cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ISLAMIC KNOWLEDGE

በዚህ ቻናል 👉👉👇👇 ☀የነብያቶች ታሪክ🌹 🌿🌺 የሰሀቦች ታሪክ🌻🌻 🌿🌺 የኡለሞች ንግግር 🌈 🌿🌺 ኢስላማዊ ተአምራቶች🌻 🌿🌺 አስተማሪ ኢስላማዊ ታሪኮች🌈 🌿 🌺 አስተማሪ ግጥሞች 🌿🌻 🌹የኡለሞች የህይወት ተሞክሮዎች🌺 🌹🌹ሀዲሳዊ ምክሮች🌹🌹 for any comment 👉 @Amuu77bot Owner 👉 @Amuu77

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
203
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

☪☪......ረመዳን.....☪☪ የወር ሁሉ ንጉስ የኢስላም ስጦታ መጣልን ረመዳን የሙስሊሞችደስታ ፁመን ልናሳልፍ በአላህ ችሮታ እጅጉን ተቃርበን ወደ አለማት ጌታ አላህ ከጅሎልን ዘንድሮን ወፈቀን ድጋሚ ውዱን ወር ለማየትም በቃን እስኪ እናሳልፈው በፆም በኢባዳ በዘካ በሰላት በሀምድ በሰደቃ ከአላህ ጋር እንሁን በእያንዳንዷ ቅፅበት ለከርሞ እንዲያደርሰን ከልብ በመመኘት ታላቁ ወር መጧል ብስራት ዜና ይዞ መንገድን ሊያመቻች ለጀነቱ ጉዞ ሸይጣንን አባሮ ከምድር አፈር ላይ ወደአላህ ሊያቃርብ በዲናችን ጉዳይ ከአላህ አስተሳስሮ እጅግም አቃርቦ ቶሎ ያልቅብናል ሳንጨብጠው ቀርቦ ህልም ይመስለናል የረመዳን ማብቃት ወር ሲፈጥን ስናይ ልክ እንደ ሳምንታት ታዲያ አንዘናጋ እያየነው እስኪያልቅ እንጠባበቀው ቆመን በተጠንቀቅ ተጠቃሚ እንሁን በታላቁ ወር ውስጥ ካለፉት ጊዜያት በደረጃ እንድንበልጥ ከልብ ተመልሰን ወደ አለማት ጌታ ረመዳንን እንፁም በጤና በደስታ የተቸገሩትን ሳንዘነጋ ላፍታ ተግባራችን ሆኖ ዘካናእርዳታ ለሌለው አካፍለን ያለንን በደስታ ከአላህ ምንዳን ሽተን እናግኝ እርካታ ረመዳን ተባለ በአራት ፊደላት መቼ ይገልፁታል ሺ የሆኑ ቃላት!!☪☪ °°°°°°°°°❤️ረ °°°°°°°°°°°°°❤️መ °°°°°°°°°❤️ዳ °°°°°°°°°°°°°❤️ን @Islamic_Poem_Ss °°~°°~°~°°~°~°~ @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
🛑ወዴት እየሄድን ነው❓ ተፈጥረን ነበረ ከአንድ አይነት አፈር ፍቃድም ተሰጥቶን ለመኖር በምድር ምድር ላይ መጥተናል በአላህ ችሮታ ለምን እንደመጣን አንዘንጋ ላፍታ አላህን በጥራት መገዛት ሲገባን ወንጀል እየሰራን እኛ እሱን ዘነጋን አለባበሳችን ብሎም ተግባራችን አላህን ሚያስቆጣ ሆነኮ ስራችን አላህ እንዲህ አለ"እኔ ፈጠርኳችሁ" እኔን ልታመልኩ በጋራ ሆናችሁ እስኪ እንደው ንገሩኝ ምን ጎሎባችዃል የአላህን ህግጋት በድፍረት ጥሳችዃል አሁንም ጊዜ አለን ገና አልረፈደም በኢስላም ለመፅናት እድሉ አላለቀም እናም ወዳጆቼ እስኪ እንደው አድምጡኝ ጆሮአቹን ለአንድ አፍታ ለኔ ብቻ ስጡኝ ሙስሊም ላደረገን ለፈጠረን ጌታ በእውነት እናምልከው በፅናት በደስታ እመኑኝ አህባቢ በሙሉ ልባችን ወደ አላህ ከሄድን ኢንሻኣ ተአላ በጀነተል መዕዋ እንገናኛለን!!!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ @Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
🌹ግጥሜን ተጋበዙልኝ አህባቢ 🦋ቀድር........🦋 ኩንፈየኩን ብሎ ቁርአን ያሰፈረው የአላህ ውሳኔ እርሱ የደነገገው ቀድር መቀበሉ የእምነት ማዕዘን ነው ኸይሩም ሆነ ሸሩ መጨረሻው ውብ ነው ያሰብነው ባይሳካ ምኞታችን ከስሞ በአላህ ቀድር ላይ አንዘን ፈፅሞ ካሰብነው የላቀ ከጠበቅነው በላይ አላህ ይሰጠናል ሁሉንም ባንድ ላይ ክፉ ነገር በዝቶ ሀዘን ቢያጋጥመን ዱንያ ስልችት ብሎን አኼራን ቢያስመኘን ጨለማ በዝቶብን ብርሀን ቢናፍቀን ከቶ ተስፋ ሳንቆርጥ በአላህ እንመን ያማረን ውሳኔ እሱ ይሰጠናል ከጠበቅነው በላይ ብዙ ይረዝቀናል የረህማን ውሳኔ እጅግ የበላይ ነው እኛ ባይመስለንም ለኛው ጠቃሚ ነው በቀድር እንመን ያላንዳች ብዥታ ሁሉም ለኸይሩ ነው ብለን እንበርታ መታመም፣መፈወስ፣ሞት ና ህይወት መሳቅ እና ማልቀስ ማዘን መደሰት ሁሉም ነገር ያለው በአላህ ውሳኔ ነው ከሁሉ አስበልጠን እሱን እንመነው!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ 🦋 "if you like it Share it“🦋 ተቀላቀሉን👇👇👇👇 @Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
ክፍል 7⃣ 📌♻️አላህን ማውሳት♻️📌 የጠዋት እና የማታ አዝካሮች አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፦ 《يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا》 ✨{ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"} ✨ (ሡረቱል አህዛብ፡41-42) 🍁የጠዋት እና የማታ አዝካሮችን ማብዛት የቀልብ መረጋጋትን ያስገኛል። 🍁በልብ ውስጥ ደስታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል።🍁ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል። 🍁የጠዋት እና የማታ አዝካሮችን አዘውታሪ የሆነ ሰው ፡ ግርማ ሞገስን ፡ የአንደበት ጥፍጥናን ፡ የፊት ብርሀንን ፡ ይላበሳል። ♻️ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ። 【የአደም ልጅ አብዘሀኛው ስህተት በምላሱ ነው።] 🥀ምላሳቸውን በዚክር ያጠመዱት ምነኛ ታደሉ❗️ስንቶቻችን ነን ጥረት ላይ ያለን❓ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ፦ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا ۖ وَمِنْ آنَاءِ اللَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ النَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَىٰ ✨ጌታህንም ፀሐይ ከመውጣትዋ በፊት ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ኾነህ አጥራው፤ (ስገድ)፡፡ ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው፡፡ (በሚሰጥህ ምንዳ) ልትወድ ይከጀላልና፡፡✨ ጣሀ 20በሁሉም 👉በቀልባችን እና ምላሳችን በሁሉም ሁኔታዎቻችን ላይ በመደጋገም ከፀሃይ መውጣትና መግባት በፊት ዚክሮችን ልንላመድ ይገባል፡፡ ዚክር ብዙ ጥቅሞች አሉት በመልካም ጊዜ አላህን ተዋወቅ ስትጨነቅ ውጥረት ውስጥ ስትገባ ያኔ አሏህ ያስታውስሀል☝� صرع نفسه قبل أن يصرعه عدوه !! 🥀 ነፍስያን ታግሎ ማሸነፍ ጠላትን ከማሸነፍ ይቀደማል❗️ አላህ ያግዘን🤲 ✨መልእክቱን በማስተላለፍ ወንድሞችንና እህቶችን አናስታውስ!! ለቀጣይ ትውውስ ይቀላቀሉን👇 @allahisoneee
Показать все...
🌙ጨረቃዋ ቀርባለች!!🌙 ወደ ፈጣሪያችን እኛን ልታቃርብ ደርቆ ያመፀውን ልብን ልታረጥብ በኢማን ልትሞላን ከወንጀል አርቃ በሰላት፣በቁርአን፣በዚክር አሸብርቃ በስሁር፣ በዘካ፣ በተራዊህ ደምቃ የልባችን ፈዋሽ ቀረበች ጨረቃ ከኢባዳ ርቀን ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀን በዲናችን ጉዳይ እጅግ ተዘናግተን ከኢስላም መርሆች በሩቁ አፈንግጠን ዱንያ ላይ ተጥደን ሁሉን ነገር ረስተን ብዙ ስንታትር መንገዱ ጠፍቶብን ጨረቃ ቀረበች እኛን ልታግዘን የጠፋውን መንገድ ልታመላክተን ወደ ጀሊላችን እኛን ልትመልሰን ልብን በእምነት ሞልታ 1 ልታረገን በጉጉት ተናፍቃ እኛን ልታልቀን ሁሉን አሰባስባ በእምነት በጋራ አንድ ልታረገን ሸይጣንን አባራ ከውሸት፣ከፈሳድ፣ከሀራም አፅድታን ለደከመው ኢማን ይዛ መድሀኒትን የጀሀነምን በር ከሩቁ አስዘግታ የጀነትን በሮች ለእኛ አስከፍታ ቀረበች ጨረቃ ብስራቱን ነጋሪ የወርሃ ረመዳን ጅማሬን አብሳሪ!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ 🌙🦋 "if you like it Share it“🦋🌙 Join & give us comment @Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
🌺 ግጥሜን ተጋበዙልኝ አህባቢ 🌸 🦋 ሁላችንም ሟች ነን 🌹 በተፃፈው ሰአት አዎ እንሞታለን ምድርን ትተናት ቀብር እንገባለን ከጥሩ እስከ መጥፎ ከስራችን ጋራ እንገናኛለን ቀብር ውስጥ በየተራ ፀጉር ሲነቃቀል ስጋ ሲበጣጠስ አካላችን ሸቶ ጥፍር ሲበሰብስ አደለም ሰው ቀርቶ አእዋፍ ይርቁናል ብቻችንን መኖር እጅግ ይከብደናል ስራችን ሚዛን ላይ ወጦ ይመዘናል ከጥሩ እስከ መጥፎ ሁሉም ይነገራል መልካሙ እንዲያደፋ ልብ ትመኛለች ጌታየ ሆይ እርዳኝ ደጋግማ ትላለች ዱንያ ላይ ኖራለች ምንም ሳይጎድልባት ከልጅ እስከ ጤና ከሀብት እስከ ንብረት ጀሊሉ አንድ ላይ ሁሉን ነገር ሰጣት እሱን ታመልክ ዘንድ ብዙ አስጠነቀቃት ነፍስ ግን ከጀለች ዱንያዊ ነገርን አጥብቃ ፈለገች ዘውታሪ መሆንን አላህን ዘንግታ ዱንያ ላይ ዋለለች ሞትን እና ቀብርን ሂሳብን ዘነጋች ቀኔ አልደረሰም ብላም አንቀላፋች ድንገት ቀኗ ሲደርስ ያኔ ትነቃለች ዋ ነፍሴ ዋ ነፍሴ አብዝታ ትላለች ሁሉን ነገር ትታ ቀብር ትገባለች ሰለዚህ ነቃ እንበል ላፍታ ሳንዘነጋ ሞትን እንጠብቀው ሲመሽም ሲነጋ!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ 🌙❤️ "if you like it Share it“❤️🌙 Join & give us comment @Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
ረጀብ ላይ ያልዘራ... ሻዕባን ላይ ያላጠጣ.... ረመዷን ላይ ሊያጭድ አይችልም!! 🤲🤲ያ ረህማን ረመዷንን በሰላም አድርሰህ አስፁመን!! @Islamic_Poem_Ss🦋 @Islamic_Poem_Ss🦋
Показать все...
☪☪ ያ አቅሷ······☪☪ በያንዳነዱ ሙስሊም ልብ ውስጥ የተፃፈች በእስልምና ታሪክ ትልቅ ስፍራ የያዘች የተቀደሰች ቤት ውብ የአምልኮ ስፍራ በምድረ ፍልስጤም ደምቃ ምታበራ በመስዋትነት በደም ፀንታ የቆመች የሁሉም ሙስሊሞች መመኪያ የሆነች ከደም ከአጥንታችን በአንድ የተሳሰረች የታላቅነት ምንጭ፣የድል ዜና የሆነች የህብረት፣የሰላም፣የእምነት መገኛ ከሽንፈት፣ከውድቀት፣ከህመም መዳኛ ትልቋ ማዕከል የሙስሊሞች ሀብት ብዙ ተከፈለላት ከደም ና ከአጥንት ሙስሊሞች በጋራ በአንድነት ሆነን አቀሷን በእጃችን ሳንይዝ ጨብጠን ቂያማ አትቆምም አለም አታበቃም ፈትህ ለሙስሊሞች ይገባል ዘላለም መከፋፈል ሳይኖር እንቁም በጋራ መጨረሻው አምሮ ፍሬ እንዲያፈራ ከአላህ ጋር ሁነን ተውሂድን አንግበን አቅሷን ለማስመለስ እንጓዝ ተባብረን ሁሉም በየፊናው የአቅሙን ከጣረ አላህ ታክሎበት ውጤቱ ሰመረ!!!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ ተቀላቀሉን👇👇👇👇 ☪🦋☪@Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss☪🦋☪ Share🦋🦋🦋🦋🦋 Share🦋🦋🦋🦋 Share🦋🦋🦋
Показать все...
🦋ጁመአችንን በሰለዋት እናድምቅ🦋 ተቀላቀሉን👇👇👇👇 @Islamic_Poem_Ss @Islamic_Poem_Ss
Показать все...
9.82 KB
🦋🦋 ያ አዚዙ........🦋🦋 ያ አላህ ያ አዚዝ የአለማት ፈጣሪ ምድረ አለማቱን በአንድ አስተናባሪ ለባሮቹ አዛኝ ወንጀልን መሀሪ እሱን ለታዘዙ ጀነትን አብሳሪ በውቧ ምድሩ ላይ ጥፋት ቢንሰራፋ የሰው ልጆች ወንጀል በእጅጉ ቢሰፋ ፈሳድ ግልፅ ሆኖ በአደባባይ ቢታይ እውነት ተናጋሪ በእጅጉ ቢሰቃይ ሩህሩህ እና አዛኙ የአለማት ጌታ በእኛ አልጨከነም ለአንዴ እና ላፍታ እኛ እሱን ዘንግተን ወንጀልን ተዳፍረን ከተከለከልነው ብዙዎቹን ሰርተን ሞት እና ሂሳብን አኼራን ዘንግተን ከሀላሉ ይልቅ ሀራሙን አብልጠን ነፍስያን ማሸነፍ በእጀጉ አቅቶን ዱንያ ላይ ዋልለን ሁሉን ነገር ረስተን ከሳሪ ሰው ሆነን ወድቀን ብንገኝም ያረሂም ያአዚዝ በእኛ አልጨከነም በእጅጉ የሰፋ ምህረትን የሰጠን የማያሳፍረን እኛ እሱን ጠይቀን ነውር እና ስህተትን ገመናን ደባቂ በያንዳነዷ ልብ ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ያ ረህማን ያ አዚዝ ንጉሶች ንጉስ ጥበበኛ ፣አዛኝ ፣መሀሪ እና ለጋስ!!! ✍✍ሱመያ ቢንት ኑሬ ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ👇👇👇👇 💫@Islamic_Poem_Ss ❤️🦋❤️🦋❤️🦋❤️🦋❤️ ¤∝¤💫@Islamic_Poem_Ss 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹Share 🌹🌹🌹🌹🌹Share 🌹🌹🌹Share
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.