cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Saxxx Bcha ✍✍✍

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
152
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
Ye 03 Azgochu😜😜😜

Armazon

እንደምን ከረማችሁልኝማ?? ተጠፋፋንኣ?? ከጀርባዬ የተቀመጡ ባልና ሚስት ወይም ፍቅረኛሞች እሷ :- ይሄኛው አይሻልም? እሱ:- ይሄ ብዙ ኪሎ ሜትር ተነድቷል:: ሌላ ምረጪ... (አንድ የሆነ ያገለገለ መኪና የሚገዛበት ሳይት ውስጥ መኪና ሊገዛላት ይመስለኛል እየመረጡ ነው::) እሷ:- እሺ የቱ ይሁን? እሱ:- ደስ ያለሽን... "ደስ ያለሽን" ይላታል እንጂኮ ያሳይችውን ሁሉ በሆነ ሰበብ ይጥልባታል:: .. ተወደደ... ቀለሙ ደስ አይልም.... መልሶ ደግሞ "ደስ ያለሽን" ... ይላታል .... የሆነ ካፌ ምናምን ተቀምጣችሁ የሚቀጥለው ወንበር ላይ ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ልቅም አድርጋችሁ ከመስማታችሁ የተነሳ ከእነርሱ ጋር የመጣችሁ ምናምን ወይም የምታውቋቸው ነገር መስሏችሁ አያውቅም?? ዞር ብዬ "አንቺ አይገባሽም እንዴ በቃ ብሩ የሚቀንሰውን ምረጪ !" ልላት ሁላ ምንም አልቀረኝም:: መዓት ካሳየችው በኃላ የሆነኛውን "አዎ ይሄ አሪፍ ነው!! ይሄን እንገዛለን" ሲላት ወሬውን በጣም ከመሳተፌ የተነሳ "እስኪ እስኪ??" ልል ነበር🤣🤣🤣🤣 ውብ ምሽት ውብኛ አመሻሽ አምሹልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ መጥቻለሁ ለማለት ነው::meri fkr
Показать все...
መምሰል 👣 በሆነ ወቅት እግዚአብሄርን መምሰል መሻቴ ነበረ ከዛም ባለፈ እርሱን ለመምሰል ብዙ መንገድ ተጉዤ አልቻልኩም አቃተኝ።😭 በሆነ አጋጣሚም ላይም ደግሞ በተቃራኒው ሰይጣንን🌚 መምሰል ፈልጌ እሱንም መምሰል ሳልችል ቀረሁ። ስለዚህ ሁለቱንም መሆን ስላልቻልኩ እራሴን መስዬ ቁጭ ብያለሁ።💀✳🙄😑 ግን ምን እመስላለሁ ? ሰዎችዬ አስተውሉ (መምሰል እንጂ መሆን አላልኩም) °-° ((አልቻልኩም እንጂ አይቻልም አላልኩም።))-% ምንም ያልከው ሀሳብ አልገባኝም 🙄 ይገርማል ሆሆሆ 😅 ተረድቼሀለሁ ለማለት የፈለከው ገብቶኛል። ✋ ✍abel
Показать все...
~~የአዞ እንባ ~~(ሳሙኤል አዳነ) ባልበሰለ አይምሮ ሀገር ልናቆስል ፣ ከራስ ጋር ተጣልተን ብሄር እንገምዳለን አዋቂ ይመስል ። . እምነት አለኝ የሚል መፆም ያላቃተው ፣ መነው ይችን ሀገር ካለችበት ፍዳ መታደግ አቃተዉ ። . ለካስ ውሸት ኖሯል ያዞ ነው እንባችን ፣ ከይቅርታ ጀርባ ከሳሽ ነው ልባችን ። ፀሎት መፃፍ ይዘን ጦር አለ በጃችን ። የይምሰል ለቅሷችን ግፍ እየቋጠረ ፣ ዞሮ እሚያቃጥለን አሲድ ሆኖ ቀረ ። . እባክህ አምላኬ ፅድቁም ይቅርና በቅጡ ኮንነን ፣ የአንድናት ልጆች ተባልተን እንዳናልቅ አስታራቂ ሆነን ። @one love abyssiniya
Показать все...
🍃አእምሯችን ልክ እንደ ሰውነታችን ነው ሰውነታችን ለመጠንከርና ለማደግ ምግብ እንደሚፈልግ ሁሉ አእምሯችንም በየቀኑ እና በየሰዓቱ እውቀትን ይሻል። ያልበላ ሰውነት በየቀኑ እንደሚቀጭጭ ሁሉ አእምሮም እውቀትን ባጣ ቁጥር የማመዛዘን ብቃቱ ይቀንሳል። @Ashebariw
Показать все...
🍃በገንዘብ ብቃት ማደግ በገንዘብ ብቃት ማደግ ማለት ገንዘብን የማግኘትና በሚገባ የመጠቀም ብቃትን ማዳበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ከገንዘብ ውጪ ብዙም እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማትችል እወቅ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብን ለማግኘት መሞከር እንደ ክፋት ይቆጥሩታል፡፡ በሃብታችን ከራሳችን አልፈን ለሌላው የሚጠቅም ዓላማ ውስጥ እስከገባን ድረስ ብልጽግና ውስጥ ለመግባት ማቀድም ሆነ ጠንክሮ መስራት ጤናማ ነው፡፡ መበልጸግ መፈለጋችንም ሆነ መበልጸጋችን ችግር የለበትም፤ መታሰብ ያለበት ለመበልጸግ የፈለግንበት መነሻ ሃሳብና ያገኘነውን ሃብት የምንጠቀምበት ጉዳይ ነው፡፡ በገንዘብ ብቃት ለማደግ የሚከተሉትን እውነታዎች መለማመድ ትችላለህ፡- 1. እውቀትን ማሻሻል መጠየቅ ያለብኝ ጥያቄ፣ “የገንዘብ ገቢ የማግኛና ገቢዬንም የማሻሻያ እውቀት አለኝ?” በብቃት ሳላድግ በገንዘብ ማደግ አልችልም፡፡ ስለዚህም፣ በእውቀትና በሙያ የማድግበትን መንገድ ማመቻቸት አለብኝ፡፡ 2. የእቅድ ሰው መሆን መጠየቅ ያለብኝ ጥያቄ፣ “በእጄ ያለውን ገንዘብ የመጠቀሚያ የበጀት እቅድ አለኝ?”፡፡ ገንዘብ በእጅ ማስገባት አንድ ነገር ነው፣ ያንን ገንዘብ በተገቢው መንገድ ተገቢው ነገር ላይ ማዋል ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡ ገንዘብ አያያዝን ይጠይቃል፡፡ 3. ጤናማ መሆን መጠየቅ ያለብኝ ጥያቄ፣ “ገንዘብን አስመልክቶ ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነት ጤናማ ነው?” ሃብትና ገንዘብ ተከማችቶ የቤተሰብ ግንኙነቴም ሆነ ማሕበራዊ ኑሮዬ የተበላሸ እንዳይሆን ጥንቃቄን ማድረግ ጠቃ ነው፡፡ @Ashebariw
Показать все...
እነጌታቸው ረዳ ሊጥ መስረቃቸውን ስትሰማ ለዛ ነው እንጀራ 20ብር የገባችው 😆😂🤣
Показать все...
ታገል ሰይፉ የተማረ ይግደለኝ ! Abel
Показать все...
📖ወንዶች ተሰልፈው እግዜር ጋር ቀረቡና ቅሬታቸውን አቀረቡ.... 😝😄😝😄😝😄 ✍በአሌክስ አብርሃም . . . ‹‹ እኛ ለፍተን ጥረን ግረን ላባችንን ደማችንን ጠብ አድርገን ባመጣነው ገንዘብ ሴቶቻችን እቤት ተጎልተው ይበላሉ ይጠጣሉ ...ይለብሳሉ ይዋባሉ...ሶፋ ላይ እየተንፈላሰሱ ፊልም ያያሉ !! እኛ በስፒል እንደተወጋ ፊኛ እየሞሸሽን እነሱ ዝናብ እንደጠገበ ዱባ ይደነድናሉ ....በቃን እነሱን መሸከም .....›› አሉ፡፡ እግዜር ታዲያ ምን ይደረግላችሁ ሲል ጠየቀ ....ወንዶቹ ቀጠሉ ‹‹ጌታ ሆይ ድፍረት አይሁኑብና ከአሁን ጀምሮ ቦታ እንቀያየር እነሱ የእኛን ቦታ ይውሰዱ እኛ የእነርሱን ቦታ እንውሰድ ››እግዜር ‹‹ከመጭው ሰኞ ጀምሮ ቦታ እንድትቀያየሩ ወስኛለሁ››... አለ ፡፡ ወንዶች በደስታ ፈነደቁ! ሰኞ.... ሚስቱ የባሏን ጎን ደቃችውና ‹‹የስራ ሰአት እየደረሰ ተጋድማሃል ተነስ ቁርስ ስራ ›› ወንዱ ደንግጦ ተነሳና ወደመፀዳጃ ቤት ሂዶ ሽንቱን ሊሸና ሲል ነገሩ ሁሉ ተቀያይሯል ፡፡ቀስ ብሎ ተቀመጠና ሸና፡፡ ኩሽና ገብቶ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረ ‹‹ እንዲህ ነበር የምቀሰቅሳት ለካ› እያለ፡፡ እንደምንም ቁርስ ሰርቶ አቀራረበ ሚስት ተነስታ ሸሚዜን ተኩስ ጫማየንም ወልውል ቁርስ እስከምበላ›› አለችና ቁርሱን መብላት ጀመረች ...‹‹ኤጭ ምንድነው ይሄ ሁሉ ጨው ምላስ የለህም አትቀምስም ›› ብላ በብስጭት ሳህኑን ወርውራው ልብሰዋን ለባብሳ ቦርሳዋን አንስታ ወጣች ፡፡ቁርስ የተበላበትን ሰሃን ለማጠብ አልጋ ለማንጠፍና ቤት ለመጥረግ ሲንደፋደፍ የመሳ ሰአት ደርሶ ሚስት ከተፍ አለች ምሳ የለም! ብስጭት ብላ ‹‹ እዚህ ተጎልተህ ቴሌቪዥን ላይ ስጣፈጥ በየጎረቤቱ እየዞክ ወሬ ስታወራ ምሳ ሳተሰራ ሰአቱ ሄደ ምናይነት ድድብና ነው ›› አበደች ባል ተሸማቀቀ ራት ሰአት ላይ ሚስት ስትመለስ አንድ ሁለት ብላ ሞቅ ብለዋት ነበር የመጣችው ....ባል ድክም ብሎት ወገቡ ተንቀጥቅጦ መተኛት አምሮት ‹‹ እስቲ ቆንጆ ቡና አፍላ›› አለችው ...እንደምንም አፈላ ›› ቡና ተጠጥቶ እንደተኙ ምንድነው ሽንኩርት ሽንኩርት የምትሸተው ተነስና ታጠብ ›› አዘዘች ሚስት.... ባል ማልቀስ እየፈለገ ተነስቶ ታጠበ....ልክ ጋደም ከማለቱ ሚስት ትነካካው ጀመረ! ምንም ነገር አላማረውም ድካሙ ...እንቅልፍ ብቻ ነበር የፈለገው ...በየት አስተኝታው! ጭራሽ ሲነጫነጭ ‹‹ ምነው ሌላ ትዳር አማረህ ዙር እባክህ እግርህን ክፈት....›› ሂሳቡን!! ሌሊት 3 ጊዜ ....ጠዋት እንደገና ተነስቶ ቁርስ ስራ.....እየተማረረ ....ማክሰኞ ጠዋት ሰውየው እግዜር ጋር ሲሄድ ሌሎች ብዙ ወንዶች ቀድመውት ደርሰው ነበር ....እግዜር ጠየቀ ‹‹ደግሞ ዛሬ ምን ሆናችሁ‹‹ አይ ባለፈው የተየቅነው ነገር በስህተት ነው ወደቦታችን እንመለስ ሚስቶቻችንም ባል መሆናቸው ይቅርና ወደሚስትነታቸው ይመለሱ›› እግዜር ‹‹ጥሩ ሌሊት ሚስቶቻችሁ ጋር ግንኙነት ፈፅማችኋል ››ሲል ጠየቀ ...ወንዶች- ‹‹አወ በጣም ያስመርራል ለካ......›› ሲሉ መለሱ፡፡ እግዜር ‹‹ እንግዲያውስ ሁላችሁም በፈፀማችሁት ግንኙነት ስለፀነሳችሁ ወደወንድነታችሁ ለመመለስ ዘጠኝ ወር ጠብቁ›› ጨርሻለሁ!! 😝😜😜😜😄😄 @abel
Показать все...