cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

✝💒የቅዱስ ሚካኤል የበረከት ስራ ማህበር ስብከቶች ኪነ ጥበብ ምክር አበው መዝሙሮች ዝክረ ቅዱሳን ሁሉም አሉ አብረን እንማማር💒✝

https:t.me/joinchat/kine tibeb@21

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
145
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ጠ አባት) 4.ቅዱስ ሰብስትያኖስ ሰማዕት 5.ቅዱስ አስኪላ ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት 2.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ 3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 4.አቡነ አቢብ 5.አባ አቡፋና ††† "የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . " ††† (ዕብ. 11:35) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Показать все...
†✝† እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል ††† ††† ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው:: ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር:: አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር:: እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል:: እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው:: "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት:: ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ:: አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው:: ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ:: ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ:: በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው:: እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ:: በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት:: በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ:: ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቋቋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት:: እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም:: ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ:: በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው:: "ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው:: ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:- "አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም:: እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም:: አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት:: ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል:: እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል:: ሰማዕቱ በዚህች ዕለት : በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖችን ያሰቃይና ይገድል የነበረውን ዑልያኖስን ያጠፋበት መታሠቢያ ይከበራል:: የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው! ††† አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: ቸሩ እግዚአብሔር እድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍሥሃ አይንሳን:: ††† ጥር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ 2.ቅዱሳን ባስልዮስና ጎርጎርዮስ 3.ብፁዕ አባ ዼጥሮስ ጽሙድ (ለምጽዋት ራሱን የሸ
Показать все...
. "" እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ . . . "" (መዝ. ፻፳፮:፩) (ዝክረ ቅዱስ ዳዊት ዘወርኃ ጥር) (ጥር 23-2012) ✝ _በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ_ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Показать все...
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ.m4a29.63 MB
†✝† እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ††† ††† ልደት ††† ††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል:: በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል:: ††† ዕድገት ††† የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል:: ††† መጠራት ††† አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ:: የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ:: ††† አገልግሎት ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት:: 1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል:: 2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር:: ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል:: ††† ገዳማዊ ሕይወት ††† ††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል:: እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል:: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል:: ††† ስድስት ክንፍ ††† ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: ከወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:- *በቤተ መቅደስ ብስራቱን *በቤተ ልሔም ልደቱን *በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን *በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን *በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር:: የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ:: በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው:: ††† በዚያም:- *የብርሃን ዐይን ተቀብለው *6 ክንፍ አብቅለው *የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው *ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው *ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው *ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው *"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል:: ††† ተአምራት ††† የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው:: *ሙት አንስተዋል *ድውያንን ፈውሰዋል *አጋንንትን አሳደዋል *እሳትን ጨብጠዋል *በክንፍ በረዋል *ደመናን ዙፋን አድርገዋል:: ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና:: ††† ዕረፍት ††† ††† ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው: መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል:: ††† በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሠበሩንና በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስባለች:: ††† ጥር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅድስት ማርያ ግብጻዊት 3.ታላቁ አባ ቢፋ 4.አባ አብሳዲ ቀሲስ 5.ቅዱሳን ጻድቃነ ሐውዚን ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ ዘዮሐንስ (ዘክብራን ገብርኤል-ጣና) 2.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ 3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ 4.ቅዱስ ሙሴ ጸሊም 5.ቅዱስ አጋቢጦስ 6.ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማይ ††† "በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (፪ቆሮ ፲፩፥፳፫) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Показать все...
✝ንስሐ እንዴት መግባት እንችላለን?✝ ክፍል ፮(6) ✝የንስሐ በረከቶች ✝መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝ http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn
Показать все...
''የንስሐ በረከቶች''.mp310.94 MB
✝ገድላትን ሰለማሳተም የተላለፈ መልእክት✝ ✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ ወንድማችን ገብረ ስላሴ ሰላም ኦርቶዶክሳውያን እኅት ወንድሞቼ! እንደምን ዋላችሁ አደራችሁ። ከዚህ በፊት በዝርዝር በገለጥንላችሁ መሠረት ትናንት ጥር 21 ቀን ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ጋር ተነጋግረን ሁሉንም ዝግጅት ጨርሰናል። ዲዮርዳኖስ የሚኖረው ጎንደር ስለሆነ ሁለታችንም አብረን ነገሮችን በአካል እየተገናኘን ማስኬድ ባንችልም በስልክ እያወራን እየተመካከርን ነው የምንሠራው። እርሱም በራሱ ጉባኤና በማኅበራዊ ገጾቹ ጉዳዩን ይነግራችኋል፤ ዝግጅታችንን ጨርሰን አገልግሎቱን ጀምረናል። በዚህም መሠረት፦ 1ኛ. ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆነንን የባንክ አካውንት በጋራ ከፍተናል። 2ኛ. ለመጀመሪያ ጊዜ የማንን ቅዱስ (የየትኛውን ጻድቅ) ገድል እንደምናሳትም ተነጋግረን መርጠናል። (ፈተና እንዳይሆን ለጊዜ ስማቸውን አንናገርም።) 3ኛ. የትርጉምና የጽሕፈት ሥራውን የሚሠሩልን አንድ የቤተክርስቲያናችን መተርጉም አነጋግረን ተስማምተን ጨርሰናል። 4ኛ. አሜሪካ የሚኖሩ ወንድሞቻችን ገድላቱን ከየገዳማቱ ቀድተን የምናመጣበትን ዘመናዊ መሣሪያ (scanner) ልከውልን ተረክበናል። በመሆኑም ገዳማትን ገድላቸውን ስጡን ብለን አናስቸግርም፣ ገድሉ ከእነርሱው ጋር እንዳለ "ስካን" አድርገን ወስደን አሳትመን መልሰን ለገዳማቱ እናስረክባለን። ስለዚህ ለዚህ ገድላትን ለማሳተም ፕሮጄክት አገልግሎት ብቻ የሚውል በጋራ የከፈትነው የባንክ አካውንቱንና የ swift code ቁጥሩን መጨረሻ ላይ ታገኙታላችሁ። የማኅበራችን ስም በዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ አመላካችነት "አባ በፍኑትዮስ ገድላት አሳታሚዎች ማኅበር" ብለነዋል። ይኸውም አባ በፍኑትዮስ በገድል ተጠምዶ የኖረ ሲሆን በኋላም እግዚአብሔር ወደ በረሓ ሔዶ የቅዱሳንን ገድል ከራሳቸው ከቅዱሳኑ እየጠየቀ እንዲጽፍ ያዘዘው ነው፤ እርሱም በታዘዘው መሠረት በየበረሓው እየዞረ የገዳማውያን አባቶችን ገድል ለመጻፍ ብዙ የደከመ ስለቅዱሳንም ብዙ ምሥጢራትን ያወቀ ነው። በገድል ከመጠመዱ የተነሣ ጥቂት የሰሌን ፍሬዎችን ብቻ እየተመገበ የሰውን ፊት ሳያይ 60 ዓመት በበረሃ ውስጥ የኖረውን የታላቁን ጻድቅ የአቡነ አቡናፍርን እና የሌሎቹንም ቅዱሳን ገድላቸውን የጻፈልን ታላቅ አባት ነው-አባ በፍኑትዮስ። የማኅበራችንን ስም ያደረግነው በዚህ ምክንያት ነው። በማኅበር ስም የባንክ አካውንት ለመክፈት ባንኮች የራሳቸውን ሕግና ደንብ አላቸው። ማኅበሩ የተቋቋመበትን የጋራ መተዳደሪያውን ጨምሮ ከቤተክህነት እና ከፍትሕ ሚኒስቴር ደብዳቤ ማምጣት አለብን። ያንን ለማድረግ ደግሞ ወራቶቾ ከመፍጀቻቸውም በላይ በእኛ ቤት ውስጥ ያለውን ፈተና ታውቁታላችሁ። አገልግሎቱ በራሱ ብዙ ፈተናዎች ያሉት ስለሆነ ያንን ያህል እዩኝ እዩኝ እያልን ይህን ልንሠራ ነው እያልን በአደባባይ እያወራን እኛም ራሳችንን ለፈተና ማጋለጥ የለብንም። ቤተክህነቱ በተቋም ደረጃ ሥራውን መሥራት ከቻለ ወደፊት እኛም ሥራውን አሳልፈን እንሰጣቸዋለን። ከዚያ በረፈ ግን "በእኛ በኩል ካልሆነ..." በሚል ፈሊጥና በሌላም በብዙ ምክንያቶች ይህን ገድላትን የማሳተም አገልግሎት ለማስተጓጐል የሚፈልጉ እንዳሉ እርግጥ ነው። ስለዚህ ባንክ የሚሠሩ ኦርቶዶክሳውያን እኅት ወንድሞችን ስናማክር የሰጡን አስተያየት "...ፈቃድ ምናምን እያላችሁ ራሳችሁን አላስፈላጊ ፈተና ውስጥ ከምትከቱ ቀጥታ ወደ ሥራው ግቡ፤ ሥራችሁን አብሯችሁ መሥራት ከሚችል ሰው ጋር ሆናችሁ ሥራው ላይ አተኩሩ በኋላ ላይ ሥራችሁ ሲታይ ያንጊዜ የፈቃዱን ነገር በቀላሉ መጨረስ ትችላላችሁ... የሚል ነው። እንዲሁም "ባንኩ በማኅበር ስም አካውንት ለመክፈት ብዙ መስፈርቶች ስላሉት ለጊዜው በጋራ የሚንቀሳቀስ (joint account) ከፍታችሁ ሥራችሁን ጀምሩ" የሚል ምክር ስለሰጡን በዚሁ ተስማማን። ነገር ግን ዲያቆን ዮርዳኖስና እኔ የተለየ ቦታ (አ.አ እና ጎንደር) ስለምንገኝ በጋራ የምናንቀሳቅሰው አካውንት (joint account) ሊኖረን ስለማይችል ከዲዮርዳኖስ ጋር ተማክረን እዚህ አ.አ የሚኖረውን ወንድማችንን ዲያቆን መልአኩን ወክሎታል። ዲ/ን መላኩ ጎንደር ተምሮ የመጣ አርክቴክቸር ሲሆን የዲ/ን ዮርዳኖስ ተማሪና ደቀ መዝሙር ስለሆነ አሁን ላይ በራሱ ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ጀምሮ እያስተማረ ያለ ወንድማችን ነው። የአባ እንጦንስንም ገድል በቅርቡ ተርጎሞ አሳትሟል። ስለዚህ በጋራ የሚንቀሳቀስ (joint account) የተከፈተው በእኔና ዮርዲ በወከለው በዲ/ን መላኩ ይፍሩ ስም ነው። ገድል የሚተረጉሙት አባትም ሆኑ ማተሚያ ቤቱ አ.አ ስለሚገኙ ይህን ማድረጉ ግዴታ ሆኖብናል። ነገር ግን የአካውንቱን እያንዳንዷን ወጪና ገቢ፣ ቀሪውም ስንት እንደሆነ ደብተሩን ፎቶ እያነሣን እዚሁ የቴሌግራም ግሩፑ ላይ ስለምንለጥፈው ምንም የሰውን ሕሊና በጥርጣሬ የሚያባክን ነገር ፈጽሞ የለም። ገድላቱን ለማሳተም እኛ በጋራ እናንቀሳቅሰው እንጂ የአካውንቱ ባለቤት እናንተው የዚህ ግሩፕ አባላት ናችሁ። በመቶ ብር አካውንቱን ስለከፈትነው በፎቶው ላይ በምትመለከቱት መልኩ እያንዳንዷን ገቢና ወጪ በየቀኑ ፎቶ እያነሣን (ከሞባይል ባንክም screenshot) እያደረግን ሁሉንም ነገር በግልጽ እንድታውቁትና እንድታዩት ይደረጋል። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቡን መርሐ ግብር ስለጀመርን ሁላችንም የአቅማችንን ያህል እንረባረብ። ፩. Account Name፡ mikyas woldemedhin & melaku yifru ፪. Account Number፡ 1000374445476 ፫. Swift code፡ CBETETAA የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምላከ ቅዱሳን የጀመርነውን መልካም አገልግሎት ያስፈጽመን ዘንድ ጸልዩ። እመብርሃን ወላዲተ አምላክ፣ ቅዱሳኑ ኹላቸው በምልጃቸው ይርዱን። (በነገራችን ላይ ገዳማትን ለመሳለም እና ለዚሁ ለገድላት ማሳተም ፕሮጄክት አገልግሎት ከነገ ሰኞ ጀምሮ ለ8 ቀናት ያህል ወደተለያዩ ገጠር ወደሚገኙ ገዳማት እሄዳለሁ።)
Показать все...
✝እንኳን አደረሳችሁ::✝ "" የእመቤታችን ዕረፍት/ ዕረፍተ ሶልያና "" 👉(ጥር 21 - 2013) ✝በመምህር ዲ/ዮርዳኖስአበበ ✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝ " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/zikirekdusn '
Показать все...
ዕረፍተ ሶልያና.m4a67.91 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.