ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ETHIO CRYPTO ™

ETHIO CRYPTO ™

Открыть в Telegram

Join us✨ for insightful analysis, expert tips, and exclusive strategies to maximize your returns in the dynamic world of digital assets. we launch projects on how to make money online🌟

Больше
3 571
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-8230 дней
Архив постов
#Grade_12
#Grade_12

#12 የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5  ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን። የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት t.me/student-text

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል። https://t.me/student_text

በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ። ቀን ሚያዚያ 16/ 2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ አካሄደዋል ። የመስክ ምልከታው የካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መሪ ህዳሴ ቅድመ አንደኛ ደረጃ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተካሄደ ሲሆን በምልከታው የቢሮው አማካሪን አቶ ጥላሁን ፍቃዱን ጨምሮ የየክፍለ ከተሞቹ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ሎሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸን አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። ጉብኝቱ በዋናነት ሁለቱ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን በትምህርት ቤቶቹ ግንባታዎችን ጨምሮ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በማየት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ የተካሄደ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በጉብኝቱ ባስተላለፉት መልዕክት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት ከተደረገባቸው ዘርፎች አንዱ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ህጻናት ትምህርታቸውን ጨዋታን መሰረት ባደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ እንዲማሩ ማስቻል መሆኑን ጠቁመው በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታዎችን ጨምሮ ለህጻናቱ ምቹ የመማሪያ ቦታ ሆነው ሞዴል እንዲሆኑ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በጉብኝቱ ማረጋገጣቸውን በመግለጽ የተጀመሩት ግንባታዎች ተጠናቀው ለሚፈለገው የመማር ማስተማር ስራ እንዲውሉ ቢሮው ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አስገንዝበዋል። በተመሳሳይ ዶክተር ዘላለም ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች ጋር በመሆን በሶስቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን እና አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን የተመለከተ ምልከታ አካሂደዋል። https://t.me/student_text

photo content
+3

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር ጋር በመሆን Top Gravity ከተባለ የህትመት ተቋም
የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር ጋር በመሆን Top Gravity ከተባለ የህትመት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ከዚሁ ተያያዘ ክቡር ሚኒስትሩ ጃፓን፣ ቶኪዮ በሚገኘው የ Top Gravity ዋና መስሪያ ቤት የስራ ጉብኝት በማድረግ ከተቋሙን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ፤ https://www.linkedin.com/posts/toppan-gravity_toppan-eih-innovation7-activity-7188069238941638656-TVHw?utm_source=share&utm_medium=member_android https://www.linkedin.com/posts/ethiopian-investment-holdings_commencing-their-networking-and-collaboration-ugcPost-7188069533868261376-IycV?utm_source=share&utm_medium=member_android https://www.linkedin.com/posts/ethiopian-investment-holdings_ethiopia-partnership-globalbusiness-ugcPost-7185619860398219264-O1h0?utm_source=share&utm_medium=member_android https://www.linkedin.com/posts/toppan-gravity-ethiopia_industrialprinting-collaboration-innovation-ugcPost-7185654197235683329-d7XZ?utm_source=share&ut m_medium=member_android T.me/student_text

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህር
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር  አሳውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ https://t.me/student_text

photo content

የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለኡጋንዳ የትምህርት ፓሊሲ ክለሳ ኮሚሽን ልምድ አካፈለ። የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለኡጋንዳ የትምህርት ፓሊሲ ክለሳ ኮሚሽን የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ
+1
የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለኡጋንዳ የትምህርት ፓሊሲ ክለሳ ኮሚሽን ልምድ አካፈለ። የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለኡጋንዳ የትምህርት ፓሊሲ ክለሳ ኮሚሽን የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ ስላለው የትምህርት ስርዓትና ፓሊሲ ጉዳዬች ላይ ገለጻ አድርገዋል። በልምድ ልውውጡ መርሃ ግብር መክፈቻ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዘርፉን የፓሊሲ አቅጣጫና የተከናወኑ ተግባራት ለኡጋንዳ ወገን በማካፈል ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት ያለ መሆኑን አብራርተዋል። በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እፀገነት በዛብህ ይመኑ በበኩላቸው የልምድ ልውውጡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትምህርትና የህዝብ ለህዝብ ትብብርና ግንኙነት ለማሣደግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ የትምህርት ፓሊሲ ይዘትና መርሆችን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ለልኡካን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል። በተመሳሳይ በዘርፉ በተመዘገቡ ስኬቶችና ባጋጠሙ ፈተናዎች ዙሪያ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጀና ገለጻ ያደረጉአድርገዋል። ከገለጻው በኋላም ሁለቱ ወገኖች ሰፊ ውይይት አድርገዋል። የኡጋንዳ የትምህርት ፓሊሲ ክላሳ ኮሚሽን ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ጆሴፍ ሙቫዋላ በበኩላቸው የልምድ ልውውጡ የሁለቱ ሀገራት የትምህርት ፓሊሲ ያላቸውን ተመሣሣይነትና ልዩነት በማጥናትና በመቀመር ጠቃሚ ግብአት ለማግኘት እንደሚረዳቸው ገልጸዋል። የልኡካን ቡድኑ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና እና በመዲናችን ያሉ ልዩ ልዩ ቦታዎች ላይ ጉብኝት እንደሚያደርግ ተገልጿል። @Student_text

የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪ የምግብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ የምግብ በጀት እጥረት ገጥሞናል ያለውን ብሉ አይነት ማስታዎቂያዎች መለጠፋቸውን ተከትሎ በበርካቶችን አነጋግሯል። ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ምንድነው የሚሉት ? እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል። ተቋማችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል። ከአሁን በኃላ የተሻሻለው ሜኑ ተግባራዊ ይሆናል። በተወሰኑ በስቶራችን ውስጥ ባሉ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች እና በአትክልት የምግብ አገልግሎት እየሰጠን ነው። በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦት እንዲሟላ ጠይቀናል ዩኒቨርሲቲን የሚያክል እጅግ ትልቅ ተቋም እንዴት መጭውን የዋጋ ንረት እንዲሁም የዓመቱ የምግብ ወጪ ያላገናዘበ በጀት ይይዛል ? ለረጅም ዓመታት ለተማሪ በቀን የሚመደበው ገንዘብ አነስተኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ይህ ሊፈጠር ቻለ ? የሚሉና ሌሎች ነቀፌታዎች ተሰምተዋል። - የተከሰተው ችግር ምንድነው - በዚህ አይነት ሁኔታ ተማሪዎች ከመጎዳታቸው በላይ ወላጆችንስ አያስጨንቅም ሲል ለዩኒቨርስቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ጥያቄ አቅርቧል። ዶ/ር ሀብታሙ ማስታወቂያውንም ሆነ ሀሳቡን እንደማያዉቁት በመግለጽ ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን ብለዋል። ተማሪዎች ሆኑ ወላጆች ምንም የሚያሳስባቸዉ ነገር ሊኖር አይገባም ያሉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉም ሆነ እርሳቸዉ የሚመሩት የተማሪዎችን ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ችግሩ እንደሌለበት ገልጸዋል። https://t.me/boost/student_text https://t.me/boost/student_text

#Exit _Exam የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ማሰባሰብ ሥራ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከናወነ ይገኛል። ተቋማቱ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች የተሟላ መረጃ እስከ ሚያዚያ 5 2016 ዓ.ም ድረስ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተረጋግጦ እንዲላክ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ተሰምቷል። የመውጫ ፈተናው በሰኔ ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። Https://t.me/student_text https://t.me/boost/student_text

photo content
+2

#12_ክፍል የ 2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ Https://t.me/student_text

ለጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ውጤታማነት አጋር አካላት የድርሻቸውን እንዲውጡ ጥሪ ቀረበ። ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት የ30 ዓመታት ጉዞን የተመለከተ ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማትር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሽቴ ሀገራችን መደበኛ ትምህርት ያላገኙ ዜጎችን የመማር መብት ለማረጋገጥና የተማሩ ዜጎችን ቁጥር ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራምን በመዘርጋት ውጤታማ ስራ ሰርታለች ብለዋል። በዚህም ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም በሀገራችን ተደራሽ እንዲሆንና ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ድጋፎችንም አድርጓል ብለዋል። ድርጅቱ በሀገራችን ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የተለያዩ ስትራጂዎችን ፣ መመሪያዎችን፣ አዳዲስ የማሰተማሪያ ስነ-ዘዴዎችን መቀየስ፣ የጎልማሶች ትምህርት መሰረተ ልማትን በማስፋትና የማህበረሰብ መማማሪያ ማዕከላትን በማቋቋም ረገድ ድጋፍ ማድረጉንም አንስተዋል። በዚህም ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር የዘረጋውን ፕሮግራም ለማሳካት ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። “ትምህርት የማህበረሰብ ለውጥ ሀይል ነው” ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የጀርመን መንግስት በዲቪቪ ኢንተርናሽናል በኩል በሀገራችን የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን አንስተው ሌሎች የትምህርት ዘርፉ አጋር አካላትም ለጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር በበኩላቸው የጀርመን መንግስት በዲቪቪ ኢንተርናሽናል በኩል ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት በኢትዮጵያ ውጤታማ እንዲሆንና የዜጎችን የመማር መብት ለማረጋገጥ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል። አክለውም ጀርመን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትምህርትና በሌሎች ዘርፎችም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑ ተናግረዋል። የዲቪቪ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አባተ በበኩላቸው ይህ ኮንፈረንስ ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የሰራቸውን ስራዎች ለመመልከትና በቀጣይ እንዴት የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራምን ያለ ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ውጤታማነቱን ጠብቆ ማስቀጠ ይቻላል የሚለውን በጋር ለመመካከር መሆኑ አንስተዋል። ዲቪቪ ኢንተርናሽናል በጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሲያደርግ የነበረው ድጋፍ የተጠናቀቀ መሆኑም በመደረኩ ተገልጿል። Https://t.me/student_text

#የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የሙያ ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ አይነቶች ይፋ አደረገ። ቢሮው በክልሉ ከቀለም ትምህርት ጎን ኑጎን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት በ2017 የትምሀርት ዘመን መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል። የሙያ ትምህርቱ በ12 የሙያ አይነቶች የሚሰጥ ሲሆን፣ የትግበራው ዝግጅት ተጠናቆ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ትግበራው እንደሚጀምርም ተገልጿል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምሀርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ የሙያ ትምህርት ተማሪዎች የፈጠራ ክህሎታቸውን በማጎልበት ፍላጎታቸውን ያማከለ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል። የሙያ ትምህርቶች በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ትግበራ የሚገባ መሆኑን የጠቁሙት አቶ አንተነህ የሚሰጡት የሙያ ትምህርቶች የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ፣ የተማሪውን ፍላጎት፣ የሠው ኃይልና የግበዓት አቅርቦትን ማዕከል ባደረገ መልኩ የሚሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አቶ አንተነህ ገለፃ በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቶች በተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል። በዚህ መሰረትም:- 1 በተፈጥሮ ሳይንስ 1.የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ 2 ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ 3 ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት 4 ኮምፒውተር ጥገናና ስራ 5 አኒማል ፕሮዳክሽን 6 ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር 7 ማህበረሰብ ጤና 2 በማህበራዊ ሳይንስ 1 ጆርናሊዝም 2 ስነ ልቦናዊ ክብካቤ 3 አካውንቲንግ እና ፋይናንስ 4 ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር 5 ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸውንም ገልፀዋል። እንደ ሀገር በ40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ ሲሆን፣ በክልሉ በ12 አይነት የሙያ ትምህርቶች የሚጀመረው የሙያ ትምህርት እንደየ ተማሪዎች ፍላጎት በቀጣይ ተጨማሪ የሙያ አይነቶች እንደሚካተቱም ተጠቁሟል ከማዕላዊ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሚያዚያ 12/2016 @StudenT_Text

Cross metfelegu be @onee16 ley anagrun

የምንለቃቸው መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ፤ ከስልካቹ እታች ያለው ከላይ በፎቶላይ እንደምትመለክቱት (MUTE) ማለቱን አረጋግጡ፤        UNMUTE ከሆነ የሚለው፤ አንዴ ብቻ ተጫኑት @student_text   @student_text     @student_text        @student_text          @student_text