cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሳሙኤል አለሙ-Samuel alemu

ሌላ መገኛዬ... facebook.com/samialemu

Больше
Рекламные посты
305
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
-130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#በማርያም_በኩል.. ( ሳሙኤል አለሙ) |-| |-| ከላይ-- ከሰማይ ከታች-- ከምድር መንገድ ጠበበ --ለመገናኘት-- ባንዲት እንኳ ድር። |-| |-| በምን ይቋጠር በምን ይገመድ ማላው አይ'ፈፀም! መሬቱ ሳይታረስ በሬው ሳይጠመድ። |-| |-| ፈቅዳ ለቀንበር ፈቅዳ ለሞትበር ባንድ ልጇ መሰላል ሆነች እንዳንሰበር። @Samuelalemuu
Показать все...
👍 2
ጥለሽኝ ልውደቅ ከክብሬ ልልቀቅ ደብዛዬ ይጥፋ ደግሜ አልጽደቅ። ጀግና ይበሉሽ ይበሉኝ ሰነፍ ከድል እኩል ነው ባንቺ መሸነፍ ። @getem @getem @paappii By Hab Hd
Показать все...
👍 2
አለሁ እንደ ሾላው (በእውቀቱ ስዩም) በገዛ ጆሮና ፥ በገዛ አይኖችሽ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለሽ ከቶ እንደምን አለሽ? አለሁ እንደ ሾላው እንደ ወፍ መነሻው እንደ ወፍ መሸሻው ጸሐይ እየሞቀ ከመተንፈስ በቀር፤ ሌላ እንደማይሻው፤ መኖር ብቻ ሲሆን ፥ የሰው ልጅ እቅዱ በሲኦልም ቢኖርም፥ አይቀርም መልመዱ እኔም ከመበላት፥ መብላት ይሻል ብየ’ ‘ፍሪደም ‘ ቢርቀኝ፥ ፍሪዳየን ጥየ ነጻነት ቢርበኝ፥ እየበላሁ እህል አለሁ ይህን ያህል ፡ ፡ ( ከ"የማለዳ ድባብ " የተወሰደ) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19   
Показать все...
👍 1
ሚበርዳቸው ይመስለኛል ወንዙ ሀይቁ ውቅያኖሱ አራዊቱ ለምለም ዛፉ በኔ በኩል በእቅፍሽ ካልታቀፉ። ሚበርዳቸው ይመስለኛል ታሪክና ትንቢታችን አሁንና ትላንታችን ጊዜ ስፍራ ግራቀኙ ደስታው ዋየይታው መኖር መሞት ማግኘት ማጣት ሚበርዳቸው ይመስለኛል ካልነካሁሽ ካልነካሽኝ በፍቅር ጣት ለምን? በደምሽ ውስጥ በደሜ ውስጥ ሁሉም ነገር አለው ቅንጣት። ቅዝቃዜሽ፣ የኔ መብረድ ሲተላለፍ ሲቆላለፍ ከሚመጣው ከሚሄደው ከሚወጣው ከሚወርደው ነይ እቀፊኝ ነይ ልቀፍሽ ብሎ ብሎ እግዜራችን እንዳይበርደው። ትንሽ መሻት ጥቂት ናፍቆት አንጠልጥለው ነፍስ አጠገብ ካልተገኙ ቆፈን አለ እሳት አቅፈው እየተኙ። [ ያዴል ትዕዛዙ ]
Показать все...
👍 1
_ ሌላ መንገድ _ [ እንደ_ደጋ ቆሎ በኑግ እንደታሸው እንደ_ጀግና ሂወት ቶሎ እንደሚመሸው እንደ_ስለት ግልገል ፈፋ ተባ ሲሉት እንደሚሟሽሸው ጠቆረ ጊዚያቱ ሻከረ ወራቱ ምኑንም ምኑንም እያግበሰበሰ ሊኮል ነው ሲሉት ጎሼ ደፈረሰ እቴ ነይ እንግዲህ ሰጥቸሽ ሰጥተሽኝ ተካፍለን ለማደር ካይኖችሽ ካይኖቼ እንባ እንበዳደር እቴ ነይ እንግዲህ እንስቃለን ብለን ጥርስሽን ፍቀሽው ጥርሴን ተወቅሬ የወይራ ማሟጫ ከጉንጬ ሰንቅሬ እስከመቼ ድረስ ደስታን እየጠበቅን ከወቅት እንታገል ተሸርፎ ተሸርፎ አለቀ አደለምወይ እድሜ'ያችን እንደገል እቴ ነይ ዝምብለሽ ካለው እንስማማ ርሃብ ጥማችንን በሳቅ እንድንገፋው በባዶው እንቦርቅ በመልካ በፈፋው አዚሚልኝ ዘፈን ሂወት የዳበሰው ምጣድ ቃል ንገሪኝ መኖር የዳሰሰው ምናቤን ዘርግቼ በፍም የተለካ ላቀብልሽ ግጥም 'ላለም እንናገር እንባን ወዶ መኖር እንዴት እንደሚጥም እቴ ነይ ዝምብለሽ እንዲህ ባለ ጊዜ ተስፋ ሆኖ ሲቀር የሂወትን ጀምበር በሳቅ ማገባደድ ሽክረትን ነው ማፍቀር መከራን ነው መውደድ [ አማረ ዘውዱ ]
Показать все...
እግዜር ያለልምዱ እዚህ በረሃ ላይ ዶፍ ዝናቡን ጣለ ፍጥረት ታዛ ቢያጣ ከደመናው ግርጌ ሄዶ ተጠለለ። ለዚህ ምድረ በዳ እንግዳ ነው ዝናብ ደልቶት ተራመደ ብቻ በመንገዱ አንዷን ምስኪን ፅጌ ጎርፍ ጠርጓት ሄደ። እና ማን ግድ አለው? ሁሉም ዝም ሁሉም ጭጭ! ዝናቡ ዶፍ ቢያወርድ ዝናቡ ቢያባራ እግሮቹ ስር ሳለች አይተዋወቅም ካንዲት ጽጌ ጋራ። ደመና ስር ሆኖ አበባ አለማወቅ ሰማይ ስር ተገኝቶ ሕይወት አለማድመቅ ተረሳስቶ መኖር አንዳችን ላንዳችን እንደሆንን ባዳ ቅጣቱን ሲጀምር በገዛ ቤታችን አረገን እንግዳ። [ ያዴል ትዕዛዙ ]
Показать все...
ስውር ጩኸት አለኝ እኔው አምቧርቄ እኔው የማደምጠው ሽሽግ ምጥም አለኝ ጠርቅሜ ደጃፌን በሌት የማምጠው . እሰየው ይሁነው አይከፋኝ! ምን ላተርፍ ከዕድሌ አጋፋኝ? እጣ ነው ፈንታ ነው አልሸሸው! ሲሸሽ ነው ስንቱ ላይ የመሸው! . እስከመቼ ሽሽት በቃ ልጋፈጠው ብሮጥ ከራሴ እንጂ ከእድሌ አላመልጠው! [ ዮናታን ጌታቸው ] @yourpoim @yourpoim
Показать все...
👍 2
#ረድኤት_አሰፋ Rediet Aseffa ደሊላ ያኮረፈችኝ “ትጠላኝ ነበር!” ያለችኝ ማልቀሷ መነፋረቋ ድክመቴን ባለማወቋ፤ ጉልበቴን መደባበቄ ኩታዬን አለማውለቄ ጭኗ ላይ አለመውደቄ ቀበቶ አለመፍታቴ አቅፌያት አለመሞቴ ነበረ ለካ… ጥፋቴ። “እንተኛ!” አለችኝ ደሊላ ዓይኖቿን ብርሃን ተኩላ ስለት ያዥ የሙት መላኳን በነጭ ቀሚስ ከልላ “እንተኛ!” አለችኝ ደሊላ… ራሴን ክጄ እስካምናት እወዳት ነበር እንደእናት “እሺ” አልኳት ልቤን ሳይበርደኝ ግን አምላክ ቢያዝን ቢወደኝ እንቅልፍም አላስወሰደኝ ተኝቼም አላሳረደኝ። ባምናትም አልሞትኩምና አኮረፈችኝ ደሊላ በፍቅር ቃሏ ድለላ “ለምንድን አልተጋደምክም… ?” “ለምንድን አልሞትክም?” ብላ… ጭኖቿ ላይ ስላልተኛሁ እንቅልፍ ስላልወሰደኝ የሸሸገችው አጋንንት ተገልጦ ገና ሳያርደኝ መንቃቴ ቢያንገበግባት አኮረፈችኝ ደሊላ… ከልላ ያስሞረደችው ባያርደኝ የቤቷ ቢላ … ያኮረፈችኝ ደሊላ… ባለመሞቴ'ንጂ አይደለም በሌላ @topazionnn @topazionnn
Показать все...
👍 1
እንደ ፡ ለጋነታችን ፡ ቅጠል ፥ መዳፌን ፡ መስቀለኛ፥ ምታኛ! እውነታችን ፣ እምነታችን ፥ ሳይገነትር ፡ ገር ፡ እንዳለ፣ ልብ ፡ ያበለ! ያልበደለ። አንተን ፡ ለመቅደስ ፡ ያሳጨ ፥ እኔን ፡ ለሹመት ፡ የጠራ፣ ነበራ! በየሜዳ ፣ በየመስኩ ፥ የሚመዘዝ ፡ መታረጃው፣ ምን ፡ አገኘን ፡ ስንሸመግል ፡ ሙቅ ፡ ገላችን ፡ በመብረጃው?! እስቲ ፡ ምኔ ፡ ተጋፋህ ፥ ተአፈር ፡ ብነሳ ፡ ያው ፡ አፈር፣ ለኩርማን ፡ እንጀራዬ ፡ ሞፈር። ደጄ ፡ ብታድር ፡ ማጀቴ ፡ ክፍት ፥ ፍቅር ፡ የምፈተፍት ፡ ለጉርሻ፣ ማን ፡ ፈታብነ ፡ ውሻ?! [ አስካለ ልቅና ] @yourpoim @yourpoim
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሳድስ ቤት ፍቅር ( ሳሙኤል አለሙ) ° ° ከኢያሪኮ ግንብ የሚነቀንቅ ከመኺና ክላክስ የሚተልቅ ከሙት ጡሩንባ የሚያስንቅ ከመድረክ አጋፋሪ ፥ ማይክ የሚተናነቅ ልሳኔ እስኪዘጋ ፥ ጉሮሮዬ እስከሚታነቅ። ጠርቼሽ ነበረ። ጠብቄሽ ነበረ። ° ° ካንቺ ቤት ሳይሻገር ፥ ጎረቤቶችሽ  ያሉ                         ስጠራቸው አለን አሉ። ካንቺ ቤት ተሻግሮ ፥ አንድ ባለሱቅ  ያለ                    ስጠራው ግዜ  አቤት አለ። ° ° ስላንቺ ሳነሳ...አቤት ካሉኝ ጎረቤቶችሽ ጋ ስላንቺ ሳነሳ...የሚነግሩኝ እንዳልመጣሽ ነሱ ጋ። ስላንቺ ሳነሳ...አላለፍኩትም የሰፈሩን ባለሱቅም ስላንቺ ሳነሳ...ላስቤዛ እንደመጣሽ አንዴ'ኳ አያውቅም። ° ° አቤታቸው ትዝዝ  ሲለኝ ምላሻቸው ትውስ ሲለኝ እንደ ገደል-ማሚቱ እስኪያስተጋባ፤ ያንቺ መጣው። ያንቺ ቀረው። ከወዴት ገባ?! ° ° ጆሮዬ ተስፈኛው ለመረገጡ ይናፍቃል ፥ በግራና በቀኝ ከነዓን ሆነበት'ጂ ፥ ድምፅሽ እየራቀኝ ° ግን ° የት አደረ ድምፅሽ ድምፅሽ የትስ ውሏል ድምፅሽ የት አምሽቷል አንቺን የበላ ጅብ መጮኽ እንኳን ትቷል። ° ° ቆይ ግን... በትላንቱ ቀልዴ ተናደሽ ይሆናል? መልክት ዘግይቼ መላኬ ይሆናል? መልሼ ሳልደውል ቀርቼ ይሆናል? ዝምታ'ኮ ሲበዛ ፥ እንዳይሆን ይሆናል። ° ብቻ ° ከመንገዱ ዳር ቆሜ ስጠይቅ ደና ናት የሚል ቃል ስጠብቅ አየሁሽ የሚል ቃል ያሻው ጥሎኝ ሲሄድ ያሻው ወሮታ ይጠይቃል። ° ° የዚኽን ኹሉ ሰዎች ፥ ምላሽን ሳጣጥም ይኼን ኹሉ ግዝያት ፥ በሀሳብ ስሰጥም ወይ እንዳለ መገጣጠም ወይ ደሞ እንዳለ መታደል ድምፅሽን ያልሰማው ፥ እንደ ሳድስ ፊደል ኹሉንም ዘንግተሽ ጠርተሽኝ...ጠርተሽኝ...ጠርተሽኝ ወይ መጣው ወይ ቀረው እንዳይሆን ብለሽኝ! @Samuelalemuu
Показать все...
👍 1