cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

በዝሙት አንዘምን 🚫

የተለያዩ ባለንበት ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንመካከር እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል ቻናሉ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ያምብቡ። ከሃራም መንገድ(ፍቅር)መውጣት ለምትፈልጉ በውስጥ መስመር እንመካከር 👉 @Jezakellah ሙሂዲን ሰኢድ ጆይን ግሩፕ👉 @bezemut_anzemn كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون بالمعروف و تنهون عن المنكر

Больше
Рекламные посты
11 568
Подписчики
Нет данных24 часа
+597 дней
+47530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

00:19
Видео недоступноПоказать в Telegram
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላህ ውድ በዝሙት አንዘምን ቤተሰቦች ቴሌግራም እየገባሁ ስላልሆነ ነው የጠፋሁት በውስጥ እያማከራችሁኝ ያላችሁም ጠብቃችሁ በትእግስት አውሩኝ አይኔን ስላመመኝ ነው ወደ አዲስ አበባ አልሃምዱሊላህ በሰላም አሁን አካባቢ ከመሸ ገብቻለሁ ህክምና አድርጌ ኢንሻ አላህ እገባለሁ። በዱአችሁ አትርሱኝ የሸዋልን ፆም ከቻልን ነገ ማክሰኞና እሮብ ለመፆም እንሞክር። ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ @jezakellahT ሽገሮች ሃገራችሁን ከላይ በማታ እዩዋት
Показать все...
2.78 MB
👍 20👌 2💯 2🔥 1
→ክፍል ሁለት → የዚና ወንጀል ዱንያዊ ቅጣቶች  «ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን(ያላገቡ እንደኾኑ)መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደኾናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡»(አን-ኑር24፡2)  ሆኖም ግን አንቀጹ ጥቅል በመሆኑ ባገባውና ባላገበው ወንጀለኛ መካከል ልዩነትን ያደረገ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በዓረብኛ ቋንቋ ውስጥ ዝሙትም ሆነ ምንዝርነት በዚና ውስጥ ይካተታሉና ነው፡፡ ቁርኣን ደግሞ በባህሪው ለአብዛኞቹ ድንጋጌዎች ሃይላይትን ከመስጠት ባለፈ ወደ ዝርዝር ማብራሪዎች አይገባም፡፡ ይህንኑ ማድረግ ደግሞ የመልዕክተኛው(ﷺ)ሚና ነው፡፡  «…ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን(ፍች)ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡»(አን-ነሕል 16፡44) በጥቅሉ ያገቡ ዝሙተኞች የወንጀለኝነታቸው ቅጣት በኢስላማዊው ወይም በፊቂህ መሰረት በድንጋይ ተቀጥቅጠው መገደል ነው፡፡ ይህም ከላይ ያለውንና ሌሎችንም ሐዲሦች ማስረጃ በማድረግ ነው፡፡ ይህንኑ የሚያጠናክሩና የሚደግፉ በርካታ ተግባራዊ ማስረጃዎችም አሉ፡፡ ለምሳሌም ታላቁ ዓሊም ኢብን መስዑድ(ረድየላሁ አንሁ)ባወሩት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ)እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡-   «የሙስሊሙ ደም፣ እርሱ ያ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለና እኔም የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን የመሰከረ ሰው፣ ከሦስቱ ድርጊቶች መካከል በአንዱ ቢሆን እንጂ ማፍሰሱ አይፈቀድም፡፡ ያገባ ሆኖ ዚናን የሠራ ሰው፣ ነፍስን በነፍስ(የገደለ ይገደል) እና እርሱ ያ ዲኑን የተወና ከ(ሙስሊሞች)ሕብረት እራሱን የገነጠለ ሰው ናቸው።» (ሰሒሕ ቡኻሪና ሰሒሕ ሙስሊም)  በሌላም ዘገባ ታላቁ ሰሓባ ጃቢር ቢን ዐብዱሏህ(ረድየላሁ አንሁ)እንዳወሩት አንድ ጊዜ ከሰለም ጎሳ የሆነ አንድ ሰው ወደ ነብዩ(ﷺ)መጣና ዚና እንደፈጸመ በማመን ኃጢአቱን ተናዘዘ፡፡ ሰውየው በራሱ ላይ አራት ጊዜ እስከሚመሰክር ድረስም ነብዩ(ﷺ)ፊታቸውን አዞሩበት፡፡ ከዚያም ነብዩ(ﷺ)«አንተ እብድ ነህ እንዴ  አሉት፡፡ ሰውየው «አይደለሁም» አላቸው፡፡ ነብዩ(ﷺ)«አግብተሃል ወይ?» አሉት፡፡ እርሱም «አዎ!» አላቸው፡፡ ከዚያም ነብዩ(ﷺ)ሰውየው በድንጋይ ተቀጥቅጦ እንዲገል አዘዙ፡፡ እርሱም በሙሰል-ላ ላይ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ተገደለ።(ሰሒሕ ቡኻሪ)     (አላህ የላቀላ ይበልጥ አዋቂ ነው)         👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 🧲 ሁላችንም ለጓደኞቻችንና ባሉን ቻናልና ግሩፕ እናሰራጫቸው። ከኛ የሚጠበቀው በጥበብ ማድረስ ነው አላህ የወደደውን ይመራበታል።        ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ          @jezakellah በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ተቀለቅለው ይከታተሉን ያተርፉበታል👇 https://t.me/latekrebu_zina https://t.me/latekrebu_zina የዝሙት ሌላኛው ስሙ የሃራም ፍቅር ነው!
Показать все...
👍 34
Ke afta deyka buhala ye zina qetatoch kefl hult yeketelal
Показать все...
👍 5
🔥ክፍል አንድ → የዚና ወንጀል ዱንያዊ ቅጣቶች       🔥 🔥 🔥 🔥 🔥 🔥 የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፡- «ሙስሊሞች ሆይ!ዝሙትን ተጠንቀቁ(ራቁት)። እርሱም ስድስት ጉዳቶችን ያስከትላል፤ ሦስቶቹ በዚህ ዓለምና ሌሎቹ በቀጣዩ ዓለም ሲሆኑ። ዱንያዊ ጉዳቶቹን በተመለከተ የፊት መገርጣት/መደብዘዝ፣ አጭር ዕድሜና ረጅም ድህነት ናቸው። የቀጣዩ ዓለም ጉዳቶቹ ደግሞ የአላህ ቁጣን መውረስ፣ ጥብቅ(ኮስተር ያለ) ምርመራና በእሳት ውስጥ መቀጣት ናቸው።»(አቡ ዐዲይ) እንደሚታወቀው የዚና ወንጀልን የሚመለከቱ ቁርኣናዊ አንቀጾች የወረዱት ተራ በተራ(ደረጃ በደረጃ)ነበር። ያም ማለት አንዱ ትዕዛዝ ከወረደ በኋላ ሌላው ቆይቶ መምጣቱን ይጠቁማል። ከዚህ በስተጀርባ ያለውን ጥበብ ስንመለከት ደግሞ እነዚህ ትዕዛዛት በአዳዲስ ሰለምቴዎች መካከል በቀላሉ ተቀባይነትን እንዲያገኙ ለማስቻል ነበር። ማህበረሰቡ በጃሂሊያው(በድንቁርናው)ዘመን ዚናን ጨምሮ በተለያዩ ታላላቅ ወንጀሎች ውስጥ የተዘፈቀና የዘቀጠ እንደመሆኑ መጠን መጥፎ ልማዶቻቸውን በአንዴ እንዲተውት ማድረግ ከባድ ነው። ልክ እንደ ዚና ሁሉ የኸምር ክልከላዎችም የወረዱት በሦስት ደረጃዎች ተከፋፍለው እንደነበር ይታወሳል። የዚናን ቅጣት የሚመለከተው የመጀመሪያው አንቀጽ ዚናን የሠራች ሴት አራት ሰዎች ከመከሩባት በኋላ ቅጣትዋ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አልያም አላህ(ﷻ)ተለዋጭ ድንጋጌን እስከሚያመጣ ድረስ በቤት ውስጥ እንድትጠበቅ የሚያዝ ነበር። እሱም ሱረቱን ኒሳእ አንቀጽ 15 ላይ በግልጽ ተቀምጧል። «እነዚያም ከሴቶቻችሁ መጥፎን ሥራ(ዝሙትን)የሚሠሩ በነሱ ላይ ከናንተ አራትን(ወንዶች)እስመስከሩባቸው፡፡ ቢመሰከሩም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለነሱ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውሰጥ ያዙዋቸው(ጠብቁዋቸው)፡፡»(አን-ኒሳእ፡15) ሁለተኛውም ሱረቱን ኒሳእ አንቀፅ 16 በግልፅ ተቀምጧል። ↓ «እነዚያንም ከእናንተ ውስጥ(ዝሙትን) የሚሠዋትን አሰቃዩዋቸው፡፡ ቢጸጸቱና ስራቸውንም ቢያሳምሩ ከእነርሱ ተገቱ(አታሰቃዋቸው)፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡»(እንኒሳእ 4፡16)   ነገር ግን ከወንጀሉ አስከፊነትና አደገኛነት የተነሳ የዚና ቅጣት በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ቀጣዩና የመጨረሻው እርምጃ ሊወሰድበት ግድ ሆነ፡፡ ያ ማህበረሰብም በኢስላም የዳበረ ስለሆነ ለዚና ተለዋጭ ቅጣት ብቁ መሆኑ ታመነበት፡፡ ይህም በመሆኑ ማህበረሰቡን ከዚህ ክፉ በሽታ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማራቅና መታደግ ስለሚያስፈልግ ሦስተኛውና የመጨረሻው የዚና ወንጀለኞች ቅጣት ወረደ፡፡ ይህም የኢስላምን ተልዕኮ ምሉዕ የሚያደርግ ነበር፡፡ የሦስተኛው ደረጃ ተለዋጭ ቅጣት የቀድሙትን በመሻር እነዚያን ዝሙትን የሚዳፈሩትን አሳማሚ ቅጣት እየቀጡ መቀጣጫ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ በመግለጽ አዲስ ጠበቅ ያለ ድንጋጌን አፀና፡፡ ከዚህም የተነሳ አላህ(ﷻ)ቀጣዩንና ብዙዎች የሚያውቁትን አንቀጽ አወረደ፡፡  «ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን(ያላገቡ እንደኾኑ)መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደኾናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡»(አን-ኑር24፡2)   ሆኖም ግን አንቀጹ ጥቅል በመሆኑ ባገባውና ባላገበው ወንጀለኛ መካከል ልዩነትን ያደረገ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በዓረብኛ ቋንቋ ውስጥ ዝሙትም ሆነ ምንዝርነት በዚና ውስጥ ይካተታሉና ነው፡፡ ቁርኣን ደግሞ በባህሪው ለአብዛኞቹ ድንጋጌዎች ሃይላይትን ከመስጠት ባለፈ ወደ ዝርዝር ማብራሪዎች አይገባም፡፡ ይህንኑ ማድረግ ደግሞ የመልዕክተኛው(ﷺ)ሚና ነው፡፡  «…ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን(ፍች)ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡»(አን-ነሕል 16፡44)  (አላህ የላቀላ ይበልጥ አዋቂ ነው)         👉 ይ ቀ ጥ ላ ል 🧲 ሁላችንም ለጓደኞቻችንና ባሉን ቻናልና ግሩፕ እናሰራጫቸው። ከኛ የሚጠበቀው በጥበብ ማድረስ ነው አላህ የወደደውም ይመራበታል።        ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ          @jezakellah በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ተቀለቅለው ይከታተሉን ያተርፉበታል👇 https://t.me/latekrebu_zina https://t.me/latekrebu_zina
Показать все...
👍 47🔥 1
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላህ ውድ በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች ስለ ዚና እና መግቢያ መንገዶች ብዙ አውርተናል ያላወራናቸውም ቢኖሩም ስለ ዚና ወንጀል ክብደት ያላችሁ ግንዛቤም ከፍ እንዳለተ ተስፋ አደርጋለሁ። አልሃምዱሊላህ የአላህ ፍቃድ ሁኖም ለብዙዎች የመመለስ ሰበብና ወደዛ ወንጀልም እንዳይገቡ ሰበብ ሆኗቸዋል። በዚህ ቻናል ላይም ጥቅል ነገሮች ሳይሆን ለየት ባለመልኩ የተደበቁት ወጥመዶች በግልፅ ተብራርተው ስለሚቀርቡ ብዙዎች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ኢንሻ አላህ ከዚህ በኋላም ይቀጥላሉ እናንተም እየተጠባበቃችሁ ሼር በማድረግ ሃላፊነታችሁን ተወጡ። በመቀጠልም በተከታታይ የምናየው ፕሮግራም ስለ ዚና ቅጣቶች ይሆናል ዚና ከባድ ወንጀል ነው አላህ በዱንያም በቀብርም በአኼራም ከባድና አሰቃቂ ቅጣትን አድርጎበታል። ነገር ግን ከተመለስንና ተውበት ካደረግን አይምረንም ማለት አይደለም። በዚህ ወንጀል ላይ በስተት ወድቀን ከሆነ ትክክለኛ ተውበት አድርገን ከተመለስን አላህ ወንጀላችንን ይምረናል። ካልተመለስን ግን ወላሂ አላህ አላህ አያያዙ ብርቱ ነው በአኼራ ላይ ያለውን ቅጣት ብንረሳው እንኳ በዱንያ ላይ የጭንቀትና የጥበት ህይወት እንድንኖር ያደርገናል ብዙዎችም ብዚህ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። 🎤 ከፍ ባለ ድምል ወደ አላህ ተመለሱ አላህ ወንጀላችሁን ሁሉ ይምራችኋል እንላችኋለን። ኢንሻ አላህ በቀጣዩ ፕሮግራማችን የዚናን ቅጣቶች ባጭሩ በማያሰለች መንገድ እናያቸዋለን። ሁላችንም እናንባቸው። ኢንሻ አላህ ፁሁፉን በፒዲኤፍና በወረቀት የሚወጣ በማያሰለች መልኩ ለማዘጋጀት ሞክራለሁ። ክፍል አንድ ኢንሻ አላህ ማታ ይለቀቃል አድ የምታደርጉ እንዲሁም ሼር የምታደርጉ ንያችሁን አስተካከላችሁ ከሆነ ወላሂ ትርፋማ ናችሁ እንደ ቀላል ነገር አትዩት የአንድ ሰው የመመለሰ ሰበብ መሆን ማለት በጣም ትልቅ ምንዳ አለው ከኛ የሚጠበቀው ማድረስ ነው አላህ የፈለገውን ይመራበታል። ሁላችንም እንግባና ግሩፑን እናሳድገው 👇👇 አድ👇 👇 አድ👇 👇 https://t.me/bezemut_anzemn https://t.me/bezemut_anzemn https://t.me/bezemut_anzemn የፊት መገርጣት/መደብዘዝ፣ አጭር ዕድሜና ረጅም ድህነት አንዱ የዚና ዱንያዊ ቅጣት ናቸው።❗️
Показать все...
በዝሙት አንዘምን❗️ግሩፕ

አላማ፦ ብዙዎቻችን ፁሁፍ ሼር ማድረግ ስለሚከብደን በግሩፑ ምክንያት ብዙ ሰዎች አድ ተደርገው ስለሚገቡ በሚለቀቁት ፁሁፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ነው። እናም ስልካችሁ ላይ ያሉትን ሰዎች አድ አድርጉ። ክፍያው ከአላህ ነው የውስጥ መስመር→ @jezakellah ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 @latekrebu_zina كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون بالمعروف و تنهون عن المنكر

👍 18
🚨 ለኢንትራንስ ፈተና ወደ ግቢ ለምትሄዱ ውድ እህት ወንድሞች አጠር ያለች ማስታወሻ። በትኩረት ይነበብ ከዛም ሼር ማድረግ አትርሱ 🧲 ትልቁ ፈተና የተቃራኒ ፆታ ፈተና ነውና በዚህ መንገድ ለመውደቅም የተለያዩ መንገዶች አሉ መንገዶች ቢለያዩም ግኑኝነታችንን ሃላል ስለማያደርገው ለራሳችን ብለን ጥንቃቄ እናድርግ። የሰፈርሽ ልጅም ሆነ፣ አብሮሽ አንድ ክላስ የተማረም ሆነ፣ ዘመድሽም ሆነ አጅ ነብይነታችሁን ወይም ወደ ዚና ለመግባት የሚያስቀረው ነገር የለም ስለዚህ እነዚህ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ ርቀን የሄድንበትን አላማ ብቻ ፈፅመን እንመለስ። ወላሂ ቁጥብነት ለራስ ነው! ቁጥብ በመሆን ራሳችንን እንጂ የምንጠቅመው የአላህን ክብር አይጨምረውም። 🧲 ውድ ወንድሜም ለእህቶችህ ፈተና ከመሆን ልትቆጠብ ይገባል አንድ እህተጋ መጥፎ ነገር ልታደርግ ስታስብ ወይም ክልክል በሆነ መንገድ ለማውራት ስታስብ የስጋ እህትን እና ነገ የሚኖርህን ሴት ልጆች አስባቸው በነሱ ላይ እንዲደርስ የማትፈልገውንም በሌሎች ላይ አታደርግ። 🧲 እንዲሁም እህቶች ለወንድሞች በአለባበሳችሁ ፈተና ከመሆን ልትቆጠብ ይገባል። ወንድ ልጅ ወደ ዚና አብዝቶ የሚሳበው በሴቶች መረን የለቀቀ አለባበስ ነው ስለዚህ ሰፋ ያለ፣ ረጅም የሆነ፣ ወፍራም የሆነ ልብስ ልትለብሱ ይገባል። ይሄም ብዙ ጥቅም አለው አንዱ ዱንያዊ ጥቅም ማንም ጋጠወጥ ወንድ እንዳይዳፈራችሁና ክብራችሁን እንድጠብቁ አጥር ይሆናችኋል። 🧲 እንዲሁም ዶርምሽ አካባቢ በምትሆኝበትም ጊዜ ቀንም ሆነ ማታ ከጥሩ ከእህቶችጋ መሆንሽን አትርሺ በጭራሽ ለብቻሽ መንቀሳቀስ የለብሽም። ጓደኞችሽንም ልትመርጭ ይገባል የቀረቡሽን ሁሉ ልትቀርቢ አይገባም። ትርፍ ለሆኑ ነገሮችም ለመገባበዝ በሚልም ሰበብ ወደውጭ አንውጣ ከተመሳሳይ ፆታ ጋርም ቢሆን። 🧲 እንዲሁም የጡሃትና የማታ አዝካሮችን አትርሺ አታል ኩርሲይን፣ ቁል ሁወላሁ አሃድን፣ ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅን፣ ቁል አዑዙ ቢረቢናስን ሶስት ሶስት ጊዜ፣ እንዲሁም ሱረቱል በቀራ መጨረሻ ላይ ያሉትን አንቀፆች "አመነ ረሱሉ" ከሚለለው ጀምረን እንቅራ፣ እንዱሁም "ቢስሚላሂ ለዚ ማአ ኢስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዲ ወላፊሰማእ ወሁወሰሚኡል አሊም" የሚለውን ዚክር ጧትና ማታ ሶስት ሶስት ጊዜ ማለትን አትርሱ። አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ሸሪማ ኸለቅ" የሚውን አዝካር እናዘውትር በትንሹ እነዚህን አዝካር አንርሳ ሌሎችንም ለማለት እንሞክር እነዚህ ጧትና ማታ ካልናቸው በአላህ ፍቃድ ምንም መጥፎ ነገር አይነካንም። ከነካንም አይጎዳንም ሌሎችንም ሰበብ ከማድረስጋር። 🧲 ሶላታችንንም ዶርም ውስጥ እንስገድ፣ ከመሸም በጭራሽ መውጣት የለብንም ሃላል ለሆነ ነገር የግድ መውጣት ካለብንም ከጥሩ ጓደኞችጋ መሆን አለበት። ጥሩ ጓደኛ እንኳ ባይኖረን በጭራሽ ብቻችንን እንዳንወጣ።❗️ አላህ እህት ወንድሞቻችንን ባሉበት ከመጥፎ ነገር ይጠብቃቸው። 🏆 ሁላችንም በተለያዩ መንገዶች ሼር እናድርጋቸው በትኩረት ደግሞ ለመፈተን ለሚሄዱት ልጆች እንላክላቸው። የሚለቀቁ ፁሁፎችን እየተጠባበቃችሁ በቻላችሁት ሼር እያደረጋችሁ ያላችሁ እህት ወንድሞች አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ @jezakellah ይህ በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ነው ይቀላቀሉ ያተርፉበታል 👇👇 https://t.me/latekrebu_zina https://t.me/latekrebu_zina
Показать все...
በዝሙት አንዘምን 🚫

የተለያዩ ባለንበት ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንመካከር እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል ቻናሉ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ያምብቡ። ከሃራም መንገድ(ፍቅር)መውጣት ለምትፈልጉ በውስጥ መስመር እንመካከር 👉 @Jezakellah ሙሂዲን ሰኢድ ጆይን ግሩፕ👉 @bezemut_anzemn كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون بالمعروف و تنهون عن المنكر

👍 54💯 5👌 4💊 2
🌍 ካካፊር ጋር ግኑኝነት ያለን ማወቅ ያሉብን ነገሮች 👇 🧲 ክፍል አንድ https://t.me/latekrebu_zina/1949 🧲 ክፍል ሁለት https://t.me/latekrebu_zina/1951
Показать все...
በዝሙት አንዘምን 🚫

📌 ክፍል አንድ (①) 🔥ከካፊር ጋር ግኑኝነት ያለን ማወቅ ያለብን መንገዶችና ማስታወሻዎች። ምን አልባት በዚህ መንገድ ትሆናላችሁ ካልሆናችሁም ልንፈተን ስለምንችል ትልቅ ትምህርት ይሆነናል። እንዲሁም ጓደኞቻችንም ሆነ በዚህ የገቡበት የምናውቃቸው ካሉ ልናስታውሳቸው ግድ ይለናል። ትለለች እንዲህ አሰላሙዓለይኩም ወንድም አንድ ነገር ለማክርህ ነበር አንድ ልጅ ላግባሽ እያለኝ ነበር ግን ልጁ ክርስቲያን ነው ግን ያው እሰልማለሁ እያለኝ ነው መጀመሪየ እንደመይሆን ነግሬው ነበር ግን አሁን ሙስሊም ልሁን አስተምሪኝና ልስለም አለኝ  ግራ ገባኝ ምን ላድርግ። በመጀመሪያ ማወቅ የለብን ነገር ይሄ አንዱ ማጥመጃ መንገዳቸው ነው ማለትም እሰልምልሻለሁ አስተምሪኝ የሚሉት በደካማ ጎን በመግባት ላማሳመን ነው ምክንያቱም ያኔ እንደዛ ሲላት በኔ ምክንያት ከሰለመ ጥሩ ነው ብላ እንጂ ሌላውን መጥፎ ነገር አታስታውልም። ብዙዎችን በዚህ መንገድ እየገቡ ማጥመድ ችለዋል። አንዳንዶች እንዳሉትም ይሰልማሉ ግን እምነቱን ፈልገውት ሳይሆን እሷን ለማክፈር ነው እሱም ከተጋቡና ልጅ ከወለዱ በኋላ በነበሩበት እምነት ይመለሳሉ። ያኔ ያችም ልጅ ልጆቹን ማሳደግ ስለማትችል ሳትወድ በግዷ ለአባቶቻቸው ትሰጣለች። እሷም የመክፈር እድሏ በጣም ሰፊ ነው። ወይም እስልምና ባይፈቅድም እሷም በሃይማኖቷ እሱም በሃይማኖታችን ብለው የዚና ህይወት ይቀጥላሉ። ግን በዚህ ህይወት ላይ ስትኖር ከአላህ እርቃ በኢባዳዋ ላይ ተዘናግታ የሚያስጠላ ህይወት ነው የምትኖረው። አንዳንድ እህቶችም በዚህ መንገድ የገቡትን ልጆች ስልክ ሰጠውኝ ላወራቸው ሞክሬ ነበር የመለሱልኝ ምክንያት ያስለቅሳል ከላይ እንደነገርኳቹህ ነው። ህይወቱን ፈልገውት አይደለም። የሚያስጠላና የጭንቀት ህይወት ነው የሚኖሩት! መኖር አትበሉት። እስካሁን የገቡበትን ልጆችም ማትረፍ ይቻል…

👍 1
ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ የከፈረችው ልጅ ደወልኩላት ማን ነህ አለችኝ እንዳማታወቀኝና ስላለችበት ሁኔታ እንደማውቅ የደወልኩትም ላግዛትና ለምን እንደዛ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደገባኝ ምክንያቷን ከማወቅ እንደሆነ ነገርኳት። እሷም ማላውቀውን ሰው አላወራም አለችም በግድ አሳምንኳትና ፍቃደኛ ሆነች። ከዛም የተፈጠረውን ነገረችኝ ልጁጋ በጓደኝነት ብዙ አመት እንደቆዩ መጨረሻ ላይ ልጅ ተፈጠረና ወደ እናቴ ቤት መሄድ ስፈልግ እናቴ በዚህ ሁኔታ ልትቀበለኝ እንደማትፈልግ ነገረችኝ እኔም ተስፋ በመቁረጥ ሃይማኖቴን ቀየርኩ አለችኝ። ልጁም መጀመሪያ ላይ ይሃይማኖቱን እንደሚቀይር ነበር ያወራነው ግን አሁን ላይ እኔ ሃይማኖቴን እንድቀይር ባያስገድደኝ እንኳ እሱ ለመስለም ፍቃደኛ አይደለም አለችኝ። ከዛም ብዙ ደይቃ ዳእዋ አደረኩላት አላህ ብትመለስ እንደሚምራት ወደ እምነቷም እንድትመለስ ወደ እምነቷም ስትመለስ ልጁ አልፈልግሽም ካለሽ እኔ ወጠሽ የምትኖሪበትን ሁኔታ ከሰዎች ጋር አውርቸ አመቻችልሻለሁ ልጅሽን በነፃነት ከጌታሽ ጋር ማሳደግ ትችያለሽ። ልሄን መንገድም ስትመርጭ ምን አልባት ዱንያ ላይ ልትሰቃይና አልጋ በሰልጋ ላይሆን ይችላል ነገር ግን አኼራ ላይ ካለው ዘላለማዊ እሳት ይሄ ቀላል ነው አልኳት። እሷም በስርጋት ሁሉንም ካዳመጠችኝ በኋላ ሃሳቧን ስጠይቃት አሁን ከልጁ ቤተሰብ ነው ያለሁት ለመውለድ ትንሽ ቀን ነው የቀረኝ መወሰን አልችልም እንዳለችኝ ስልቁ ተቋረጠ ድጋሚ ስደውል አይሰራም። ግን መደወል እንደምችልና እሷም እንደምደውል ነግራኛለች ኢንሻ አላህ ተስፋ አንቆረወጥም ምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። ያለው ሁኔታ ባጭሩ ይሄ ነው ከዚህ በፊትም በዚህ ሁኔታ የገቡ ልጆችጋ አውርቸ ነበር ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያሉት እኛ በደንብ ልናግዛቸው ብንችል ካሉበት ህይወት ልናወጣቸው እንችላለን። አንዳቸውም ደስተኛ ሁነው አይደለም ከእምነታቸው የራቁት ነገር ግን ኢማናቸው ደካማ ስለሚሆንና ቤተሰብም በዛ ሁኔታ ስለማይቀበላቸው እንዲሁም ከልጁ ርቀው ብቻቸውን በሚሆኑበት ሰአት የሚያግዛቸው ስለማይኖር የሚመጣውን ችግርና ስቃይ ሲያስቡ እምነታቸውም ይቀይራሉ። ሃቅም ያላችሁ በወጣቱ ጉዳይ የምትሰሩ ተቋማቶች በዚህ ጉዳይ በደምብ ሊሰራበት ይገባል። ሌላው በዚህ መንገድ ያላችሁ እባካችሁ ከመንገዱ ራቁ እሰልማለሁ፣ ስለ እምነቱ መረዳት እፈልጋለሁ፣ እሰልምልሻለሁ እያሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ይደረድራሉ ይሄ ውሸት ነው። ካለፉት እህቶች እንማር መንገዱን እንራቅ። ወላሂ አላህ የተሻለ በሃላሉ መንገድ ይሰጣችኋል። ለሰላምታ እንኳ ቢሆን ይሄን መንገድ አትቅረቡት። የሰፈርልሽ ልጅም ሆነ፣ በትምህርት ቤትም ሆነ፣ በስራ ጉዳይም ሆነ ካፊር ወንድ ጋር ከማውራት ወንዶችም ከካፊር ሴት ጋር ከማውራት እንራቅ። ቁጥብነትን የመሰለ ነገር የለም። ሁሉም እየከፈሩ ያሉ እህቶች አንድም ቀን እከፍራለሁ ብለው አስበው አያውቁም ነገር ግን አላህ "አትቀረቢው ይሄ መንገድ የከፋ ነው" ያለንን መርህ በመልቀቃችን መጨረሻችን እየተበላሸ ይገኛል። ከዚህ በፊት ከካፊር ወንድ ጋር በተመለከተ በክፍል ሁለት ያለቀ ትምህርት ለቅቄቄችሁ ነበር ኢንሻ አላህ ከታች በድጋሚ ሊንኮችን እለቅላችኋለሁ እንድታነቡት። (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው) 🧲 መልእክቱን በቻልነው ሼር እናድርገው። በተለይ ዩንቨርስቲ ላይ ይሄ ነገር ተስፋፍቶ ይገኛል ግሩፖች ላይ ሼር ማድረግ ስቶሪያችሁ ላይም ልቀቁት። ባረከላሁ ፊኩም በተለያየ ክልክል በሆነ መንገድ ከተቃራኒ ፆታጋ የምታወሩ እህት ወንድሞች በነፃነት መመካከር እንችላለን። ጉዳዩን ወደ አላህ ያስጠጋ አፍሮ አያውቅም የሃራም መንገድ የትም አያደርስም! ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ @jezakellah በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን ያተርፉበታል 👇👇 https://t.me/latekrebu_zina https://t.me/latekrebu_zina
Показать все...
👍 55🏆 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይሄ ፎቶ መጨረሻ ላይ በድጋሚ የላኩት ታሪክ ባለቤት ነው። ከልጁና ከወለደችው ልጇጋር የተነሳችው ፎቶ ነው። በርግን ምንም ጥቅም ላይኖረው ይችላል ፎቶው መለቀቁ ነገር ግን በዚህ ጉደሰይ ላይ በሰፊው እንዲሰራበትና ትኩረት እንዲሰጠው ያግዛል ብየ አስባለሁ። ወላሂ ዱንያ ምንም ዋስተና የላትም አሁን ላይ አንድ ሰው 50/60 አመት ከኖረ በጣም እድለኛ ነው የሚባለው። እናም በዚች አጭር እድሜ አኼራቸውም ማጣታቸው ልባችንን ሊሰብረው ይገባል። ማንም ሴት አስባበት አምናበት አትከፍርም ምክንያት ባይሆናትም ከገባችበት በኋላ መውጫ እያጣች እንጂ።! ከካፊርጋ ግኑኝነት ያለን ሙስሊም ሴቶች አላህን እንፍራ መንገዱን እንዝጋ እንራቅ ካለንብት የሸይጧን ወጥመድ! ቀን የለቀቀኩላችሁን ልጅ ሁኔታ ኢንሻ አላህ ነገ እንመካከርበታለን።
Показать все...
👍 59
ከዚህ በፊት ይሄን ከላይ ያለውን ፁሁፍ ልኬላችሁ ነበር ተያያዥ ሃሳብ ስለሆነ ብዙ ያላነበባችሁት ስለመትኖሩ አንቡት። ከላይ ባለችው በልጅቷ ጉዳው ነስልክ አውርቻት ነበር ያልኳችሁን ሃሳብ እፅፍላችኋለሁ። ኢንሻ አላህ
Показать все...
🏆 9👍 5🔥 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.