cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ያህዌህ ንሲ(እግዚአብሔር ዓላማዬ )✟

እንሆ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆነ አንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው ። መዝ 122÷1 ➕ይህ የጃራ ደ/ፀ/ቅ/ሚካኤል ፍኖተ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ቻናል ነው ። በዚህ ቻናል የሰትቤቱ ወቅታዊ መረጃዎች ትምህርቶች መዝሙሮችና የመሳሰሉት ስራዎች ይለቀቃሉ ።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
162
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

📖📖📖📖📖 ስለ ጸሎት የቅዱሳን አባቶች ብሒል 📜📜📜 << ጸሎት ገንዘብ ሊያስገኝ ይችላል ፤ ገንዘብ ግን ጸሎትን ሊያመጣ አይችልም >> 📜📜📜 <<ጸሎት የኛን ፍቃድ ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር አስማምተን የምንመራበት ነው >>[ ቅዱስ ኤፍሬም] 📜📜📜 << ጸሎት የትካዜና የውስጣዊ ኀዘን ማስረሻ ነው >>[አባ ኔላስ] 📜📜📜 << ጸሎት በሃይማኖት ፈጣሪውን እያመሰገነና ስርየተ ኀጥያትን እየለመነ ከፈጣሪው ጋር የሚነጋገርበት ቃል ነው>> [ፍትሕ መንፈሳዊ] 📜📜📜 <<በጸሎት ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ተጫወት ፣ ተነጋገር ልጅ ከአባቱ እንዲጫወት >> 📜📜📜 የልብ ጸሎትን በአንድ ወይም በሁለት ለቀናት ወስጥ ገንዘብ ማድረግ አይቻልም ጠላት ተወግዶ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን እስኪያድር ድረስ ያለውን እረጅም ጊዜ ይወስዳል [ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ] 📜📜📜 <<ያለ ጸሎት ከሚፈጸም አገልግሎት ይልቅ ያለ አገልግሎት የሚፈጸም ጸሎት ይሻላል>> [አቡነ ሺኖዳ ] 📜📜📜 <<ሌሊትስ እግዚአብሔርን ለማመስገን የተፈጠረ ሰዐት ነው>> [ ብጹሕ አቡነ ይስሐቅ ] 📜📜📜 <<የቂመኛ ሰው ጸሎት በጪንጫ ላይ እንደተዘራ ዘር ነው >> 📜📜📜 << ፈጣሪዪ መከራዪን ድንቁርናዪን አርቅልኝ ብለህ ለምን፣ ጸልይ ። ያን ጊዜ ልቡናኽ መዓልቱንም ሌሊቱንም በፍቅረ እግዚአብሔር ይቃጠላል >> [ ማር ይስሐቅ ] ቻናላችንን ይቀላቀሉ
Показать все...
❤️ 2
🙏
ብጹ አቡነ ሺኖዳ ብዙ ሺህ ህዝብ በተገኙበት ጉባኤ እያስተማሩ እያሉ ከግብፅ ገጠራማ ቦታ የመጣ አንድ ዲያቆን ጥያቄ በወረቀት ጽፎ ላከ፡፡በአካባቢያቸው በአክራሪዎች ብዙ ክርስቲያኖች እንደሚገደሉ እና መፍትሔ እንዲሠጣቸው ነበር የጠየቀው፡፡ ሺኖዳም ከአስር ሺህ ለማያንሱ ተማሪዎቻቸው እንዲህ ሲሉ ጠየቁ # ኢየሱስ ክርስቶስን ትወዱታላችሁ ? ህዝቡም ለ3 ደቂቃ ያህል በእልልታ አጨበጨበ፡፡ ምን ጥያቄ አለው ብለው መመለሳቸው ነበር፡፡ ጳጳሱም ሌላ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ # አብራችሁት ትሞታላችሁ ? በዚህን ጊዜ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሱ፡፡ለረዥም ደቂቃዎች አጨበጨቡ፡፡ # ያመኑት ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለመሞት እንደሆነ አረጋገጡ፡፡ # ይህ ነው ጥሪያችን ! #ይህ ነው ክርስትና! ትንሣኤ ያለ ሞት የታለ? ••••••ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንድንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? ሮሜ 6÷3 ቅድስነታቸው አቡነ ሺኖዳ በረከታቸው ይደርብን from ኑ በብርሃኑ እንመላለስ
Показать все...
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
Показать все...
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም
Показать все...
✥ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን ! ✥ በፍቅር ተስቦ የወረደው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ፍፃሜ በመስቀል ላይ ገልፆልን ሀያል ጌታ በመሆኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ! ✥ ረድኤት በረከቱ በእያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ! ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💚 •✥• •✥•💚 💛 •✥• •✥•💛 ❤️ •✥• •✥•❤
Показать все...
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡ በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡ በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡ መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡ ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡ መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡ ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡ በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡ ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት! ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት! [መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም! ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ? ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ! ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ! ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ! ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች! ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች! ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показать все...
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ #ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
Показать все...