cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተዋሕዶ መዝሙር

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮነ ስርአት የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደነንተ ያቀርባል። ይቀላቀሉ አስተያየት ሀሳብ ጥያቄዎች ከአላቸው (0979871602) ✟✟✟✟

Больше
Рекламные посты
3 391
Подписчики
Нет данных24 часа
-47 дней
-230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሰላም የድንግል መርያም የፍሬው ልጅ ልጆች ዛሬ channel ቢያንስ ለ5 ስው share በማረግ channel እናሳድግ 🙏🙏🙏🙏
Показать все...
በድንግል አማረ ህይወቴ በድንግል አማረ ህይወቴ በማርያም አማረ ህይወቴ ስጠራት ገብታልኝ ከቤቴ በድንግል አማረ ከሞት መሀል ነጥቀሽ በድንግል አማረ ነፍስን ዘራሽብኝ በድንግል አማረ ሀጥያተኛ ሳለው በድንግል አማረ ሰው አርገሽ አቆምሺኝ በድንግል አማረ ሀዘን መከራዬ በድንግል አማረ ታሪክ ሆኖ ቀረ በድንግል አማረ ህይወቴም ባንቺ በድንግል አማረ በድንግል አማረ በማርያም አማረ አዝ.... በድንግል አማረ ሀጥያትን አብዝቼ በድንግል አማረ ለምፅ ቢያጠቃኝም በድንግል አማረ አንቺ እያነፃሺኝ በድንግል አማረ ዳግም ብጨቀይም በድንግል አማረ እሩሩህ ነሽ እና በድንግል አማረ ምልጃሽ አይዘገይም በድንግል አማረ ስምሽን ስጠራ በድንግል አማረ አታሳፍሪኝም /2/ አዝ.... በድንግል አማረ ሐዘኔ በርትቶ በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድም በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሽልኝ በድንግል አማረ ስሜ ተከየረ በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ በድንግል አማረ በድንግል አማረ በማርያም አማረ አዘ.... በድንግል አማረ ሐዘኔ በርትቶ በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድም በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሽልኝ በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ በድንግል አማረ በቃጥላ አማረ በግሸን አማረ @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
_አዲስ_ዝማሬ_በድንግል_አማረ_ሂወቴ_ዘማሪ_ያብስራ_ሲሳይ_Bedengel_Amare_Offi_EZ8tNeD.mp39.87 MB
2
"ቅዱስ ዑራኤል-መልአከ ሰላምነ" ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል ሰዓል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ፀሎተነ ቅደመ መንበሩ ለመድኃኔዓለም @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
_ቅዱስ_ዑራኤል_መልአከ_ሰላምነ_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኃይሉ_lz16DJ5vmkw_140.mp35.65 MB
1
✞መንፈስቅዱስ✞ ከፍርሃት ማዕበል በጥብአት መጽንዒ ከኃጢአት ባርነት በአማን መንጽሒ ከአብ ከወልድ ጋር የተካከለ ነው ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው አምላክን በመውለድ በሕቱም ድንግልና መሰቀል መሞቱን በፍጹም ትህትና በነቢያት አድሮ ምስጢር ያናገረው መንፈስቅዱስ በእውነት ከሳቴ ምሥጢር ነው ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው        አዝ= = = = = በሰይፍ ሲመተሩ በገመድ ሲሳቡ በአላውያን ክፋት ለፍርድ ሲቀርቡ በእምነት አጸናቸው ፈርተው እንዳይክዱ አጽናኝ መንፈስቅዱስ ከሦስቱ አካል አንዱ ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው        አዝ= = = = = የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ልባችን በአደፈብን ጊዜ በዝቶ ኃጢአታችን በንስሐ ሆነን ወደ እሱ ብንመጣ ያነጻናል ፍጹም ጰራቅሊጦስ ጌታ ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው                 መዝሙር ኆኀተ መንግስተ ሰማያት ሰ/ት/ቤት "የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"              መዝ ፴፫ ፥፭-፮ @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
መንፈስቅዱስ.mp35.36 MB
👍 3
አንድ እርምጃ ሳልራመድ አንቺን ይዤ ተነሳሁ(2) እመቤቴ ዛሬም ባርኪኝ ውዳሴሽን አበዛለሁ የአምላኬ እናት ዛሬም ባርኪኝ ውዳሴሽን አበዛለሁ(2) (አዝ) ---አዝ------------ ምልጃሽ እየደገፈኝ በጌታ ፊት ስትቆሚ ጸሎቴን እያሳረግሽ ልመናዬን ስትሰሚ ከጎኔ ሳትለዪ ተቆጠሩ ዘመናት ይሄው ለዚህ ደረስኩኝ ከእናትም በላይ ሆነሽ እናት ---አዝ------------ በጎጆዬ ስላለሽ መጉደልን አላውቅም የአንደበቴ ቋንቋ ነው እናቴ ያንቺ ስም ሰንደቄና አርማዬ የኔ መታወቂያ ነሽ ከእግረ መስቀሉ ሥር ቀራንዮ ላይ ያገኘሁሽ ---አዝ------------ ፈውስን የቀዳሁብሽ የበረከት አዘቅት ለዚህ ቀን የደረስኩት ሆነሽኝ ነው ብርታት ስንቱን አለፍኩት ባንቺ ወጣሁ ስንቱን ተራራ መከታ ጋሻዬ ነሽ የከሳሹን ቀስት እንዳልፈራ ---አዝ------------ ጌታዬን ከእቅፍሽ ፍቅርን ከመቅደስሽን ትህትናን ተምሬያለው ፊደሌ ስለሆንሽ ከቶ ነግቶ አይመሽም ለውዳሴሽ ሳልቆም ብዙ ነው ምስጢራችን የኔ እና ያንቺ ማርያም ---አዝ------------ አንድ እርምኛ ሳልራመድ አንቺን ይዤ ተነሳሁ እመቤቴ ዛሬም ባርኪኝ ውዳሴሽን አበዛለሁ የአምላኬ እናት ዛሬም ባርኪኝ ውዳሴሽን አበዛለሁ! @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
ተሰምቶ_የማይጠገብ_መዝሙር_እመቤቴ_ዛሬም_ባርኪኝ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.mp31.64 MB
👍 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰኔ____21 እንኳን #ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሰኔ ጐልጐታና ሕንጸተ ቤተ ቤተክርስቲያን (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችኹ #ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏😢😢 ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው #ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ #የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም #ቃል_ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ። #ድንግል_ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው #በልጅሽ ፈት ቁሚልን ። #እናታችን__ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ። ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ #በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ #እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ። ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው። ደምህ ይጋርደን #ሐጢአታችንን_አታስብብን የእናታችን እረድኤት በረከት ፍቅር አይለየን አሜን 🙏🙏 @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
👍 3 1
✞መንፈስቅዱስ✞ ከፍርሃት ማዕበል በጥብአት መጽንዒ ከኃጢአት ባርነት በአማን መንጽሒ ከአብ ከወልድ ጋር የተካከለ ነው ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው አምላክን በመውለድ በሕቱም ድንግልና መሰቀል መሞቱን በፍጹም ትህትና በነቢያት አድሮ ምስጢር ያናገረው መንፈስቅዱስ በእውነት ከሳቴ ምሥጢር ነው ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው        አዝ= = = = = በሰይፍ ሲመተሩ በገመድ ሲሳቡ በአላውያን ክፋት ለፍርድ ሲቀርቡ በእምነት አጸናቸው ፈርተው እንዳይክዱ አጽናኝ መንፈስቅዱስ ከሦስቱ አካል አንዱ ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው        አዝ= = = = = የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ልባችን በአደፈብን ጊዜ በዝቶ ኃጢአታችን በንስሐ ሆነን ወደ እሱ ብንመጣ ያነጻናል ፍጹም ጰራቅሊጦስ ጌታ ጰራቅሊጦሰ መንፈስቅዱስ የባሕሪይ አምላክ ነው                 መዝሙር ኆኀተ መንግስተ ሰማያት ሰ/ት/ቤት "የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"              @mazmur2122 @mazmur2122 @mazmur2122
Показать все...
መንፈስቅዱስ.mp35.36 MB
👍 8
"በእጸ መስቀሉ የተከፈለልኝ" ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ +++በእፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ+++ ======================= በእፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ ከፍቅርም በላይ ሆነና መሰጠኝ ከመስቀል ስር ሆኜ ፊቱን እያየሁኝ አዝ… አለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ የፀብን ማዕበል በፍቅሩ የገታ ህይወቴን ፀጥ አርጎ ይምራት በብህላቱ እኔ ምን አለፋኝ አልደክምም በከንቱ አዝ . . . ደሙ ከወዙ ጋር ተዋህዶ ሲወርድ በኔ በደል ጌታዬ ቀረበልኝ ለፍርድ ሀጢያቴን በጫንቃው ተሸክሞልኛል በደሌን ደምስሶ ንፁህ አድርጎኛል አዝ… የቀራንዮ ግፍ በአንተ ላይ የሆነው ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣው እሾህ አሜኬላው ተደምስሶሎናል የንፁሁ በግ ደሞ አዳምን ታድጓል አዝ . . . ይህንን ስጋዬን ብሉ ይላችኋል ይህንን ደሜንም ጠጡ ይላችኋል ከመስቀሎ ስር ሆነን ደሙ እንቀበል ስጋውን እንብላ ሰዎች ችላ አንበል @mazmur2122🟢🟢🟢 @mazmur2122🟡🟡🟡 @mazmur2122🔴🔴🔴
Показать все...
_በእጸ_መስቀሉ_የተከፈለልኝ_Be_etse_meskelu_yetekefelelegn_ሊቀ_መዘም_skUdqgXQXQU.mp34.10 MB
2👍 1
🕊 †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  † [ †  እንኩዋን ለአራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] 🕊 † አራቱ ቅዱሳን አበው ሰማዕታት † 🕊 ፬ [4] ቱ ቅዱሳን አበው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ሲሆኑ ስማቸው አባ አክራ አባ ዮሐንስ : አባ አብጥልማ እና አባ ፊልዾስ ይባላሉ:: ከመከራ ዘመን በፊት [ማለትም በቀደመ ሕይወታቸው]  ካህናትና ሃብታሞች ነበሩ:: ሀብቱ ግን በሥራ ብቻ የተገኘ ነው:: ታዲያ ቅዱሳኑ በያሉበት ሆነው በሀብታቸው እንግዳ እየተቀበሉ : ድሆችን እያበሉ: በክህነታቸው ደግሞ እያስተማሩና እየናዘዙ ትጉሃን ስለ ነበሩ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ነበራቸው:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳሉ ዘመነ ሰማዕታት አሐዱ አለ:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" እያሉ መኩዋንንቱና ነገሥታቱ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሰቃዩ ገቡ:: በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን አንድ ነገር መከሩ:: በየእሥር ቤቱ የተጣሉ ክርስቲያኖችን ለማገልገል ቆረጡ:: እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩ እሥረኞችን ያጽናኑ ገቡ:: የራበውን ያበላሉ: የተሰበረውን ይጠግናሉ: በቁስሉም ላይ መድኃኒትን ያደርጉ ነበር:: የመከራው ዘመን ግን እየረዘመ: ግፉም ከልክ እያለፈ መጣ:: በዚህ ጊዜ ፬ [ 4 ] ቱ ቅዱሳን ትልቁንና የመጨረሻውን ውሳኔ አስተላለፉ:: ከሰማዕታት ወገን ይቆጠሩ ዘንድ መርጠዋልና: ክርስቶስን በሞቱ ይመስሉት ዘንድ ሽተዋልና: የሩጫቸው መጨረሻ ሰማዕትነት እንዲሆን መረጡ:: አራቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሰብስበው ለነዳያን አካፈሉ:: በትከሻቸው ካለች አጽፍ በቀር ስባሪ ገንዘብ ከሃብታቸው አላስቀሩም:: ከዚያ ጉዞ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ዐውደ ስምዕ] አደረጉ:: በዙፋኑ የተቀመጠው የመኮንኑ ግርማ: መሬት ላይ የፈሰሰው የወገኖቻቸው ደም: የሠራዊቱ ድንፋታ ቅዱሳኑን አላስፈራቸውም:: በይፋ "ክርስቲያን ነን" ሲሉ ተናገሩ:: በዘመኑ እንዲሕ ብሎ መናገር አንገት የሚያስቆርጥ ትልቅ ድፍረት ነበር:: መኮንኑም ከበጐ ሃይማኖታቸው ይለያቸው ዘንድ በእሳት አቃጠላቸው:: እግዚአብሔር አዳናቸው:: በቀስትም: በስለትም: በብረትም ለቀናት አሰቃያቸው:: ቅዱሳኑ ግን አምላካቸውን አምነው ሁሉን በአኮቴት ተቀበሉ:: በመጨረሻ ግን በዚሕች ዕለት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገድለዋል:: ስለ ምጽዋታቸው: በጎ አገልግሎታቸውና ሰማዕትነታቸው ጻድቅ: ፈራጅ ከሆነ ፈጣሪ አክሊልን ተቀብለዋል:: የበረከት አምላክ ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱሳን አበው ሰማዕታት [አባ አክራ: አባ ዮሐንስ: አባ አብጥልማ: አባ ፊልዾስ] [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ] ፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ ፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ ፬. ቅዱስ ሙሴ [ የእግዚአብሔር ሰው ] ፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ ፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ ፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት " እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። " [ዕብ.፮፥፲-፲፫] (6:10-13) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
👍 6🔥 1
🕊 [ † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊 †  ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት  †  🕊 † ቅዱስ ገብርኤል :- - በራማ ከሚኖሩ ሊቃናት አንዱ:: - አርባብ በሚባሉ አሥር ነገዶች ላይ አለቅነትን የተሾመ:: - የስሙ ትርጓሜ "እግዚእ ወገብር" [ጌታና አገልጋይ] አንድም "አምላክ ወሰብእ" [የአምላክ ሰው መሆን] ማለት የሆነ:: - በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ያረጋጋ:: - ብርሃናውያን መላእክትን የሚመራ:: - በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብሣሪነቱ በስፋት የተነገረለት:: - በተለይ ደግሞ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ዜና ይሸከም ዘንድ ያደለው:: - ከድንግል ማርያም ጎን በፍጹም የማይርቅ:: - በፈጣን ተራዳኢነቱ ብዙ ቅዱሳንን ያገለገለ ታላቅ ቀናዒ መልአክ ነው:: በዚሕች ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ባቢሎን ልኮታል:: ሊቀ መላእክት ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስቱ ጥርስ እንዳዳነው መጽሐፍ ነግሮናል:: ይልቁኑ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል የተማረኩ ወገኖቹን መመለስ እያሰበ በሃዘን ሲጸልይ በዚሕ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ዳስሶታል:: ባርኮታል:: አጽናንቶታል:: ለዳንኤል በዋነኛነትም ሦስት ምሥጢራትን ገልጾለታል:- ፩. የቤተ እሥራኤልን ከሰባ ዘመን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ:: ፪. የክርስቶስን ሰው መሆንና መሞት:: ፫. የሐሳዌ መሲሕን በመጨረሻ ዘመን መምጣት ነግሮታል:: ስለዚህም እኛ ቅዱስ ገብርኤልን እንድናከብረው : በጸሎትም እንድንጠራው አባቶቻችን አዝዘውናል:: 🕊 † አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም †  🕊  † ጻድቁ ሃገራቸው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ሲሆን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ባልንጀራ ናቸው:: ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በክርስትና አድገው : ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው ወደ ገዳም መንነዋል:: ከታላቁ ኮከበ ገዳም አባ ኢላርዮን ሥርዓተ መነኮሳትን አጥንተው አባ ኤስድሮስን በረድዕነት አገልግለዋል:: ከብዙ ዓመታት ትሕርምትና ገዳማዊ ሕይወት በኋላ የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል:: በጵጵስናቸው ዘመን አንድ ከባድ ስሕተት ሠርተው ነበር:: እርሱም ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ከምእመናን የተሠበሠበውን ገንዘብ ለግል ጉዳያቸው አውለው ልብሳቸውና ቤታቸው ወርቅ በወርቅ ሆኖ ነበር:: ፈጣሪ ግን ይሕንን ብክነት ከእርሳቸው ያርቅ ዘንድ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ላከው:: እርሱም በምክንያት ከቆጵሮስ ኢየሩሳሌም ገባ:: ጓደኛ ናቸውና አሳምኖ የወርቅ ንብረቶቹን ሁሉ ወሰደ:: ለነዳያንም ሰጣቸው:: አባ ዮሐንስ ሊቁን "እቃየን ካልመለስክ" ብለው ቢይዙት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸልዮ ዐይናቸው እንዲታወር አደረገ:: አንዳንዴ የታወረ ልብ የሚገለጠው እንዲሕ ነውና:: በደቂቃዎች ልዩነት ዐይነ ስውር የሆኑት አባ ዮሐንስ አለቀሱ:: ሊቁንም "ራራልኝ : አማልደኝ?" አሉት:: እርሱም ጸልዮ አንድ ዐይናቸውን ብቻ አበራላቸው:: "ለምን?" አሉት:: "ተግሳጽ ነው" አላቸው:: ከዚያች ቀን በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ልቡናቸው ተመለሱ:: ቤታቸውን ገዳም አደረጉት:: በሚደነቅ ቅድስና : ፍቅርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ምዕመናንን አገልግለው በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል:: † የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት : የአባ ዮሐንስ በረከት አይለየን:: 🕊 [ †  ሰኔ ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ወደ ዳንኤል የወረደበት] ፪. አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ፫. አባታችን ቃይናን [ከአዳም አራተኛ ትውልድ] ፬. አባ ማትያን ጻድቅ [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. እግዚአብሔር አብ ፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ፫. ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ፬. ቅዱስ አስከናፍር ፭. አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች ፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ ፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ † " . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም: ተናገረኝም:: እንዲህም አለ :- "ዳንኤል ሆይ! ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ::" † [ዳን. ፱፥፳-፳፪] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.