሌላው ሁሉ በእግረመንገድ የሚደረስበት እሸት ይሆናል። ከኢየሱስ ጋር በተሻለ ከፍታና ፍቅር ወደምንኖርበት የከረመ ወይናዊ ደረጃ መድረስም ይሆንልናል። አሜን!! @marsilchannel ❇️
Показать все...
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6 ) ------------ 10 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። 11 የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ #የእግዚአብሔርን #ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። 12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። 13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። 14-15 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ 16 በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ✅✅ የጌታ ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የቻናሌ ቤተሰቦቼ ደግሞ እንኳን አደረሳችሁ❗ አደረሰን ❗ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። 🔑🔑ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ይህን ነገር ወደ እናንተ ማድረስ እንዳለብኝ በጣም በብረቱ ይፈልጋል። ወደ 2014 ለመግባት ጥቅት ቀናቶች ብቻ ቀርተዋል፤ ታዲያ 2014 ላይ ምን መሆኑ ፈልጋችሁ ይሁን❓❓ በpornography #masturbation Alcohol #መጠጥ እና #የዝሙት ሀጢያት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ክርስቲያን ወጣት ወንድና ሴት ልጆች❓❓ 😭😭ዓመቱን ሙሉ #ዝሙት #pornography #alcohol #masturbation ሀጢያት ውስጥ ስታልፉ እኔ በእናንተ ውስጥ ነበርኩ😭 ይላችኋል መንፈስ ቅዱስ፤ አቤት ይህ ነገር ለመንፈሳዊ ሰው ለአንድ ክርሰቲያን እንዴት ልብ የሚሰብር ነው🙄 መንፈስ ቅዱስን የመሰለ ድንቅ አፅናኝ በውስጣችሁ አስቀምጣችሁ በየቀኑ በየሳምንቱ ሀጢያት ልምምድ ልክ እንደ ምግብ ስሆን በጣም ከባድ ነው በእንደዚህ አይነት ልምምድ ውስጥ ሆናችሁ ምንም የመውጣትና የመለወጥ ሀሳብ በውስጣችሁ ከሌለ😭። አዎ ዝሙት የምትሰሩት ሰዓት መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ አለ ፖርኖግራፊ masturbation እያያችሁትም እያደረጋችሁትም ይሆናል ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ አለ ምክንያቱም ከእኛ ጋር ለዘለዓለም ለመኖር ነው መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድር የመጣው እንጂ ሀጢያት ስንሰራ በፍፁም አይሄድም፤ ሀጢያት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ ወጣት መንፈስ ቅዱስ አለ በውስጣችሁ ግን ዝምብሎ ነው ያለው። 🔑🔑እናንተን ብሎ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ለመኖር ወዶና ፈቅዶ እኔ በእነሱ ውስጥ ሁኜ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምራችኋለሁ ኃይል ሰጣችኃል ብቸኝነት እንዳይሰማቸው የማይከዳ ወዳጅ እሆናችኋለሁ ብሎ ከሰማያዊ ስፈራ የመጣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ አለ እኮ። ወዳጅ ለመሆን ስመጣ እናንተ ሌላ ወዳጅ ያዛችሁ በቃ ይብቃችሁ አሁን 2014 ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ብቻ ዝምድና ፍጠሩ ከሱ ጋር ብቻ እባካችሁ መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑ ሃሌሉያ ለእኔ ክብርና ቦታ እየሰጡ አይደለም በቃ ልሂድ አይልም እርሱ እንደ ሰው አይደለም ስሙ ይባረክ ከሀጢአት ይጠብቃል ይጠብቃል ይጠብቃል ሙሉ ሰው እስከምንሆን ድረስ። ይህ ማለት በቃ ችግር የለም ሀጢያት ውስጥ ኑሩ ማለት አይደለም በፍፁም እንድትወጡ ነው እንጂ በፍቅሩ ተሸነፋቸሁ። 🔑🔑አሁን 2014 ይህ ድንቅ ወዳጃችሁ ጋር በየቀኑ መነጋገር እንዲሆንላችሁ በቃ ይብቃችሁ ያ ሀጢያት ልምምድ ከዚህ በፊት በየቀኑ በየሳምንቱ ከሀጢአት ጋር ከጨለማ ፕላን ጋር ተነጋግራችሁ የሰይጣን እቅድና አላማ ፈፀማችሁኋል አሁን ቦታና ወዳጅ ቀይሩና ለመንፈስ ቅዱስ ስሩ የተፈጠራችሁበት ዓላማ እሱ ነውና። ሃሌሉያ እስከመቼ ትኖራላችሁ ሀጢያት ልምምድ ውስጥ ❓❓ የሀጢያት #ባሪያ ሆናችሁ ❓❓በ2014 ግን ወደ መንፈስ ቅዱስ ቅረቡ ጉልበት አቅም ይሆናል ። ✔✔መንፈስ ቅዱስ ድንቅና የማይጠገብ ነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት ውስጥ ከገባችሁ በቃ ያን ሁሉም ነገር አበቃለት የዚህ ዓለም ጥሩና ወድ የሚባል ነገር እንደ ቆሻሻ ታያላችሁ ምንም ነው ግን ሁልጊዜ አድስና ልዩ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ✅✅ church ውስጥ ሰዎች ሲወድቅ የምናየው እሱ ብቻ አይደለም መንፈስ ቅዱስ እጅግ በጣም ትልቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ነው። ❤መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር አለ እንደሰው የስጋ አካላቴን ይነካል ለእኔ የምጠቅመኝን ነገር ይናገራል ማታ 9:00 ወይም 8:00 ሰዓት ላይ መፀለይ አለብኝ ብዬ ከተኛሁበት በስሜ ጠርቶኝ ሰዓቱ ደርሶዋል ተነስ ይላል ሃሌሉያ ለእኔ መንፈስ ቅዱስ ምናብ አይደለም አካል ነው ከእኔ ጋር አብሮኝ ያለው ከሰማይ የመጣ ያለኝ ብቸኛ ወዳጄ ነው ሃሌሉያ❗ ሃሌሉያ ❗ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት ውስጥ መግባት አለባችሁ ከሀጢአት ልምምድ ወጥታችሁ።
Показать все...
🌼🌻🌼🌹በሚመጣው ዘመን!!🌹🌼🌻🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ✍️መጽሐፍ ስነጋገር “በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።” (ኢሳይያስ 27፥6) ይላል። ክብር ለጌታ ይሁን። ✅ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እኔም ዛሬ ቃሉን መሰረት አድርገ እንደ ልበላችሁ.. ✍️እግዚአብሔር ይባርካችሁ፥ ይጠብቃችሁ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራላችሁ፥ ይራራላችሁም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እናንተ ያንሣ፥ ሰላሙንም ይስጣችሁ። ፍሬያችሁም የምድርን ፊት ይሙላ። ✍️ስታወሩ ተሰሙ። ስትናገሩ ተደመጡ። የሚያያችሁ ሁሉ ይውደዳችሁ። ሞገሳችሁ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ሁሉ ይጨምር። የሚሰማችሁ ሁሉ ይቀበላችሁ። የነካችሁት ይለምልም። የተከተላችሁት ነገር ሁሉ ይብቀል። ✍️እስከ ዛሬ ያጣችሁት ነገር ፈልጎ ያግኛችሁ። ያሰባችሁት ይሳካ። በእግዚአብሔር ክበሩ። በትዳራችሁ ተባረኩ፤ በልጆቻችሁም እረፉ። ዓመቱ የምርኮ ዓመት ይሁንላችሁ ... አሜን። 🌼#መልካም_አዲስ_ዓመት🌼 @mizan_aman @mizan_amann 🌼🌻🌼🌻🌼
Показать все...
#በፀጋ_ድነህ_በህግ_አትኑር! ይህ ቃል በክርስቶስ ድነን የቆምንበትን እውነት የሚያብራራ ሲሆን ብዙ ጊዜ የምንጠቀምበት #ከእግዚአብሔር_ጋር ላለን ግንኙነት እንጂ #ከሰው_ጋር ላለን ግንኙነት አይደለም። 👉 የዳንከው በፀጋ ነው። እንድትኖርም የሚጠበቀው በፀጋ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ላለህ ግንኙነት በፀጋ ብለህ፣ ከሰው ጋር ለሚኖረህ ግንኙነት ህግ ላውጣ አትበል። 👉 ክርስቶስ = ፍቅር = የህግ ፍፃሜ ተብሎ በሮሜ 10:4 እና 13:10 እንደተቀመጠ እይ! 👉 የፀጋ ትዕዛዝ = #ፍቅር ነው!! (..እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ #ትዋደዱ ዘንድ #አዲስ_ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።” ዮሐ 13፥34)፣ “እርስ በርሳችሁ #ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” ዮሐ 13፥35) 👉 ከሰዎች ጋር የሚኖርህን ግንኙነት ከፍቅር ውጭ ባለ ህግ "እንዲህ ከሆነ እንዲህ አደርጋለሁ..." በሚል ህግ ቀድመህ አትጠረው! 👉 ወደፊት ለሚፈጠር ማንኛውም ነገር፣ ከመፈጠሩ አስቀድመህ መፍትሔውን ካስቀመጥክ፣ ከመንፈስ የሆነ እውነተኛ መፍትሄ ጋር ትተላለፋለህ፤ ፍቅርን መኖርን ትቸገራለህ። 👉 ስለዚህ ላልተፈጠረ ነገር መፍትሔ አስቀድመህ አትወስን። ሲደርስ መንፈስ ቅዱስ ራሱ የምትወስነውን ይሰጥሀል። (ማቴ 10፥20) 👉 የብዙ ሰዎች ግንኙነት የሚበላሸው ቀድሞ በሚወጣ ህግ ነው። ቀድመህ ካወጣህ አይቀርም: "ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር_አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ … ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።1ኛ ቆሮ13" ብለህ አውጣ። 👉ይህን የሚያስችል ፀጋ በውጥህ አለ።።
Показать все...
ብዙ ሃያላን ነበሩ በአምላኬ ላይ የተኩራሩ ቅዱሱ ላይ የተገዳደሩ ያ ዝናቸው አምድ ለብሶ ታሪካቸው ተቀልብሶ አለ ጌታ በላያቸው ነግሶ አዝ፦ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (2x) ሃብታም በሃብቱ ይኮራል ሃያል በኃይሉ ይመካል ስልጣን ያለው ጭቁኑን ይንቃል ነገር ግን ቅኑ ፈራጅ ከላይ ተቀምጧል ከዙፋን ላይ ክንደ ብርቱ ጻድቁ ኤልሻዳይ አዝ፦ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (2x) የመከራ ወንዝ ሲሞላ የጐበዝ ወኔ ሲላላ ማነው ጽኑ ከአምላካችን ሌላ የፈረሰ ሕይወት ጠጋኝ ሁሉ ሲክድ ቀሪ ታማኝ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ታማኝ አዝ፦ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (2x) ለዛለው ምርኩዝ ደጋፊ የደከመን አሳራፊ ሁሉን ታጋሽ ፍፁም ልበ ሰፊ የመሸበት አሳዳሪ ለተጠቃ ተቆርቋሪ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ነዋሪ አዝ፦ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (3x)
Показать все...
"አትፍሩ፥ ጸንታችሁ ቁሙ ዛሬ እግዚአብሔር የሚያመጣላችሁን ማዳን ታያላችሁ።"  - ዘፀአት 14:13            እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት እግራቸውን አንስተው ከወጡ በኋላ የማያፈናፍን ችግር ገጠማቸው። የኤርትራ ባህር ከፊታቸው፣ ከግራና ከቀኝ የማይገፉት ተራራ ከኋላ ለ430 አመት በባርነት ያኖራቸው ፈርዖንና ሰራዊቱ እየተከተላቸው ነው። በዚህ ሁኔታ ከጠላት ማምለጥ አይቻልም። አንዳንድ ጊዜ ሕይወታችን መፈናፈኛ የሌለው ችግር፣ የማንወጣበት አጣብቂኝ ቅርቃር ውስጥ ትገባለች። አይናችን በምታየው ጠላትና መከራ፣ ጆሯችን በምትሰማው የጠላት ዛቻና ፉከራ፣ ልባችን በጭንቀትና በተስፋ መቁረጥ ትረበሻለች። ስለዚህ በዚህ ጊዜ ማድረግ የምንችለው ከሁሉ የተሻለው መንፈስ ቅዱስን ብቻ መስማት ነው። ምክንያቱም ሌሎች ጥቆማዎቻቸውን እና ፈሪሃ እግዚአብሔርን የማይከተሉ ምክሮችን ይዘው ይመጣሉ ጌታ ግን “ዝም በሉ ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ እወቁ” ይላል (መዝሙር 46:10)      የእግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ልባችን ሜዳ ላይ በሆነች ሰዓት ሳይሆን ነፍሳችን በተጨነቀች ጊዜ በማዳኑ ይታያል። መከራ እግዚአብሔርን አጉልቶ የሚያሳየን መነጽር ነው። አንዳንዱን መከራ በራሳችን ተስበን እንገባበታለን፣ አንዳንዱ መከራ ደግሞ ወደኛ ይመጣብናል። ሔደንበትም ይሁን መጥቶብን ከገባንበት አንዳንዱ መከራ ውስጥ ለመውጣት ራሳችንን መርዳት፣ ሰዎችም ሊያግዙን አይችሉም። እግዚአብሔር ብቻ ረዳታችን ይሆናል። ዙሪያው ሁሉ ጨለማና ረመጥ ሲሆንብን ሰማይ ብቻ ወለል ብሎ ይታየናል አይዟችሁ አትፍሩ ይለናል። የሰዎች ማፅናኛ ርቆን አንደበታቸው ሲከደን የሚያነሳን ክንዳቸው ሲታጠፍ ባህሩን ለሁለት የሚሰነጥቅ ትራራውን የሚያቀልጠው ጠላታችንን የሚያሰጥመው የእግዚአብሔር ክንድ ይገለጣል።          ዛሬ ከፊታችሁ የሚያገሳውን ዮርዳኖስን ከፍሎ የሚያሻግራችሁ ያሳደዳችሁን ጠላት ከባህር ጋር የሚቀላቅልላችሁ የእግዚአብሔር ማዳን መመልከት ይሁንላችሁ። በጠላታችሁ ፊት ከፍ ከፍ ማለት ይሁንላችሁ። የጠላታችሁ ሟርትና ዛቻ ይገልበጥላችሁ። እግዚአብሔር አይታ ሕይወታችሁ ድና ትቅር!
Показать все...
#ቤተክርስቲያን_ማለት_ምን_ማለት_ነው?{ክፍል፩} 👉ቤተክርስቲያን ስንል በጣም ሰፊ መሰረታዊ ሚስጥሮች አሉት በቀጣይ ጊዜያቶች ታዲያ እናያለን። ➬በእግዚአብሔር አዕምሮ ውስጥ ያለውን የቤተክርስቲያን ሚስጥር ትርጉሙን እሱ እንዲህ ናቸው ብሎ ያለንን እንመለከታለን። እይታችሁ እንደቃሉ እንደ እርሱ ሆኖ ይቀየራል። ከመሰረታዊ ሚስጥሮች ውስጥ ታዲያ ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው ብለን ባነሳነው ርዕስ ውስጥ በዋናነት የምናነሳቸውና እንደ እግዚአብሔር ቃል ልንመልሳቸው የተገቡ ጥያቄዎች አሉ። ❶.የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ትምህርቶች ምንድናቸው ?➬ለምን አላማ ጌታ መሰረታት? ❷.ታሪካዊ ይዘቷ ምን ይመስላል ?➬አሁን ያላት ምልልስ ምንድነው ? ❸.ስለቤተክርስቲያን የተነገሩ ነገሮች ምንድንናቸው?➬እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ ያለው አላማ {Purpose}ምንድነው ? ❹.የምትነጠቀው ቤተክርስቲያን ማናት ?➬ጋለሞታ የሆነችውስ ቤተክርስቲያን ደግሞስ ማናት ? ❺.በምንድነው የምትቃወቀው፣ምልክቶቿ ምንድንናቸው ?➬መገለጫዎቿስ ምንድናቸው ? ❻.እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ብሎ የሚተረጉማት ቤተክርስቲያን የትኛዋ ናት ?➬ምን አይነት ትሆን?➬ምንድነው መገለጧ? በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ  አሳያችኋለሁ ተከተሉኝ....፤ ❼.ምን አይነት ሀይል ተጥቷታል?➬ምንድነው ሀይሏ? ✍️ስልጣኗ የሃይሏ ግልጠት እስከምን ድረስ ነው ?እነዚህንና ሌሎችምን Deep ነገሮችን በውስጡ የያዘ ነው በመግቢያችን ላይ ምን ማለት ነው ብለን በጥያቄ ያነሳው የቤተክርስቲያን ሚስጥር ....ለትምህርቱ በሚሆን መነሻ ቃል እንጀምር ...ወይም ደግሞ ከመሰረታዊ ሃሳቦች እንነሳ...እንግዲህ ስለቤተክርስቲያን ሲነሳ ቤተክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠሩት በአንፆኪያ እንደሆነ እናውቃለን ነገር ግ፤ #ቤተክርስቲያን_የሚለውን_ስያሜ_ለመጀመሪያ_ጊዜ_የወጣው_ከኢየሱስ_አፍ_ነበር። መነሻችን ራሱ የሚሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ያለውን የእሱን ሃሳብ የእሱን ፈቃድ የእሱን እውቀት መሰረት አድርገን ማየት ይገባናል።➬ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በምድር ላይ ነው የመሰረታት?➬ቤተክርስቲያን የሚላት ማን ናት? የሚለውን ማየት በቅድሚያ ይኖርብናል። የእግዚአብሔር ቃል ስለቤተክርስቲያን ምንድነው የሚለው?  ከሚለው መነሳት መልካም ነው። 📚“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።”   — ማቴዎስ 16፥13-20👉በዚህ ክፍል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ብሎ የተናገረበትን ሚስጥር በግልጽ ተቀምጦ እናገኛለን። የቤተክርስቲያን ጥልቅ ነገር ሚስጥር ያለው በዚህ ክፍል ነው። ✍️ሰው የተሰወረበት፣የታወረበትም ሚስጥር እሄው ነው!{በሀዋሪያቶች አይን ግን እንዲያ አልነበረም} 👉ስለዚህ ኢየሱስ መለየት ነበረበት ወይ ብዙ ሰዎች ከከተቱት ጎራ ወይ ከጴጥሮስ መገለጥ አንዱን ማፅናትና መልስ መስጠት ነበረበት! 📚“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።”   — ማቴዎስ 16፥17 👉ሰው ወይም [ የአዳም ልጆች አልገለጡልህም] የሊረዱት አይችሉም ምክንያቱም መፅሐፍ መናገር 📚“ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ።”   — ሉቃስ 10፥22 {#አብ_ወልድ} {#ወልድ_አብ}➬ስለዚህ ግዴታ ስለወልድ መናገር ያለበት፣መግለጥ፣መመስከር ያለበት እግዚአብሔር አብ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ነው! #ስጋና_ደም_ወልድን_መግለጥ_አይችሉም! ምክንያቱም ወልድን ለመግለጥ በእርሱ የህይወት መለኪያ ልክ መሆን አለበት። ኢየሱስ ጴጥሮስን አባቴ ነው የገለጠልህ ያለው ከዚህ አንፃር ነው። ቤተክርስቲያን የምትባለው፣የምትጀምረው፣የምትነሳው ፣የእኛ ዘላለማዊነት የሚጀምረው የእናንተ የእሱ አካልነት የሚጀምረው የእርሱ ራስነት፤ሁሉን ባስገዛበት ስርአትና በሰማያዊ ስፍራ በተባረከችሁበት በረከት የዙፋኑ ህይወት ተካፋይ መሆናችሁ የእሱ ህይወት ተካፋይ መሆናችሁ ከመለኮታዊ ባህሪ ተካፋይ የሆናችሁባቸው የህይወት ስርአቶች የሚነሱት የሚጀምሩት የእናንተ አለመኖር ወደ መኖር መምጣት ነው፤ #ከሰዋዊነት_ከምድራዊነት_ከስጋና_ደም_ከማያውቀው እሱን ወደሚያውቀው መምጣታችን የሚጀምረው ከአዳም ልጅነት ከሰው ልጅነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት የመቀየራችን ሚስጥር የሚነሳበት {Springboard}Foundation መሰረቱ በዚህ እያየን ያለነው መነሻ ቃል 📚ማቴዎስ ወንጌል 16፥13-20 ላይ ነው። #ኢየሱስ_እርሱ_ክርስቶስ_የህያው_የእግዚአብሔር_ልጅ_ነው። [መሲህ] የሚለው ላይ ነው! 📌እዚህ ጋር ነው የጀመረው መሰረቱ ያለው፤የቤተክርስቲያንነታችን ሚስጥር መሰረቱ እሄ ነው፤ .....ይቀጥላል https://www.ttlic.org Join👉 https://t.me/ttlic Apostle Born
Показать все...
ያያል ይሰማል! " ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤ " (ትንቢተ ኢሳይያስ 11:3) እግዚአብሄርን አይሰማም! አያይምም! ለማለት ሞራል የሰጠህ ማነው? እርሱ ሰሚ ደግሞም ተመልካች ነው ለመባል የግድ አንተን ብቻ ነጥሎ ማየትና መስማት መስፈርቱ እንዴት ይሆናል? አንተ እኮ የወደድከውን ታያለህ፣ የፈቀድከውን ትሰማለህ፣ ደስ ያላለህን ትኩረትህን ትነፍገዋለህ፣ ደግሞም አልሰማህም ብለኸው ትሄዳለህ ታድያ አንተ ባለመብት ሆነህ እግዚአብሄርን አስገዳጅ ያደረገህ ማን ይሆን? ሳያይህ ቀርቶ ሳይሰማህ አልፎት እስክትደግመው እየጠበቀህ አይደለም። ይልቅ ተመስገን በል እንዳየህ ስላልፈረደብህ እንደሰማህ ስላልበየነብህ እድለኛ ነህ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ አኗኗሩ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት የነበረበት ነው። እንደ አብዛኞቻችን በቀኝ አውለን ብለን በአቦ ሰጥ እንደምንውለው፣ ሲነጋ ከሰይጣን ጋር ብሉቱዝ ተላልከው የቀን ፕሮግራማቸውን እንደሚቀርፁት፣ እንደ አይሁድ ሳምራዊና ፈሪሳዊ አታሳየኝ ብለው እንደሚውሉት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተቃኘ ኑሮ ነበረው። ጌታችን ህይወትን በሚታየውና በሚሰማው አልወሰናትም ነበር። የሚታየው በነፍሳቸው ተስፋ ያጡ በስጋቸው የተጎሳቆሎ ወገኖች ናቸው። ብሄራዊ አልጠግብ ባይነት ሰፍኗል፣ የሃይማኖት መሪዎች በወንጀል ተጠምቀዋል፣ ቅኝ ገዥዎች ህዝቡን ያዋክባሉ፣ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ጥላቻን ይሰብካሉ፣ በጎዳና የወደቁ ህፃናትና አረጋውያን ቁጥር የላቸውም ...ጌታ ግን ህይወትን በሚታየውና በሚሰማው አልወሰናትም ነበር። ይህ መንፈሳዊ ምሪትን የሚጠይቅ እግዚአብሄርን እያዩና እየሰሙ መጓዝን የሚፈልግ ብቃት ነው። ክፉውን በማየት በቃ ከዚህ በኋላ መልካም አይበቅልም አላለም፤ ክፉን በመስማት የምስራች ተናግሯል። ከዚህ በኋላ ከእጅግ ክፉ ትንሹን ክፉ እየመረጡ መኖር ነው አላለም። ጨለማውን ሳያዳንቅ ብርሃንን ፈነጠቀ። መንፈስ ቅዱስ የሚመራው ሰው የጥበብና የምክር መንፈስ ያደረበት ባለ ራዕይ አርቆ ተመልካች ነው። ህይወትን በሚታየውና በሚሰማው አይገድባትም። እየሆነ ካለው ይልቅ እግዚአብሄር በትውልድ ላይ ያለውን እቅድ እያሰበ ያን ተግባራዊ ለማድረግ ይጥራል። ረጅም ጊዜያችንን ስለ ችግሩ እያወራን ከሆነ የምናሳልፈው የክፉውን ስራ እያደነቅን ነው ማለት ነው። ጊዜያችንን የምንሰዋለት ነገር እርሱ የምንኖርለት ነገር ነው። አብዛኛውን ጊዜ ስለ ችግሮች ስናወራ እንውላለን እንኖራለን። የውሎ ብዜት ኑሮ ይሆናል። ስለዚህ እየኖርን ያለነው ለችግሩ መፍትሄ አይደለም ማለት ነው። ምክንያቱም ሰፊ ጊዜያችንን የያዘው ነገር የምንኖርለት ነገር ነውና። ማውራት መስራት የሚመስላቸው ኮሚቴዎችና ቦርዶች ምነው በገባቸው! እኛ ግን በምናየውና በምንሰማው አንወሰንም። ህይወት ይህች ብቻ ናት ብለን አንፈርዳትም። ያለ መንፈስ ቅዱስ ምሪት ኑሯችን ከተቃኘ አደጋ አለው። እኛ ተመሪዎች ነን እኛ ተገዢዎችም ነን። መንፈስ ቅዱስ ካልመራን ክፉ እየመራን ነው። የህይወታችን ሹፌር መንፈስ ቅዱስ ሊሆን ይገባዋልና መሪውን እንልቀቅለት።
Показать все...
አይዞሽ እግዚአብሔር ያዘጋጃል              አንቺ ከመኖሪያሽ ተነስተሽ ወደ አንድ ከተማ በመኪና ስትጓዢ ለዓይን ያማረሽን ለምላስ የጣመሽን ምግብ ቋጥረሽ ትጓዣለሽ። እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው የሲና ምድረ በዳን ሲያልፉ የቋጠሩት ምሳና እራት አልነበረም። በማያርሱበት በማይዘሩበት በማያጭዱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ጎራ ብለው የሚበሉበት ሬስቶራንት በሌለበት፣ የታሸገ ምግብ የሚገዙበት ሱፐርማርኬት ባልኖረበት ምድረ በዳ ላይ እግዚአብሔር መናና ድርጭት እየመገበ መራቸው። ከመሀላቸው አንዳች የተራበ አልነበረም። እግዚአብሔር መሪ የሆነበት ህይወትና ጉዞ በጉድለት ሳይሆን በበረከትና በጠል የተመላ ነው። ወዳጄ አምላክሽ እስራኤልን በምድረ በዳ የመገበ፣ እውር አሞራን የሚቀልብ፣ ድንጋይ የተጫነውን ትል የማይረሳ፣ ትንሿን ትንኝ ሳይዘነጋ የሚመግባት ጌታ ነው።  አንቺንማ ሞቶልሽ እንዴት ይረሳሻል ርቦሽ እንዴት ይጨክንብሻል በፍፁም!        ምድረ በዳ በሆነ የህይወት ቀጠና ብታልፊ፣ ዘርተሽ የማታጭጂበት ሰርተሽ የማታተርፊበት፣ ቀድተሽ የማትጎነጪበት ሁኔታ ላይ ብትሆኚ እንኳ በሚያስፈልግሽ ሁሉ መለኮታዊ እጁን ይገልጥልሻል።            ምድረ በዳ ነው ብሎ ሰው ሲጨነቅ በምድረ በዳ አንቺን ለመርዳት የማይከለክለው ጌታ የበረከቱን ጠል ያዘንምልሻል። በሲና ምድር እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች ለጉብኝት አልፈዋል፣ ሀገር አቋርጠው ሄደዋል ያቋርጡ እንጂ መና አልበሉም ከአለት ውኃ አልጠጡም የጠጡት በእግዚአብሔር ያመኑት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ሰው በሚራብበት ዘመን ትጠግቢያለሽ፣ ሰው በሚጠማው ዘመን ትረኪያለሽ፣ በሚሞትበት ዘመን በህይወት ትኖሪያለሽ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያዘጋጃል! እናት ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ታበላለች እግዚአብሔር ግን ከሞትም ቀስቅሶ ይመግብሻል። አትጨነቂ እግዚአብሔር ያዘጋጃል።
Показать все...
አትጨነቅ      ዓለም መኖሪያ ብላ ብዙ ነገሮችን ሰብካናለች። መኖሪያ ያለችውን አምነን ለመኖር ብናስብም ለመኖር ቀርቶ ለመዋል እንኳ የማይደላ መሆኑን አውቀናል። ታዲያ መኖሪያችን ማን ነው?      አዕምሮህ በጭንቀት ተወጥሮ፣ በሃሳብ ተፈትሎ መኖሪያ ያልኩት ሁሉ የጉም ዝግን ሆነብኝ፣ የህልም እንጀራ መቁረስ ሆነብኝ ኸረ.... መረረኝ እያልክም ቢሆን ስልክህን ከፍተህ ይሄን ፅሁፍ እያነበብክ ነው። ማንበብህን ቀጥል               ውዷ እህቴ በአጣብቂኝ ህይወት ውስጥ ሆነሽ ይሆናል፤ ዛሬ በሰንጣቃ አለት መሀል ነፍስሽ ቆማ ይሆናል፤ ችግር በአራቱም አቅጣጫ ወጥሮሽ ይሆናል፤ ብቻሽን ምድረበዳ ላይ ተጥለሽ ይሆናል፤ ብትጮሂ የሚሰማ ብትጣሪ የሚደርስልሽ አጥተሽ ይሆናል፤ ኪስሽ ባዶ ሆኖ ተጨንቀሽ ይሆናል፤ በሰው ሀገር በስደት ባይተዋር ሆነሽ ይሆናል፤ በአስጨናቂ ገዢዎች እጅ ወድቀሽ ይሆናል፤ የኑሮ ውድነት፣ የበሽታው ማየል፣ የድርጅትሽ መክሰር፣የወዳጅ ክዳት በቃኝ አስብሎሽ ውሰደኝ እያልሽ ሞትን እየለመንሽ ይሆናል።         እመኑኝ ይህንን ሁሉ አስጨናቂ ጊዜ በተአምር የሚያሳልፍ ተአምር ሰሪ ጌታ አለ።  ለሚያስጨንቃችሁ ነገር መፍትሔው የሚያኖራችሁን ማወቅ ነው፡፡ የሚያኖረን ዘላለም የሚኖር ነው። በዘላለም ክንዶቹ ደግፎ፣ አእምሮን ሁሉ በሚያልፍ ሰላሙ አሳርፎ፣ ሳይዘነጋ አስቦ፣ ቸል ሳይል እንደ ዐይኑ ብሌን ጠብቆ፣ ሳይሰስት ሰጥቶ እና ሳይደክም ተሸክሞ የሚያኖረን እግዚአብሔር ነው፡፡ ለሚታየው ኑሮአችን መሰረቱ የማይታየው እምነታችን ነውና በእግዚአብሔር እንመን፤ በእግዚአብሔርም እንተማመን፡፡ "መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው" ኦሪት ዘዳግም 33 : 27          ትላንትን በእውቀትህ አልኖርክም አውቆልህ ኖርክ እንጂ! ታዲያ ለምን ዛሬን በእውቀትህ ለመኖር ታስባለህ? ትላንት ተጠበህ አልኖርክም ተጠቦልን እንጂ! ታዲያ ዛሬን ለመጠበብ ልብህ ለምን ዳዳ? ትላንት ተጨንቀን አልኖርንም አስቦልን ቀለባችንንም ሰፍሮልን እንጂ! ታዲያ በጭንቀት የሚታለፍ ቀን ሳይኖር ለምን ለመጨነቅ ራስህን አሳልፈህ ሰጠህ? ትላንት ያኖረክ ጌታ ዛሬን ለማኖር ምን ያንሰዋል? እርሱ አንተን ማኖር ሳይሰለቸው አንተ ለመኖር ለምን ትሰለቻለህ ? ምንም ይሁን ምን! ምንም ውስጥ ሁን የትም! መኖሪያህ የዘላለም አምላክ መሆኑን እመን።
Показать все...
የእግዚአብሔር ተስፋ ደረቅ ቼክ አይደለም              ዓለም የእድሜ ማስረዘሚያ መድኃኒት ትቀምም ይሆናል ሰው ግን በዓለም የላብራቶሪ ምርት ሳይሆን በተስፋ እድሜውን ያረዝማል። ተስፋ ነገን የመኖር ጉጉትና አቅም ነው። ተስፋ የሌለው ሰው በራሱ ላይ ህይወትን ሳይሆን ሞትን የሾመና ያነገሰ ስለሆነ ለመኖር አቅምም ፍላጎትም የለውም።  የኑሮ ትልቁ ጉልበት ተስፋ ነው። ተስፋ ካለህ ሸለቆ ወርደህ ተራራ ወጥተህ ካሰብከው ትደርሳለህ           አንድ ሰው ደረቅ ቼክ ሊፅፍልህ ይችላል። ቼኩ ላይ ያለው የገንዘብ መጠን የኔ ነው እያልክ ልብህን ደስ ደስ ሊለው ይችላል። ባንክ ስትሄድ ግን እጅህ ላይ ያለው ቼክ ከገንዘብነት ወደ ባዶ ወረቀትነት ይቀየራል። ሰው እንዲህ ነው ተስፋ እየሰጠህም ሊዋሽህ ይችላል። እግዚአብሔር የሰጠህ ማንኛውም ተስፋ እንደ ቼኩ ደረቅ አይደለም።          ሰው ሞቅ ሲለው ቃል ይገባልህና ተስፋ እንድታደርገው የአዕምሮህን ሆድ ይሞላዋል። አንተም ከዛሬ ነገ ተስፋዬን እውን አደረገው ስትል ያልኩህን ነገር ትቼዋለሁ ብሎ ያስተነፍስሀል። ወዳጄ እግዚአብሔር ሞቅ ብሎት የገባልህ ተስፋ የለም። አፉንም አዳልጦት የተናገረህ ተስፋ የለም። ሁሉንም ተስፋ በእቅድና በእውነት ተናግሮሀል።            እግዚአብሔር ፍቃደኛ ሳይሆንና ሊደግፋችሁ ወደማይችለው ነገር አይዟችሁ እኔ ከናንተ ጋር ነኝ ብሎ አይጠራችሁም። በእውነትም የሚያስመካና የማይክድ አጋር ስለሆነ ክንዴን ተንተራሱት ይላችኋል። ጥንካሬ እንደሌለን ስለሚያውቅ እኔ ኃይላችሁ ነኝ ይለናል። ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ አንስተን በእግዚአብሔር ላይ ካደረግን ከእርሱ ጋር ሁሉ እንደሚቻል ያሳየናል።            እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ሰጥቶን በሌላ ነገር አንጠረጥረውም። ትልቁን ስጦታ ተቀብለን በትንሿ ተስፋ ማጉረምረም የለብንም። ተስፋችሁ ይፈፀማል።
Показать все...
🛐ፊትህን አሳየን ክፍል-1 የእግዚአብሄርን ታላቅነትና አስፈሪ ክብር ማወቅ ለሚፈልግና ሀይሉን ሊረዳ የሚፈቅድ ካለ እግዚአብሄር ለህዝቡ የተገለጠበትን ሁኔታ እንዲያይ እንዲያስፈልግ ለመታሰቢያነት በቃሉ ላይ ሰፍሮአል፡- ዘጸ.19:10-11 “እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፡- ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገም ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ይዘጋጁ።” የእስራኤል ህዝብ በግብጽ ሳለ በሙሴ በኩል ስለ እግዚአብሄር አዳኝነት ሰምቶ ነበር፡፡ በተወሰነለት ቀንም የእግዚአብሄርን ክብር የመመልከት እድል አግኝቶአል፡፡ ያም ህዝቡ በእርሱ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጠነክሩና እርሱን በመፍራት እንዲኖሩ የሚረዳ መገለጥ ሆኖ ነበር፡፡ ዘጸ.19:16-25 “እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው፤ ከተራራውም እግርጌ ቆሙ። እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር። የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት። እግዚአብሔርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራራው ራስ ወረደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።” የእግዚአብሄርን ክብር ያዩ ህዝቦች ቀጣዩ ጉዞአቸው እንዴት ነበር፣ አንዳዩትና እንደሰሙት ወይስ ፈጥኖ የሰራውን ስራ በዘነጋ መንፈስ? የአርባ አመቱ የበረሀ ጉዞአቸው በብዙ ማነከስና እንጉርጉሮ እንደነበር ስንረዳ በተገለጠላቸው አምላክ ፊት እንዴት ባለ ድካም እንደኖሩ፣ እርሱ ግን ቃሉን ሳያዛንፍና ሳያጎድል እንደተገለጠበት አገላለጥ ወዳሰበላቸው ምድር እንዳገባቸው እንመለከታለን፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ስንመላለስ በረከትና ምህረት በሚያመጣ አካሄድ ውስጥ መሆናችን ቀርቶ በፊቱ ሳለን መተላለፍን ከወደድን እስከመርገም በሚያደርስ ጥፋት ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን፣ ለዚህም እስራኤላውያን ምሳሌ ናቸው፡፡ በሲና ተራራ በሚያስፈራ ክብር የመጣው አምላክ ዛሬም አለ ወይም ከዘመን ብዛት ሲቆይ አልተለወጠም፣ ስለኛ ሲልም ራሱን አልቀየረም፡፡ ዘዳ.31:16-18 ” እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፡- እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፥ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፥ እኔንም ይተወኛል፥ ከእነርሱም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ፡፡ በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፥ እተዋቸውማለሁ፥ ፊቴንም እሰውርባቸዋለሁ፥ ለአሕዛብ መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፡- በእውነት እግዚአብሔር በእኛ መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል። ሌሎችን አማልክት ተከትለዋልና ስላደረጉት ክፋት ሁሉ እኔ በዚያ ቀን ፈጽሜ ፊቴን እሰውራለሁ።” እግዚአብሄር ከባሪያው ከሙሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው፤ ሊሰበስበው በፈቀደም ጊዜ ያን እቅዱን (የመጨረሻ የመሰብሰቢያ ሰአቱን) ሳይቀር ነገረው፡፡ ህዝቡን በተመለከተ ግን ከርሱ ሞት በሁዋላ እንደሚተዉት ሙሴ በህይወት ሳለ መስክሮባቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ያን የተናገረው ህዝቡ ሊሄዱ ያለበትን አካሄዳቸውን አስቀድሞ ስላየ እንጂ እርሱ በህይወታቸው የሚፈጠረው ስህተት አልነበረም፤ ያ ክፋታቸውም ፊቱን እንዲሰውርባቸው አድርጎአል፡፡ እግዚአብሄር መቼም ይገለጥ፣ ሲገለጥ ግን ቁጣውን በሚያነሳሳ አካሄድ ውስጥ ሆነን አያግኘን፣ ፍርድ ውስጥም አይክተተን፤ ይልቅ በምህረት ይመልከተን፣ ለጠላት አሰራርም አሳልፎ አይስጠን፣ ጠላታችንን ይዋጋልን እንጂ፡፡ ለታመነው ፊቱ ተገልጦ ጠላትን ይምታለት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ሆኖ መኖር እንዴት ይቻላል፣ እስከ ምን ያህል የጊዜ ርዝመትስ በዚያ ህይወት ውስጥ መቀጠል ይቻላል? ያን እውቀት ባለማስተዋል ምክኒያት ነው እግዚአብሄርን ትቶና ያለማወቅ ውስጥ ታስሮ ወደ ብዙ ጥፋት መወርወር የሚከተለው፡፡ የዚያ ያለማወቃችን ምንጭ የተለያየ ምክንያት ቢኖረውም፣ የፈቃዱንም ሙሉ ምስል ለማየት ቢያዳግተንም ባለማወቃችን ጠንቅ ቁጣውን ወደሚያነሳሳ እንቅስቃሴ ውስጥ ላለመግባት ስንል ቆም ልንል ይገባል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ እውቀት ቢኖረን፣ በአለም ያሉ መንፈሳዊ ጥበቦቹ ቢበሩልን ወደ ፈቃዱ እውቀት ካልደረስን ረጋ ስከን እንበል፤ ብዙ ከማውራት፣ የገመትነውን ከማድረግ፣ ያየነውንም ከመመኘት እንዲሁም እርግጠኛ ባልሆንበት ጉዳይ ዘው ከማለት ሰብሰብ ማለት፣ ያን ማድረግ አይጎዳንም እንዲያውም ያለማወቃችን እንዳያጠፋን ያስጥለናል እንጂ፡፡ እግዚአብሄርን አውቀዋለሁ ብለን ታምነን እንኩዋን ቢሆን እግዚአብሄር የሚቀጥለውን ስራውን አስኪነግረን/እስኪያሳየን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ጸሎት አለ፣ ቃሉን መጠበቅ አለ፡፡ ይቀጥላል ... ምንጭ:- tsionvoice.com Join us 📚@Holy_scriptures📚 📚@Holy_scriptures📚 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
Показать все...
. እሷን ማየት ያስጠላኛል የመልካም ወጣት ምስክርነት 🕑-6:15Min💾-17.6MB @marsilchannel @marsilchannel △Join Us△
Показать все...
ከመሰበር መታጠፍ      "  በጅረት ዳርቻ ያደገ አንድ ትልቅ የሾላ ዛፍ ነበር። ይህ ሾላ ዛፍ በባህሩ ዳር የሚነፍሰውን ነፋስ ለመቶ አመታት ተቋቁሞ ቆይቷል። አንድ ቀን ግን ብርቱ ዓውሎ ንፋስ ተነስቶ የሾላውን ዛፍ አናወጠው ጉልበቱን አቅሙን ነጥቆ ወደ ባህሩ ገንድሶ ጣለው። ባህሩም የሾላውን ግንድ እገላብጦ ዳር ወዳለው የሸንበቆ ስፍራ ወስዶ ጣለው። ዛፉም ከወደቀበት ስፍራ ሆኖ የቆሙትን ረጃጅም ሸንበቆዎች ተመልክቶ ተገረመ። የሾላውም ዛፍ " ብዙ አመታት ዓውሎ ንፋሶችን ተቋቁሜ ኖሪያለሁ ነገር ግን ይሄኛው ለኔ በጣም ብርቱ ነበር" አለ።       ሸምበቆዌቹም " ችግሩ ያንተ ነው" ብለው መለሱለት። ቀጥለውም  "በእነዚህ ሁሉ ዓመታቶች ብርታትህን በነፋሱ ላይ አሳይተሀል። ትንሽ ጎንበስ ለማለት ፈቃደኛ አልነበርክም። እኛ በሌላ በኩል ድክመታችንን እናውቃለን ሊሰብረን ሊያጠፋን የሚመጣውን ንፋስ ጎንበስ ብለን በላያችን እንዲያልፍ እናደርጋለን። ንፋሱ ይበልጥ በበረታ ቁጥር እኛም ራሳችንን የበለጠ ዝቅ እናደርጋለን" አሉት። "          ወዳጆቼ ማጎንበስ የመሸነፍ ምልክት ብቻ ሳይሆን የመኖርና ህይወትን የመቀጠልም ጥበብ ነው። ብዙ ጊዜ ግጭት የሚደርስባቸው ጎንበስ ብለው የሚያልፉትን ተገትረው ለማለፍ ሲሞክሩ ነው። የመጣው ችግር ከሚሰብረን በትህትና ልባችንን ሰበር ብናደርግ ሳንቆስል በሰላም እናልፋለን። በትዕቢታችን ከመሰበር በትህትና መታጠፍ መልካም ነው። " ትህትና ክፋት ከሞላባቸው ዓይኖች የምትከልል ጋሻ ናት።" ከትዕግስት የበለጠ በፈተና የሚያፀና እንደሌለ ሁሉ ከትህትናም የበለጠ መልካም ምግባር የለም። ጌታችን ኢየሱስ ከእኔ ተማሩ ብሎ ከነገረን ሁለት ነገሮች መሐል አንዱ ትህትና ነው።  “ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”( ማቴ 11፥29)         ክርስቶስ ያለ ልክ ከፍ ከፍ የማለቱ ምስጢር ያለ ልክ ዝቅ ዝቅ ማለቱ ነው። ቀና ለማለት ማጎንበስ፣ገንዘብ ለማግኘት ጊዜን ጉልበትን ማጣት፣ ለመሳቅ ማልቀስ፣ ለመጥገብ መራብ መስፈርት ነው።  ልክ እንደዚሁ ሁሉ ለመክበር ዝቅ ማለት ያስፈልጋል። ዝቅ ብለን የተቀበልነውን ፅዋ ነው ቀና ብለን የምንጎነጨው። ያለ ልክ ዝቅ ዝቅ ባልን ቁጥር ያለ ልክ ከፍ ከፍ እንላለን። የትህትናን ዙፋን ለመቆናጠጥ የትዕቢትን ወንበር ሰብሮ መጣል ያስፈልጋል።         አንዳንድ ሰዎችን የምናጣቸው በኩራታችን ምክንያት ነው። መልካም ሰዎችን ከምናጣ የማይጠቅመንን ኩራታችንን ብናጣ ይሻላል።                 
Показать все...
እሺ እንበል! “ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው። ( ማቴዎስ 14፥22 )   እናት እሺ ብሎ የሚታዘዛትን ልጅ ትወዳለች ምክንያቱም የልቧን ያደርስላታል። እግዚአብሔርም ሲልካቸው እሺ የሚሉትን ይወድዳል። እግዚአብሔር ዮናስን የልቤን አድርስልኝ ብሎ ወደ ነነዌ ቢልከው ዮናስ ግን እንደልቡ ሆኖ አልታዘዝ አለ። እግዚአብሔር ወደላከው ሳይሆን ራሱን ወደሚፈልገው አሰማራ። እግዚአብሔር እረኛ ሆኖ ሲያሰማራን ታካችና እምቢተኛ ስንሆን በመንገድ የሚገጥመን ማዕበልና ወጀብ ያንገላታናል አሳ ነባሪው ይውጠናል። የሚከበን የሄድንበት መከራ ነውና ህይወትን መራር ያደርግብናል። ያለ እግዚአብሔር ጉዞ ለመደናበር ብሎም ለመሰናከል ነው። ከእግዚአብሔር ስንርቅ ወደ ጠላት እየቀረብን እንሄዳለን።    ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ወደማዶ ቀድመውት እንዲሻገሩ ጠየቃቸው። ካንተ ጋር ነው የምንሆነው አንሄድም፣ ካንተ መለየት አንፈልግም ቢሉትም ግድ ሂዱ ብሎ ላካቸው። (ማቴ 14፥22) ጌታ በላካቸው መንገድ ሲጓዝ የሚያስጨንቅ ማዕበል አላሳልፍ አላቸው ነፍሳቸውንም አስጨነቀው።         እርሱ ሒዱ በሚለን ጎዳና ስንጓዝ ፈተና መከራ ይገጥመናል ግን ኃላፊነቱን የሚወስደው ጌታችን ነውና የሚያስጨንቀንን ባህር እየረገጠ ይመጣል፣ ችግራችንን እየደፈጠጠ ይመጣል። (ማቴ 14:25) ራሳችንን ለፍቃዳችን ሳይሄን ለፍቃዱ አሳልፈን ሰተናልና ለሚገድለው መከራ አሳልፎ አይሰጠንም። እርሱ እረኛችን ነውና በጎቹን ለአውሬ አያስበላም። (መዝ 23:1)       እግዚአብሔርን አምናችሁ በምትወጡበት መንገዳችሁ ሁሉ የሚገጥማችሁን የጠላት ኃይል ይስበርላችሁ፤ አላሳልፍ ብሎ የሚገዳደራችሁን እንቅፋት በብርቱ ክንዱ ጠርቆ ያርቅላችሁ፤ በሰላም ከወደባችሁ ያድርሳችሁ። አሜን!
Показать все...
#በፀጋ_ድነህ_በህግ_አትኑር! ይህ ቃል በክርስቶስ ድነን የቆምንበትን እውነት የሚያብራራ ሲሆን ብዙ ጊዜ የምንጠቀምበት #ከእግዚአብሔር_ጋር ላለን ግንኙነት እንጂ #ከሰው_ጋር ላለን ግንኙነት አይደለም። 👉 የዳንከው በፀጋ ነው። እንድትኖርም የሚጠበቀው በፀጋ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ላለህ ግንኙነት በፀጋ ብለህ፣ ከሰው ጋር ለሚኖረህ ግንኙነት ህግ ላውጣ አትበል። 👉 ክርስቶስ = ፍቅር = የህግ ፍፃሜ ተብሎ በሮሜ 10:4 እና 13:10 እንደተቀመጠ እይ! 👉 የፀጋ ትዕዛዝ = #ፍቅር ነው!! (..እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ #ትዋደዱ ዘንድ #አዲስ_ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።” ዮሐ 13፥34)፣ “እርስ በርሳችሁ #ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” ዮሐ 13፥35) 👉 ከሰዎች ጋር የሚኖርህን ግንኙነት ከፍቅር ውጭ ባለ ህግ "እንዲህ ከሆነ እንዲህ አደርጋለሁ..." በሚል ህግ ቀድመህ አትጠረው! 👉 ወደፊት ለሚፈጠር ማንኛውም ነገር፣ ከመፈጠሩ አስቀድመህ መፍትሔውን ካስቀመጥክ፣ ከመንፈስ የሆነ እውነተኛ መፍትሄ ጋር ትተላለፋለህ፤ ፍቅርን መኖርን ትቸገራለህ። 👉 ስለዚህ ላልተፈጠረ ነገር መፍትሔ አስቀድመህ አትወስን። ሲደርስ መንፈስ ቅዱስ ራሱ የምትወስነውን ይሰጥሀል። (ማቴ 10፥20) 👉 የብዙ ሰዎች ግንኙነት የሚበላሸው ቀድሞ በሚወጣ ህግ ነው። ቀድመህ ካወጣህ አይቀርም: "ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር_አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ … ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።1ኛ ቆሮ13" ብለህ አውጣ። 👉ይህን የሚያስችል ፀጋ በውጥህ አለ። #Share
Показать все...
አካሄዳችን “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።” (ዘፍጥረት 5፥24)       የእግዚአብሔር እግሮች ይጓዛሉ። እግሮቹ አድነኝ ለሚሉት ፈውስን አዝለው ይፈጥናሉ፣ ማረኝ ለሚሉት ምህረትን አንግበው ይገሰግሳሉ፣ ላዘነው በትካዜ ውስጥ ላለው ማፅናናትን ይዘው ይጓዛሉ፣ ለተራበው እርካታን ይዘው ይሄዳሉ፣ ለተሸበረው ሰላምን አዝለው ይሮጣሉ። እግዚአብሔር ዱካው ፍቅር፣ ምህረት፣ ሰላም ነው። እግሮቹ የጫማ ቁጥርን ሳይሆን የመልካምነት አሻራን ይተዋሉ።         የእግዚአብሔር ተረከዞች የሚነሱት ያጎረሱ እጆችን ለመንከስ ሳይሆን ለመሳም፣ ኃጢአተኞችን ለመቅጣት ሳይሆን ከሸክም ለማሳረፍ፣ የተጨነቁትን ለማረጋጋት፣ ልባቸው የታወከባቸውን በማይናወፅ ሰላሙ ለማሳረፍ ነው።          ወዳጆቼ አዳም ምቹ በሆነችው በገነት ውስጥ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ አቅቶት ወድቋል ሄኖክ ግን ምቹ ባልሆነች ምድር ላይ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ ችሏል። የሁኔታዎች፣ የቦታዎች፣ የጊዜዎች መመቸት ከእግዚአብሔር ጋር ለመጓዝ አስተዋፅዖ አያደርግም። ከእግዚአብሔር ጋር የምንጓዘው በልባችን ነው።         ልባችንም እግራችንም ጉዞው ወዴት ነው? ወደ ኃጢአት መንደር? ወደ ሴሰኝነት ሰፈር? ወደ ሙስና ስግራ፣ ወደዝሙት ከተማ? ወደ ወንጀል ቀጠና? ወዴት ነው? ወደነዚህ ስፍራዎች ሁሉ ብዙ ዘመን ተጉዘናል አሁን ግን በልባችን ወዳልተጓዝንባቸው መንገዶች እንራመድ። ክርስቶስ በተጓዘባቸው የህይወት አሻራዎች ላይ እንጓዝ።          የእግራችንን እርምጃ ጸሎትን አንግበን ሆስፒታል ወደተኙ ወገኖች፣ ማፅናናትን ታቅፈን ወደታሰሩ ሰዎች፣ ፍቅርን አዝለን ወደተገለሉ ሰዎች፣ ምግብ ቋጥረን ወደተራቡ ሰዎች፣ ቃል ይዘን ተስፋ ወደቆረጡ ሰዎች እንጓዝ። የእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ደስታና እግሮች ያሉት በዚህ ውስጥ ነውና። ይህን ማድረግ እግዚአብሔር ወደየትኛው አቅጣጫ እንደሚሄድ ማወቅ ነው።          አቤቱ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ልባችን ዓለምን ከመከተል መልሰህ ካንተ ኋላ አስከትለው። አዕምሯችን ፍቃዳችንን ከመከተል መልሰህ ፍቃድህን አንግስበት። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እርምጃችን አንተን የሚያከብር ይሁንልን፣ ተረከዛችን ሰዎችን ለማስከፋት ሳይሆን ለሰዎች እረፍት የሚሰጥ እንዲሆን በፀጋህ አግዘን። ኃጢአታችንን ሳንጨርሰው ጣልቃ ገብተህ ታደገን።          
Показать все...
🚫ገንዘብ > ክርስቶስ “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤”   — ዕብራውያን 13፥5 የህይወታችን ፍልስፍና አባቴ ከእናቴ ይበልጥብኛል፣ ፍቅረኛዬ ከወንድሜ ይበልጥብኛል፣ እህቴ ከሚስቴ ትሻለኛለች፣ ጎረቤቴ ከዘመዴ ይልቅ ይበጀኛል በሚል ማበላለጥ ውስጥ ተጠልፈን ህይወትን እንመራለን። በእርግጥ ከአባትህ እናትህን አስበልጠህ ከሚስትህ እህትህን አተልቀህ ትኖር ይሆናል ነገር ግን ከክርስቶስ ገንዘብን አስቀድመህና አስበልጠህ መኖር ከባዱ ስህተት ነው። እግዚአብሔር የነፃነት አምላክ ነው ምርጫህን የማይጋፋ አባት ነው። ስለዚህ ጌታ የሆነውን ክርስቶስን ወይም ጌታ የተባለውን ገንዘብ በራስህ ላይ ማንገስ ኃ.የተ.የግ.መብትህ ነው።     በዚህች ምድር ላይ ለመኖር ገንዘብ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ክርስቲያኑም ዓለሙም በገንዘብ ፍቅር ተነድፏል። ክርስቶስ በሙሉነት ያልማረከውን ማንነታችንን ገንዘብ በሙሉነት ተቆጣጥሮታል። ብዙ የቸርች አዳራሾች የገንዘብ እዳህ ተከፍሏል፣ ባንክህ በብር ተሞልቷል፣ ሃክታር መሬት ትገዛለህ በሚል ኢ-ወንጌል በሆኑ ትምህርቶች ተመልተዋል። ሰውም ክርስቶስ ሞቶልሀል ከሚለው ድምፅ ይሳካልሀል፣ ኢየሱስ ይመጣል ከሚለው አዋጅ ገንዘብ ወዳንተ ይመጣል ለሚለው ከንቱ ምኞት አሜን ይላል።  ወዳጆቼ ገንዘብ መግዛት የሚችለው የአቅሙን ያህል ነው አቅሙ ደግሞ ውስን ነው። ክርስቶስ ግን የሚገዛው ዓለማትን ሁሉ ነው። አቅሙ ከአድማሳት ያለፈ ነው። የያዝነው ክርስቶስ ከምንኮራበት በላይ ያኮራል፣ ከምንመካበት ገንዘብ በላይ ያስመካል። የማያሳፍር ትምክህት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
Показать все...
በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ከሚኖር ሰው ይልቅ በፈተና መሀል እያለፈ ያለ ሰው እምነት ጠንካራ ነው። የእግዚአብሔር አብሮነት ከ'ኛ ጋር መሆን እንጂ የሁኔታ መመቻቸት እምነታችንን አያጠነክረውም። አንዲት እናት ካረገዘችበት ሰከንድ አንስቶ ልጅዋን እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ ያለው ውጣ ውረድ፤ ኃላፍትና፤ የተረገዘውን ልጅ በሆድ ተሸክሞ መዞር ምን ያክል ዋጋ እንደሚያስከፍል እናቶቻችንን ጠይቀን መረዳት እንችላለን። ወንድ ልጅ ስለ ሴት ልጅ ምጥ ሲያወራ የተረዳውን ያክል ነው እንጂ 'ፕራክቲካሊ' ማለቴ በተግባር ግን ወላድ የሆነች ሴት ስለ ሁናቴው ብታስረዳ ይቀላል። ይሁንና አንተ አንብቢዬ ሆይ እናትህ አንተን ወልዳሃለች፤ ወደዚህ ምድር አካል ለብሰህ ወንድ ሆነህ እንድትፈጠር የእናትህ አስተዋጽኦ የራሱ የሆነ ሚና አለው። በምጥና ጣር ወልዳህ እራስህን ችለህ እስከተንቀሳቀስክበት እለት ድረስ ያየችው መከራ የዋዛ አይደለም።ከሚገርምህ ዛሬም ላንተ ያላት ፍቅር ልክ እንደ ልጅነትህ ወራት ይሆን ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ አምላክህን ወንድ አድርጎ ስለ ፈጠረህ አመስግነው። እናትህን አንተ አልመረጥክም፤ እንድትወልድህም አላማከርካትም። አምላክ በገዛ ፈቃዱ እንደወደደ አስቀድሞ በወሰነው መሰረት ከእርስዋ ተወልድክ ማለት ነው። እኔስ? ያልሽው አንባቢዬ ሆይ ስሚኝ፤ ሴት ሆነሽ ስለተፈጠርሽ እግዚአብሔርን አመስግኝ። ወንድ ያለ ሴት ሴትም ያለ ወንድ የሚሆን ነገር ስለሌለ። አምላክ አዳምን ከምድር አፈር ወስዶ አበጅቶ ሰርቶ ካስዋበው በኋላ በአፉ የህይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤ እርሱም ህያው ነፍስ ሆነ። ቀጠለና አምላክ አዳም ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ብሎ ከጎድን አጥንቱ ወሰደና ሴት አድርጎ ሰርቶ አምጥቶ ሚስት እንድትሆነው ሰጠው። አዳምም ሔዋንን የራሱ አድርጎ ወሰዳት። ከዛ ጊዜ ጀምሮ አምላክ በብዙ ተባዙ ብሎ ባወጀው ዘላለማዉ ቃል መሰረት እየተዋለዱ በዝተው ይኸው ምድርን ሞልተዋታል። የሚገርመው የሚወለደው ልጅ ንጉስም ይሁን አሽከር፤ ንግስትም ትሁን ሞግዚት፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በምድር ላይ ሰው ተብሎ ስጋ ለብሶ የተመላለሰ የሞተም ይሁን በህይወት ያለ ማንኛውም አካል ከሴት ነው የተወለደው። ታላቅ አክብሮት ለሴቶች ይገብቸዋል! በተለይ ደግሞ ጥበበኛ ሴት ከእርስዋ የተሻሉ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ጀግና ወንዶችንና ጀግኒት ሴቶችን ትወልዳለች። ከነዛ መሀል ያንቺ እናት ያንተ እናት ተጠቃሽ ናቸው። እኛን ለመውለድ እናቶቻችን የነበራቸው እምነትና ጽናት ወደር የለውም። ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመጣ እግዚአብሔር በተመቻቸ ሁኔታ ሊያኖረን ሳይሆን ቃል የገባልን በየትኛውም አደገኛ ሁኔታ አብሮን እንዳለና እንደሚረዳን ነው እንጂ። አያችሁ በእንደዚህ አይነት በከፍተኛ የህይወት ፈተና ውስጥ ስናልፍ በ'ኛ ውስጥ ያለው አምላክ ያስቀመጠው መልካም ነገር ፈንቅሎ ይወጣል ማለት ነው። የትኞቹም ታላላቅ ሰዎች ናቸው ብላችሁ የምታውቋቸውና የምታከብሩዋቸው ሰዎች በህይወታቸው ዘመናቸው ከአንዴም ሁለቴ፤ በተደጋጋሚ አደገኛ በሆነ መከራና ግፊት ውስጥ ያለፉ ናቸው። በቀላሉ የኋላ ታሪካቸውን ማጥናት ነው። መውደቅ ካለ መነሳት አለ፤ መዝራት ካለ ማጨድ አለ፤ እምነት ካለ ጽናት ካለ መውረስ አለ፤ ያመኑትን መሆነ አለ። አምላክ አብርሃምን ከታዋቂዎቹና ከባለጠጋ ቤተሰቦቹ ተለይቶ እርሱ ወደሚያሳየው ምድር፤ ወደማያቀው ቦታ ትቶዋቸው እንዲወጣ ትእዛዝ ሰጠው። የነገረውና የገባለት ኪዳን የተስፋ ቃል ልክ ወደተናገረው ስፍራ ሲደርስ በእርሱ በኩል አዲስና የተባረከ ህዝብ እንደሚወልድ እንደሚባርከው ነበር። የምድር አህዛብ ሁሉ በእርሱ እንደሚባረኩ ነገሮት ነበር።እርሱም ታዘዘ አባታችን አብርሃም እንደተናገረው ያችን ምድር ሲረግጥ ነገር ጀመረ፤ እኛም ከእርሱ የተነሳ ተባረክን፤ አህዛብ ሁሉ። ያ ሁሉ ግን ከመሆኑ በፊት አብርሃም ያለፈው እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ድንኳን እየተከለና እየነቀለ እየተጓዘ ነበር የኖረው። አስተውሉ ሙሴን ልኮት ከፈርዖን ጋር ነበር የተጋፈጠው፤ ከዛም የቃል ኪዳኑን ህዝብ ከፈሮዖን ጭቆና አዳናቸው፤ ወደተስፋይቱ ምድር ከነዓን እንዲገቡ 40 አመት በብዙ ድንቅና ተዓምራት አምላካቸውን እያሳወቃቸው እያሳያቸው መራቸው፤ ኢያሱን ተክቶ ሞተ። ኢያሱም ህዝቡን ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ከነዓን አስገባቸው። ለኢያሱ ደግሞ የረገጣትን ምድር ሁሉ እንደሚያወርሰው ተናገረው ፈጸመለትም። ከኢያሱ ይጠበቅ የነበረው እውነት በእምነት አብዝቶ በጠላቶቻቸው የተያዘውን ምድር መርገጥ ነበር፤ በተለይ ኮረብታማና ተራራማ የሆነውን ምድር እየተዘዋወረ እየሰለለ መርገጥ ብቻ፤ የረገጠውን ምድር ማውረስ ደግሞ የተናገረው የአምላኩ ፈንታ ነበር። እንዳለውም ውጊያው እያለ ወረሰ። ንጉስ ዳዊትን ጎሊያድ ገጥሞት ነበር፤ ኤሊያስን የበዓል ነቢያት ገጥመውት ነበር፤ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ነበር። እነዚህ ሁሉ በአስፈሪና በአስቸግሪ አጣብቂኝ በሞላበት ህይወት ቢያልፉም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ከመሆኑ የተነሳ አሸነፉ እንጂ አልተሽነፉም።መከራ በበዛባቸው ቁጥር እምነታቸው ጨመረ እንጂ አልዛሉም። ለጠላቶቻቸው እጅ አልሰጡም። ኤቨረት ፈርጉሰን የተባለ ሰው አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ከጥንት ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የሞቱት በእምነታቸው ምክንያት ላመኑበት ጉዳይ መታገል ሲጀምሩ ነው ይለናል። እኛም ምስክር ነን። ስለዚህ የተወደዳችሁ አንባቢዎቼ በእናንተም ህይወት በተመሳሳይ መልኩ ፈተና በዝቶባችሁ ይሆናል። አይዞዋችሁ! ክርስቶስ "እኔ አለምን አሸንፌያለሁ" ነው ያለን። ደስ የሚለው መልካሙ ዜና ደሞ እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ሁሌ ከኛ ጋር ነው። የትም ሁኑ በምንም ሁኔታ ውስጥ እለፉ እርሱ ከናንተ ጋር አለ። ያያችኋል፤ ጩኸት ጸሎታችሁን ይሰማል። ስሜታችሁን ይጋራል! ሁሉም ያልፋል! እናንተ ብቻ ጌታ በተናገራችሁ የተስፋ ቃል እና ኪዳን ላይ ጸንታችሁ ስትቆሙ ማንም አይቋቋማችሁም! በመንፈሱ ብርታት በጸጋው ብዛት ያም ይህም ያልፋል። እምነታችሁ ተፈትኖ ያላችሁን ቁርጥ አቋም ሲታወቅና ሲገለጥ እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ! ጽኑ በርቱ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅርቡ ይመጣል! #እስከመጨረሻ_የሚጸና_ግን_እርሱ_ይድናል!
Показать все...
ሰውን በማመን ተጎዳሁ ምን ላድርግ? ለምትሉ “እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።”( ሉቃስ 10፥27)       ወዳጆቼ ከሰው ጋርና ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖርበት የህይወት መስፈርት አንድ ዓይነት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ባህሪና የሰው ልጅ ጠባይ የተለያየ ነው። እግዚአብሔር ባህሪው እምነትን መቀበል የሚችል፣ አምልኮን የሚቀበል፣ ምስጋና የሚገባው ነው። ሰው ደግሞ እምነትን መቀበል የማይችል፣ አምልኮ የማይገባው፣ ምስጋና የማይቀርብለት ፍጡር ነው።       ብዙ ጊዜ ህይወታችን የሚበላሸው ከሰው ጋርም በሰላም ለመኖር የሚከብደን ለእግዚአብሔር ልንሰጠው የሚገባንን ለሰው መስጠት ስንጀምር ነው። ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት እንኖራለን ከሰው ጋር ግን በፍቅር እንኖራለን። እግዚአብሔርን ስናምነው እምነትን መቀበል የባህሪው ስለሆነ አይከብደውም ሰውን ግን ስናምነው እምነትን የመቀበል ትከሻ ስለሌለው ወድቆ ይሰበራል። እግዚአብሔርን ስናምነው ፀጋ ይበዛልናል ህይወታችን ይሰምራል ሰውን ስናምነው ግን ጉዳትን እናጭዳለን፣ እንዴት አምኜው ይከዳኛል? እንዴት ራሴን ሰጥቼው ይሸሸኛል? እንላለን። ሰውዬው ያልታመነው በአምላክ ትከሻ የሚታዘለውን እምነት በሰውዬው ትከሻ ስናሸክመው አልችለው ብሎ ነው። በአጭሩ እምነት ለሰው ልጅ ከአቅሙ በላይ የሆነ ሸክም ነው።        ታዲያ እምነትን መቀበል ከማይችል ሰው ጋር እንዴት እንኖራለን? በፍቅር! ሁልጊዜም እምነታችን ወደላይ (ወደ እግዚአብሔር)፣ ፍቅራችን ወደጎን (ወደ ሰው) መሆን አለበት። የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ውደዱ እንጂ እመኑ የሚል መልዕክት የለውም።         ሰዎችን የማናምነው እንደኛ ስለሆኑ ነው። እኛ እምነት ሲጣልብን መታመን የሚከብደን፣ አደራ ሲሰጠን አደራ የምንበላ ነን። ስለዚህ የምናምነው ሰው ልክ እንደኛ እምነት አጉዳይ ነውና ልናምነው አይገባም። እምነት ስላችሁ በትንንሽ ነገሮችም ጭምር ተጠራጣሪ መሆን ማለት አይደለም። የተሸከመችንን መሬት ብትክደንስ ብለን ሳንጠራጠር እናምናታለን እግዚአብሔርንም ይክደናል ብለን ሳንሰጋ እናምነዋለን። ነገ አየር ባይኖርስ ብለን አንሰጋም ነገ አየር እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን እግዚአብሔርንም ነገ ከዙፋኑ ቢገለበጥስ ነገ ቢሞትስ ሳንል ዘላለም ይኖራል ብለን ተስፋ እናደርገዋለን። እናቴ ትጠላኛለች ልጄ አይደለህም ብላ ትክደኛለች ብለን ስጋት ሳይገባን እናፈቅራታለን እግዚአብሔርንም እኔን ትቶ ሌላ ይወዳል ልቤን ሰብሮ ጉድ ያደርገኛል ሳንል እናፈቅረዋለን። ሰውን ማመን የለብንም ማለት ለእግዚአብሔር የምንሰጠውን ፍፁም እምነት፣ ፍፁም ተስፋና ፍፁም ፍቅር አንሰጠውም ማለት ነው።         ሰዎችን አይስቱም፣ አይክዱም፣ አይጠሉም በሚል አመለካከት ታውረን አምነናቸው ልንቀርብ አይገባም። ይልቁንም ደካሞች ናቸው እኔ እንደምደክመው እነርሱም ይደክማሉ፣ እኔ እንደምፈተን እነርሱም ይፈተናሉ ብለን ልንቀርብ ይገባል። የተወዳጀነው ከመላዕክት ጋር ሳይሆን ደካማ ስጋን ከለበሱት እኛን መሳዮች ጋር ነውና።         ሰዎችን በጣም እያመንን ስንሄድ በጣም እየተጎዳን እንመጣለን። ታማኝ ሰው ጠፋ ብለን ብቸኝነትን ገንዘብ ልናደርግ እንችላለን። እምነት የሰውዬውን ድካም አይሸፍንም ይበልጥ ያጎላዋል። ፍቅር ግን ድክመትን ይሸፍናል። ፍቅር ሰውዬውን የሚያይበት መነፅር ተፈትኖ ነው የወደቀው፣ እንደኔ ደካማ ስለሆነ ነው የዛለው፣ እኔም በእርሱ ቦታ ብሆን የማደርገውን ነው ያደረገው ብሎ ነው። ፍቅር በደልን የሚሸፍን ስህተቱን አሳንሶ መልካምነትን አጉልቶ የሚያይ ነው። “ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።” ( 1ኛ ጴጥሮስ 4፥8) ። በፍቅር ውስጥ የተዘረጋ የይቅርታ እጅ አለ፣ በፍቅር ውስጥ የሚያቅፍ ምህረት አለ፣ በፍቅር ውስጥ የሚታጨድ የደስታ አዝመራ አለ። t.me/mizan_amann join join ☝ ☝ 👆👆
Показать все...
እኔ የተጠምኩበት ምክር ነው እናንተም ለኔ ብላችሁ ተጠቀሙበትና ለሌሎችም ሼር በማድረግ ጥቀሟቸው:: እወዳችሁዋለው:: ……..⏳ዘመኑን የሚቆጥር ሰው ባህሪያት🕰 ✍️ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸው እያንዳንዱ ቀን የስራ ጊዜ አይመስላቸውም ብዙ ሰው በወሬ የሚጠመደው ለዚህም ነው። ከዚህ ምድር እንደምናልፍ ማወቅ በምድር ላይ ሰርተን ማለፍ ያለብንን መልካም ነገር ቶሎ ቶሎ እንድንሰራ አቅም ይሰጣል። ዘመኑን በመቁጠር የሚኖር ሰው ባህሪያት ፦ 1. በአላስፈላጊ ነገሮች ላይ ጊዜ አያጠፋም 2. አላስፈላጊ ጦርነቶችን አይዋጋም 3. ሕይወቱን በትኩረት ይኖራል 4. ለእግዚአብሔር ለመስራት ይቸኩላል 5. የመዘግየትና የመዘናጋት ሰለባ አይሆንም ለሁሉም ነገር የተወሰ ጊዜ አለው በተሰጠን የመኖሪያ ጊዜ ውስጥ እግዚአብሔር ለእኔ ምን ሰራልኝ ብቻ ሳይሆን እኔ ለእግዚአብሔር ምን ሰራሁ የሚለውን በትኩረት በማጤን መኖር አለብን። መዝሙረ ዳዊት 39:4 አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። Talk is cheap. Don’t tell me please show me!!! መልካም ቀን!!! ❣️
Показать все...
ያህዌ ትልቅ ነህ      እግዚአብሔር ሆይ አንተን ማንም የማያውቅህ ትልቅ አምላክ ነህ። ስላንተ በጨረፍታ ካወቅናት በላይ ነህ። አንተን ወስነን እንዲህ ነህ እንደዚያ አንልህም ከዚያም ታልፋለህ። አንተ በልኬ የተሰፋህ አምላኬ፣ በፍላጎቴ የተጠረብክ ጣዖቴ አይደለህም። የምሸከምህ ሳትሆን የተሸከምከኝ፣ የምንከባከብህ ሳትሆን የምትንከባከበኝ፣ የምረዳህ ሳትሆን የምትረዳኝ ፈጣሪዬ ነህ።          ለኔ ያልገባኝ ነገር ላንተ ያልገባህ ነገር አይደለም፤ ለኔ የተሳነኝ ነገር ላንተ የተሳነህ ነገር አይደለም፤ ለኔ የተሰወረ ነገር ላንተ የተሰወረ ነገር አይደለም፤ ለኔ የጠፋብኝ ነገር ካንተም የጠፋ አይደለም። አንተ ሁሉን አዋቂ ነህና ስምህ ይክበር።        “አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።” ( 1ኛ ሳሙኤል 2፥3)
Показать все...
የሕግና የጸጋ ንጽጽር ሕግ በሙሴ ተሰጠ___ጸጋ በኢየሱስ ተሰጠ ➣ዮሐ 1:16 ➣ ዮሐ 1:17 ሕግ ተቀባዮች እስራኤል ➣ሮሜ 9÷4 ጸጋ ተቀባዮቹ እስራኤልም አሕዛብም ➣ሮሜ 3፡22 ሕግ አድርግና በሕይወት ኑር ➣ሮሜ 10÷5 ጸጋ እመንና በሕይወት ኑር ➣ሮሜ 4÷5 ሕግ ፍላጎት ፡ እግዚ/ር ጽድቅን ከሰው ልጅ ይጠይቃል ። ጸጋ አቅርቦት ፡እግዚአብሔር ጽድቅን ለሰው ልጅ ይሰጣል ➣ ኤፌ2÷8:9 ➣ዮሐ 1÷17 ሕግ ያለ እምነት ነው። ሕግም ከእምነት አይደለም።➣ ገላ፡3÷12 ጸጋ በእምነት ነው። ➣ገላ፡3÷23 ሕግ ይኮንናል ➣ሐዋ.13÷39 ጸጋ ያጸድቃል ➣ሐዋ 13÷39 ሕግ ይኮንናል ➣ ገላ.5÷4 ጻጋ ሕይወት ይሰጣል ➣ሮሜ 6÷23 ሕግ ይገላል ➣ሮሜ 8÷2 ጸጋ አርነት ያወጣል ➣ሮሜ 8÷2 ሕግ የሃጢአት ዕውቀት ይሰጣል ። ➣ሮሜ 7÷7 ጸጋ የሃጢአት መፍትሄ ይሰጣል ። ➣ ዕብ 4÷16 ሕግ የተሻረ ተስፋ ➣ዕብ 7÷18_19 ጸጋ የተሻለ ተስፋ➣ ዕብ 7 18_19 ሕግ አሮጌ ኪዳን ...አሁን ግን ለእሱ ለታሰርንበት ሰለ ሞትን ፥ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህ በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ #በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም ። ጸጋ አዲስ /የሚሻል ኪዳን ➣ሮሜ 8÷13 ➣ዕብ 7÷22 ሕግ አሮጌው የፊደል ኑሮ ➣ሮሜ 7÷6 ጸጋ የአዲስናየመንፈስ ኑሮ ➣ሮሜ 7÷6 ሕግ በድንጋይ የተጻፈ ሕግ ➣2ቆሮ 3÷3 ጸጋ በልብ የተጻፈ ሕግ ➣ዕብ 8÷10 ሕግ የፊደል አገልግሎት 👇 እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድአበቃን ፡ፊደል ይገድላልና በመንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል ። ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለ ተሻረ ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ ፡ ጸጋ የመንፈስ አገልግሎት 2ቆሮ 3÷6_9 ሕግ ይረግማል ➣ገላትያ 3÷10 ጸጋ ይባርካል ➣ገላትያ 3÷14 ሕግ የኪዳኑ ካህናት ደካሞች ➣ዕብ 7÷ 28 ጸጋ የኪዳኑ ካህን ፍጹም ➣ዕብ 7÷28 ሕግ ነቀፋ ያለው ኪዳን ➣ ዕብ 8:7 ጸጋ ፍጹም ኪዳን ➣ዕብ 8÷6 ሕግ መልካሙን ሰው ይኮንናል ➣ዕብ 1÷15 ጸጋ የከፋውን ያጸድቃል➣ 1ጢሞ 1÷15 ሕግ በጉ ለእረኛው ይሞታል➣ ዕብ 9÷19_20 ጸጋ እረኛው ለበጉ ይሞታል ➣ማቴ 26÷28 ሕግ ፡ባርነት ገላትያ ➣5÷1 ጸጋ:ነጻነት ➣➣ገላትያ 5÷1 ሕግ:በሕግ ፍትህና ፍርድ ጉልህ ስፍራ ይይዛሉ ➣➣ዮሐ 8÷4_5 ጸጋ: በጸጋ ምህረትና ፍቅር ያይላሉ ➣➣ዮሐ 8÷10_11 በክርስቶስ የሚሰራ እምነት ነው ገላትያ 5÷6 t.me/mizan_amann join
Показать все...
1ኛ ክፍል ተመዘገብኩ አስደናቂ የመልካም ወጣት ምስክርነት። @christ_zene @christanzenabo
Показать все...
ልጄን ለማን ትቼ ሊታይ የሚገባ የመልካም ወጣት ምስክርነት። @christ_zene @christanzenabo
Показать все...
. 10 ሺ አይበቃኝም የመልካም ወጣት ምስክርነት 🕑-4:20Min💾-.14.5MB @marsilchannel @marsilchannel △Join Us△
Показать все...
​​👇👇👇 በትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ !! የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡ ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ፡፡እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ... በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡ በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡ ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡ በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡ እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ፡፡ #Eldaah-Knowlege Of God Join us 👇👇👇👇👇 @One_way_He @One_way_He @One_way_He @One_way_He ይ🀄️ላ🀄️ሉን
Показать все...
"የዳሰሰኝ ማን ነው?" ሉቃ 8:44         አንዳንድ በሽታዎች ከሚያደርሱብን ጉዳት በላይ ስለበሽታው የተዛባ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ይበልጥ ይጎዱናል። በሽታው ስጋችንን ይጎዳዋል ሰዎች ግን ስነ ልቦናችንን ይጎዱታል። ፈልገን ባልሸመተው በሽታ ለምን ሰዎች ፈልገው ያገሉናል? ለምን አቅደው ይርቁናል? ፍቅር እኮ ህመማችንን አጉልቶ የሚያይ ሳይሆን መዳናችንን እየናፈቀ ድነን መቆማችንን እያሰበ ከኛ ጋር የሚጣበቅ ነው። ወዳጆቼ አንዳንዴ የታመመ ሰው የምትጠይቁት ሳይጠይቀኝ ከሚል ወቀሳ ለመሸሽ ብላችሁ ወይም ግዴታ ሆኖባችሁ አይሁን፤ ከጠየቃችሁም በሚጠግን ቃልና ህመሙን በሚያስረሳ ፍቅር እንጂ ስነልቦናን በሚጎዳ መልኩ አይሁን!!           አስራ ሁለት አመት ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት ጉዳቷ እጅግ ከባድ ነበር። አስራ ሁለት አመት ቀርቶ ለሰባት ቀን እንኳ የወር አበባ የሚፈሳቸው እህቶቻችን ያላቸውን ስቃይ ማየት ከባድ ነው። በዚህ ላይ አምልኮ ስፍራ መገኘት የማትችል፣ ራሷን ማፅናናት ከምትችልበት ስፍራ የተባረረች፣ ሰው እንደረከሰች ቆጥሮ ያገለላት፣ ደፋ ቀና የሚያደርጋት ቤተሰብ የራቃት፣ እግዚአብሔር ይማርሽ ብሎ የሚጎበኛት አንድም ሰው የሌላት እጅግ የደከመች ምስኪን እህት ናት። በሽታዋ ከአገር ወደ ሌላ አገር ሪፈር ተፅፎ የምትታከመውና የሚድንላት አይደለም። ከዓለም አዋቂና መርማሪዎች በላይ ነው። መፍትሄ ይኖረዋል በተባለችበት ሁሉ እየዞረች አንዳች ላይጠቅሟት ገንዘቧን የጨረሰች ምስኪን ናት።         ገንዘብ ከእጇ ይንጠፍ እንጂ፣ ጤና ከሰውነቷ ይጥፋ እንጂ፣ የከበባት ሰው አይኑር እንጂ፣ ሀገሩ ሙሉ አድሞ ይራቃት እንጂ የሚያስቀና እምነት ነበራት። አንድ ቀን ከዚህ ችግሬ እላቀቃለሁ፣ ቀና ብዬ የምሄድበት ቀን ይመጣል የሚል ተስፋ ነበራት። ለካ ተስፋ የመኖር አቅም ነው። እምነት የህይወት ጉልበት ነው።          ይህቺ ሴት ክርስቶስ ያድነኛል ብላ የምታምን ድንቅ ሴት ናት። እጁ ዳብሶኝ አይደለም የልብሱ ጫፍ ደሜን ለማቆም በቂ ነው ብላ የምታምን ግሩም ሴት ናት። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንም የልብሱን ዘርፍ ዳሰሰችው ወድያውም ደሟ ቆመ እርሱም የዳሰሰኝ ማን ነው? አለ። የሚገርመው ከእርሷ ይልቅ ለእርሱ የቀረቡት፣ ያቀፉት፣ ጎኑን ይዘው የሚጎተቱት አሉ። ብዙዎች ይጋፉታል ይታሹታል ግን በእምነት አይዳብሱትም። እርሷ ግን ክርስቶስ የሚዳሰሰው በእምነት እንጂ በአጀብ አለመሆኑ የገባት ናት።          ወዳጆቼ ዛሬ እንደዚህች ሴት አይነት ችግር ባይኖርብን እንኳ እንደ አቅማችን እንደ ትከሻችን ስፋት የተለያዩ ችግሮች ይኖሩብን ይሆናል። ነገር ግን ዘመንና እድሜ ያስቆጠረውን ችግራችንን ለማስወገድ በህክምና፣ በጠቢብ ነን ባዮች እና በሌሎችም ለማስወገድ ገንዘባችንን ጨርሰን፣ ከሰው መፍትሔ አጥተን ያለኸኝ አንዱ አንተ መድኃኒዓለም ብቻ ነህ እያላችሁ ይሆናል።         አዎ መድኃኒዓለም የችግራችሁ ሁሉ የመፍትሄ ቁልፍ ነው። እኛ ክርስቶስን እየተጋፉ ከሚከተሉት ወገን ሳይሆን በእምነት ከሚዳስሱት ወገን እንሁን። ፀሎታችን በልማድ እንደምደግሙት ሳይሆን በእምነት የሚቀርብ ይሁን። ፈውስን ልሞክረው እስቲ ብለን ሳይሆን ያድነኛል ብለን ዋጋ በመክፈል መቅረብ ይኖርብናል። በእምነት ስንዳስሰው አንገት ያስደፋንን ቀንበር የሚሰብር ኃይል ከእርሱ ይወጣል። ክርስቶስ ሆይ እንዳስስሀለን ኃይልህን ላክልን።
Показать все...
ዛሬ ነገ ነው? "አባዬ ዛሬ ነገ ነው?" አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ። አባት እየተበሳጨ "ምንድን ነው የምትለኝ?" አለ። ልጅም "ዛሬ ነገ ነው ወይ?" አባት እንቅልፉ ስላለቀቀው "ሂድና እናትህን ጠየቃት በቃ ልተኛበት" አለና እየተበሳጨ ፊቱን ቨፈነ። ልጅ ወደ እናቱ ሄዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት " እማዬ ዛሬ ነገ ነው?" እናት ፈገግ አለች "ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?" አለች የልጇን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች "ትናንት አስተማሪያችን 'ነገ ትምህርት የለም' ብላን ነበር፣ ዛሬ ነገ ነው?" አላት። እናት "እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው" አለች እየሳቀች። ይህ ለሕፃኑ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም። ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው። ለነገ እንማራለን፣ ለነገ እንሰራለን፣ ለነገ እንገነባለን። የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ። ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን። ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን። እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን። መጽሐፍ" ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ ተመልከቱ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና" "ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ!" ይላል። ያዕ 4:15 / ማቴ 6:34 ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሳሪያም አንዱ "ነገ" በሚል ቃል ማዘናጋት ነው። ነገ እማራለሁ፣ ነገ እሔዳለሁ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ፣ ነገ ንስሐ እገባለሁ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሰራለሁ ነገ ነገ ነገ። ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉስ በመቅሰፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር። በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ:- ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው። ፈርኦንም :- ነገ አለ። እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው። ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን አይነት ክፉ አመል አለብህ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ፣ አልተስተካከል ያለህ ድክመት፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? "አቤቱ አሁን አድን" ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ። ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም። ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግስቱም መልሳችን ነገ ነው። "ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው" እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሰራ የማንፈልገውን እየሰራን እንኖራለን። ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም "የተወደደ ሰዓት አሁን ነው" መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትስጥ። ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው። ማንም ሊሰራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት። አሁኑኑ ተነስ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመስራት፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅ "ነገ አደርገዋለሁ" ብለህ ነበር፣ ዛሬም "ነገ" አትበል ምክንያቱም ሕፃኑ እንዳለው "ዛሬ ነገ ነው!"
Показать все...