cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2) Ignorance of the law is no excuse. civil code article 2035(2) ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም [email protected] ይላኩልን።

Больше
Рекламные посты
2 581
Подписчики
+324 часа
+67 дней
+4530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የገንዘብ ሚኒስቴር የደመወዝ ገቢ ግብር ለማሻሻል ጥናት መጀመሩ ታወቀ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ በደመወዝ ገቢ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ ለማሻሻል የገንዘብ ሚኒስቴር ጥናት መጀመሩ ታወቀ፡፡ ማንኛውም ተቀጣሪ የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ600 ብር በላይ ከሆነ አሥር በመቶ የደመወዝ ገቢ ግብር የሚከፍል ሲሆን፣ ከአሥር ሺሕ ብር በላይ ገቢ ያለው ተቀጣሪ ደግሞ 35 በመቶ የግብር ምጣኔ ይጣልበታል፡፡ ይህ የደመወዝ ግብር ምጣኔ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጫና እየፈጠረባቸው በመሆኑ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ https://www.ethiopianreporter.com/130806/?sfnsn=mo&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR0N4gxIUZJO1XCV3Ip9LVfIM79fGyxjJM8iXmhNEQOpI8wP8HaF2YbGr40_aem_kLLsxujrpnlV6FWervIW4g&sfnsn=mo
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595 #ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak አለሕግ #Alehig 👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👉Telegram👈 https://t.me/lawsocieties 👉Facebook Page 👈 https://www.facebook.com/lawsocieties/ 👉YouTube 👈 https://youtube.com/@Ale_Hig 👉Website 👈 http://alehig.wordpress.com
Показать все...
የገንዘብ ሚኒስቴር የደመወዝ ገቢ ግብር ለማሻሻል ጥናት መጀመሩ ታወቀ - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best And Reliable News Source In Ethiopia

ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ በደመወዝ ገቢ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ ለማሻሻል የገንዘብ ሚኒስቴር ጥናት መጀመሩ ታወቀ፡፡

Показать все...
አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሞዴል ውል.pdf2.62 KB
የንብረትማስመለስ ረቂቅ አዋጅ.pdf https://t.me/ethiolawtips
Показать все...
የንብረትማስመለስ ረቂቅ አዋጅ.pdf3.71 MB
Показать все...
አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሞዴል ውል.pdf2.62 KB
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
የአዋጁ አስፈላጊነት 👇👇👇👇👇👇👇 በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል። • የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ከአንድ ክፍል ጀምሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የተከራየና ገንዘብ የሚከፈልበትን ማንኛውም ቤት ላይ ሲሆን በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ • ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በወረዳ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት፡፡ የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። የአከራይ እና ተከራይ ውሉን ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሁሉም ወረዳዎች ፅ/ቤቱ የማረጋገጥና የመመዝገብ ስራውን ጀምሯል፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አከራይና ተከራይ በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል እስከ ሶስት ወር የሚደርስ በውሉ ላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ያስቀጣል፡፡ ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የኪራይ ውል ካልሆነ በስተቀር የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ የኪራይ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። በዚህ የውል ዘመን ውስጥ ተከራይን ከቤት ማስወጣትም ሆነ በአዋጁ ከሚፈቀደው አግባብ ውጭ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም፡፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ አዲስ የሚወጣ የቤት ኪራይ ዋጋ አሁን ላይ የለም። አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ በአመት አንድ ጊዜ በሰኔ ወር ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ብቻ ነው። አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል። ነገር ግን አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከስድስት ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ 1. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ 2. ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት 3. የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች 1. የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ 2. ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣ 3. ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣ 4. የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ 5. በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈፅም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀምበት ከሆነ፣ 6. አስቦ ወይም በቸልተኝነት በቤቱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት ከተፈጠረ ተከራይ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቤቱን እንዲለቅ በህግ ሊገደድ ይችላል። በውል ምዝገባ ወቅት ስለሚቀርቡ ሰነዶች ማንኛውም አከራይ እና ተከራይ ለምዝገባ ሲቀርብ ፡- 1. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሰነድ፤ 2. የአከራይና ተከራይ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ተመጣጣኝ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ (የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ሕጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ) 3. አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ በማንኛውም ምክንያት የተሻሻለ ውል በ30 ቀናት መመዝገብና መረጋገጥ አለበት፡፡ የተከለከሉ ተግባራት እና ጥቆማ የሚቀርብባቸው ጉዳዮች 1. የተመዘገበ ውል ሳይኖር የመኖሪያ ቤት ማከራየት፤ 2. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየትና ማከራየት ወይም በአዋጁ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዝገብ፤ 3. በተመዘገው ውል ላይ ከተቀመጠው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በላይ ክፍያ መፈጸም 4. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ወይም ከ2 ወር በላይ የቅድመ ክፍያ እንዲፈጸም ማስገደድ፤      5. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የቤት ኪራይ ዘመን ውል ማቋረጥ፤ 6. በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀም ሀሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ፤ 7. መኖሪያ ቤቱ ከመኖሪያነት ዓላማ ውጪ አገልግሎት ወይም ለወንጀል መፈጻሚያነት ወይም ለወንጀል ተግባር ላይ እየዋለ ከሆነ፤ 8. አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ከቤት ማስወጣት፤ 9. በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂ ጊዜ ሳይሰጥ ውል ማቋረጥ፤ 10. በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈጸም፤ 11. ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ መኖሪያ ቤት ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ፤ ስለ ቁጥጥር ጽህፈት ቤቱ ቁጥጥር የሚያደርገው ለቁጥጥር በተመደበ ባለሙያ ይሆናል፤ ተቆጣጣሪ ባለሙያው በመንግሥት የሥራ ሰዓት ተቆጣጣሪ መሆኑን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የቁጥጥር ተግባሩን ይፈጽማል፤ የቁጥጥር ሥራ የሚከናወነው በተናጠል በአንድ ባለሙያ ሳይሆን በቡድን ከአንድ በላይ ተቆጣጣሪዎች በመሆን ነው፡፡ #አለሕግ #Alehig @NegereHig https://t.me/NegereHig
Показать все...
ነገረሕግ NegereHig

About laws Ethiopia.......ስለ ኢትዮጵያ ህግጋት.... ስለህጎችና ህግ ጉዳዮች ብቻ.......የህግ ነገሮችን It is All About Laws....Only Law Matters...... It is about law. ስለህጎች....... ጠበቃና የህግ አማካሪ ቢሮ አዲስ አበባ @AboutLaws_bot

  ስለኪራይ ውል ------------------------- የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት እንደወሰነው "የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የሌለ በመሆኑ በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚፀና ውል ህጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1719(1),-1930,2898(3) በማጣቀስ በቅፅ 7 በመቁ 25938 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ⚖♦️እንዲሁም ደግሞ ከኪራይ ቤቶች አስተዳደር ጋር የተደረገን የኪራይ ውል መሠረት በማድረግ የተያዘ ቤትን ያለአከራይ ፍቃድ ለሌላ ወገን ማስተላለፍ ለኪራይ ውሉ መሠረዝ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ በቅፅ 7 በመ/ቁ 24221 ላይ አስገደዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። #ethiolawtips
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌍 UNDP is offering a Business and Human Rights Internship! Apply by June 2024 to gain hands-on experience in promoting ethical business practices globally. https://lnkd.in/d95rVfvp #Internship #UNDP #BusinessAndHumanRights #CareerOpportunity 🌐
Показать все...
Показать все...
ለሕዝብ ጥቅም ክስን ማንሳት?

#በሰለሞን እምሩ ክሱን ማንሳት ለሕዝብ ጥቅም ይበጃል ለማለት ከተቀመጡት ዘጠኝ መሰፈርቶች መካከል አንዱ “ተከሳሹ በዕድሜ መጃጀት ወይም በማይድን በሽታ ወይም በአዕምሮ ልልነት ምክንያት ጉዳዩን መከታተል የማይችል እንደሆነ ነው” ተብሎ በመመሪያው አንቀፅ 5 (3) ላይ ተመልክቷል፡፡ አንድ ተከሳ…

Фото недоступноПоказать в Telegram
ሟችን የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት ከሟች መኖሪያ ቤት በመግባት አፏን በጨርቅ ጠቅጥቆ፣ አንገቷን አንቆ በመያዝ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት አላዩ ሞገስ ደሳለኝ የተባለ ተከሳሽ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት በመግባት በጥፊ በመምታት፣ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባትና አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ/620/2/ሀ/ እና /3/ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ (ፍትህ ሚኒስቴር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) አንዳንድ መረጃዎች 1. የመሳሪያው አቅራቢ መሳሪያውን ከውጪ ማስገባትና አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት እውቅና ከሚኒስቴሩ ሊያገኝ ይገባል፡፡ 2. መሳሪያው ብልሽት ቢያጋጥመውና ተጠቃሚው የመሳሪያውን እሽግ ሳይሰብር ሊያስተካክለው የማይችል ከሆነ በመሳሪያው መጠቀሙን ወዲያውኑ አቋርጦ ብልሽቱ ያጋጠመበትን ጊዜ በምርመራ መዝገቡ ላይ መመዝገብና በ2 ሰአት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ለአገልግሎት ማእከሉ በስልክ ማስታወቅ አለበት፡፡ ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/u0obhb https://t.me/AboutJustices @AboutJustices
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.