cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

፩ማኋደረ ስብሓት ቅድስት ልደታ ለማርያም፩

፩አቤቱ ደግ ሰው አልቁኀልና አድነኝ።መዝ ፲፩። ፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩ ፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
151
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ዓመታዊ የተዓምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

ቸርነት ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† "በዛቲ ዕለት #እግዚአብሔር ገብረ: በእደ ባስልዮስ መንክረ::" (በዚህች ዕለት እግዚአብሔር በባስልዮስ እጅ ድንቅን አደረገ) ††† ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ††† ††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ #አርእስተ_ሊቃውንት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ነው:: አባቱ #ኤስድሮስ(ባስልዮስ የሚሉ አሉ): እናቱ ደግሞ #ኤሚሊያ ይባላሉ:: ባልና ሚስት ከተቀደሰ ትዳራቸው 5 ወንድና 1 ሴት ልጅን አፍርተዋል:: የሚገርመው ሴቷ ( #ቅድስት_ማቅሪና) ገዳማዊት ስትሆን 5ቱም ወንዶች ዻዻሳት መሆናቸው ነው:: የሁሉ የበላይ የሆነው ግን ቅዱስ ባስልዮስ ነው:: አባቶቻችን እንዳስተማሩን ቅዱሱ ሊቅ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ነው:: #ቅዱስ_ኤፍሬም ሶርያዊንም ያስተማረው እርሱ ነው:: ነገር ግን ቅርብ ጊዜ ከድረ ገጾች (websites) እየገለበጡ የሚጽፉ…

*አንብቡት*👇 "ሰይጣን ቤተክርስቲያን ሄድሽ አልሄድሽ አይጨንቀውም፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ፡፡ ቀጥለውም፡ "መጽሐፍ ቅዱስም አነበብሽ አላነበብሽ ሰይጣን አይከፋውም፡፡" አሉ "ታዲያ ሰይጣን የሚጨንቀው እና የሚከፋው መቼ ነው?" ስትል ጠየቀች ሳያት፡፡ "ቤቴክርስቲያን ሄደሽ የሰማሽውን እና መጽሐፍ ቅዱስ አንብበሽ የተረዳሽውን ነገር መኖር ስትጀምሪ ሰይጣን አብዝቶ ይከፋል፡፡" አሉ፡፡ "ልጄ ዋናው ነገር መኖር ነው፡፡ያወቅሽውን ካልኖርሽ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፡፡የህይወትሽ ቤት አሸዋ ላይ የተገነባ ነው፡፡መኖር ስትጀምሪ ግን በማይናወጥ አለት ላይ የተገነባ ህይወት ይኖርሻል፡፡ለመኖር ደግሞ በጀመርያ ፈጣሪሺን ከልብ ማክበርና ማፍቀር አለብሽ፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ ደግሞ፡፡ "ችግሩ የዘመኑ ወጣቶች የአምላክን ፍቅር አታውቁም፡፡ልባችሁን የሞላው አለማዊ ነገር ብቻ ነው፡፡" ሲሏት የቆሙት እማሆይ፡ "ቆይ የፈጣሪ ፍቅር ምን ይመስላል?" ብላ ጠየቀቻቸው፡፡ "ይሄውልሽ ልጄ ሰው የሚሰጥሽ ፍቅር ወቅታዊ ነው፡፡ገንዘብ፣ ዝና፣ ውበት፣ ሀብት፣ እውቀትም ሆነ ሁሉም የአለም ነገሮች ከንቱ ናቸው፡፡አላፊ እና ጠፊ ናቸው፡፡አንድ የማያልፍ ነገር የፈጣሪ ፍቅር ብቻ፡፡ፈጣሪ ራሱ ደሞ ፍቅር ነው፡፡ስትቀምሺው በቃ ነፍስሽ እረፍት ታደርጋለች፡፡ከእሱ ውጪ ምንም አያምርሽም፡፡ልብሽ ቅልጥ ትላለች፡፡" አሉ የተቀመጡት እማሆይ፡፡ "ይገርማል!. ....ታድላችኋል!" አለች ሳያት አቀርቅራ፡፡ "አንቺም እኮ ታድለሻል!" ሲሉ የቆሞት እማሆይ መለሱላት፡፡ካቀረቀረችበት ቀና ብላ፡ "ምንድን ነው የታደልኩት?" ስትል ጠየቀቻቸው፡፡ "ውበት ነዋ፡፡በጣም ውብ እና ቆንጆ ልጅ ነሽ፡፡" "ታዲያ ምን ያደርጋለ አላፊ እና ጠፊ ነው አላላችሁም!" "ቢሆንም እስኪጠፋ ድረስ በተሰጠሽ ጸጋ የማይጠፋ ስራ መከወን አለብሽ፡፡እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው የተለያየ ጸጋ ስጥቷል፡፡ለሙሴ ህግ ለሰለሞን ጥበብ፣ ለዕዮብ ትዕግስት፣ ለጳውሎስ መልዕክ፣ ለማርያም ቅድስና እንደሰጠው ለእኛም የሰጠን ጸጋ አለው፡፡እግዚአብሔር ቁንጅና፣ ስልጣን፣ እውቀት፣ ምንኩስና፣ ድምጽ ወዘተ ነገር ሲሰጠን በአላማ ነው፡፡" አሉ የተቀመጡት እናት፡፡ "አላማው ምንድን ነው?" አሁንም ጠየቀች ሳያት፡፡ "አላማው በተሰጠን ጸጋ ማገልገል ነው፡፡ሰዎችን መርዳት እና በመልካም ስራችን የፈጣሪ ብርሃን በእኛ ውስጥ እንዲያበራ ማድረግ ነው፡፡አለምን የተሻለች ቦታ ማድረግ ነው፡፡በጎ ስራችንን ሰዎች ተመልክተው ፈጣሪን እንዲያመሰግኑ ማድረግ ነው፡፡" አሉ እማሆይ፡፡ "ብዙ ሰው ግን እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ ይጠፋበታል፡፡አብዝቶ በዛ እየተመካ ይሰነካከላል፡፡ይወድቃል፡፡አንቺ እንዴት ነሽ? በቁንጅናሽ ምን እያደረግሽ ነው? " ተጠየቀች ሳያት፡፡ "እንዳላችሁት ባይሆንም በተቻለኝ መጠን በምሰራው ስራ ሰዎችን ለማነቃቃት እጥራለው፡፡በተለይ የአገሬ ሴቶች የተሻለ ቦታ ደርሰው የማየት ጉጉት አለኝ፡፡" ስትል መለሰች፡፡ "አይዞሽ ልጄ፡፡ጉጉት ካለሽ መንፈስ ቅዱስ ያሳካልሻል፡፡ባንቺ ውስጥ አልፎ የልብሽን መሻት ይፈጽማል፡፡ዋናው ነገር ያለው ልብ ላይ ነው፡፡እሱ ከጸዳ ሌላው ቀላል ነው፡፡" አሉ የቆሙት እማሆይ፡፡ "መጠንቀቅ ያለብሽ ደስታሽን አለማዊ ነገር ላይ እንዳይሆን ነው፡፡ሁላችንም በዚህ ምድር ለኮንትራት ህይወት የመጣን ነን፡፡ቀናችን ሲደርስ እንሄዳለን፡፡እስከዛ ግን ራሳችንን ለዘለዓለማዊው ህይወት ማሰናዳት ይገባናል፡፡እሱም ከምንም ነገር በፊት ፈጣሪን አስቀድሞ መኖር ነው፡፡በሙሉ አእምሮ፣ አንደበት፣ መንፈስና ጉልበታችን ፈጣሪን ካፈቀርን የምድር ህይወት አይከብደንም፡፡እንዲሁም ወደ መንፈሳዊው አለም የምንወጣበት ቆንጆ መሠላል ይሆናል፡፡" ሲሉ አጽናኗት የተቀመጡት እማሆይ፡፡ሳያት ከጠበቀችው በላይ እጅግ በጣም የከበረ መረጃ ስላገኘች ፊቷም ልቧም ሳቀ፡፡ከተቀመጠችበት ተነስታ እቅፍ አድርጋ ሳመቻቸው፡፡ጨዋታቸው ሲያልቅም ተለያዩ፡፡
Показать все...