cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ

መልካም ምሳሌነት አላማው ለክርስቶስ ተልዕኮ ይህ channel ለመልካም ስራ የሚውል በመልካም አላማ የተቀናጀ ነው

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
138
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
🍇ያማረውንና የጣፈጠውን የአንደበታችሁን ፍሬ ጌታ በጊዜው ያብላችሁ 🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇 🍇 በምላስ ላይ ትልቅ ኃይል እንዳለ ያወቀ ሁሉ ከእኛ ጋር በአየሩ ላይ ይህንን ያውጅ 🍇 "ምላሴ ፅድቅህን ሁልጊዜ ምስጋናህን ይናገራል 🍇 የእግዚአብሔር ዘር--የእግዚአብሔር ቃል ራሱ እግዚአብሔር ነው እኔም የተወለድኩት ከእግዚአብሄር ነው ስለዚህ የእግዚአብሔር ዘር ነኝ 🍇 እግዚአብሔር በእውነት ቃል አስቦ ወልዶኛል 🍇 ዳግመኛ የተወለድኩት ከሚጠፋ ዘር አይደለም በህያውና ለዘላለም በሚኖር ከእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ 🍇 እግዚአብሔር ባለበት ሁሉ እኔ አለሁ እኔ ባለሁበት ሁሉ እግዚአብሔር አለ 🍇 ከመለኮት ባህሪ ተካፍያለሁ 🍇 መለኮትን ተሸክሚያለሁ 🍇 የክርስቶስ ሙላቱ ነኝ 🍇 በአንደበቴ የመትከል የመፍጠር የመንቀል የመስራት የመፈወስ ሃይል አለ 🍇 የእግዚአብሔር ሙላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ አለ 🍇 እግዚአብሔር ጋር የሌለ ነገር በእኔ ውስጥ አለ 🍇 በሽታ በእሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 ሞት በእርሱ የለም በእኔም የለም 🍇 ጨለማ በእርሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 ድህነት በእርሱ ዘንድ የለም በእኔም የለም 🍇 አባቴ ደስታ ነው እኔም ደስታ 🍇 አባቴ ፍቅር ነው እኔም ፍቅር 🍇 አባቴ ሠላም እኔም ሠላም 🍇 አባቴ ባለፀጋ እኔም ባለፀጋ 🍇 አባቴ ዲታ እኔም ዲታ 🍇🍇🍇ያማረውንና የጣፈጠውን የአንደበታችሁን ፍሬ ጌታ በጊዜው ያብላችሁ 🍇🍇🍇 እልፍ ጊዜ ሃ... ሌ ... ሉ ...
Показать все...
ድንቅ ግጥም 🙈🙈👏👏 ✍ እምነት ከፋለ ርእስ: ስሜን ደብቅልኝ ቃልህን ሳስተምር ጸጋህ ቢገለጥም፣ ያልኩት የለመንኩት ካንተ ዘንድ ቢሰጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። ብዘምር ባመልክህ በመረዋው ድምፄ፣ ባስደናቂ ዜማ በመልካም ቅላፄ፣ ቃላት ብደረድር በሚያስደንቅ ግጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። በስምህ ስጸልይ አጋንንት ቢወጣ፣ ያላመነው ቢያምን የካደው ቢመጣ፣ ታላቅ ነገር ቢሆን በውጪም በውስጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። የአገልግሎት በር በብዛት ቢከፈት፣ ቆሜ ሳገለግል ቢደረግ ታምራት፣ ተራራው ተንዶ ጫካው ቢገለጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። ዉሃው ወይን ቢሆን ትንሹ ቢበዛ፣ በነፃ ቢበላ ማንም ሰው ሳይገዛ፣ በኔ አገልግሎት የማይጥመው ቢጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። የዚህ አገልግሎት መስራችና መሪ፣ ስመጥር ሰባኪ ደሞም አስተማሪ፣ በዚህ በዚያ ስፍራ ይሔን ሰርቻለሁ፣ በብዙ አማኞች ዘንድ ዝናን አግኝቻለሁ፣ ብዙ አማኝ ወደ እኔ ቢንጋጋ ቢሮጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። የሰራኽው አንተ በኔ ላይ ተጠቅመህ፣ የወደኩትን ሰው በጸጋህ አቁመህ፣ ያላንተ ባዶ ነኝ ለማንም የማልጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። ራሱን የሚያዳንቅ አገልጋይ ሞልቶናል፣ ስሙን ሲያስተዋውቅ ፎቶውን አይተናል፣ እንደሚለው መዝሙር ማስታወቂያው በዝቶ፣ በየድሕረ ገጹ አስለጥፌ ፎቶ፣ መንፈስህን ገፍቶ ሰው እኔን ቢያጣጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። ካልተመታች በቀር ምንም የማይገባት፣ ለጥሩ ምሳሌ የማንጠቀማት፣ አህያዋ አንድ ቀን አንተን ተሸክማ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ውቢቱ ከተማ፣ በላይዋ ላይ ጎልተህ እስዋን ማን ልብ አላት፣ ዘንባባና ልብሱ መሬት ተነጥፎላት፣ ካንተ የተነሳ ማንነትዋ ጠፍቶ፣ አንተን ከፍ አድርጋ ማንነትህ ጎልቶ፣ የተነጠፈውን ሁሉንም ብትረግጥም፣ አህያ ናት እንጂ ፍጹም ካንተ አትበልጥም። ለኔም ይሔ ይግባኝ እውነቱን ልረዳ፣ መንገድህን ስቼ ራሴን እንዳልጎዳ፣ የአገልግሎት ክብር ለሰዎች ብትሰጥም፣ እኔ ሰው ነኝ እንጂ ፍጹም ካንተ አልበልጥም። እኔን ማስተዋወቅ መለጠፍ ይብቃና፣ ሰው ካንተ ይጠብቅ ከእንግዲህ ይንቃና፣ ሰው እኔን እንዲያውቀኝ አልለማመጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። የዘመኑ አገልጋይ እባክህን ንቃ፣ ለስምህ መሮጡ ከእንግዲህ ይብቃ፣ ሁሉ ከእርሱ በእርሱ ለእርሱ ነው ሚሆነው፣ ስምህን ደብቀህ ጌታህን ግለጠው፣ እኔም ከዚህ ወዲያ ራሴን አልገልጥም፣ ስሜን ደብቅልኝ እኔ ካንተ አልበልጥም። 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Показать все...
✨✨✨ተፈላጊ ናችሁ ✨✨✨ ☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️ ወንድሜ እህቴ አንተና አንቺ አስፈላጊ ናችሁ ለዛዉም እጅግ በጣም💥💥💥 🔥🔥🌧🌧🔥🔥🌧🌧🔥🔥🌧🌧 አሁን #ኢየሱስ #በምድር #የለም #ነገር #ግን #ባንተ #ባንቺ #ዉስጥ #አለ 🔥🔥🔥☁️🔥☁️☁️☁️☁️🔥☁️ የህይወት ጣዕም የጠፋቸዉ እርሱ ጋር ሲመጡ መኖር መኖር ይላቸዋል መኖራቸዉን ይወዱታል 💥🔥💥💥💥💥🔥💥🔥💥🔥 #በጨለማ #ላይ #አለማብራት #አይችልም #ጨለማ #እርሱ #ባለበት #መሰልጠን# አይችልም ☁️🌧☁️🌧☁️🌧☁️🌧☁️🌧☁️ #እናንተ #የምድር #ጨው #ናችሁ (የማቴዎስ ወንጌል 5: 13) ☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️ ወጥ ምንም ያህል ቆንጆ ተደርጎ ቢሰራም ጨዉ እስከሌለዉ ድረስ ሊጣፍጥ አይችልም 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ይህቺ ምድርም እናንተ የክብሩ ተካፋይ ልጆች እስከሌላችሁባት ድረስ ጣዕም አልባ ናት ምክንያቱም የክርስቶስ እንደራሴ ስለሆናችሁ 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #እናንተ #የዓለም #ብርሃን #ናችሁ። #በተራራ #ላይ #ያለች #ከተማ #ልትሰወር #አይቻላትም።" (የማቴዎስ ወንጌል 5: 14) 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 #እናንተ #ባላችሁበት #የጨለማዉ #አለም #አቅም #አይኖረዉም #ስራዉም #የተገለጠ #ይሆናል ፈፅሞ ልትደበቁና ልትሰወሩ አትችሉም #ተራራ ላይ ያለን ቤት አለማየት አይቻልም ባትወዱም ከፍታ ላይ ስላለ ታዩታላችሁ። 😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳 በእናንተም ያለዉን #ብርሀን #የልጁን #መልክ #ማንም #አለማየት #አይችሉም #ምክንያቱም #ልጁ #በእናንተ #ስለተሳለ #እናንተ #የራሳችሁ #ስላልሆናችሁ
Показать все...
የእውነትም፣ የህይወትም፣ የመንገድም ህያው ኮምፓስ             ኢየሱስ ክርስቶስ ነው       ወላጆች በእርግዝና ላይ ላለው (ላልተወለደው) ልጃቸው አልጋ፣ ልብስ፣ የሚመገበውን የተለያዩ ነገሮችን አስቀድመው በመግዛት ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ። እግዚአብሔርም እኛን ድንገት ሳይሆን አቅዶና አልሞ ፈጥሮናል። እኛን ከመፍጠሩ በፊት ለኛ የሚያስፈልገንን በሙሉ አዘጋጅቶ ጠበቀን። ለአንድ አዳም የፈጠረው ግዙፍ ዓለማትን ነው። እዚህ አለማት ላይ እንደፈለክ ተሽከርከር ብሎ በዘፈቀደ አለቀቀውም ጭንቅላቱ ውስጥ ህሊና የሚባል ኮምፓስ ገጠመለት። እኛም የዚህ ኮምፓስ ተካፋይ ሆነን ከማህፀን ይዘን ተወልደናል።       አንድ⁠ መርከበኛ በተንጣለለው ውቅያኖስ ላይ ሞገዱን እየሰነጠቀ ይጓዛል፤ አንድ መንገደኛ ጭው ባለው በረሃ ላይ በእግሩ ይገሰግሳል፤ አንድ አውሮፕላን አብራሪ ደግሞ ከአድማስ አድማስ ከተዘረጋው ደመና በላይ ይበርራል። እነዚህን ግለሰቦች የሚያመሳስላቸው ነገር ሦስቱም አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ያስፈልጋቸዋል። ይህ መሣሪያ ባይኖራቸው በተለይ ደግሞ ሌሎች ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም ባይችሉ ከባድ ችግር ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። ልክ እንደዚሁ ሁሉ እኛም እንደ ፍጥረታዊ ሰው ህይወትን ለመምራት ይህንን ኮምፓስ ( ህሊናችንን) መጠቀም ያቆምን ይመስላል። እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍሎች የተሰጡን ለተገቢው ዓላማ እንዲውሉ ነው። እጃችንን ለመመገብ፣ ለመጨበጥ፣ እቃ ለመያዝ ስንጠቀምበት ኮምፖሳችንን ስራ ላይ አውለነዋል ማለት ነው። በዚሁ በእጃችን ደግሞ የሰው ጥርስ ስናረግፍ፣ ሰው ስንደበድብበት፣ ለመሳደቢያ ስናውለው ኮምፓሱ እንደጠፋባት መርከብ ዝም ብለን የምንንቀዋለል ሆነናል ማለት ነው።        እንደ ክርስቲያን ኮምፓሳችን የእግዚአብሄር ቃል(መፅሀፍ ቅዱስ) ነው። ክርስቲያን ሆነን እንደ ፍጥረታዊ ሰው ልንኖር አይገባም። ዛሬ ግን በእያንዳንዳችን ህይወት ምሪት እየሆነን ያለው ቃሉ ሳይሆን የግል ልምምዳችን፣ ህይወት ማለት እንዲህ ነው ብለን በራሳችን ሞልድ የሰራነው ኮምፓስ ነው። እንዴት ሰው በሁለት የተለያየ ኮምፓስ ወደ አንድ መንገድ ለመሄድ ይሞክራል? በኛ ላይ እየታየ ያለው ይህ ነው። ከህይወት በኋላ ከእግዚአብሄር ጋር ዘላለማዊ ህይወትን ለመኖር እንመኛለን ነገር ግን ወደዛ የሚወስደውን መንገድ መከተል አንፈልግም። ይህ መንፈሳዊ ኮምፓስ በሚገባ ከተከተልን የሚወስደን ህይወታችን ወደተገኘችበት እስትንፋስ፣ ሀዘንና እሮሮ ወደሌለበት ደስታና ተድላ፣ በአይን ወዳልታየው ከተማችን ያደርሰናል።       ብዙ የመንገድ ጠቋሚ ምልክቶች በዘመን ብዛት ያረጃሉ መልካቸው ይወይባል፣ የቀደመ ጉልበታቸውን ያጣሉ። ይህ ህያው ኮምፓስ የማያሳስት፣ የማያወናብድ፣ ዘመናት ውበቱን የማያደበዝዙት፣ ጉልበት የማይከዳው የዘመናት ብርቱ ነው። ስለዚህ ወዳጆቼ የምትመኙትን የዘላለም ህይወት ለመኖር የዘላለም ህይወት የሆነውን ኢየሱስን ማመን፣ ወስኖ ለመጓዝ ብቸኛ መንገድ በሆነው በኢየሱስ ብቻ መጓዝ፣ ሀሰት ካደከማችሁና እውነትን ብቻ ከፈለጋችሁ ሀሰት በእርሱ ዘንድ በሌለበት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ልታምኑ ይገባል። ምክንያቱም እርሱ በአንደበቱ እንዲህ ብሎናል። " ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"  (የዮሐንስ ወንጌል 14 : 6)
Показать все...
       አለማመናችንን እርዳው       ካህኑ ዘካርያስ የመውለጃ ጊዜውን ሳይሆን የሚሞትበትን ቀን በሚጠባበቅበት ጊዜ እግዚአብሔር መልዓኩን ልኮ የልጅን ብስራት አበሰረው። ዘካርያስ ግን ከሰውነቱ ስለጠፋው ስሜት፣ ስለራቀው ሙቀት እያሰበ ይህማ አይሆንም ብሎ ማመን አቃተው። ማመን ባለመቻሉ ልጁን እስኪወልድ ድረስ ዲዳ ሆነ።        እኛ ሁላችን ዲዳ ያልሆነው ከዘካርያስ የተሻለ እምነት ስላለን አይደለም። ይልቅ በብዙ ነገር ከእምነታችን ማማ ላይ የምንንሸራተት፣ ጥቂቷ ነገር የምታናውፀን፣ በተለያየ ነገር እምነታችን ተፈትኖ የሚወድቅብን ነን ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ግን አልተቀጣንም ዲዳም ከመሆን ተጋርደናል።         በየዕለቱ ባለማመን እንፈተናለን፣ በየዕለቱ ብዙ ኃጢአትን እንሰራለን እግዚአብሔር ግን እንደ ግብፃውያን በወረርሺኝ እንደ ሰዶናውያን በእሳት ዲን ሳያጠፋን በታላቅ ትዕግስቱና በምህረቱ እያለፈ የንስሀ ቀኖችን እየሰጠን ነው። ኃጢአታችንን ስናስባቸው ለመፈፀም ቀርቶ ለማሰብ እንኳ የሚከብዱ ናቸው። ራሳችንን ተፀይፈነዋል፣ራሳችን ለራሳችን ከብዶናል አንተ ግን በማይጠላው ፍቅርህ ወደኸን በምህረትህ ስበህ አስጠግተኸናል።   “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?”(መዝሙር 71፥19) እንዳንተ ከነኃጢአታችን ያቀፈን ሳይፀየፍ የቀረበን የለም አንተ ብቻ ከኃጢአታችን ባህር አውጥተህ በፅቅህ ትከሻህ ላይ አኑረኸናልና ተመስገን። ስለታላቁ ትዕግስትህ እናመሰግንሀለን፤ ስለታላቁ ምህረትህ እናመሰግንሀለን። ሳትዝል የተሸከምከን ሳትሰለች የያዝከን አንተ መድኃኒታችንን እናመሰግንሀለን። አፈር መሆናችንን አውቆ የሚራራልን ካንተ በቀር የለምና እናመሰግንሀለን። አለማመናችንን እርዳው። አሜን
Показать все...
"በቶሎ እመጣለው" ራዕይ 22:12 እናንተዬ ክርስቶስ በቶሎ እመጣለው ብሎ ቀረ እንዴ? በቶሎ ካለ እኮ ሁለት ሺህ አመት ሞላው ኸረ አይመጣም መሰለኝ! የሚሉ ቀልድና ቁምነገር የተምታታባቸው ሰዎች ንግግርን መስማት እየለመድን ነው። እውነት ክርስቶስ ዘገየ እንዴ? ብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃላት ለአንዳንዶች ቅኔ ናቸው። ይህን ቅኔ ለመፍታት ብዙ መማር እንኳን መፍትሄ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም አራትና አምስት ዲግሪ የያዙ ለእግዚአብሄር ቃል ምስጢር እንግዳ ሲሆኑ አይተናል። ከዚህ ይልቅ ልብን እንደህፃናት ለእግዚአብሄር ቅርብ ማድረግ ይሻላል። ለዚህ ነው ጌታችን ሲፀልይ "ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለህፃናት ስለገለጥህላቸው አመሰግንሃለው" ያለው። ማቴ 11፥25 ናፖሊዮን እንኳ "ተዝካሬን የምታወጡልኝ በደም ነው" ያለውን የቃል ፍቺ ከቅርብ ወዳጆቹ ውጭ ማን የገባው ነበር? ለንጉስ ቅርብ መሆን ለቅኔውም ቅርብ ያደርጋል። እግዚአብሄር ሊናገር የፈለገውን ለማወቅ እግዚአብሄርን መቅረብ ያስፈልጋል። ምድራዊ እውቀት ኖሯቸው ለእግዚአብሄር ቦታ ሳይሰጡት በእውቀታቸው ለነፍሳቸው መቅሰፍት የገዙ ስንቶች አሉ? እውቀታችንን ከእግዚአብሄር ስር ስናውለው እርሱ ሊል የፈለገው ምስጢር ግልፅ ይሆንልናል። ድርቅ ብለው መፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም አያስፈልገውም የሚሉ አሉ። እነዚህ ሰዎች ያገኙትን ነገር በጥሬው የመብላት ሱስ ያለባቸው ጥሬ ወዳጅ መሆን አለባቸው። ሁሉን እንደወረደ ከተቀበልነውማ " ቀኝ እጅህ ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት" ማቴ 5፥29 የሚለውን ቃል በቃል ብንተረጉመው ኖሮ ዛሬ ከዓለም ህዝብ አብዛኛው እጀ ቆራጣ በሆነ ነበር። ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ መተርጎምን ይፈልጋልና ይህን ጥቅስ በቃል አንወስደውም። ክርስቶስ በቶሎ እመጣለው " እነሆ በቶሎ እመጣለው" ብሏል። ራዕ 22፥12 ይህን ካለ ግን ሁለት ሺህ ዘመን ሞልቶታል። ክርስቶስ በቶሎ ሲል በራሱ አቆጣጠር እንጂ የመምጫውን ቀን በኛ የሰዓት አቆጣጠር አስልቶት አይደለም። ቅዱስ ጴጥሮስ " በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት ሺህ አመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ አትርሱ" 2ኛ ጴጥ 3፥8 ይሄንን ከተረዳን የእግዚአብሄርን የሰዓት ስሌት እንመልከት። ሺህ ቀን በርሱ ዘንድ እንደ አንድ ቀን ከሆነ 500 ዓመት 12 ሰዓት ማለት ነው። 250 ዓመት 6 ሰዓት ሲሆን 125 ዓመት 3 ሰዓት ነው። 62 ዓመት ደግሞ 1፡30 ነው። ጌታ ኢየሱስ በቶሎ እመጣለው ያለው በጥድፊያ እመጣለው ማለቱም አይደለም። በራሴ የጊዜ ሰሌዳ እንጂ በኛ ካላንደር አይደለም። ይህን ካላ ገና ሁለት ቀኑ ነው። ለኛ ግን ራቀብን አይደል? እርሱ ግን በቃሉ የታመነ ነውና በቶሎ ይመጣል። ✍አዶኒ 👍 @ActsOfHolySpirit 👍 @ActsOfHolySpirit
Показать все...
ክፍል-አንድ መግቢያ ወደ ሮሜ ሰዎች የመክፈቻ አንቀጽ ሀ. ሮሜ በእጅጉን ስልታዊ፣ አመክኖአዊ መሠረተ እምነት የሆነ የሐዋርያው ጳውሎስ መጽሐፍ ነው። ሮም የነበረው ሁኔታ ተጽእኖ ስላለበት “ሁኔታዊ” ዶሴ ነው። ጳውሎስ መልእክቱን ይጽፍ ዘንድ አንድ ምክንያት ተፈጥሯል። ቢሆንም ከጳውሎስ ጽሑፎች መካከል እጅግ ገለልተኛው ይሄ ነው። ማለትም፣ ጳውሎስ በችግሮች ላይ ከሚያተኩረው (በተለይ በአማኝ አይሁድና በአሕዛብ አመራር መካከል ባለው መቀናናት፣ 14፡1-15፡13) ግልጽ የሆነ የወንጌል አስተዋጽኦ እና የእሱም የየእለት ሕይወት ተጽእኖ ያሳያል። ለ. የጳውሎስ ወንጌል በሮሜ የቀረበው በሁሉም ዘመን ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት ይመለከታል። 1. አውግስጢኖስ በ386 ዓ.ም የተለወጠው ሮሜ 13፡13-14 አንብቦ ነው። 2. የማርቲን ሉተር የደኅንነት መረዳት በ1513 ዓ.ም ፍጹማዊ ለውጥ ያሳየው መዝ. 31፡1 ከሮሜ 1፡17 (እንባ. 2፡4) ጋር እንዳወዳደረ ነው። 3. ጆን ዌስሊ በ1738 ለሜኖናይት ስብሰባ ለንደን ላይ ሲጓዝ የተለወጠው የሉተርን ስብከት፣ በሮሜ መግቢያ ላይ ያለው ሲነበብ ነው፤ በወቅቱ የተመደበው ሰባኪ በመዘግየቱ ሳቢያ! ሐ. ሮሜን ማወቅ ክርስትናን ማወቅ ነው! መልእክቱ ሕይወትን ያንጻል፣ እንደዚሁም የኢየሱስን ትምህርቶች፣ የሁልጊዜም የሆነችው ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ እውነት ነው። ማርቲን ሉተር ስለዚህ ሲናገር፣ “የሐ.ኪ. ዋነኛው መጽሐፍና ንጹሑ ወንጌል!” ብሎታል። ጸሐፊው ጳውሎስ በትክክል ጸሐፊው ነው። የተለመደው ሰላምታው በ1፡1 ይገኛል። በአጠቃላይ እንደ ተስማሙበት የጳውሎስ “የሥጋዬ መውጊያ” የአይኑን ችግር ሲሆን፣ ራሱ ጽሑፉን እንዳልጻፈና ተርቲዩስ በተባለ ጸሐፊ እንዳስጻፈ ይታመናል (16፡22)። ጊዜው ሀ. የሮሜ መልእክት የተጻፈበት ጊዜ ከ56-58 ዓ.ም እንደሆነ ይገመታል። ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል ጊዜአቸው በትክክልና በርግጠኝነት ከታወቁት አንዱ ነው። ይህም የሆነው ሐዋ. 20፡2 ከሮሜ 15፡17 ጋር በማነጻጸር ነው። ሮሜ ምናልባት ከቆሮንቶስ ሳይጻፍ እንዳልቀረና በጳውሎስ ሦስተኛው ሚሲዮናዊ ጉዞው ማገባደጃ ላይ ልክ ከኢየሩሳሌም ከመልቀቁ በፊት እንደሆነ ይገመታል። ለ. የጳውሎስ ጽሑፎች በጊዜ ቅደም ተከተል፣ ኤፍ. ኤፍ. ብሩስ እና ሙሪ ሃሪስ በመጠነኛ ማስተካከያ ቀጥሎ ቀርቧል። መጽሐፍ ዘመን የተጻፈበት ስፍራ ከሐዋ ሥራ ጋር ግንኙነቱ 1. ገላትያ 48 ሶሪያ አንቲሆች 14፡28፤ 15፡2 2. 1ኛ ተሰሎንቄ 50 ቆሮንቶስ 18፡5 3. 2ኛ ተሰሎንቄ 50 ቆሮንቶስ 4. 1ኛ ቆሮንቶስ 55 ኤፌሶን 19፡20 5. 2ኛ ቆሮንቶስ 56 መቄዶንያ 20፡2 6. ሮሜ 57 ቆሮንቶስ 20፡3 7.-10. የእስር ቤት መልEክቶች ቆላይስስ በ60ዎቹ መግቢያ ኤፌሶን በ60ዎቹ መግቢያ በሮሜ ፊሊሞን በ60ዎቹ መግቢያ ፊሊጵስዩስ ከ62-63 ማገባደጃ 28፡30-31 11.-13. አራተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ 1ኛ ጢሞቲዎስ 63 (ወይም ወዲህ፣ መቄዶንያ ቲቶ 63 ግን በፊት ኤፌሶን (?) 2ኛ ጢሞቲዎስ 64 ዓ. ም 68) ሮም ተቀባዮች የደብዳቤው መቀበያ አድራሻ ሮም እንደሆነ ያመለክታል። በሮም ቤተ ክርስቲያንን ማን እንደመሠረተ አናውቀውም። ሀ. ምናልባት በበዓለ ሃምሳ ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት ከሄዱት ሰዎች አንዳንዱ የተለወጡት ወደ አገራቸው ሲመለሱ ቤተክርስቲያኑን ጀምረውት ይሆናል (ሐዋ. 2፡10) ለ. ከእስጢፋኖስ መገደል በኋላ በኢየሩሳሌም በተፈጠረው ስደት የሸሹት ሐዋርያት ሊሆኑ ይችላሉ (ሐዋ 8፡4) ሐ. ከጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞዎች በኋላ የተለወጡት ወደ ሮም ተጉዘው ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ ይሄንን ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝቶት አያውቅም፣ ምንም Eንኳ ጉጉት ቢኖረውም (ሐዋ. 19፡21)። እዛ ብዙ ጓደኞች አሉት (ሮሜ16) አጠቃላይ ሐሳቡ፣ ወደ ስጳንያ በሚያደርገው ጉዞው ሮምን ለመጎብኘት ነበር፣ (ሮሜ 15፡28) ኢየሩሳሌምን ከጎበኘና “የፍቅር ስጦታ” ከተቀበለ በኋላ። ጳውሎስ ከሜዲትራንያን በስተምስራቅ ያለው አገልግሎቱ እንደተገባደደ ተረድቷል። ሌሎች አዳዲስ ቦታዎችን ቃኘ (15፡20-23፣28)። ደብዳቤውን ከጳውሎስ፣ ከግሪክ ወደ ሮም ይዛ የሄደችው በዛ አቅጣጫ በጉዞ ላይ የነበረችው ዲያቆኒቷ ፎቤ ሳትሆን አትቀርም (ሮሜ 16፡1)። ይሄ በቆሮንቶስ መንደሮች በአንደኛው ክፍለ ዘመን በአንድ ድንኳን ሠሪ ይሁዲ የተጻፈ ደብዳቤ ለምን ይሄን ያህል ዋጋ ያለው ሆነ? ማርቲን ሉተር “የሐዲስ ኪዳን ዋነኛው መጽሐፍና ንጹሑ ወንጌል” ብሎታል። የዚህ መጽሐፍ ዋጋ የሚገኘው በጥልቀት ከተብራራው እውነት በተለወጠው ራቢ (የአይሁድ መምህር)፣ የተርሴሱ ሳኦል፣ ለአሕዛብ ሐዋርያ ሊሆን ከተጠራው ነው። አብዛኛዎቹ የጳውሎስ መልእክቶች አገሬያዊ ሁኔታዎችን የሚያንጸባርቁ ሲሆኑ፣ ሮሜ ግን እንዲህ አይደለም። የሐዋርያውን እምነት የሚያሳይ ስልታዊ አቀራረብ ነው። ወንድም ክርስቲያን አስተውለዋልን፣ በዚህ ዘመን የምንጠቀምባቸውን አብዛኞቹን ሞያዊ ቃላት፣ “እምነት” (“መጽደቅ፣” “ኃላፊነት” “ልጅነት” እና “መቀደስ”) ከሮሜ እንደተገኙ አውቀዋልን? ይህ (ሮሜ) የገላትያ መልእክት ሥነ መለኮታዊ እድገት እውነታ ነው። እግዚአብሔር ይህንን አስደናቂ መልእክት እንዲገልጽልዎ ይጸልዩ፣ ሁላችንም የሱን ፍቃድ እንደምንፈልገው፣ ለአሁኑ ሕይወታችን እንዲሆነን! ተግባር ሀ. ወደ ስጳንያ ለሚያደርገው ሐዋርያዊ ጉዞው ርዳታ ለማግኘት የጠየቀበት ነው። ጳውሎስ በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም የነበረው ሐዋርያዊ ተግባር መገባደዱን ተመልክቷል (15፡20-23፣28)። ለ. በሮሜ ቤተ ክርስቲያን በአማኝ አይሁድና በአማኝ አሕዛብ መካከል የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ነው። ይህ ምናልባት ሁሉም አይሁድ ከሮሜ እንዲወጡ የተደረገበትና ኋላ ላይ መመለሳቸው የፈጠረው ይሆናል። በወቅቱ የአይሁድ ክርስቲያን መሪዎች በአሕዛብ ክርስቲያን መሪዎች ተተክተው ነበር። ሐ. ራሱን ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን ለማስተዋወቅ። በጳውሎስ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ በኢየሩሳሌም ካሉት በእውነት ከተለወጡት አይሁድ የሰነዘር ነበር። (የኢየሩሳሌም መማክርት ሐዋ. 15)፣ ከእውነት ካልሆኑት አይሁድም (የገላትያ ይሁዲዎች እና 2ኛ ቆሮንቶስ 3፣ 10-13)፣ እንዲሁም ከአሕዛብ (ቆላስይስ፣ ኤፌሶን) ወንጌልን በራሳቸው አግባቢ ንድፈ-ሐሳብ ወይም ፍልስፍና (ግኖስቲስዝም) ለመደባለቅ ከሚሞክሩት። መ. ጳውሎስ አደገኛ አነሣሽ ተብሎ ተከሶ ነበር፣ ከኢየሱስ ትምህርት ጋር ያለ አግባብ በማከል። የሮሜ መጽሐፍ በተለመደው ስልታዊ በሆነ መልኩ የሱ ወንጌል ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየትና ለማስረገጥ ሲሆን ከብሉይ ኪዳንና ከኢየሱስ ትምህርቶች (ከወንጌል) ተጠቅሟል። ✍️ሳምንት ይቀጥላል…
Показать все...
ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሁን        ክርስቶስ ከፊታችሁ ይሁን፣ ክርስቶስ ከኋላችሁ ይሁን፣ ክርስቶስ በውስጣችሁ ይሁን፣ ክርስቶስ ከስራችሁ፣ ክርስቶስ ከበላያችሁ ይሁን፣ ክርስቶስ በቀኛችሁ ይሁን፣ ክርስቶስ በግራችሁ ይሁን።       ክርስቶስ በተኛችሁበት ይሁን፣ ክርስቶስ በተቀመጣችሁበት ይሁን፣ ክርስቶስ በምትነሱበት ይሁን፣ ስለእናንተ በሚያስቡ ሰዎች ልብ ውስጥ ይሁን፣ በሚናገሯችሁ አፍ ውስጥ ይሁን፣ በሚያይዋችሁ አይን ውስጥ ይሁን።       ማዳኑ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ማፅናናቱ ከናንተ ጋር ትሁን፣ በረከቱ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ፈውሱ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ምህረቱ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ቸርነቱ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ፍቅሩ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ማስተዋሉ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ጥበቡ ከናንተ ጋር ትሁን፣ ረድኤቱ ከናንተ ጋር ትሁን።        ክርስቶስ እንደ አየር በውስጣችሁም በውጫችሁም ይሁን!
Показать все...
ሁለት ጡረታ የወጡ ሽማግሌዎች ነበሩ፡፡ አንዱ ፓይለት ሌላው ደግሞ መምህር የሆኑ ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ ሁለቱም አንድ ወቅት ላይ ተመሳሳይ ችግኞች በጓሮዋቸው ተከሉ፡፡ ፓይለቱ ለተከለው ችግኝ ያለው እንክብካቤ የተለየ ነበር፡፡ ከመጠን በላይ ይንከባከበዋል፡፡ ውሃ ከመጠን በላይ ያጠጣዋል። ለችግኙ የተለያየ ማዳበሪያ እየገዛ ያደርግለታል፡፡ መምህሩ ደሞ ጠዋት ይነሳና ዉሃ ያጠጣል፡፡ እንደ ፓይለቱ ግን ብዙ እንክብካቤ አያደርግም፡፡ አንድ ቀን ከባድ ዝናብ ጣለ። ሌሊቱን ሙሉ ዘነበ፡፡ ጠዋት ችግኞቻቸውን ለማየት ሁለቱም ወደ ጓሯቸው ሄዱ፡፡ የፓይለቱ መሉ በመሉ ወድሟል፡፡ ተነቃቅሎ ወድቋል፡፡ የመምህሩ ደግሞ በውሃ ከመሞላት ውጪ ምንም አልሆነም፡፡ ፓይለቱ ገረመው፡፡ እንደዛ የተንከባከበው ችግኝ ወድቋል፡፡ ምክንያቱን ለማወቅ በመጓጓት ወደ መምህሩ ሄዶ "አንድ አይነት ችግኝ በተመሳሳይ ጊዜ ተክለን እንደውም እኔ ችግኘን ከአንተ በላይ እየተንከባከብኩት ነበር የቆየሁት። ግን የኔ በዚህ ዝናብ ወደመ፡፡ ያንተ ደግሞ ምንም አልሆነም፡፡ እንዴት??? ለምን???" ብሎ እየተገረመ ጠየቀው፡፡ መምህሩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "አንተ ለችግኝህ የተለየ እንክብካቤ ብዙ ውሃ እና አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ትሰጥ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ችግኙ ውሃና ንጥረነገር ለማግኘት ስራ አይሰራም፡፡ ሁሉንም አንተ ታቀርብለታለህ። እኔ ደግሞ እንዳይደርቅ የተወሰነ ውሃ አጠጣዋለሁ፡፡ ከዚያ በላይ ከፈለገ ስሮቹን (roots) በመጠቀም እንዲፈልግ እተወዋለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት ስሮቹ (roots) ተጨማሪ ውሃና ንጥረ ነገር ፍለጋ ወደ ውስጥ ይገባሉ፡፡ለዚህም ነው የዳነው። ስሮቹ ወደ መሬት በደንብ ስለተቀበሩ፡፡" ይህን ችግኝ ልጅ ያላችሁ እንደ ልጃችሁ፤ ትንሺ እህትና ወንድም ያላችሁ ደግሞ እንዲሁ አንደሆኑ ቁጠሩት። ስታሳድጓቸው እንደ ፓይለቱ ሁሉን ነገር እየሰጣችሁ በራሳቸው እንዳይቆሙ ካደረጋችሁኋቸው፤ በችግር ግዜ ወድቀው ታገኟቸዋላችሁ። እንደ መምህሩ ደግሞ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ እያደረጋችሁ ካሳደጋችኋቸው በመከራ ተከበውም ቢሆን ቆመው ታገኟቸዋላችሁ። ምርጫው የናንተ ነው!
Показать все...
🙏ሰው #ሦስት ወዳጆች አሉት🙏 👆#ትናንት ፦ የተሰኘው ወዳጁ ቀድሞ አብሮት #የነበረ አሁን ግን #የተለየው ወዳጁ ነው። እሱም ባለፈው ህይወቱ #በተሳኩለት ሁኔታዎች ላይ እንዲገነባና ወደሌላ ከፍታ እንዲያልፍ እንዲሁም ደግሞ #ካልተሳኩለት ሁኔታዎች #በመማር ነገ የማይደገምን ስህተት እንዲለይ #ያስተምረዋል። 👇#ዛሬ፦ የተባለው ወዳጁ #አሁን አብሮት ያለውና ከእርሱ #የማይለይ የቅርብ ወዳጁ ነው። ትናንት ከተሰኘው ወዳጁ ጋር ብዙ ሲያሳልፍ ይህ "#ዛሬ" የተባለው ወዳጁ እጅግ #ያዝናል። "ነገ" የተባለው ወዳጁ መጥቶ ቦታውን #ሳይወስድበት ከዚህ ሰው ጋር ማሳለፍ #ይመኛል። ይህ ሰው 👉#ነገ ፦የተባለውን ሶስተኛ ወዳጁን ገና አልተዋወቀውም። "#ትናንት" ያስተማረውን እንደመሳሪያ በመያዝ ከ"#ዛሬ" ጋር ሲያሳልፍ "#ነገ" የተሰኘውን ገና የሚተዋወቀውን ወዳጁን በእንዴት ሁኔታ ሊይዘው እንደሚችል ከማወቅና ከመዘጋጀት ውጪ ስለ "ነገ" #ምንም ማድረግ #አይችልም። #የትናንቱን ሲያስብ #የዛሬውን የሚሰረቅ ሰው አስዛኝ ሰው ነው። ስለ #ነገውም በመጨነቅ ከዛሬው ህይወቱ ጋር #የተለየ ሰውም እንዲሁ። (የማቴዎስ ወንጌል 6:34) " ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ #ለቀኑ #ክፋቱ ይበቃዋል።" " ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ #ነፍስ_ከመብል #ሰውነትም_ከልብስ #አይበልጥምን?" (የማቴዎስ ወንጌል 6:25)
Показать все...
💐 ፍቅርንና የልብን ሚስጥር መረዳት .....በመጀመሪያ ደረጃ አጋፔ ፍጥረታዊ ኬሚካላዊ ወይም ፍልቅ ስሜታዊ አለዚያም ፍልስፍና አይደለም። አጋፔ ስብእና ነው:: 1ዮሐ 4 ፥ 8 እንደሚነግረን እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ብሎ ነው:: አጋፔን ስናውቅ ጽንሰ ሀሣቡን የፈጠረው ማን እንደሆነ እናውቃለን:: ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ አጋፔ ነው፤ እርሱም ፍቅር የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ነው:: 💐ሁለተኛ ፤ አጋፔ አህዳዊነት ነው:: አጋፔን የሚያውቁ ሁሉ በልብም በመንፈስም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ናቸው፤ እርስ በእርሳቸውም አንድ ናቸው:: ቀጥተኛ በሆነ ቋንቋ አጋፔ ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው:: በክርስቶስ ዝቅተኛ ማንነታችንን ወሰደ፤ እርሱን እንድንመስል ያደርገን ዘንድ እኛን ይመስል ተገባው። 💐ሦስተኛ፧ አጋፔ በሌሎች ላይ ያተኮረ እንጂ በራስ ላይ ያተኮረ አይደለም:: አጋፔ ያለምንም ማቋረጥ በመጀመሪያ በሌሎች ሁለተናዊ ደህንነት ላይ ያተኩራል፤ ባለማቋረጥም ለሌሎች መስጠት የሚችልበትን አጋጣሚ ይመለከታል:: እውነተኛ ፍቅር ራሱን አሣልፎ እስካልሰጠ ድረስ ሙሉ አይደለም:: 💐አራተኛ፤ አጋፔ የራስ ተነሳሽነት ነው:: አጋፔ ሃላፊነትን የሚሸከምም ነው:: ሌሎች ቀድመው እንዲንቀሣቀሱ የሚጠብቅ አይደለም:: ሮሜ 5፥ 8 እንዲህ ይላል፤ “ነገር ግን ገና ሀጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል:: አጋፔ ቀድሞ የሚንቀሳቀስ ነው:: ማንም ምላሽ ቢሰጥ ወይም ባይሰጥ አጋፔ ቀድሞ ይንቀሳቀሳል:: ኢየሱስ “ሌሎች ለእናንተ ሊያደርጉላችሁ የምትሹትን እናንተ ደግሞ ለሌሎች አድርጉ” ይላል (ሉቃ 6፥31 አጋፔ የሚያደርገው እንደዚያ ነው፡፡ አጋፔ ቀዳሚውን እንቅስቃሴ ይጀምራል፡፡ 💐በመጨረሻም፧ አጋፔ ምርጫ ነው:: የተመሠረተው በፍልቅ ስሜታችን ላይ ሳይሆን፤ አውቀንና ይሁነኝ ብለን በምንወስነው ውሳኔ ላይ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚነግረን፤ እግዚአብሔር እንደሚወደን እንጂ ለምን እንደወደደን አይደለም:: ለምን የሚል ነገር የለም:: እግዚአብሔር የወደደን ፍቅር በመሆኑና ማፍቀርም ባህሪው ስለሆነ ነው:: እግዚአብሔር እኛን የወደደበት ምክንያት እኛን መውደድ በመፈለጉ ነው:: የእርሱ ፍቅር ማንንም የማይለይና አድሎ የሌለበት ነው:: አጋፔ ማንን መውደድ እንዳለበት አይመርጥም፧ በቀላሉ የሚመርጠው መውደድን ነው:: የሚወደው ነገር ምን መሆኑ ዋጋ የሚሰጠው አይደለም:: ሆን ተብሎ በተወሰነ ውሣኔ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አጋፔ የማይለዋወጥ ነው:: ፍልቀስሜታዊ እንደሆነ ፍቅር አጋፔ የሚለዋወጥ አይደለም:: 💐 አጋፔ በአለም ላይ ብቸኛው እውነተኛ ፍቅር ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ጊዜ “ፍቅር” እያልን ለምንጠራቸው ሁሉ መሠረት ነው:: ፊሊዮ፣ ስትሮጅ ፣ኢሮስ በአግባቡ ከተገነዘብናቸውና በተገቢው ሁኔታ ውስጥ ከተለማመድናቸው ለአጋፔ እውቅና የሚሰጡና ውበትን የሚጨምሩ ናቸው:: ይሁን እንጂ ማናቸውም ሲሆኑ በራሳቸው ትርጉም ያለውና ዘላቂ የሆነ ግንኙነት ለመገንባት በቂ መሠረት ሊሆኑ አይችሉም:: ለዚህ በቂ የሆነው አጋፔ ብቻ ነው:: አጋፔን መረዳት ማለት የሰውን የልብ ሚስጥር ለመረዳት ቁልፍ የሆነ ጉዳይ ነው:: ይህንን ለማድረግ አንጻባራቂ የከበረ ጌጥ የሆነውን የአጋፔን በርካታ እውነታዎች ልንዳስስ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር፣ እኛ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር፣ እኛ ለእራሳችን ያለንን ፍቅርና ለሌሎች በተለይም ለሚስቶቻችንና ለእጮኞቻችን የሚኖረንን ፍቅር ሁሉ ልንመለከት ግድ ነው::
Показать все...
የአሸናፊነት ማማ፦ ይቅርታ ይቅርታ ነጻነት ይሰጣችኋል። ይቅርታን የማይጠይቅና የማይቀበል ሰው የሴጣንን አሰራር እየተከተለ ነው። ለሴጣን እድል አትስጡት። ማህበረሰባችን እልከኛ፥ ትምክህተኛ፥ ትዕቢተኛ እንዲሆን ያደረገው ለይቅርታ ያለው አመለካከት ዝቅተኛ በመሆኑ ነው። በክርስትና ሕይወታችን የተሻለ ነገር ላይ መድረስ ያልቻልነው የይቅርታን ጥቅም ባለመረዳታችን ነው። ይቅርታን የሚያክል ስለ ነገ የተሻለ ኑሮ ቁልፍ ነገር የለም። ይቅርታ የትላንት የስህተት፥ ያለማወቅ ጊዜ በአዲስና በተሻለ ነገ መተካት ማለት ነው። ይቅርታ የበታችነት፥ ሽንፈት አይደለም። ይቅርታ የሕይወት ትክክለኛ መንገድን መምረጥና መከተል፣ ጠላትነትን ማብረድ፥ ሰላምን መመስረት ነው። ይቅርታ ከኋላ ያለውን ጥሎ አዲስን መንገድ ለመገናኘት መዘጋጀት ነው። ይቅርታ የተሻለ ጥበብ የክብር መለኮታዊ መንገድ ነው።      ስህተቱን እያወቀ በግትርነት የሚራመድ ሰው በይቅርታ አዲስ ቀንን ለመፍጠር አልተዘጋጀም ማለት ነው። ሕይወታችን በቀላሉ የሚለወጠው በይቅርታ ውስጥ ስናልፍ ነው። ዘወትር እንደሚያድግ ሰው የምታስብ ከሆነ የትላንትናው እውቀትክ ያለፈ እውቀት ይሆናል። ስለዚህ ትላንትና ሁሉን ኮንነህ በነበርክበት ጊዜ ዛሬ በእድገትህ ውስጥ ልክ እንዳልነበርክ ይገባሃል። ይቅርታ ማድረግ መሸነፍ ሳይሆን ከትላንት የተሻለ እውቀት ላይ መድረስ ነው። ሰፋ አድርገህ አሰብክ ማለት ነው። የይቅርታ ምስጢር ታላቅ ነው። ተሳስቼ ነበር ማለትን ልመዱ። አንደክምም፥ አንታክትም በሰይጣን አንታለልም። ይቅር አለማለት የሰይጣን ምክር ነው። ይቅርታን የማይጠይቅና የማይቀበል ሰው የሰይጣንን አሰራር እየተከተለ ነው። በማንም ላይ አትፍረዱ። ሁሉም በደረሰበት እውቀት ነው የሚመላለሰው ቁምነገሩ በግትርነት አለመመለስ ላይ ነው። በይቅርታ ውስጥ ግን ግትርነት የለም። ይቅር በሉ የሰላምን አየር ተንፍሱ!
Показать все...
#2013 የመልካም ወጣት ስልጠና የምዝገባ ቀናቶች ይፋ ተደርገዋል ....... # የመመዝገቢያ ስልክ ቁጥሮች ... 0462123801 0462123898 0462124387 0462124791 0462124813 0462124875 0462124981 በመደወል ይመዝገቡ Website (ድህረ ገፅ) http://www.melkamwetat.com ይመዝገቡ
Показать все...
"መልካም ወጣት የመሻገር ብስራት 2013" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የመልካም ወጣት ስልጠና ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል።ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች እና የWebsite(ድረገጽ) Link(ማስፈንጠሪያ) በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ። የመመዝገቢያ ስልክ ቁጥሮች ... 0462123801 0462123898 0462124387 0462124791 0462124813 0462124875 0462124981 በመደወል ይመዝገቡ Website (ድህረ ገፅ) http://www.melkamwetat.com ይመዝገቡ @marsilchannel ❇️
Показать все...
መልካም ዜና እንኳን ደስ ያለን! መልካም ወጣት 2013 ምዝገባ ሰኔ 1 ይጀመራል!!!! #share #share #share #melkamwetat2013 @marsilchannel ❇️
Показать все...
ሕይወታችን የምታሣሣ ችግኝ ነች። እግዚአብሔር ራሱ ከሕይወት ውሃ ካላጠጣን ለዘላለሙ ደርቀናል። እርሱ ጥላ ከለላ ካልኾነልን ላለመለምለም ጠውልገናል። እርሱ ካላቆመን ላለመነሣት ወድቀናል። እርሱ ካልሰበሰበን ለዘላለሙ ተበትነናል። ቃሉ እንደሚል፥ “ሰው ዓለሙን ኹሉ ቢያተርፍ፥ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማቴ. 16፥26)። ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለመወደዴ ማስረጃው ከእልፍ አእላፋት ምስክሮች በላይ ገዝፎ ቆሟል። መድኅኔ ፍቅሩን ለመግለጥ በመስቀል ላይ በደሙ ቀለም ጽፎ ደብዳቤውን (ክቡር እሱነቱን) በችንካር ላይ ለጥፎታል (1ዮሐ. 3፥16)። ዓለሙን የወደደው ቸሩ እግዚአብሔር የአልማዝ ፈርጥ ሳይኾን ሕይወቱን በልጁ ሰጠን። ሰው በዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚድነው ዘላለምነት በኢየሱስ ሕይወት ልክ የሚገኝ ስለ ኾነ ነው። የኢየሱስን ሕይወት በማያኽል ማንኛውም ነገር መዳን ያልተቻለው ለዚህ ነው።
Показать все...
የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ! . ቡሌሆራ, እንጅባራ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የደረሳችሁ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ወደ ጊቢ ስትመጡ እንድንቀበላችሁና በምያስፈልጋችሁ ነገር እንድናግዛችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ስልክ ቁጥሮች ደዉሉልን። Bule hora university Fellowship Leaders:- 0920097944 ቃል 0932189067 አራርሳ 0960256615 ዋሴ 0935093348 ኪያ 0943364234 በርኒ 0978868090 ቤኪ (EvaSUEsaff) Injibara Univeristy Fellowship leaders:- 0906211320 0989102233 (Tselot) 0976041226 (Media) 0951024732 (Rahel) 0929139768 0966714846 0941916852 (Mamush) 0954667502 (Marta) 0953617966 (Gulilat) 0979818609 (Biruk) 0964885913 (Adane) 0901334885 (Sam) Wollaga University Fellowship Leaders:- +251911870627 Menge +251902782728 Amanuel +251923149163 Tigist +251960926449 Melese +251922789569 Abdisa +251910232627 Gedion . የፌሎሽፑ senior ተማሪዎች አዳዲስ ተማሪዎች ወደ ጊቢ በሚገቡ ጊዜ ተገቢውን ድጋፍ ስጡአቸው፤ ይህን ጽሁፍ ለሌሎች በማጋራት ይተባበሩን ተባረኩ። @christ_zene @christanzenabo
Показать все...
ምንም ሳታጠፋ እንደ ጥፋተኛ እምንት ሳትሳሳት እንደ ስህተተኛ፣ በብላሽ ክንዳቸው አንተን ብይዙህም አስረው ቢገርፋህም፣ የጤፍ ፍሬ ተሀል ትንሽዬ ስህተት ፍፁም የለብህም! አልነበረብህምም! ነገም አይኖርህም !!! ምክንያቱም .... አንተ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለህም!!!!!!!!!! ደግሞም ቢያንገላቱህ ቢያዳፋህ ቢያቃኑህ ዝምም ብትላቸው ስለ ድንቅ ትህትናህ፣ ጦሯቸውን መዘው አጉል ቢኮፈሱም ሀይል ባንተ እጅ እንጂ በነሱ አይደለችም !!!!! **** አየ ክፋታቸው! አየ እርግማናቸው! አየ ጥፋታቸው! ከአምላካቸው ላይ እጅ መሰንዘራቸው። አየ ቆፎ መሆን.... ወሰን ያጣ ድፍረት ውል የለሽ ቅልነት "የዓለም ፈውስ ነኝ" ብለህ ስትላቸው እምቢ ማለታቸው። *** ዳሩ ግን እንዲህ ነው... ሀሰተኛ ብለው አንተን ቢገርፉህም አንተ እውነት እንጂ ሀሰት አይደለህም፤ አንተ ፀዳል እንጂ ከል አይደለህም!!!!!! "ይሰቀል ይሰቀል" ብለው ቢሰቅሉህም ቢቸነክሩህም ኮሶ ቢያጠጡህም ደግሞ .................ቢቀብሩህም ድል ይነሳል እንጂ ሞት ድል አይነሳህም!!! ምክንያቱም.... አንተ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለህም!!!! አዎ!!! እዉነቱን እንዲህ ነው... ከዓለም በፊት ቅድመዓለም በመዋዕለ አለም ግዜዓለም ከዓለምም በኋላ ድህረዓለም ኃይል ያንተ እንጂ... የማንም አይደለም!!!!! ጌታ ሆይ ክበር ተመስገን!!! አሜን!!!! / #ከምናባዊ_ፀዳል/ ተፃፈ 2011 ዓ.ም ደሴ
Показать все...
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌺 መልካም 🌺🌻 🌻🌻 በዓል! 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻💐💐💐🌻🌻 🌻🌺 እንኳን 🌺🌻 🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻 🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
Показать все...
DEM.mp32.08 MB
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏 በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ 🙏✝😍✝😍
Показать все...
Alamirew_Eyasu_ፋሲካዬ_Fasikaye_አላምረዉ_ኢያሱ_New_Ethiopian_Go_low.mp34.43 MB
የማያለፍየለምRingtone.mp36.22 KB
ዘማሪጳውሎስRingtone.mp39.94 KB
#እንዳለ_ወልደጎርጊስ ማን ተወኝ ማን ተቀየር እያልኩኝ ዛዝን መኖሬ አብቅቷል ልቤ በርትቷል ጌታ ኢየሱስ ስላለ ጎኔ የማንም ፊት እንደ ቀድም ባይሆን ከእኔ ጋ ሀሴት ከእኔ ጋር ነው መሽቶ ሲነጋ @One_way_He @One_way_He @The_grace_bot @The_grace_bot
Показать все...
ነብሴን_የሚያረካት_Pastor_Endale_Woldegiorgis_Official_Video_2020256k.mp321.23 MB
    የማይጠገብ ብፌ      " እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። መዝሙረ ዳዊት 34 : 8       ካልቀመስናቸው ጣዕማቸውን ልናውቃቸው የማንችላቸው ነገሮች ብዙ አሉ። አንድን ነገር ጣዕሙን ለማወቅ መቅመስ የተፈጥሮ ህግ ነው። የማርን መጣፈጥ ለማወቅ የሬትን መምረር መቅመስ ያስፈልጋል። ኃጢአትን፣ በደልን፣ ክፋትን፣ አመንዝራነትን፣ ዘፋኝነትን ያወቅነው ሰይጣንን ቀምሰነው ነው። አዎ ሰይጣን የሚቀመስ ነው ጣዕሙ ግን እንደ ሬት መራራ ነው።       እግዚአብሔር የሚቀመስ አምላክ ነው። አንድን ነገር በመመኘት ብቻ ጣዕሙን ልናውቀው አንችልም። ሰዎች ቀምሰው ሲያጣጥሙት አይተን እኛ ልንረካ አንችልም። እግዚአብሔርን ልንቀምሰው ይገባል። ጣዕሙ ከማር በላይ ጣፋጭ ነው።        የእግዚአብሔር ጣዕም የማያልቅ ብፌ ሆኖ ዘወትር በፊታችን የቀረበ ነው። ፍቅሩ፣ ምህረቱ፣ ቸርነቱ፣ መልካምነቱ፣ ይቅርታው፣ በጎነቱ፣ ፈውሱ፣ በረከቱ ሁሉ በፊታችን የተንጣለለ ገበታ ነው።         ወዳጆቼ የትኛውም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል የማይሰጠን የተሰናዳ ብፌ እግዚአብሔር ነው። ሰው የሚወደውን ምግብ ነው መርጦ ከብፌ የሚያነሳው ነገር ግን ወዶ ባነሳው ምግብ ሊታመም ይችላል። እንዴት? ካልከኝ ዝሙትን ፈፅሞ ሰው በኃጢአት በሽታ ይታመማል፤ ሰው ገድሎ በፀፀት ቁስል ይመታል ምክንያቱም ከሰይጣን ብፌ መርጦ ያነሳው በመሆኑ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ተጓዳኝ ችግር በሽታ የሌለበት የዘላለም ምግባችን ነው። ምህረቱን ዕለት ዕለት ባንቀምሰው መች የዛሬ ሰው እንባል ነበር? ምህረቱ የመቆማችን ምስጢር ነው። ፍቅሩ ከአራዊትነት የለየን ሰዎችንም ራሳችንንም ወደን እንድንኖር ያደረገን የህይወት ቁልፍ ነው። ቸርነቱ እንደኛ ብኩንነት በአንድ ቀን የምንጠፋውን ደግፎ ያቆመ ምርኩዛችን ነው። ይቅርታው የእንደገና እድል የሚሰጠን መሀሪያችን ነው።     ወዳጆቼ ህይወት የመረረባችሁ ጣዕሙ የጠፋባችሁ፤ መድከማችሁ ፍሬ አልባ የሆነባችሁ፤ ተግባራችሁ ውሉ የጠፋባችሁ፤ እርካታ ከህይወታችሁ የተሟጠጠባችሁ፤ ደስታ የራቃችሁ ሁላችሁ እግዚአብሔርን ቅመሱት ህይወታችሁ ትጣፍጥላችሁ፤ ወደ ማዕዱ ቅረቡ ተቋደሱት ነፍሳችሁ ትማረክላችሁ። ከእግዚአብሔር መፆም አንችልም ፆም የለውም። በማለዳም በቀትርም፤ በምሽትም በሌሊትም የምንመገበው የሰላማችን ብፌ ነው።     አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፦        ስለበዛልን ምህረትህ፣ ስለበዛልን ማዳንህ፣ ስለበዛልን ትድግናህ፣ ስለበዛልን ባርኮትህ፣ ስለበዛልን ቸርነትህ፣ ስለበዛልን ፍቅርህ፣ ስለበዛልን ጥበቃህ ተመስገን። የማትጎድል መሶባችን ሆነህ አጥግበኸናል፤ የማታልቅ ወይናችን ሆነህ ተጎንጭተንኻል ስለዚህም ተመስገን። ስለማይጠልቅብን መልካምነትህ በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናመሰግንሀለን።                
Показать все...
ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡ ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??” ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል...የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ” የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡ የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል " እናም እግዚአብሔርን እንጠብቅ በጊዜው ውብ አድርጎ ይሰራዋል የተናገራችሁን ፣ የገባላችሁን ኪዳን አካል ለብሶ እስክታዩ ድረስ የእግዚአብሔርን ጊዜ ጠብቁ።
Показать все...
SELOMON 0916558591 3.mp36.84 MB
19/07/2013 🔷 እርግማንን መስበር 🔷 #በሐዋርያው ዳንኤል ጌታቸው የእርግማን ውጤት የታወቀ ነው ክፉና ሞት ነው የተለያዩ የመርገም መናፍስትዎች አሉ ከእነዚህ ውስጥ 🔥🔥"የእግዚአብሔርን ስራ በቸለልተኝነት አትስራ" የእግዚአብሔርን ቤት መርዳት እየቻልህ አለመርዳት መሳፍንት 5:23 -24 መሣፍንት 5 (Judges) 23፤ የእግዚአብሔር መልአክ፡— ሜሮዝን እርገሙ፤ እግዚአብሔርን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምናየተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ፡ አለ። 24፤ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔልከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን፤ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን። #⃣የእግዚአብሔርን ቤት መርዳት መልካም ነው ። #⃣አንተ ለቤትህ ማድረግ የምታስበውን ለእግዚአብሔር ቤት ታደርጋለህን ? #⃣ቤተክርስቲያን እንደ ቢዝነስ ተቋም የምትታይበት ጊዜና አስተሳሰብ ውስጥ ነን ንቃ? #⃣እግዚአብሔርን መርዳት እስካልቻልክ ድረስ ለውጥህ እዚህው ነው ። #⃣የእግዚአብሔርን ቤት እርዳ ውጤቱን ታየዋለህ 🔥🔥ጠንቋይ ወይም ሟርተኛ እናት አባት ካለህ እንዳትረዳ ትያዛህ #⃣እንዳልሞት ብለህ የእግዚአብሔርን ቤት አሳንሰህ ለጠንቋይ ቤት የምትረዳና ተገዥ የሆንክ ወንድሜ እመነኝ የእርግማኑ ተካፋይ ነህ ። #⃣በህይወት ዘመንህ ደሃን አትግፋ ። እግዚአብሔርን የምትፈራ ከሆነ ደሃን አትንካ #⃣ደሃን መንካት ስትጀምር ውድቀትህ ይጀምራል #⃣ለደሃው ኃይልን ትሰጥ ዘንድ እንጅ ትገፈው አልተፈቀደም ። ምሳሌ 28:27 ምሳሌ 28 (Proverbs) 27፤ ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፤ ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል። #⃣የአንዳንድ ሰዎች ውድቀትና ጥፋት ከደሃ ጋር ይያያዛል ። #⃣በረከትህ ያለው ከደሃ ጋር ነው ። #⃣ደሃ ከናቅህ እርጉም ነው የምትሆነው ። #⃣በብሉ ኪዳን መጽሐፍ ደሃን መናቅ እና መግፋት እርግማን ከሆነ በአዲስ ኪዳን እንዴት አብልጦ ከብዶብህ አይታይህም ። ኢሳይያስ 24 (Isaiah) 3፤ ምድር መፈታትን ትፈታለች፥ ፈጽማም ትበላሻላች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና። 4፤ ምድርም አለቀሰች ረገፈችም፤ ዓለም ደከመች ረገፈችም፤ የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ። 5፤ ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች፥ ሕጉን ተላልፈዋልና፥ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፥ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። 6፤ ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች በእርስዋም የተቀመጡ ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ። Do u believe ምን አይነት መርገም ነው? #⃣መርገም ማለት በደለኛ ነህ ማለት አይደለም መርገም ማለት የምትሰራውና የምታስበው አለመሳካት ማለት ነው ። #⃣መንፈሳዊ አለም ስትመጣ በህይወትህ በረከት ከብዶብህ ይታይሀል ። ንቃ ንቃ ባለመታዘዝህ ጥፋትህን ስበር ይብቃ ምህረት ይደረግልኝ ይቅርታ ጥፋተኛ ነኝ ቸርነትህ ህይወቴን ያግኝ ጉብኝት ይሁንልኝ ከጥፋት መንገድ መልሰኝ አሜን ተፈፀመ ተፈፀመ ተፈፀመ
Показать все...
ውስጥን መስማት በህይወት መንገድ ስንሄድ ወደ እኛ ብዙ ድምጾች ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ መሆን ወደምንፈልገው የምመሩን ሳይሆን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩን ድምጾች ናቸው፡፡ ብዙዎቻችን መሆን የሚንፈልገው ሌላ ነው፡፡ አሁን ሆነን ያለነው ደግሞ መሆን ከምንፈልገው ጋር የተቃረነ ነው፡፡ የዚህ መንስኤ ደግሞ ውስጣችን የሚለውን ለመስማት እራሶቻችንን ለማዘጋጀት አለመብቃታችን በዋናነት ይጠቀሳል ፡፡ እራስን መስማት ወደ ትክክለኛ መንገድ የሚመራን መሳሪያ ነው፡፡ አሸናፊና ስኬታማ ለመሆን፣ መሆን የሚንፈልገውን በጓደኛ፣ በቤሰብ፣ በዘመድ መምረጥ ሳይሆን ውስጥን ከሰሙ በኃላ መምረጡ የሚመከር ነው፡፡ የዛን አሸናፍዎችና ስከታማዎች እንሆናለን፡፡ በዙርያህ ከሚጮሁ መንገድ አሳች ጩኸቶች ፈቀቅ ብለህ እራስህን በመስማት መሆንና መድረስ የሚገባህን በመምረጥ የአሸናፊነትንና የስኬታማነትን ኃይል ተላበስ፡፡
Показать все...
የልዑል መጠጊያ #በክርስቶስ "በልዑል መጠጊያ #የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።" (መዝ 90:1) ~የልዑል መጠጊያ ያለው የት ነው? የልዑል መጠጊያ፣ እኛ በክርስቶስ ያለንበት ቦታ ነው። በክርስቶስ መሆን፣ እጅግ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመደበቂያ ሥፍራ መሆን ነው። ~ግን ሰው በክርስቶስ ወደመሆን የሚመጣው እንዴት ነው? መልሱ፣ ጌታ ኢየሱስን እንደግል ጌታና አዳኝ አድርጎ በመቀበል ነው! ሰው አንድ ጊዜ በክርስቶስ ካመነና ዳግም ከተወለደ በኋላ እግዚአብሔር አብ ሰውየውን የሚያየው በክርስቶስ ነው። እንግዲያውስ አንተ ደኅንነትህ የተጠበቀ፣ በጥበቃ ስር ያለህና በመደበቂያ ሥፍራ ውስጥ #በአስተማማኝ_ሁኔታ_ውስጥ ያለህ ሰው ነህ። ~በዚያ የጥፋት ውሃ ጊዜ፣ ኖኅ በመርከቧ ውስጥ እንዴት ደኅነነቱ እንደተጠበቀ እስኪ ጥቂት እናስታውስ። ኖኅ ፍፁም ባይሆንም፣ እግዚአብሔር ግን በእርሱ ላይ እምነት ያለው መሆኑን ስላወቀ ጻድቅ አድርጎ ቆጠረው። (ዕብ 11:7) ~የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ከመርከቧ ውጪ የነበሩት ሁሉ ሲሞቱ፣ ኖኅና ቤተሰቡ ግን ተደብቀውና ድነው ነበር። ለምን? ምክንያቱም የክርስቶስ እና #የደኅንነታችን_ምሳሌ በሆነው በመርከቡ ውስጥ ስለነበረ ነው። (ሐዋ 4:12) ~በጣም የሚገርመው መርከቧ ከጣራዋ አጠገብ ብቻ እንጂ #ከጎንና_ከጎኗ መስኮት አልነበረባትም። ለምን? እግዚአብሔር በዙሪያህና በዓለም ውስጥ ባለው ጨለማና ሽብር ላይ ትኩረት እንድታደርግ ስላልፈለገ ነው። እርሱ የሚፈልገው፣ ወደ ላይ ብቻ እንድትመለከትና ልጁ ተመልሶ እንደሚመጣ እንድታውቅ ነው! ~ሌላም ነገር አለ፤ መቼም ማዕበሉ መርከቧን ከወዲያና ወዲህ ሲያላጋት፣ ኖኅ ሚዛኑን አጥቶ የወደቀበት ጊዜ ይኖራል። የምሥራች! ሲወድቅ ግን #መርከቧ_ውስጥ እንጂ #ከመርከቧ_ውጪ አይደለም !!! ~በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዛሬ ዲያብሎስ ዓለምን በተለያየ ነገር ከወዲያ ወዲህ ቢያላጋትም፣ አንተ ግን በክርስቶስ ካለህ ቦታ #ውጪ አይደለህም!!! በክርስቶስ ውስጥ ነህ!!! ~አሁንም #መርከባችን_በሆነው #በክርስቶስ ውስጥ ስለሆንን፣ የእርሱን የጥበቃውን በረከት በፍጹም አናጣውም!!!
Показать все...