ETHIO CRYPTO ™
Открыть в Telegram
Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟
Больше3 571
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-8230 дней
Архив постов
3 571
#Bahirdar_university
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀመር ተማሪዎች ኃላፊነት ለመውሰድም ይዘጋጁ ብሏል።
በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድ ፖስት፣ የፀጥታ አደረጃጀቶች፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቶ የውይይቶቹ የመጨረሻው ክፍል ሐሙስ ከተደረገ በኃላ ነው ውሳኔው የተላለፈው።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ምን አሉ ?
- ከመስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተን የነበረ ቢሆንም፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ ተሰናክሏል።
- በእኛ በኩል የዝግጅት ክፍተት የለብንም።
- በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቁጥጥር ሥር የሆነ የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነም የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ውጪ በሆነው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ አንችልም። ምንም ማድረግ ባልቻልንበት ሁኔታ የሰው ልጅ ጠርቼ አንድ መጥፎ ነገር ቢከሰት ምንድነው የምለው ? የሚለውን ተማሪዎችም፣ ወላጅንም ታሳቢ አድርገን ተማምነን ይቆይ የሚል አቋም ስለነበረን በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን ቀስ እያልን የመጣነው።
- የመማር ማስተማሩ እንዲጀመር በነበረው ውይይት ሒደት አቅደን የነበረው ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ የትምህርት ግቢያቸው ማስገባት ነበር።
- እስካሁን ባለን ልምድ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። ቀጣይነታቸው ግን ብዙም አይደለም። አንድ ቀን ወይ ሁለት ቀን መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል ከዚያ ግን ያበቃል።
- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተጠርተው ሲመጡ ታሳቢ ማድረግ ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዕክሎችን ከግምት በማስገባት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።
- ተማሪውም፣ ወላጅም፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብም እንደ አገር የሚመለከታቸውም አንድ ላይ ሆነን መደበኛ ትምህርት መጀመር አለብን ብለን ወስነናል።
- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተቋማቸው ከልደት (ገና) በዓል በኋላ ባሉት ቀናት ለተማሪዎቹ ጥሪ ያደርጋል።
https://t.me/student_text
3 571
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር ብሏል ሚኒስቴሩ።
በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል።
" የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።
በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።
https://t.me/student_text
3 571
Addisababa University
በታሪክ አጋጣሚ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲን የተቀላቀሉት ሶስቱ መንትዮች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
የአብቃል አበበ፣ የአብፀጋ አበበ እና የአብስራ አበበ የተሠኙት ሶስት መንትዮች በ2015 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ የተሠጠዉን የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እያንዳንዳቸዉ ከ340 በላይ የሆነ ዉጤት በማምጣት ሶስቱም መንትያሞች አዲስ አበባን ዩንቨርሲቲን ተቀላቅለዋል።
ዩንቨርሲቲዉ በዛሬዉ ዕለት ደማቅ ዝግጅት አዘጋጅቶ አዲስ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ሲሆን ተማሪዎችም በለተደረገላቸዉ ልዩ አቀባበል ዕጅጉን መደሰታቸዉን ገልፀዋል።
በቀጣዮቹ አምስት ቀናትም አዲስ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረጉ ልዩ ዝግጅቶች በዩንቨርሲቲዉ ይካሄዳሉ።
3 571
#ትግራይ
የ12ኛ ክፍል ፈተና ተራዘመ።
" በሚቀጥለው ጥር ወር 2016 ዓ.ም ለመስጠት የታቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው ለሚድያ ባሰራጨው ፅሑፍ እንዳለው ፤ የትግራይ ትምህርት ከትምህርት ሚኒስቴር በመግባባት በክልሉ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ሳይሰጥ የቆየው የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና መስከረም 29/2016 ዓ.ም ፣ ጥር 6 /2016 ዓ.ም እና ግንቦት 2016 ዓ.ም ለመስጠት አቅዶ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ አስታውሷል።
ይሁን እንጂ በሚቀጥለው ጥር 6/2016 ዓ.ም ለመስጠት ያቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታህሳሰ 9/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል።
ቢሮው ፈተናውን ለማራዘም ያስገደዱት ሶስት ምክንያቶች ዘርዝሯል።
እነሱም ፦
1. ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች ዘግይተው ተማሪዎች በመቀበላቸው ምክንያት ሊሰጥ የታቀደው ፈተና ዩኒቨርስቲዎቹ ካወጡት የትምህርት ፕሮግራም የማይጣጣም በመሆኑ፤
2. የአገር አቀፍ የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት የዝግጅት ጊዜ እጥረት እንደገጠመው በመግለፁ፤
3. ተማሪዎች ለፈተና መዘጋጃ የሚሆን የጊዜ እጥረት መኖሩ በመረዳት፤
ጥር 6/2016 ዓ.ም ለመስጠት የታቀደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ብሏል።
በተያያዘ ከታህሳስ 18 አስከ 20/2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ፈተናውን ለመፈተን 60 ሺህ ተማሪዎች መመዝገባቸው ቢሮው ማስታወቁ ጠቅሶ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
https://t.me/student_text
3 571
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ጠርተው ትምህርታቸውን እንዲያስቀጥሉ ተነግሯል ተባለ!!
በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወቅቱ ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይጠሩ እንደቆዩ ይታወቃል።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ የሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሃሳብ ሰጥቶበታል።
በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ትምህርት እንዲያስቀጥሉ ትእዛዝ ተላልፏል ሲሉ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጀና ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተቋሟቱ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛዉም ነገር እገዛ እንዲደረግላቸዉ እንዲያሳውቁ መልእክት ተላልፏል ብለዋል። በውይይታቸው መሰረት በቅርቡ ተማሪዎች በየተቋሟቱ ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚቀጥሉ ነዉ ስራ አስፈጻሚዉ የተናገሩት፡፡
ትምህርት ያልጀመሩትን ብቻ ሳይሆን በትምህርት ገበታቸው ላይ የሚገኙትንም ተማሪዎች ሁኔታ በመከታተል ላይ እንገኛለን ያሉት መሪ ስራ አስፈጻሚው ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በመሆን የትምህርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸዉን አመላክተዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው ተማሪዎቹ መቼ ተጠርተው ትምህርት እንደሚጀምሩ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም፡፡
https://t.me/student_text
3 571
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ Remedial
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሬሚዲያል ፕሮግራም በግል መደበኛ አመልካች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ከ24/04/2016 ዓ.ም እስከ 05/04/2015 ዓ.ም ድረስ ማስታወቂያ አውጥቶ ምዝገባ ያካሄደ መሆኑ ይታወቃል::
ስለሆነም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለተራዘም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ከ11-12/04/2016 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።
የቅበላ መስፈርቶች፡-
1. የትምህርት ሚኒስቴርን የግል ሬሚዲያል የመቁረጫ ነጥብ (30%) ለማህበራዊ ሳይንስ 180 እና ከዚያ በላይ፤ ለተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 210 እና ከዚያ በላይ የሚያሟላ/የምታሟላ
2. የ8ኛ፤ የ10ኛ፤ የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና ውጤት ዋናውን እና አንድ የማይመለስ ኮፒ ማቀረብ የሚችል/የምትችል
3. ለማመልከቻ 50 (ሃምሳ ብር) መክፈል የሚችል/የምትችል
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
3 571
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስኮቻቸው የፈቃድ ወቅታዊ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡
በአጠቃላይ የ 382 ተቋማት ወቅታዊ የፈቃድ መረጃን ይፋ የተደረገ ሲሆን፦
◉ 366 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
- 5 የግል ዩኒቨርሲቲዎች
- 6 የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች
- 6 ኢንስቲቲዩቶች
- 349 የግል ኮሌጆች
◉ 16 የመንግሥት ከ/ት/ተቋማት
- 4 የርቀት ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ
- 12 የመደበኛ ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ
የተቋማቱን የትምህርት መስኮች የፈቃድ ጊዜ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት በየትምህርት መስኩ፣ በካምፓሱ እና በፈቃድ ጊዜው ላይ በአረንጓዴ፣ በቢጫ፣ በቀይ እና በወይን ጠጅ ቀለማት ምልክት ተደርጎበታል፡፡
🟢 አረንጓዴ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ6 ወራት በላይ የሚቆይ እና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ
🟡 ቢጫ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ1 እስከ 6 ወር በላይ የሚቆይና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ፡፡ ነገር ግን በቀሩት 6 ወራት ፈቃድ ሳያድሱ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡
🔴 ቀይ ቀለም የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ያለፈ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ ፈቃድ አላደሱም፡፡
🟣 ወይን ጠጅ ቀለም የተደረገባቸው
- ያቋረጡ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ የተመዘገቡ ተማሪዎች ግን ማስጨረስ ይችላሉ፡፡
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ ያገኙበትን የትምህርት መስክ፣ ካምፓስ እና መርሐግብር አሟልቶ የያዘና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድን በዚ ሊንክ ይመልከቱ፦
https://bit.ly/43Z1Rck
https://t.me/student_text
3 571
መፍትሄው ምንድነው?
በአስሩ አማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከራቁ ወራት አልፈዋል።
ተማሪዎቹ ሳይጠሩ / የሚጠሩበትን ጊዜ ሳያውቁ የፊታችን ሰኞ የ2016 ትምህርት ዘመን 4ኛው ወር ይገባል።
እስካሁን በእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ በይፋ አንዳች የተባለ ነገር የለም።
ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው የትምህርታቸው ጉዳይ ቀን ከሌት ሀሳብ የሆነባቸው ሲሆን መንግሥት አሁንም ጊዜው ከዚህ ሳይረፍድ አለኝ የሚለውን መፍትሄ እንዲያሳውቃቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ።
በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን አሁን የመግቢያ ጥሪ ያልተደረገላቸው / መቼ እንደሚደረግላቸው እንኳን የማያውቁ ተማሪዎች በምን አግባብ ከሌሎች ተቋማት ተማሪዎች ጋር እኩል ለሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እንደሚቀመጡ ከአሁኑ ጭንቀት እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከምንም በላይ ከእድሜ እኩዮቻቸውና ባቾቻቸው ወደኃላ ቀርተው ቤት መቀመጣቸው ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንደዳረጋቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አስረድተዋል።
ተማሪዎቹ በህይወታቸው መቀለድ እንዲያቆም፣ የትምህርታቸው ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም በይፋ ምን እያሰበ እንዳለ በመግለጫ እንዲያሳውቃቸው ድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ ያለው ተላዋዋጭ የሆነ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ተቋማት ተማሪዎችን ለመጥራት ፈተና እንደሆነባቸው ከዚህ ቀደም መግለፃቸው አይዘነጋም።
https://t.me/student_text
